The Gospels Matthew

The Secrets Of Parables

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 123 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ባለፊት ጥቂት ሳምንታት ዉስጥ በንጉሱ ኢየሱስ ላይ እና እንዴት አይሁዶች መግፋታቸዉን እንደቀጠሉ ተመልክተናል ፡፡ ማቴዎስ 13 ግን በምሳሌዎች የተጨናነቀ ነው ዛሬ ኢየሱስ እንዴት በእነዚህ ምሳሌያዊ አነጋገሮች መሀከል እንዳወራ እናተኩራለን ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (13፡ 1-3)፡ ልክ እነዚህ ህዝቡ ባህሩ ጋር ኢየሱስ አጠገብ እንዴት እንደተቀመጡ ያሳየናል ፡፡ ከብቦት ለነበረው ህዝብ ወደ ጀልባዋ ገብቶ በዳርቻ ላሉት ምሳሌዎችን በመጠቀም አስተማራቸው ፡፡ ዛሬ ስለ ምሳሌዎች እናወራለን ፤ ምሳሌ ምንድን ነው ? ስለ ምሳሌዎች የምናወራው ለምንድን ነው ? ወደፊትስ ጠቃሚዎች ናቸው ?

ስታንለይ ቶዉዛንት የሚለው “ ምሳሌ አንድን ነገር በሌላዉ አጠገብ የማድረግ ድርጊት ነው ስለዚህ ንፅፅር በመካከላቸዉ ማድረግ ይቻላል ፡፡ “ የኔልሰን ማብራሪያ ምሳሌን የሚገልፀው “ ስለ መንግስቱ አድስ እዉነት ለማስተማር ከየእለት እለት ህይወት የተለመደ ትርጉም መጠቀም ነው ፡፡“ ኢየሱስ በዚህ መልኩ ምሳሌዎችን ተናገረ አንዳንዶች ይናገር የነበረውን ያዙ ሌሎች ግን ኑሀዉም አልነበራቸዉም ፡፡

ማቴዎስ (13፡ 10-18)፡ ከዚህ ኃሳብ ላይ ኢየሱስ ከህዝቡ ጋር በምሳሌዎች በመጠቀም ብቻ ተነጋገረ (ማቴ 13፡ 34) ፡፡ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ ለምን ምሳሌዎችን እንደተጠቀመ ጠየቁት (ቁጥር 10) ፤ ኢየሱስም ለደቀመዛሙርቱ የነበረዉን ሚስጥር ማወቅ ተሰጥቶአችኃል “ ነገር ግን ለእነርሱ ይህ አልተሰጣችሁም “(ቁጥር 11) ብሎ መለሰላቸው፡፡ “ እነርሱ “ አይሁዶች ወይም በህዝቡ ዉስጥ ያሉት ይሆናሉ ፡፡ ማክአርቱር የተናገረው “ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ግልፅ ያደረጋቸውን ከማያምኑት ትንሽ ደበቅ ለማድረግ ተጠቀማቸው ” ፤ መረዳት በመንፈስ ቅዱስ በኩል የተሰጠ ነው ፡፡ አይሁዶች መልዕክቱን ስለገፉት በተመረጠ ሉዓላዊ የተቀመጠው ለሌሎች ስጦታው ተሰጣቸዉ ፡፡ ምሳሌ የሚረዱትን እግዚአብሄር እየመረጠ ነው ያልተረዱትን ደግሞ አይመርጥ ፡፡

ይህ ለምንድን ነው ያስፈለገው ? መጥምቁ ዮሐንስ ቃሉን ሊሰጣቸዉ መጣ አይሁዶች ግን አልተቀበሉትም ፤ በመጨረሻም ዮሐንስ መልዕክቱን የሚቀበሉ ሰዎች አገኘ ፡፡ እንደ “ድብቅ “የተተረጎመው ቃል እንደ “ የተሰወረም በሚስጥር” ሊተረጎም ይችላል ፤ ማክአርቱር የገለፀው “ ሚስጥር ቀድሙ ከሁሉም ዕድሜ ተደብቀዉ የነበሩ በአዲስ ኪዳን የተገለጡ እዉነቶች ናቸው ፡፡ “ ማቴዎስ (13፡ 11) ለደቀመዛሙርቱ የተሰጡ ነገር ግን ለሌሎች ስላልተሰጡ ሚስጥሮች ያወራል ፡፡

ሉቃ (8፡ 10) ኢየሱስ የተናገረው፡ “ ለእናንተ የእግዚአብሄርን መንግስት ምስጥር ማወቅ ተሰጥቶአችኃል ፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙ እንዳያስተዉሉ በምሳሌ ነው ፡፡ “ በኢሳ (6፡ 9) ያለዉን ትንቢት ይፈፅማል “ እርሱም ሂድ ይህን ሕዝብ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም በላአቸው ፡፡ “

ሮሜ (11፡ 25) በኡሁኑ ጊዜም እንካን አይሁዶች ለምን መልዕክቱን እንዳልተቀበሉ በዝርዝር ይገልፃል “ ወንድሞች ሆይ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምስጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው “ ፤ ይህ ማለት አይሁዶች ልባቸዉን አደንድነዋል ስለዚህም መልዕክቱ ወደ ሁሉም አሕዛብ መምጣት ይችላል ፤ ይህ ማለት ይህን እንረዳዋለን ማለት ነው ነገር ግን አይሁዶች ይህ ሁሉ ስለምን እንደሆነ ምንም ሀሳቡ አይኖራቸውም ፡፡ ይህ ከፊል ድንዛዜ ማለት 8 ሚሊዮን ከሆነ እስራኤል ከእነርሱ ግማሹ (ምናልባትም 4 ሚሊዮኑ) ይረዳል ሌሎቹ አይረዱም እግዚአብሄር ያመለከተዉ የአህዛብ ቁጥር የድነትን መልዕክት እስከሚይዙ በዚያው መንገድ ይቆያሉ ማለት ነው ፡፡

ሮሜ (16፡ 25-26)፡ “ እንግዲህ እንደ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መፅሓፍት የዘላለም እግዚአብሄር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምስጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው ፡፡ “ለረጅም ጊዜ ተደብቆ የቆየ ሚስጥር ነበር ነገር ግን በቁትር 26 መሰረት አሁን በትንቢታዊ መፅሀፍት በኩል እንዲታወቅ ተደርግአል ፤ ለምሳሌ ኢየሱስ ወደ አርሞንየም(ወይራ) ተራራ እንደሚመለስ ከትንቢታዊ ቃል እናዉቃለን ከዚያም እግሩን ባረፈበት ጊዜ የወይራ ተራራ ይሰነጠቃል ፤ ነገር ግን ተፈፅሞ አላየንም ፤ አሁንም ሚስጥር ነው ፡፡ መሲሁ እንደሚመጣ ለሚያዉቁት ለአይሁድ ሰዎችም ተመሳሳይ ነው ነገር ግን በእነርሱ ፊት ሆኖ ማየት አልቻሉም ፡፡

1ቆሮ(2፡ 7) የሚለው “ ነገር ግን እግዚአብሄር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን ተሰዉሮም የነበረውን የእግዚአብሄርን በምስጢርእንናገራለን ፡፡ “ የእግዚአብሄርን እዉነት በምንናገር ጊዜ የሌሎችን መልስ ማየት የኛ አይደለም ፤ መልዕክቱን ይረዱት አይረዱት የእግዚአብሄር ቀድሞ የተወሰነ እቅድ ነው ፡፡

1ቆሮ (4፡ 1)፡ “ እንዲሁ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ ሎሌዎችና እንደ እግዚአብሄርምስጢር መጋቢዎችይቁጠረን ፡፡” እንደ አማኞች እነዚህን ሚስጥሮች ማስተዳደር ማለት ለማንኛውም ሚስጥር እነዚህን በሚገባ ማወቅ ማለት ሲሆን ፤ መግለፅ የምንችለው፣ የለምድነው እና የምንጎአዝበት ማለት ነው ፡፡

ኤፌ (6፡ 19)፡ “ ደግሞ የወንጌልን ምስጢር በግልጥ እንዳስታዉቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ” ፤ ያ ማለት የሁሉም ኃጢዓት ያም ኃጢዓት ወደ ሞት እንደሚመራ ፍቅር እንደሚመጣና ኃጢዓትን እንደሚያስወግደው በድፍረት መግለፅ እንዲችል ማለት ነው ፡፡ በሞት በኩል በኢየሱስ የመስቀል ሞት ህይወት መቀበል ይችላሉ ፡፡

በቁጥር 12 ኢየሱስ የገለፀው ማንኛውም ይህ እዉቀት ያለዉ ተጨማሪ እንደሚሰጠው ነው ፤ ነገር ግን ይህ እዉቀት ለሌላቸዉ ሌላዉም ይወሰድባቸዋል ፤ በዚህ ምክንያት ኢየሱስ ኢየሱስ ትንቢት ይጠቀማል ፡፡ የኢሳያስ ትንቢት በኢሳ (6፡ 9-10) በኢየሱስ ትምህርት በኩል ተፈፀመ ፡፡

ማቴዎስ (13፡ 34-35)፡ ኢየሱስ ህዝቡን ለእነርሱ ለመናገር ብቻ ምሳሌ እንደሚጠቀም ነገራቸው ፤ ይህ መዝ (78፡ 2) “ አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ ከቀድሞ ጀምሮ ያለዉንም ተምሳሊት እናገራለሁ “ የፃፈውን የነቢዩ አሳፍን ትንቢት አስፈፀመ ፡፡

ማቴዎስ (13፡ 44-46)፡ በጠቅላላ በማቴዎስ ዉስጥ መልዕክቱ ያለማቐአረጥ በአይሁዶች የኢየሱስ መገፋት ነው ፡፡ በዚህ ምሳሌ “ ሀብት “ የመጀመሪያዉ የተለመደ ነገር ነው ፤ ሀብቶአ በማሳ ላይ ተቀብራለች አገኛት ቆፍሮ አወጣት ፤ ሀብቶአን ያገኘዉ ሰው ሀብቶአ ተቀብራበት የነበረችዉን ማሳ መግዛት እንዲችል ሁሉንም ነገር ሸጠ ፡፡ ለአሕዛቦች ሀብቶአ ኢየሱስን ትወክላለች እሱም ድነታችን ነው ፤ ነገር ግን አህዛቦች ድነታቸዉን ካላከኙ ምናልባት ሀብቶአ አንድ ቀን የኢየሱስን ድነት የሚቀበሉት የእስራኤልና የአይሁዶች ነበርች (ዘጸ 19፡ 5; መዝ 135፡ 4) ፡፡ ምናልባት ኢየሱስ የተለዩ እርስቶቹ ስለነበሩ ከአይሆዶች ጋር ይነጋገር(ይግባባ) ነበር ለእነርሱም ቀድሞ ሁሉንም ነገር ሰጥቶአቸዉ ነበር፡፡

መዝጊያ

በዚህ አገባብ ኢየሱስ “ እንንተ የእኔ ልዩ ህዝብ ናችሁ “ ለማለት ምሳሌዎችን ይጠቀም እንደነበር አምናለሁ ፤ እራሳችሁን ጠይቁ፡ የእነዚህ ሚስጥሮች መልካም ባላደራ እና አስተዳዳሪ ናችሁ ? በተጨማሪስ እነዚህን ሚስጥሮች ከሌሎች ጋር በግልፅ መነጋገር ትችላላችሁ ?

  1. Stanley Toussant, Behold the King: A Study of Matthew (Portland: Multnomah Press, 1980), p. 169.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1164.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1147.

  4. MacArthur, p. 1148.

ጥያቄዎች

  1. ምሳሌ ምንድን ነው ? በማቴዎስ 13 በምሳሌ ዉስጥ ለህዝቡ ኢየሱስ ይናገር የነበረው ርዕሱ ምን ነበር ? ለምን ምሳሌ ተጠቀመ ? (ሕዝ 12፡ 2; ማቴ 13፡ 13)
  2. በማቴ (13፡ 3-8) በዘሪዉ ምሳሌ ላይ ባስገነዘባችሁ ጊዜ በእነዚህ በተለያዩ አፈሮች “ ዘርን “ መዝራትን ተለማምዳችሁት ታውቃላችሁ ? በምሳሌዉ ላይ የኢየሱስን ገለፃ ባነበባችሁ ጊዜ (ማቴ 13፡ 18-23) ፍሬ ለማፍራት ትክክለኛዉ አይነት አፈር ለመሆን ልባችሁን እና አይምሮአችሁን እንዴት ማዘጋጀት ትችላላችሁ?
  3. በማቴ (13፡ 44) ላይ ያለዉን ምሳሌ ባነበባችሁ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ባላችሁ ግንኙነት እንደዚያ አይነት ደስታ ቀምሳችኋል(ተሰምቶአችኋል) ? የእግዚአብሄር መንግስትን ለመያዝ “ ያላችሁን ሁሉ መሸጥን ” አስባችሁታል ?
  4. ኢየሱስ ወደ ገዛ አገሩ በመጣ ጊዜ በእርሱ ላይ ተሰናከሉበት ( ማቴ 13፡ 57) ፤ የምታዉቋቸዉን እናወደ ክርስቶስ ከመምጣታችሁ በፊት አብራችሁ ያደጋችኋቸውን ወንጌልን ለማካፈል አስቸጋሪ እንደሆነ ይሰማችኋል ? ለእናንተ ቅርብ የሆኑት ስለ ወንጌል መልዕክት ምንድን እንደምትናገሩ ለመስማት ፍቃደኛ አለመሆን አስቸጋሪ እንደሆነ ይሰማችኋል ?
  5. በማቴዎስ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 13:44

“The kingdom of heaven is like treasure, buried in a field, that a man found and reburied. Then in his joy he goes and sells everything he has and buys that field.”

ኢየሱስ የእግዚያብሔርን መንግስት ሚስጥር የሚያመለክቱ ሰባት ምሳሌዎችን አካፍሎ ነበር፡፡ ለአማኞች የእግዚያብሔር መንግስት ውድ መዝገብ ነው፡፡ ያላችሁን ሁሉ ሽጣችሁ ከእናንተ ጋር የቀረው ብቸኛ ነገር ውድ መዝገብ የሆነው የእግዚያብሔር መንግስት ቢሆን በቂያችሁ ነው፡፡ የክርስቶስ የማዳን ፀጋ፣ የሜበዠት ሀይል፣ ፅድቅ፣ ሰላም፣ ደስታ እና ክእርሱ ጋር ለዘላላም መኖር ውስጥ ያለው ዋጋ ሁሉንም ነገር ያስተዋል፡፡

የእገዚያብሔርን መንግስት በሙላት እንዳታጣጥሙት የሚገታችሁን ነገር አሁንም ይዛችሁታል? ዛሬ ጌታ ልባቸሁን እንዲያፀዳላችሁ እና በእግዚያብሔር መንግስት ውስጥ ያሉትን በረከቶች ሁሉ ማጣጣም እንድትችሉ ጠይቁት፡፡ የሚያሰናክላችሁን ማንኛውንም ነገር አስወግዱ፡፡ ዝም ብላችሁ ልቀቁ፡፡ ኢየሱስን በሙሉ ልባችሁ ስትፈልጉት ይገኝላችኋል፡፡

“ ደግሞ መንግስተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረን መዝገብ ትመስላለች ሰውም አግኝቶ ሰወረው ፥ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ፡፡”

—የማቴዎስ ወንጌል 13:44

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኤርምያስ 29:13-14 — “‘ እናንተ ተሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ፡፡ ከእናንተም ዘንድ እገኛለው፥ ይላል እግዚያብሔር ምርኮአችሁንም እመልሳለው፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድኩበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለው፥ ይላል እግዚያብሔር፤ እናንተንምወደ ምርኮ ወዳፈለስኩበት ስፍራ እመልሳችኋለው፡፡ ’”
  • የማቴዎስ ወንጌል 6:33 – “ ነገር ግን አስቀድማቸሁ የእግዚያብሔርን መንግስት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡"
  • ሮሜ 14:17-19 — “ የእግዚያብሔር መንግስት ጽድቅ እና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብል እና መጠጥ አይደለችምና፡፡ እንደዚህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ እግዚያብሔርን ደስ ያሰኛልና፥ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው፡፡ እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በእርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል፡፡”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 13