Was John The Baptist The Second Elijah
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለማቴዎስ መፅሀፍ የተጠቀም ነው አንድ ቃል ንጉስ ነው ፡፡ ትናትና በማቴዎስ 10 ኢየሱስ 12 ሐዋሪያቱን ለጠፉት ለእስራኤል በጎች መልዕክቱን እንዲወስዱ እንዲሁም ክፉዉን እንዲያስወጡና የታመመ እንዲፈዉሱ በተልዕኮ አስታጠቃቸው ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ(11፡ 1-3)፡ ደቀመዛሙርቱ እንዲያደርጉት አዝዞአቸዉ የነበረዉን ለማድረግ እንደወጡ በእስራኤል ከተሞች ዉስጥ ሊያስተምር ወጣ (ቁጥር 1) ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም በተልዕኮ ላይ ነበሩ ፡፡ በእስርቤት የነበረው መጥምቁ ዮሐንስ በትንሹ ኢየሱስ ምን እያደረገ እንደነበር ሰማ ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ በሄሮድስና በሚስቱ ላይ አድርጎት በነበረው ክስ አስርቤት ዉስጥ ተቀምጦ ነበር (ሉቃ 3፡ 19-29) ፤ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ መታሰር ከሰማ ቦኃላ ገሊላ ሄደ (ማቴ 4፡ 12) ፡፡
መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ ምን እንደነበር በአይምሮዉ ለየት ያለ ስዕል ነበረው ምክንያቱም ሙሉ ህይወቱን ለኢየሱስ መምጣት ለማዘጋጀት የሰጠ ነበር ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እንደነበር ያ ያሳዉቀዉ የነበረው መጥቶ እንደነበር ወይስ ሌላ እንደነበር ማረጋገጫ ለመጠየው በእስር ቤት ተቀምጦ ለኢየሱስ በደቀመዛሙርቱ መልዕክት ላከ (ቁጥር 3) ፡፡ የኢየሱስን ማንነት ይህ ማረጋገጫ ዮሐንስ ለምንድን አስፈለገው ?
- ኢየሱስ በገሊላ ነበር እንጂ አድሱ ንጉስ መንግስቱ ይዞ በሚደርስበት ኢየሩሳሌም አልነበረም ፡፡
- ዮሐንስ ግራ ተጋብቶ ነበር ፤ በማቴ ( 3፡ 11-12) ዮሐንስ የኢየሱስን ጠፍሮቹን እንካን ለመንካት ብቁ እንዳልነበር እዉቅና ሰጥቶአል ፡፡
ነገር ግን ኢየሱስ በእሳት (ማቴ 3፡ 12)፣ በስልጣንና በኃይል እንደሚመጣ ጠብቆአል ፤ መሲሁ በኢየሩሳሌም ይጠበቅ እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡
መዝ 118፡ 26፡ “ በእግዚአብሄር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው ፤ ከእግዚአብሄር ቤት መረቅናችሁ ፡፡ “
ማር 11፡ 9-10፡ “ ሆሳዕና ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ! በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግስት የተባረከች ናት ! ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጮሁ ነበር !”
ዕብ 10፡ 37፡ “ ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው ሊመጣ ያለው ይመጣል አይዘገይም ፡፡ “
ዮሐንስ ተወዛግቦ ነበር በእምነት እጦት ምክንያት ነገር ግን ጠብቆት በነበረው ተግልጦም አልነበረም ፡፡
ማቴዎስ(11፡ 4-6)፡ ኢየሱስ የዮሐንስን ጥያቄ የዮሐናስ ደቀመዛሙርቱ አይተዉትና ሰምተዉት የነበረዉን የኢየሱስን ስራ እንዲነግሩት በማድረግ መለሰለት፡ “ ዕዉሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ ለምፃሞችም ይነፃሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ ሙታንም ይነሳሉ ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል “(ቁጥር 5) ፡፡ ኢየሱስ ምስክሮችን ይሰበስብና ተዓምራቶችን ያደርግ ነበር በዚህም ምክንያት ዮሐንስ የኢየሱስ ሚና እንደ መሲሁ እንደሆን ማረጋገጥ ይችላል ፡፡
ኢሳ 29፡ 18-19፡ “ በዚያም ቀን ደንቆሮች የመፅሀፍን ቃል ይሰማሉ የዕዉሮችም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተለይተው ያያሉ ፡፡ የዋሃን ደስታቸውን በእግዚአብሄር ያበዛሉ በሰዎች መካከል ያሉ ችግረኞችም ሐሴትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ ፡፡ “
ይህ ስለ መሲሁ ከኢሳያስ ትንቢታዊ ቃል ነው ኢየሱስም በዚህ ትንቢት እየተጎአዘ ነበር ፤ እነዚህ ሁሉ ቃሎች መጥምቁ ዮሐንስ ያዉቃቸዋል ስለዚህ መልዕክቱን የተረዳውን ዮሐንስን እርግጠኛ ለማድረግ ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ አደረገ ፡፡ ኢሳ (35፡ 5-8) ስለ መሲሁ መምጣት ተጨማሪ ትንቢት ነው ፡፡
ማቴዎስ(11፡ 7-10)፡ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት እንደሄዱ ኢየሱስ በዙሪያዉ ላለው ህዝብ ማስተማር ጀመረ ፡፡ ኢየሱስ ህዝቡን ወደ ምድረበዳ ወጥጣችሁ የነበረው ለምንድን ነው የዮሐንስን ስብከት ለመስማት ነው ብሎ ጠየቃቸው ፤ ምናልባት በቤተ መንግስት የሚሰራ “ቀጭን ልብስ “ ለማየት በማለት ዘና አደረጋቸው ፡፡ ኢየሱስ ዮሐንስ ነቢይና የሚበልጥ እንደነበር በደንብ ገለፀው ፤ ከዚያም ኢየሱስ ለእርሱ መንገዱን ሊያዘጋጅ መጥቶ የነበረው ሚል (3፡ 1) በመጥቀስ ወደ ዮሐንስ አመለከተ ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ለኢየሱስ መምጣት ህዝቡን ለማዘጋጀት ኃላፊነቱን ፈፅሞ ነበር ፡፡
ማቴዎስ(11፡ 11-15)፡ ኢየሱስ ማንም ከዮሐንስ የሚበልጥ አልነበረም ነገር ግን “ በመንግስተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል “ (ቁጥር 11) ባሎ ተናገረ ፡፡ ማክአርቱር የሚለው “ ዮሐንስ ከብሉይ ኪዳን ነቢያቶች ይበልጥ ነበር ምክንያቱም በትክክል በአይኖቹ አይቶአልም በግሉም የተተነበየው መፈፀም ላይ ተሳትፎአል “ ፤ ሚልክያስ መጥምቁ ዮሐንስ እንደሚመጣ ተንብዮአል ፡፡ አሁን በእግዚአብሄር መንግስት ነን ከበፊቱ(ከቀድሞው) ትንቢታዊ ቃል መለማመድ እንችላለን ይህም ከመጥምቁ ዮሐንስ እንድንበልጥ ያደርገናል ፤ የመጨረሻዉ መጨረሻ (“ የመጨረሻው”) አሁን ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ነው ፡፡
ቁጥር 12 የሚያወራው “ መንግስተ ሰማያት ትገፋለች ግፈኞችም ይናጠቐታል ፡፡” ማክአርቱር የሚያካፍለው መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነብይ ከምድረበዳ ጮኸ ከህዝብም ጠንካራ ምላሽ ቀሰቀሰ ፤ የእግዚአብሄር መንግስት ቀርባለች የሚለው መልዕክት በልደት ቀኖአ እንዲቀርብ በሄርዶስ ሴት እንጀራ ልጅ የዮሀንስ ራስ ተጠየቀ በእንደዚህ አይነት ሁከት የተመለከተ ነበር (ማቴ 14፡ 6-12) ፡፡ ይህ ጉልህ አገላለፅ ከሚመጣዉ መሲህ ከአንዱ ኢየሱስ መልዕክታቸዉ ባልተመለሱት እና በማይመለሱት ጠላቶቻቸዉ መሀከል የነበረውን ዉጥረት ያሳያል ፤ ይህ በእዉነቱ መንግስቱ ይዞ እሰኪደርስ ድረስ ይቀጥላል ፡፡ በዚህ ላይ ምሁራን የተለያየ እይታ እንዳላቸው እነግራችኃለሁ ፤ አንዱን ብቻ ነዉ ያቀረብኩት ስለዚህ በዚህ ላይ መቆፈር ለመቀጠል እንቀበላችኃለን ፡፡
ቁጥር 13-14 የሚያወራዉ “ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው ፡፡ “ መንግስተ ሰማይ ቀርባለች የሚለዉን መልዕክ አይሁዶች ከተቀበሉት መንግስቱ ይጀምራል ግልፅ የሚያደርግ ጥቅስ አይኖርም ፡፡ መልእክቱን የሚቀበሉ ከሆነ ሁሉም የአይሁድ ሰዎች ያደርጉት የነበረዉ በቀላሉ “ አዎ “ ማለት ነበር በዚህም ዮሐንስ “ የሁለተኛዉ ኤልያስ “ ትንቢት ትንቢታዊ መፈፀም ይሆናል ፤ ስለዚህ ጥያቄው “ መጥምቁ ዮሐንስ የኤልያስ ትንቢታዊ መፈፀም ነበር ?”
ማክአርቱር መጥምቁ ዮሐንስ የዚህ መፈፀም እንደሆነ ይህን መፅሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ይሰጣል፡ ሚል 4፡ 5-6; ማቴ 11፡ 14; 16፡ 14; 17፡ 3, 9; 27፡ 47-49; ማር 8፡ 28; 9፡ 4; ሉቃ 1፡ 17; 9፡ 28; ዮሐ 1፡ 21 ፡፡ በኢሳ 40፡ 3 መጥምቁ ዮሐንስ ሚናዉ ምን እንደነበር አወጀ በዚህም ማስረጃ መሰረት ማክአርቱር ያመለከተው፡
መጥምቁ ዮሐንስ “ በኤልያስ መንፈስ እና ኃይል መጣ አምነው ከነበር ትንቢቶቹን ፍፅሞአቸዋል ፡፡“
በከፊል ዮሐንስ ሚል 4፡ 5-6 ፈፅሞታል ፡፡
ሚል (4፡ 5-6) አይሆዶች የእግዚአብሄር መንግስት መልዕክት ሲይዙ በግልፅ ይፈፀማል ፡፡
ያ ሲሆን አላዉቅም ግን ለማየት በህይወት እንደምኖር ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ ማቴ 11፡ 16 እንደ መሲህ ኢየሱስን መግፋታቸዉ ላይ ያተኩራል ፡፡
መዝጊያ
በማቴዎስ 11 እንደ ሸፈነው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ያ ብዙ ነው ነገር ግን ፀሎቴ የዚህ ጥቂቶቹ ለእናንተ ቢያንስ ያልተጣራ ወርቅ እንዲሆን ነው ሁሉም እነዚህ ቁርጥራጮች የመሲሁን ሙሉ ስዕል ለመሳል በአንድ ይመጣሉ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1143.
MacArthur, p. 1144.
MacArthur, p. 1144.
MacArthur, p. 1226 (Mk 9:13).
ጥያቄዎች
-
በማቴ (11፡ 14) መጥምቁ ዮሐንስን ከኤልያስ ጋር ለምን እና እንዴት አነፃፀረው (ማቴ 17፡ 10-13; ሉቃ 1፡ 17; ዮሐ 1፡ 21) ? ሚል (4፡ 5) ከማቴ (11፡ 14) ጋር በአንድ ላይ መተሳሰር እንዴት ታስቡታላችሁ - መጥምቁ ዮንስ ያን ትንቢት ፈፅሞት ነበር ወይስ እስካሁን የሚመጣ ሌላ አለ ?
-
ማቴ (11፡ 15) “ጆሮ ያለው ይስማ “ የሚለው ሀረግ ምን ማለት ነው ? የሆነ ሰዎ እነዚህ “ጆሮዎች” የለሉት ከሆነ ምንድን ይፈጠራል(ይሆናል) ? በዚህ ቁጥር ላይ የተጠቀሱት “ጆሮዎች “ እንዳሉአችሁ ታስባላችሁ ?
-
በማቴ (11፡ 1-6) ከኢየሱስ ጋር በነበረበት ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ማንነት እርግጠኛ ያልሆነዉ ለምን ነበር ? (ዮሐ 1፡ 29-36)
-
ማቴ (11፡ 5) እንዴት የኢሳ (29፡ 18-19; 35፡ 5-6; 61፡ 1-2) መፈፀም ነው ?
-
በማቴ(11፡ 25-30) ካለው ከእርሱ ቃሎች ስለ ኢየሱስ ምን ትማራላችሁ ? ስለ ኢየሱስ በምን እዉነት ዛሬ ልባችሁን ጠልቆ እንዲገባ ትፈልጋላችሁ ?
-
በማቴዎስ 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 11:25
“At that time Jesus said, ‘I praise You, Father, Lord of heaven and earth, because You have hidden these things from the wise, and learned and revealed them to infants.’”
ኢየሱስ የሰማይ እና የምድር ጌታ ወደሆነው ወደ አባቱ በፀለየ ጊዜ፥ ከጠቢባን እና ከተማሩት የተሰወረ እውነት ለህፃናት እንደተገለጠላቸው አጋርቷል፡፡ የግሪኩ ቃል ከአንድ አመት በታች የሆነን ልጅ ህጻን በማለት በቀጥታ ይተረጎማል፡፡ ኢየሱስ ሀጻን የሚለውን ቃል የተጠቀመው ትህትና እና ቅንነትን ለመግለጽ ነው፡፡ ስለዚህ፥ ኢየሱስ ትሑት እና ቅን የሆኑ አውነትን ፈላጊዎች እውነትን እንደሚያውቁ እና እንደሚያገኙ እያስተማረ ነበር፡፡
አያችሁ፥ በእውቀታችሁ ከክፍል ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆን ወይም በእውቀታችሁ ብዛት መኩራት አያስፈልጋችሁም፡፡ ይልቁንም፥ ኢየሱስ ለእናንተ ያለውን ሁሉ ለመቀበል ፈቃደኛ ሆናችሁ ወደእርሱ እንድትመጡ ይናፍቃል፡፡ የህፃን ልጅ ልብ ላለው ሰው እና በትህትና እና በቅንነት እውነትን በመራብ ለሚራመድ እርሱ ራሱን ይገልጣል፡፡ ወደ ኢየሱስ በትህትና ስትቀርቡ፥ የእግዚያብሔር መንግስት የእናንተ እንደሆነች ይነግራችኋል፡፡ ሁሉንም በአንዴ ማግኘት እንዳለባችሁ ሳይሰማችሁ በምትኩ ራሳችሁን ሆናችው ኑ፡፡
“ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ የሰማይ እና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞች እና ከአስተወዮች ሰውረህ ለህጻናት ስለገለጥህላቸው አመሰግናለው፡፡ ’”
— የማቴዎስ ወንጌል 11:25
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የማቴዎስ ወንጌል 5:3 — “ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብጹዓን ናቸው፥ መንግሰተ ሰማያት የእነርሱ ናትና”
- የማቴዎስ ወንጌል 18:4 — “ እንግዲ እንደህጻን ራሱን የማያዋርድ ሁሉ፥ በመንግስተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው፡፡”
- የማርቆስ ወንጌል 10:15 — “ እውነት አላችኋለው የእግዚያብሄርን መንግሰት እንደ ህጻን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አላቸው፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 11
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።