The Gospels Matthew

Interacting With Hypocrites

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 125 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ያለፉት 14 ምዕራፎች የአይሁዶችን ኢየሱስን እንደ ንጉስ አለመቀበል ተመልክተናል ፡፡ ኢየሱስ 12 ደቀመዛሙርቱን በአጭር ተልዕኮ ላይ በእስራኤል ዙሪያ ከጠፋዉ ከእስራኤል(አይሁዶች) በግ በኃላ እንዲሄዱ ላካቸው ፡፡ በማቴዎስ 14 ከአይሆዶች ጉዳይ ትንሽ እርፍት ነበር ፡፡ ኢየሱስ ከማዕበል ደቀመዛሙርቱን ለማዳን በዉሃው ላይ ተጎአዘ ይህም ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደሆነና ፍላጎታችንንን እንደሚያውቅ ያሳያል ፡፡ በማቴዎስ 15 ወደ አይሁዶች ክርክር እንመለሳለ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (15፡ 7-9)፡ በቁጥር 1-6 ኢየሱስ እንደገና ከኃይማኖት መሪዎች ጋር መስተጋብር ላይ ነበሩ ፤ ኢየሱስ በትምህርታቸው ጠራቸው ግብዞችም ብሎ ጠራቸው (ቁጥር 7) ፡፡ እንደሚፈልጉት ኢየሱስ እንደማይመልስላቸዉ ስላወቁ መሮዎቹ ጥያቄዎችን ጠየቁት ፤ ይህ የቀጠለ ማመቻቸት ነበር ፡፡ ኢየሱስ የልባቸዉን ድርጊት(ፍላጎት) አገኘው፡ “ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልብ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው ፤ የሰዉም ስርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ….” አለ (ቁጥር ቁጥር 8-9) ፡፡

ማቴዎስ (15፡ 10-11)፡ ይህን ጥናት የኃይማኖት መሪዎችን እንዴት የኢየሱስ ግሳፄ ኃይለኛ እንደ ነበር ለማሳየት በቁጥር 7 ጀመርን ፤ በመቀጠል ህዝቡን በአንድ ላይ በመጥራት “ ስሙ አስተዉሉም ፤ ሰዉን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም ከአፍ የሚወጣው ግን ሰዉን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው “ (ቁጥር 10-11) ፤ ኦሪት ስለ እርኩስ እና ንፁህ ምግብ ነበር ፤ ነገር ግን በእነዚህ ቃሎች ኢየሱስ ከዚህ ቦኃላ የሚበላ ችግር የለውም በማለት እምነታቸዉን ተቃወመዉ ምክንያቱም ሁሉም ምግብ ንፁህ ነው (ማር 7፡ 19; ሐዋ 10፡ 15) ፡፡

ማክአርቱር የገለፀው “ ሰዎች እንደ በዓል የሆነ ነገር በመብላት ራሳቸዉን ያረክሳሉ (በአሮጌዉ ኪዳን ስር) ነገር ግን የሆነንገር ኃጢዓት ነዉ በማለት በአሳባቸዉ ራሳቸዉን ያረክሳሉ ፡፡ “ ይህ ማለት ከአፋችን ከሚወጣው ይልቅ ለምግብ አፋችን ላይ ስለሚቀመጠዉ በጣም እናስባለን ማለት ነው (ያዕ 3፡ 6) ፡፡

ማንም ያ ሲኦል የለም የሚል ከሆነ ለምን ኢየሱስ አስፈለጋቸዉ ? ኢየሱስ ከኃጢዓታችን እና ከሞታችን ሊያድነን መጣ ፡፡ ያ ሲዖል አይኖርም ማለት አትችሉም ለኃጢዓታችን በመስቀል ላይ ስለሞተልን ኢየሱስ ይመስገን ፡፡ ሲኦል ለብዙ በስርዓት ተቀምጦዓል የማትጠነቀቁ ከሆነ አፍን ከፍቶ ይመጣል ፡፡

ማቴዎስ (15፡ 12-13)፡ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ፈሪሳዉያን በቃሎቹ ላይ ጥፍት ወስደዉ እንደነበር ነገሩት (ቁጥር 12) ፤ ኢየሱስም “ የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል “ብሎ መለሰላቸው (ቁጥር 13) ፡፡

በእዉነቱ ማቴዎስ (13፡ 24-30) በስንዴና በአረም ምሳሌ ዉስጥ ስለዚህ ትምህርት ያወራል ፤ ይህ የሚናገረው እግዚአብሄር በግልፅ ስለ ተክል ነገር ነው (መዝ 1፡ 3; ኢሳ 60፡ 21) ፤ ይህ በተጨማሪም እግዚአብሄር ያልተከላቸዉ ሌሎች እንዳሉ ይናገራል ፡፡

ማቴዎስ (13፡ 34-36) ኢየሱስ ለህዝቡ በምሳሌ ብቻ የተናገረበትን ታስታዉሳላችሁ ? በቁጥር 36 ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ለእነርሱ የስንዴዉንና የአረሙን ምሳሌ እንዲገልጥላቸው ጠየቁት ፤ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ገለፀ፡

  • የመልካሙ ዘር ዘሪ የሰዉ ልጅ ነው (ቁጥር 37) ፡፡
  • እርሻዉ አለም ነው (ቁጥር 38) ፡፡
  • መልካሙ ዘር የመንግስት ልጆች ናቸው (ቁጥር 38) ፡፡
  • እንክርዳዱ የክፉዉ መንግስት ልጆች ናቸው (ቁጥር 38) ፡፡
  • እንክርዳዱን የዘራዉ ጠላት ሰይጣን ነው (ቁጥር 39) ፡፡
  • መከሩ የዘመን መጨረሻ ነው (ቁጥር 39) ፡፡
  • ሰብሳቢዎቹ መልዓክቶች ናቸው (ቁጥር 39) ፡፡

ዘመኑ መጨረሻ ላይ እንክርዳዱ ተሰብስቦ ይቃጠላል ፡፡ ለኃጢዓት ምክንያት የሆነውን ሁሉንም ነገር መልዓክት ይሰበስባሉ ወደ ሚነድድ እቶን ዉስጥ ይወረዉሩዓቸዋል ፡፡ በዚህ ዳራ ወደ ማቴዎስ 15 ተመልሰን ስንሄድ፡

ማቴዎስ (15፡ 14)፡ ስለ ስንዴዎና ስለ እንክርዳዱ በምሳሌው ኢየሱስ እንክርዳዱን ለብቻው ተዉት አለ ምክንያቱም በመጨረሻ ስለሚጠፋ ፤ ኢየሱስ በቁጥር 14 ተመሳሳይ ነገር አለ ፡፡ እነርሱ ላይ ሊሆን በሚችለው ለብቻቸው መተው መጥፎዉ ነገር ነበር ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሄር መጣሉን ያመለክታል ፡፡

ማቴዎስ (15፡ 15-16)፡ እንደገና ጴጥሮስ የምሳሌዎችን ገለፃ ኢየሱስን ጠየቀ ፤ እናም እንደገና ኢየሱስ አሁንም አልተረዳችሁም ብሎ ጠየቃቸው ፡፡

ማቴዎስ (15፡ 17-18)፡ ይኸ ከ18ንተኛው ክፍለ ዘመን ምሁር ከ ጄ. ኤ. ቤንጌል የሁሉም ንግግሮች ንግግር ነው፡ “ የባዶነት (የመፀዳጃ ቤት) ቆሻሻ እስካሁን ካልነፃ የሰዉ ልብ ታላቅ(በጣም የሚበልጥ) አይደለም ፡፡ “ ይህ ከዚህ ጥቅስ ጋር ይገናኛል ፤ በመፀዳጃ ቤት ያለ ቆሻሻ የሚለይ ነው ግን ከአፍ መዉጣት ከሚችለዉ ጋር ግን ምንም ነገር አይወዳደርም (መዝ 119፡ 11) ፡፡ በልባችሁ ያስቀመጣችሁት ይወጣል (መዝ 101፡ 3) ፡፡

ማቴዎስ (15፡ 19-20)፡ ከልብ ሁሉም አይነት ክፉ ሀሳብና ድረጊት ሊወጣ ይችላል ፤ ኢየሱስ እነዚህ ክፉ ነገሮች ሰዉን የሚያረክሱ ናቸዉ እንጂ ባልታጠበ እጅ መብላት አይደለም አለ ፡፡

ከዚህ የሚመጡት ጥያቄዎች በልብችን ላይ እንዴት አድርገን ነው የምንሰራው ? ልባችንን እየጠበቅን ከሆነ ከእነዚህ ነገሮች ማንኛውም ችግር አይሆንም ፡፡ ዳግላስ ሸዋን ኦ ዶነል የአፍ ምሳሌን የሚጠራበት ልባችንን ለመጠበቅ መስራት የምንችልባቸዉ ዘጠኝ ነገሮች አሉት፡

የተሰበረና የተፀፀተ ልብ (መዝ 51፡ 17) ፡፡

የተገረዘ ልብ (ሮሜ 2፡ 29) ፡፡

ንፁኅ ልብ (ዕብ 10፡ 22) ፡፡

ያልረከሰ ልብ (1ጴጥ 2፡ 2) ፡፡

አድስ ልብ (ሕዝ 36፡ 26) ፡፡

እዉነተኛ ልብ (ኤፌ 6፡ 5) ፡፡

የሚታዘዝ ልብ (ዘዳ 11፡ 13) ፡፡

ከልብ ማመን (ኤፌ 3፡ 17) ፡፡

ክርስቶስ በልብ እንዲኖር (ኤፌ 3፡ 17) ፡፡

መዝጊያ

ፀሎታችን መሲሁ በልብችሁ እንዲኖር ነው ፤ ይህ ሲሆን የዘረዘርናቸዉ ሁሉም ነገሮች ከልባችሁ ይፈሳሉ ፡፡

  1. John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1153.

  2. MacArthur, p. 1153.

  3. J. A. Bengel, Gomon of the New Testament, v. 1 (Eugene, OR: Wipf and Stock Publishers, 2016), 308; available at www.biblehub.com/commentaries/matthew/15-19.htm.

ጥያቄዎች

  1. በማቴ (15፡ 8-9) ኢየሱስ ስለተናገረው ምን እንደሆነ ምን ታምናላችሁ ? ይህ እንዴት ከኢሳ (29፡ 13-14) ይዛመዳል ? እንደዚህ ቢሆኑም እግዚአብሄር ለመጓዝ ይቀጥላል ? ለምን ወይስ ለምን አይቀጥልም ?
  2. ማቴ (15፡ 11) በሚለዉ ምንድን ታምናላችሁ ? በዚህ ፈሪሳዉያን ለምን ነበር የተሰናከሉት ? ከአፋችሁ በሚወጣዉ ትታገላላችሁ(ትቸገራላችሁ) ?
  3. በማቴ (15፡ 19) ኢየሱስ ከልብ የሚመጣዉን ምንድን ዘረዘረ ? ቁጥር 18 ይህን እንዴት ይገልፀዋል ?
  4. ከከነዓን የሆነች ሴት ለሴት ልጇ ፈዉስን በፈለገች ጊዜ ኢየሱስ ለመናገር እምቢ አለ ፤ ለምን ? በመጨረሻ ለምንድን ሀሳቡን ቀየረ ? ለፈለጋችሁት ለሆነ ነገር ከኢየሱስ ኃላ እንደምታሳድዱ(እንደምትከታተሉ) ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አልተከተላችሁም ?
  5. በማቴዎስ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 15:25

“But she came, knelt before Him, and said, ‘Lord, Help me!’”

ኢየሱስ ወደ ጢሮስ እና ሲዶና አገር ሲሄድ አንዲት ከነናዊት ሴት ኢየሱስ በጋኔን የተያዘቸውን ልጇን እንዲፈውስላት እየጠየቀችው በኢየሱስ ፊት ጮኸች፡፡ ይህች እናት በብዙ ጭንቀት ውስጥ እያለፈች ቢሆንም እና በመከራ ውስጥ ብትራመድም በኢየሱስ ተስፋን አገኘች፡፡ ለፈውስ የማይመስል እጩ ለሆነችው እናት ኢየሱስ መልሱን አዘገየ፡፡ አህዛብ በመሆኗ የእስራኤል ጠላት ነበረች፡፡ ይሁን እንጂ፥ ከነበራት ጠንካራ እምነት የተነሳ በኢየሱስ ፊት በትህትና በመንበርከክ ልጇን እንዲፈውስላት እና እንዲረዳት ተማፀነችው፡፡ ኢየሱስ የነበራትን እምነት እና በእርሱ ላይ ያላትን መተማመን አይቶ የልጇን ጤና መለሰላት፡፡

በህይወታችሁ ችግር ሲያጋጥማችሁ እና ራሳችሁን በጭንቀት ውስጥ ስታገኙ፥ በትህትና ወደ ኢየሱስ ቅረቡ፡፡ የማይመስሉ እጩዎች ወይም ብቁ ያልሆኑ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን አትመልከቱ፡፡ እርሱ ሁሉንም ሰው ይወዳል፡፡ ኢየሱስ ከእናንተ የተለየ የጊዜ ገደብ ሊኖረው ይችላል ቢሆንም በእግሩ ስር ተቀመጡ፣ አውሩት፣ የልባችሁን ሁሉ ለመሲሁ ኢየሱስ አካፍሉት፡፡ መጠበቅ እና ራስን ማዋረድ ለእግዚያብሔር ክብርን ያመጣል፡፡ እጊዚያብሔር ያያችኋል ደግሞም ያውቃችኋል፡፡ ዛሬ ምንም አይነት ነገር ቢገጥማቸሁ፥ በክርስቶስ ያላችሁን እምነት ጠብቁ፡፡ እርሱ ረዳታችሁ ነው፡፡

“ እርሰዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት፡፡’”

— የማቴዎስ ወንጌል 15:25

ተጨማሪጥቅሶች

  • የማቴዎስ ወንጌል 25:23 – “ ጌታውም መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባርያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ ሾምሀለው ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡’”
  • ዕብራውያን 11:6 — “ ያለእምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ፣ወደእግዚያብሔር የሚደርስ እግዚያብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና፡፡ ”
  • Iኛ ጴጥሮስ 1:7 – “ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል፡፡”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 15