The Gospels Matthew

Walking On Water

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 124 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዚህ ምዕራፍ ለንጉሱ ኢየሱስ በምንመለከት ጊዜ ትንሽ የሚከብድ ነው ፤ የምዕራፉ የመጀመሪያዉ ክፍል የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ መቀላቱን ይሸፍናል በመጨረሻ ቁጥሩ ምንድን ተፈጥሮ እንደነበር ሊነግሩት ደቀመዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጡ (ማቴ 14፡ 1-12) ፤ የዘመኑ መጨረሻ ነው የሚመስለው ፡፡ ከዚያም የ5,000 ሰዎች ተአምራታዊ ምገባ ተሰጥቶአል (ማቴ 14፡ 13-21) ፤ ይህ ከኢየሱስ ትልልቅ ተአምራቶች ከተመዘገቡት አንዱ ነው ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ( 14፡ 22)፡ የምግቡን መብዛት ከለመዱት ቦኃላ ኢየሱስ አድርጎ አይተውት ስለነበር ደቀመዛሙርቱ ተተናኮሉት (ደግሞ እንዲያደርግ ይጠይቁጣል) ፤ ወዲያዉኑ ከዚህ ተዓምራት ቦኃላ ኢየሱስ “ ደቀ መዛሙርት ቦታንካይቱ ገብተው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው “(ቁጥር 22) ፡፡ ዋይርስቤ ኢየሱስ በዉኃዉ ላይ በመጎአዝ አገባብ ላይ ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንዴት መስተጋብር እንደፈጠረ የ 5 መግለጫዎች ዋናዋና ሀሳቦችን ይሰጣል ፤ የዋይርስቤ መግለጫ 1) “ እዚህ እኔን አምጦቶኛል “ ፤ በዚህ ስፍራ እግዚአብሄር አስቀምጦናል ፤ ንጉሱ ኢየሱስ በዚህ ሁኔታ ባስቀመጠን ጊዜ የተደላደለ ጉዞ መጠበቅ እንደማንችል በግልፅ የተወሰደ ነው (ዮሐ 16፡ 33) ፡፡ ኢየሱስ እርሱን በብዙ እንድንመስል ለመፈተን ሁልጊዜ እያጠራን ነው ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው ልንታጭበት የምንችለው ሁለት አይነት ማዕበል አለ - “ የማስተካከያ ማዕበል እግዚአብሄር በሚቀጣ ጊዜ እና የተማላ ማድረጊያ ማዕበል እግዚአብሄር እድገታችንን በሚረዳ ጊዜ ፡፡”

ማቴዎስ(14፡ 23-24)፡ የዋይርስቤ 2 መግለጫዉ፡ “ ለእኔ እየፀለየ ነው “(ማር 6፡ 48; ሮሜ 8፡ 34) ፤ ኢየሱስ በመዓበሉ ዉስጥ ያሉትን ሁኔታዎች ያውቃቸዋል እናም ለብቻዉ በተራራው ላይ እንደፀለየው ለእነርሱ ማለደላቸው፡፡ ደቀመዛሙርቶቹ “ ነፋስ ከወደፊት ነበርና በማዕበሉ ተጨንቀው ነበር “(ቁጥር 24) ፡፡

ማቴዎስ(14፡ 25)፡ የዋይርስቤ 3 መግለጫው፡ “ወደ እኔ ይመጣል ፡፡“ ስለ ሰዎስተኛው በማለደ ደቀመዛሙርቱ በነበሩበት ኢየሱስ እየተጎአዘ መጣ ፤ በሚያስፈልገን ጊዜ በኑሮአችን ኢየሱስ ይገለጣል ፡፡ በሚያስፈልገዉ ሁሉንም ነገር በማዎቅ በመጎአዝ ስለ እኛ ፀልዮአል ፤ ምንም በሌለን ጊዜ ኢየሱስ ጥንቃሬአችን ይሆናል (ኢሳ 43፡ 2) ፡፡ ኢየሱስ ትክክለኛው ጊዜ ላይ ይመጣል ፤ እርሱን መቀበል ይጠበቅብናል ፡፡

ማቴዎስ(14፡ 26-27)፡ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ መቅረቡን ባዩ ጊዜ ፈሩ መንፈስ እንደነበርም አሰቡ (ቁጥር 26) ፡፡ የዋይርስቤ 4 መግለጫው፡ “ እድገቴን ይረዳኝል ፡፡ “ ኢየሱስም መልሶ “ አይዞአችሁ ! እኔ ነኝ አትፍሩ አላቸው “ (ቁጥር 27) ፡፡

ማቴዎስ(14፡ 28-31)፡ ጴጥሮስ ወዲያዉኑ ኢየሱስን “ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው “(ቁጥር 27) ፤ ኢየሱስም ወደ እርሱ እንዲመጣ ነገረው (ቁጥር 28) ፡፡ ዋይርስቤ 5 መግለጫው “ እንን ሙሉ ይመለከተኛል ፡፡” ጴጥሮስ እያደረገ በነበረው በደከመ(በፈራ) ጊዜ መስመጥ ጀመረ እንዲረዳውም ወደ ኢየሱስ ጮኸ ፤ ወዲያዉኑም ኢየሱስ የጴጥሮስን እጁን ያዘና “ አንተ እምነት ስለምን ተጠራጠርህ “ ብሎ ጠየቀው (ቁጥር 29-31) ?

ማቴዎስ(14፡ 32-33)፡ ኢየሱስና ጴጥሮስ ታንካይቱ ላይ በወጡ ጊዜ ንፋሱ ፀጥ አለ “ በታንካይቱም የነበሩት በእዉነት የእግዚአብሄር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት ! “ ደቀመዛሙርቱም ሰገዱለት ምክንያቱም በዚህ ጊዜ ወደ እነርሱ መጥቶ ስለነበር ፤ ምናልባት ሁሉንም ሂደት ስላሳወቁአቸዉ አዉቀዉታል ፡፡

ማቴዎስ(14፡ 34-36)፡ ጌንሴሬጥ ምድር ላይ ተቀመጡ ፤ በዚያ ያሉት ሰዎች ኢየሱስን ስላወቁት ሁሉንም በሽተኞች ወደ እርሱ አመጡ ፡፡ “ የልብሱንም ጫፍ ብቻ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ “ (ቁጥር 36)፡፡

ሊዎን ሞሪስ ከዚህ ብዙ ትምህርቶችን ልንማር እንደምንችል ያመለክታል፡

  1. የክርስቶስን ትዕዛዝ ትከተላላችሁ ማለት( በመርከቢቱዓ ዉስጥ ተገኝታችሁ) ማዕበሉን ታስወግዱታላችሁ ማለት አይደለም ፤ በእርግጥ በቁጥር 24 ደቀመዛሙርቱ ከምድር ሩቅ መንገድ ላይ ነበሩ ስለዚህ መመለስ አይችሉም ንፋሱም በእነርሱ ላይ ነበር ፤ በመሉ እንዲሸከማቸዉ በኢየሱስ ላይ ተደገፉ ፡፡
  2. ኢየሱስ ችግሩን (የስሜትን፣ የአካላዊዉንና መንፈሳዊዉን) ያውቀዋል በዚህም ምክንያት እንዴት እንደሚያድነን ያውቃል ፡፡

መዝጊያ

በዚህ ሁሉ ንጉሱ ኢየሱስ የት ነው ? በስራ ላይ ነው ፤ ስለራሳችን ጥንቃቄ ለመዉሰድ የምንሞክርባት ደቂቃ ንጉሱ ኢየሱስን በስራ ላይ እንዳይሆን እና እንዳይጠነቀቅልን መፍቀድን እንቃወማለን ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), pp. 51-52. (All 5 statements provided are from these pages.)

  2. Wiersbe, p. 51.

  3. Leon Morris, The Gospel According to John (The New International Commentary on the New Testament); available at www.logos.com.

ጥያቄዎች

  1. በማቴ(14፡ 1-12) መጥምቁ ዮሐንስ ለምን ነበር አንገቱ የተቀላው ? ዮሐንስ በከንቱ እንደኖረና እንደሞተ ታስባላችሁ ? ለምን ኢየሱስ እንዳላዳነዉ ምን ታስባላችሁ ?
  2. በማቴ (14፡ 14) ኢየሱስ ለቡድኖቹ ርህራሄ ስለነበረው በሽተኞቻቸዉን ፈወሳቸው ፤ በዚህ መንገድ እንዲሰማዉ ያደረጉት ሁኔታዎች ምንድን ነበሩ ? በህይወታችሁ የኢየሱስን ርህራሄ ያሰማ ነገር ገጥሞአቸኋል ?
  3. ኢየሱስ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ 5000 በላይ ወንዶች ሴቶች እና ልጆች ሳይቆጠሩ መገበ ፤ ኢየሱስ አካላዊ ምግብ ብቻ ሊሰጣቸዉ እንደፈለገ ታምናላችሁ ? ወይስ መንፈሳዊ ምግብ ብቻ ? ለምን ወይስ ለምን አላመናችሁ ?
  4. በኑሮአችን ማዕበል ተብሎ የሚጠራ ብዙ ችግሮች አሉ ፤ በማቴ (14፡ 24) ማዕበል ላይ ኢየሱስ ወደ እነርሱ እየተጓዘ ነበር ፤ የሆነ ጊዜ ላይ ኢየሱስ በመርከቧ ላይ ተገኘ ማዕበሉም አረጋገው ፡፡ በህይወታችሁ እናንተን ወይም ማዕበላችሁን ያረጋጋበትን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ?
  5. በማቴዎስ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 14:31-32

“Immediately, Jesus reached out His hand, caught hold of him, and said to him, ‘You of little faith, why did you doubt?’ When they got into the boat, the wind ceased.”

የኢየሱስ በወጀብ መሀል በውሃ ላይ መራመዱ እና ጴጥሮስ እንዲተባበረው መጣራቱ ኢየሱስ ንጉስ እንደሆነ በሀይል ያስረዳል፡፡ ኢየሱስ የሞገድ እና የአውሉነፋስ እንኳን ተቆጣጣሪ እና ባለስልጣን ነበር፡፡ ወጀቡ ሲጀምር፥ ኢየሱስ በተራራ ላይ ብቻውን ይጸልይ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፥ ደቀመዛሙርቱ እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ፥ አይዞአችው እና አትፍሩ እያለ በውሃ ላይ እየተራመደ ተገለጠላቸው፡፡ ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ እጁን ዘርግቶ አለው፥ " አንተ እምነት የጎደለህ፥ ለምን ተጠራጠርክ?"

ልክ እንደ ደቀመዛሙርቱ፥ እናንተም ራሳችሁን በህይወት ወጀብ መካከል ታገኙታላችሁ፡፡ ምናልባት ዛሬ ራሱ፥ የወጀቡ ነፋሶች በዙሪያችሁ እየነፈሱ ይሆናል፡፡ ኢየሱስ ስለናንተ ሊማልድ ቃል ገብቷል፡፡ እጁን ዘርግቶ ይረዳችኋል፡፡ በዛሬው ቀን፥ ጎብዛችሁ እና ጌታ ከእናንተ ጋር እንደሚሆን እና እንደሚረዳችሁ ታምናችሁ ከጀልባዎቻችሁ ውጡ፡፡ በጥርጣሬ አትራመዱ፡፡ የኢየሱስን እጅ በመያዝ እና አብሮአችሁ እንደሆነ በማመን በእርግጠኝነት ተራመዱ፡፡

“ ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና ፦ አንተ እምነት የጎደለህ ስለምን ተጠራጠርክ? አለው፡፡ ወደ ታንኳይቱም በወጡ ጊዜ ነፋሱ ተወ፡፡”

— የማቴዎስ ወንጌል 14:31-32

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኢሳያስ 43:2 – “ በውሃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ካንተ ጋር እሆናለው፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም፡፡”
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 1:8 – “ በእስያ ስለደረሰብን መከራችን ፥ ወንድሞች ሆይ ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ህይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከአቅማችን በላይ ያለልክ ከብዶብን ነበር”
  • 1 ኛ ጢሞቴዎስ 6:15 – “ ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብጹዕና ብቻውን የሆነ ገዢ፥ የነገስታት ንጉስ እና የጌቶች ጌታ ያሳያል፡፡”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 14