The Gospels Matthew

John The Baptist's Questions For Jesus

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 122 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና መጥምቁ ዮሐንስ ላይ እና ኤልያስ ነበርን የሚለውን ጥያቄ ተመልክተናል ፡፡ በማቴዎስ 11፡ 14 አይሁዶች መንግስተ ሰማይ ቀርባለችና የሚለውን መልዕክት ተቀብለዉ በነበር መጥምቁ ዮሐንስ “ሁለተኛው ኤልያስ “ ለሚለው ትንቢት ትንቢታዊ መፈፀም እንደሚሆን አጥንተኛል ፡፡ ከማቴዎስ 10 እስከ 28 ድረስ አይሁዶች ንጉሱ ኢየሱስን መግፋት ቀጠሉ ፡፡ በማቴዎስ 12 መሀል ላይ እንጀምራለን ፤ ከኃይማኖቶቹ ጋር ኢየሱስ ቐሚ መስተጋብር አለው ፡፡ በእግዚአብሄር ሰንበት እጁ ሽባ የሆነዉን አንድ ሰዉ ስለመፈወስ በዚያም እንደ እግዚአብሄር አገልጋይ እንዳገለገለ እና ስለ አንድ ቤት መከፈል ያወራል ፡፡ በቁጥር 38 እንጀምራለን የዮናስንም ምልክት እናያለን ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (12፡ 38)፡ በቁጥር 38 አንዳንድ ፃፎችና ፈሪሳዉያን ከኢየሱስስ ምልክት እንዲያዩ ጠየቁት ፤ ማማቻቻ ነበር ፡፡ ስታንሌይ ቶዉዛንት የጠቀሰው “ እርሱን መግፋታቸዉ እርግጥ ቢሆንም ከእርሱ ምልክትን በመፈለግ በተቃራኒ ባለማመን ፃፎችና ፈሪሳዉያን ንጉሱን ይቀርባሉ ፡፡ “ በዚያን ጊዜ አይሁዶች ማንኛዉም ምልክት ማደረግ ቢችልም አያምኑም ፤ ማክአርቱር የጠቀሰው “ በፈለካዊ መለኪያ ላይ የሆነ ተዓምራት “ ይፈልጋሉ ፡፡ ለምልክት ጥያቆዎች ላይ ተጨማሪ መፅሀፍ ሉቃ (11፡ 16) እና 1ቆሮ (1፡ 22) ናቸው ፡፡ አላማኞች ምልክትን ስለ ምልክትነቱ ይፈልጉታል ፤ አማኞች ምልክትን ለማረጋገጫነት ይፈልጋሉ ፡፡ በቀድሞዉ ጊዜ በጊዜዉ እግዚአብሄር ለህዝቡ ምልክትን አድርጎአል ነገር ግን ያደረገው ደካማ እምነታቸዉን ለማጠንከር ነበር ፤ አብርሃም፣ ኢያሱ፣ ጌዲዮዎን….ሁሉም ለማረጋገጫነት ምልክት አስፈለጋቸው ፡፡

ማቴዎስ (12፡ 39)፡ ኢየሱስ ጥያቄአቸውን “ ክፉና አመንዝራ ትዉልድ ምልክት ይሻል ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም “ ብሎ በመግለፅ መለሰላቸው ፡፡ በህግ መፅሀፍት አይምሮአችን እስራኤላዊያን በቐሚነት መንፈሳዊ ምንዝርና እንዴት እንደፈፀሙ ይወስደናል (ኢሳ 57፡ 3-8; ኤር 3፡ 10; ሆሴ 7፡ 13-16) ፡፡ ኢየሱስ ታአማራታዊ ምልዕክቶችን በመስጠት ፋንታ የዮናስን ምልክት ሰጣቸው ፡፡

ማቴዎስ (12፡ 40)፡ ዮናስ ሰዎስት ቀን እና ሰዎስት ሌሊት በአሳሆድ ዉስጥ ቆየ ፡፡ ዳግላስ ኦዶነል የቀድሞዋቹ አይሁዶች የተዋበ የንድግ ጊዜአቸዉን ለማገናዘብ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፆታል፡ “ አድሱ ቀን ፅሀይ ከገባች ቦኃላ ይጀምራል (ሌሊት ላይ አይደለም) እናም አንዳንድ ጊዜ የቀኑ አካል እንደ ሙሉ ቀን ይቆጠር ነበር “ ፤ (ዘፍ 40; 1ነገ 20) ፡፡

ዮናስ (2፡ 3) “ በባህሮች ሆድ ዉስጥ እንደሆነ “ ይጠቅሳል በተጨማሪም መዝ ( 46፡ 2) “ ስለ ባህሮች ጥልቀት “ ያወራል ፡፡ ኢየሱስ የራሱን ሞት እና መቀበሩን ለመጥቀስ “ በምድር ሆድ ዉስጥ እንደሚሆን “ ተናገረ (ማቴ 12፡ 40)፡፡ አንዱ ችግር አይሁዶች ኢየሱስ በእዉነት እንደሚሞት ቢያምኑም (ሉቃ 24፡ 18-20) ተመልሶ ወደ ህይወት እንደመጣ አለማመናቸው ነው ፡፡

ማቴዎስ (12፡ 41)፡ ዮናስ በአሳዉ ሆድ ዉስጥ አልቆየም ፤ ቆይቶ ቢሆን የነንዌ ሰዎች መልዕክቱንና ንስሀዉን ለመስማት በፍፁም እድል አይኖራቸዉም ነበር ፡፡ ለነንዌ ንስሀ ሲባል ዮናስ “ ከአሳዉ ሆድ ዉስጥ ይመጣል “ ፤ ኢየሱስ “ ከምድር ሆድ ወደ ህይወት ይመጣል “ ስለዚህ ንስሀ አለን ፡፡ ኢየሱስ የነንዌ ሰዎች በአይሁዶች(“ ይህን ትዉልድ(ያንን ትዉልድ)”) ላይ በፍርድ ይነሱባቸዋል አለ ምክንያቱም ከዮናስ ለመጣዉ መልዕክት “እሺ” ስላሉ (ዮና 3፡ 5-10) አይሁዶች ደግሞ ለኢየሱስ “እምቢ” ስላሉ ፤ አንዳንዶች በሁለቱም ምሳሌ መልዕክቱ ተመሳሳይ አልነበረም ይላሉ ምክንያቱም ከአንድ ትዉልድ ቦኃላ ነነዌያዊያን ወደ ቀድሞው መንገዳቸዉ ተመልሰው ሄደዋል (ናሆ 3፡ 7-8)፡፡

ትናትና ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ከብሉይ ኪዳን ነቢያቶች የበለጠ እንደሆነ አዉርተናል ምክንያቱም ለቃላቶቻቸዉ መፀም እየሄደበት ስለነበር ፤ በመንግስተ ሰማይ የመጨረሻዎቹ እንካን ከመጥምቁ ዮሐንስ ይበልጣሉ ምክንያቱም በተናገራቸዉ ትንቢታዊ ቃሎች እየሄድን ስለሆነ ፡፡

ስለዚህ ለምን ኢየሱስ ከዮናስ የበለጠ ነው ?ዋይርስቤ የጠቀሰው፡

“ በሰዎቹ የሚበልጥ ነዉ ዮናስ አንድ ብቻ ነበር ፡፡ በመታዘዙ የሚበልጥ ነበር ዮናስ እግዚአብሄርን አልታዘዘም…… በእዉነት ኢየሱስ ሞቶአል የዮናስ ሞት በትልቅ አሳ ሆድ ዉስጥ ነበር ፤ በራሱ ኃይል ኢየሱስ ከሞት ተነሳ ፡፡ ዮናስ ያገለገለው ለአንድ ከተማ ብቻ ሲሆን ኢየሱስ ለመላዉ አለም ህይወቱን ሰጠ ፡፡ በእርግጠኝነት ኢየሱስ በፍቅሩ ይበልጥ ነበር ዮናስ ለነንዌ ሰዎች ፍቅር አልነበረዉም እንዲሞቱ ይፈልጋል ፤ የዮናስ መልዕክት ነንዌን ከፍርድ አዳነ ፤ የእግዚአብሄር ቁጣ መልዕክተኛ ነበር ፡፡የኢየሱስ መልዕክት የፀጋና የድነት ነበር ፡፡ “

ማቴዎስ (12፡ 42)፡ “ የደቡባ ንግስት “ የሳባ ንግስት ነበረች የእስራኤላዊያን ሀሳብ ነበረችበት አለም መጨረሻ ላይ ትገኛለች (ኤር 6፡ 20) ፤ የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት መጣች ወደ እግዚአብሄርም ተመለሰች (1ነገ 10፡ 1-10) ፡፡ አህዛቦች (ነንዌያዊያንና ንግስት ሳባ) ምላሽ እየሰጡ ነበር ነገር ግን አይዶች አልነበሩም ፡፡ ኢየሱስ አይሁዶችን ከሰለሞን እንዲሁም ከዮናስ እንደሚበልጥ ነገራቸው ፡፡ ኢየሱስ እንዴት ነበር ከሰለሞን የበለጠው ? “ በጥበብ፣ በሀብት እና በስራዎች ይበልጥ ነበር “ ፤ የኢየሱስ መንግስት ስጦታዎች በጣም በብዙ ከሰለሞን ክብር ይበልጣል ፤ በተጨማሪም በክርስቶስ ግብዣ ላይ መቀመጥ ቃሎቹን ያሰማል በረከቶችንም ያካፍላል በጣም አስደናቂ መንግስቶችን ከሰለሞንም እንካን ከመጎብኘትና ከማድነቅ በብዙ የሚያረካ ነው ፡፡”

ኢየሱስ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ምልክቶችን ሰጣቸው…. በዮናስ በኩል፣ በነንዌያዊያን በኩል፣ በሰለሞን በኩልና በንግስት ሳባ በኩል ፤ አይሁዶች ይህን አልፈለጉም ፡፡ አይሁዶች ምልክትን በመግፋታቸው የእግዚአብሄርን በረከት ተቀበልን ፡፡ አንድ ቀን ዘካ (12፡ 10) ወደ ማፍራት ሲመጣ ያያሉ ፡፡

መዝጊያ

ዛሬ ውሳኔ ለመወሰን እየሞከራችሁ ከሆነ ብዙ ምልክቶችን ጠየቃችሁ ኢየሱስን ለመፈተን ለምልክቶቹ እንዳትጠይቁ ፤ ለቀጣዩ እርምጃ ማረጋገጫነት ብቻ ምልክትን ጠይቁ ፡፡

  1. Stanley D. Toussaint, Behold the King: A Study of Matthew (Grand Rapids, MI: Kregel Publications, 2005), p. 165.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publication, 2005), p. 1164.

  3. Douglas O’Donnell, Matthew: All Authority in Heaven and on Earth (Wheaton, IL: Crossway, 2013), p. 339.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew––Galatians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 43.

  5. Wiersbe, p. 44.

  6. Wiersbe, p. 44.

ጥያቄዎች

  1. በማቴ (12፡ 2) ፈሪሳዉያን ለኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ህጉን አየሰበሩ አንደሆነ አመለከቱት ፤ የተኛዉን ህግ ነበር እየሰበሩ ነው የተባሉት ? (ዘጸ 20፡ 8)
  2. በማቴ (12፡ 7) ኢየሱስ ከሆሴ (6፡ 6) በመጥቀስ ይህን ጥቅስ ተረድታችሁ በነበር ንፁሀንን አትኮንኑም አላቸው ፤ በዚህ ምንድን ማለቱ ነበር ? (ሚክ 6፡ 6-8)
  3. በማቴ (12፡ 10) ፈሪሳዉያን ኢየሱስን መክሰስ እንዲችሉ ማመቻቸታቸውን የሚገልጥ ነው ፤ መነሳሳታቸው ምንድን ነበር ? ይህ “ ወጥመድ “ እንዴት ተመለሰ ?
  4. ለምልክት በፃፎች እና በፈሪሳዉያን በተጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ምንድን “ምልክት “ ተሰጥቶናል አለ (ማቴ 12፡ 40) ? በአዲሱ ኪዳን ስር ለምልክቶች እግዚአብሄርን እንጠይቃለን ?
  5. በማቴ (12፡ 42) መሰረት ንግስት ሳባ ከምድር ዳርቻ ምንድን ለመስማት መጣች (1ነገ 10፡ 1-6) ? ከሰለሞን የሚበልጠዉ ማነው ? (ቆላ 2፡ 2-3)
  6. በማቴ (12፡ 48-50) ኢየሱስ እናቱ እና ወንዱሞች ማን እንደሆኑ ተናግሮ ነበር ? በክርስቶስ በመሆናችሁ ይህ በራስ መተማመን ሰጥቶአችኋል ?
  7. በማቴዎስ 12 በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Daily Word

Laura Martin Matthew 12:34b

“For the mouth speaks from the overflow of the heart.”

ኢየሱስ የፈሪሳውያንን ክፉ ቃላቶች ሲገልፅ፥ ዛፍ በፍሬው መታወቁን እንደምሳሌነት ሰጥቷል፡፡ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ እንደሚያፈራው ሁሉ ክፉ ዛፍ ክፉ ፍሬ እንደሚያፈራ አስረድቷል፡፡ ፈሪሳውያን ስለኢየሱስ ክፉ ወሬ ማውራታቸው የልባቸውን ባህሪይ ይገልጻል፡፡

ጌታ ከምንም ነገር በፊት የልባችሁ ጉዳይ እንደሚያሳስበው መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው፥ ምክኒያቱም ከአፋችሁ የሚወጣው ከልባችሁ ሞልቶ የተረፈው ነው፡፡ የአፋችሁ ቃል ሰዎችን የሚጎዳ እና ጌታን የሚያሳዝን ከሆነ፥ ልባቸሁን ለመፈተሽ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ልባችሁን የምትሞሉት በምንድነው? ልባችሁን የእግዚያብሔርን ቃል እውነት በመሰሉ ከጌታ በሆኑ ነገሮች ስትሞሉት ህይወታቸሁ ይቀየራል፡፡ በዕየለቱ ልባችሁን በጌታ ላይ አድርጉ እና ከአፋችሁ በሚወጣው ቃል ውስጥ ያለውን ለውጥ ተመልከቱ፡፡

“በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና፡፡”

—የማቴዎስ ወንጌል 12:34

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የሉቃስ ወንጌል6:45 — “በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል፡፡ ”
  • ሮሜ 12:2 — “ የእግዚያብሔር ፈቃድ እርሱም በጎ እና ደስ የሚያሰኝ ፍፁምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን አለም አትምሰሉ፡፡”
  • ኤፌሶን 3:16-17 — “ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በሀይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን ይስጣችሁ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 12