The Gospels Matthew

You Are The Christ!

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 126 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በማቴዎስ 15 ኢየሱስ ለእግዚአብሄር የከንፈር አገልግሎት ብቻ የሚሰጡትን የኃይማኖት መሪዎች ተቃዎሞአቸዉ ነበር ፡፡ በማቴዎስ 16 ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ደረሰ ፤ መጀመሪያ “ ከፈሪሳዉያንና ከሰዱቃዉያን እርሾ እንዲጠነቀቁ “ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 6) ፤ ደቀመዛሙርቱም ኢየሱስ የኅይማኖት መሪዎቹን ሲቃወማቸው ሰምተዉ ስለነበር ግንኙነት አላደረጉም ፡፡ ይልቁንም ለቀጣይ ምግብ ማናቸዎም አምጥተዉት ስላልነበረው እንጀራ እዉነት አተኮሩ ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (16፡ 8-12)፡ ከዚያም ኢየሱስ ኃሳቡን “ እናንተ እምነት የጎደላችሁ…..ገና አታስተዉሉምን ? ብሎ በመጠየቅ ደቀመዛሙርቱ ላይ አተኮረ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ ስለ እንጀራዉ እያወራ እንዳልነበር አወቁ ፤ ከሁሉም ቦኋላ ኢየሱስ ከ5000 ሰዎች ምግብ አምስት ሞሰብ እና ከ4000 ሰዎች ምግብ ሰባት ሞሰብ እንደመለሰ አይተዉ ነበር - በእያንዳንዱ ጊዜ እንጀራ ተርፎአል ፡፡ ኢየሱስ ይህን ብቻ በግልፅ የገለፀላቸዉ ከፈሪሳዉያንና ከሰዱቃዉያን ትምህርት እያስጠነቀቃቸዉ እንደነበር እንደረዱት ነበር ፡፡

ማቴዎስ (16፡ 13-14)፡ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ወደ ፊልጶስ ቂሳሪያ አገር መራቸዉ ደቀመዛሙርቱንም “ ሰዎች የሰዉን ልጅ ማን ይሉታል ?“ ብሎ ጠየቃቸዉ ደቀመዛሙርቱ በህዝቡ መካከል ይንቀሳቀሱና ይማሩ ስለነበር ሰዎች ስለ ኢየሱስ ምን እንደሚያስቡ ያዉቃሉ ፡፡ ብዙ አስተያየቶችን አቀረቡ፡ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኤልያስ፣ ኤርምያስ፣ ከነቢያት አንዱ ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የአሜሪካዊያን ባህል ኢየሱስን እንዴት ይገልፀዋል ? ሙስሊሞች ታላቅ ነብይ ነበር ይላሉ ፤ አንዳንድ ኃይማኖቶች ኢየሱስ አስደናቂ መምህር ነበር ይላሉ ፡፡ መገናኛ ሚዲያዎችም የሚያስደንቅ የሞራል እና ታላቅ አስተማሪ ብለዉ ይጠሩታል ፤ ሌሎች ደግሞ ታላቅ ታሪኪዊ ስዕል ነዉ ይላሉ ፤ ነገር ግን ጥቂቶች መሲሁ ነዉ ይላሉ ምክንያቱም ትክክለኛ አፈራረዱን ስለሚያስቡ ፡፡ የእኛ ስራ ግን በባህል በግልፅ ለመነጋገር ኢየሱስ ማነው የሚለዉን ነው ፤ ይህን ለማድረግ እያንዳንዳችን የምናስበዉ ኢየሱስ ማነዉ የሚለዉን ለመወሰን ያስፈልገናል ፡፡

ማቴዎስ (16፡ 15-16)፡ በመቀጠል ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ቀጥተኛ ጥያቄ ጠየቃቸው፡ “ እናንተስ እኔን ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ጴጥሮስ በፍጥነት መልሶ “ አንተ መሲሁ የሕያው የእግዚአብሄር ልጅ ነህ አለው “ “ ህያዉ እግዚአብሄር “ የሚለው ቃል ለእግዚአብሄር የብሉይ ኪዳን ስምን ይገልፃል - ጅሆቫህ ፤ ዘዳ (5፡ 26) ጠየቃቸው “ ከስጋ ለባሽ እኛ እንደ ሰማን በእሳት ዉስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያዉን አምላክ ድምፅ ሰምቶ በህይወቱ የኖረ ማነው ? “ ይህ ህያዉ እግዚአብሄር ለእናንተ ይጠነቀቃል ፡፡ “ ለእንናተ ኢየሱስ ማነው ?” የሚለዉን ጥያቄ በአንድ ቃል ለመመለስ ትንሽ ጊዜ ዉሰዱ ፡፡

ማቴዎስ (16፡ 17)፡ ኢየሱስ ይህን እዉነት ለእርሱ እግዚአብሄር ስለገለጠለት ጴጥሮስ የተባረከ ነው አለው ፡፡ እግዚአብሄር በማንኛዉም ህይወት ላይ በየተኝዉም ጊዜ ሊገለጥ ይችላል ማን እንደሆነም ይገልጣል ፡፡

ማቴዎስ (16፡ 18)፡ ከዚያም ኢየሱስ የስምዖንን ስም ወደ ጴጥርስ ቀየረው እና “ በዚችም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሰራለሁ የገሀነም ደጆችም አይችሉዓትም “ አለ ፤ ሁለት ተመሳሳይ ቃሎች እዚህ ተጠቅሞዓል፡ “ ጴጥሮስ “(የጴጥሮስ ስም) ማለት ትንሽ ድንጋይ ሲሆን “ ጴጥራ” (“ በዚህ አለት “) ማለት መሰረት ነው ፡፡ ለቤተ ክርስቲያን መሰረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ 1ጴጥ (2፡ 6) ኢየሱስን እንደ “ የተመረጠና የከበረ ደንጋይ በፂዎን አኖራለሁ “ ይጠቅሰዋል ፤ በሐዋ (4፡ 11) ጴጥሮስ በእርግጥ የመዓዘን ድንጋይ የነበረዉን ኢየሱስን አይሁዶች ገፍተዉት እንደነበር አመለከተ ፤ በኤፌ (2፡ 20) ጳዉሎስ “ በሐዋሪያትና በነቢያት መሰረት ላይ ታንጻችኋል የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው “ ገልፆዓል ፡፡ ቤተ ክርስቲያን “ ኤክሌሺያ “ ወይም “ የተጠራ “ በአድስ ኪዳን 114 ጊዜ የተጠቀሱ ናቸው ፤ ቤተ ክርስቲያን ሁሉም በሚሰበሰቡበት ትልቅ ህንፃ አያስከትልም ፤ በጋራ ስለ ሚመጡት “ የተጠሩት” እርስ በእርሳቸዉ ስለ ሚጠባበቁት ከዚያም የጠፋዉን በግ ለመፈለግ ተመልሰዉ ስለ ሚሄዱት ነበር ፡፡

ማቴዎስ (16፡ 19)፡ “ የመንግስተ ሰማያትን መክፍቻዎች እሰጥኃለሁ ….” ቁልፎች ያሉት የሆነን ነገር መክፈትም መዝጋትም ይችላል ፤ ቁልፎቹ የስልጣን ምልክቶች ነበሩ ፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ የሐዋሪያነት ስልጣን ሰጥቶአል ፡፡ በምድር ላይ የምናጸናቸው ምንድን ናቸው ? የእግዚአብሄር ባልሆነ በምድር ላይ የምንፀና ነገሮች ከሆንን ነገሮቹ ነፃ የማይሆኑ ከሆነ ነገሮቹ ቀድመው ከሰማይ ጋር የተያያዙ ናቸው ፡፡ ማንኛዉም በሰማይ ያጣነዉ በዚህ በምድርም ላይ ልናጣዉ እንችላለን ፡፡ ጥቂት ምሳሌዎች በማቴዎስ(10፡ 8) ኢየሱስ ለሐዋሪያቱ ሰዎችን ከበሽታቸዉ እንዲፈዉሱ፣ የሞተን እንዲያስነሱ፣ ከለምፅ እና ከክፉ ሰዎችን እንዲያነፁ ስልጣን ሲሰጣቸዉ ተገልፀዋል ፤ ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ኃይል እንዲገልጡ ስልጣን ሰጣቸዉ ፡፡ ሰማይ ምን እንደሚመስል ባለን ጠባብ አስተሳሰብ ምክንያት በምድር ላይ የምናደርገዉን እንገድበዋለን ? (ለምሳሌ ለፈዉስ መፀለይ አልችልም እንላለን ?) በስልጣናችን ሙሉ መተማመን ስናገኝ በሰማይ የሆነውን በምድር እናደርጋለን ፡፡

ማቴዎስ(16፡ 20)፡ ደቀመዛሙርቱ “ እኔ መሲሁ እንደሆንኩ ለማንም እንዳትናገሩ” ተብለዉ ተነገሩ ምክንያቱም ለአለም ኢየሱስ እንደነበር ለመግለፅ ጊዜ ነበር ፡፡ አሁንም ዋጋ ይከፍላል፣ ይሞታል ከዚያም ማንነቱ ከመገለጡ በፊት ወደ ህይወት ተመልሶ ይመጣል ፡፡

ማቴዎስ (16፡ 21-23)፡ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ እና ዋጋ እንደሚከፍል(እንደሚሰቀል) ለደቀመዛሙርቱ መናገር ጀመረ ፤ ኢየሱስ በህይወቱ ለሚፈፀመዉ ጥሪ ላይ በጣም ያተኮረ ሆነ ፡፡ እንደ መሲህ ለይቶት ስለነበር በተናገረዉ ነገር ጴጥሮስ ኢየሱስን ገሰፀዉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ጴጥሮስን የገለፀው የሐዋሪያዉ ፈጣን ድርጊቶች አንዳንድ ጊዜ ራሱን ከራሱ በላይ ያገኘዋል ለምሳሌ በዉሀው ላይ ከጀልቧዋ ወደ ኢየሱስ ለመጓዝ በመሞከር ( ማቴ 14፡ 22-32) ወይም በፍፁም ኢየሱስን ላይከዳው ቃል መግባቱ (ማቴ 26፡ 35) ወይም በመጨረሻዉ ራት ላይ እግሮቹን እንዲያጥበዉ ለኢየሱስ ለመፍቀድ እምቢ ማለቱን (ዮሐ 13፡ 5-11) ፡፡ በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ዞሮ “ ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይን አለው !” ምክንያቱም ጴጥሮስ ስለ እግዚአብሄር ፍላጎት አያስብም ነበር የሰዉን እንጂ፡፡ ኢየሱስ በፈተናዉ ጊዜ ለሰይጣን መልሶለት እንደነበረው ለእርሱም መለሰለት ፡፡

ማቴዎስ (16፡ 24-26)፡ ለደቀመዛሙርቱ በእግዚአብሄር ሀሳብ እንጂ በሰዉ ኃሳብ ላይ ትኩረት ማድረግ የማይፈልጉ “ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ “(ቁጥር 24) ፡፡ ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ላይ ለማተኮር ህይወታችሁን ለማጣት ፈቃደኛ መሆን ይጠቅባችኃል ፡፡

ማቴዎስ (16፡ 27-28)፡ ኢየሱስ “ የሰዉ ልጅ ይመጣል…….ለሁሉም እንደ ስራዉ ያስረክበዋል “ ፤ አንዳንዶች በመንግስቱ የሰዉን ልጅ መምጣት ሳያዩ ሞትን አይቀምሱም ፡፡ ለእኛ ጥያቄዉ ኢየሱስ ያለዉን እንዴት እናድርግ ነው ? መዉሰድ የምንችለዉ ተጨባጭ ደረጃዎች ምንድን ነው ?

ዋይርስቤ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሁለት ወደ ህይወት መቅረቢያ ነገሮችን እንዳቀረበ ተናግሮአል፡

ራስን መካድ ወይም ለራስ መኖር

መስቀሉን መሸከም(መቀበል) ወይም መስቀሉን አለመቀበል

ክርስቶስን መከተለ ወይም አለምን መከተል

ህይወትን ማጣት ወይም ህይወትን ማዳን

አለምን መተዉ ወይም አለምን ማግኘት

ነፍስን መጠበቅ ወይም ነፍስን ማጣት

ሽልማቱንና ክብሩን መካፈል ወይም ሽልማቱንና ክብሩን ማጣት

ንጉሱን መከተል ከባድ ነው ፤ ተግቶ መስራት እና በሞት ማድረግን ይፈልጋል ፤ ወይም ቀላልና ምቹ የሆነዉን ነገር ግን ወደ ጥፋት የሚመራዉን ሰፊዉ መንገድን የሚወክለዉን መምረጥ እንችናለን ፤ ጠባቡን መንገድ መምረጥ አስቸጋሪና ዋጋ ያስከፍላል ግን ወደ ህይወት ይመራል ፡፡

መዝጊያ

ወንጌል ለቀራጮችና ለኃጢዓተኞች የታሰበ ነው ፤ ወንጌል ለአይሁዶችና ለአሕዛቦች የታሰበ ነው ፡፡ ለራሳችን ብቻ አድሱን አቁማዳ ሜዝ የለብንም ነገር ግን ሁሉም ስለ እግዚአብሄር መስማትና ከኃይማኖት ነፃ የመሆን እድል አላቸው ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል በቋሚነት በምታጠኑ ጊዜ መላዉ ማህበረሰባችሁ ሊቀየር እንደሚችል እናምናለን ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1172.

  2. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 49.

ጥያቄዎች

  1. በማቴ (16፡ 1-4) ኢየሱስ ለምንድን ክፉና አመንዝራ ትዉልድ አላቸው ? በኢየሱስ ላይ ከማድረግ ይልቅ ራሳችሁን በምልክቶች ላይ ስትመለከቱ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ?
  2. እርሾ ምንድን ነው ? እንዴት እንጀራን(ዳቦን) ይጎዳል(ያደርጋል) ? በማቴ (16፡ 6-12) ኢየሱስ ሲያወራ የነበረው ስለ ዳቦ ነው ?
  3. ኢየሱስ ጴጥሮስን “ እኔን ማን ትሉኛላችሁ “ ብሎ በጠየቀዉ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስ የህያዉ እግዚአብሄር ልጅ ክርስቶስ እንደ ነበር መለሰለት ፤ ኢየሱስም በዚህ አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኑን እንደሚሰራ እና የገሀነም አይቋቋሟቱም ብሎ ተናገረ ፡፡ እነዚህ ሰዎስት ጥቅሶች ማቴ (16፡ 18); ሐዋ (4፡ 11) እና ኤፌ (2፡ 20) ይህን ለመግለፅ እንዴት በጋራ ይሰራሉ ? ኢየሱስ የጠቀሰው “ አለት “ ምንድን ነበር ?
  4. በማቴ (16፡ 22) ጴጥሮስ ኢየሱስን ለምን ገሰፀዉ ? ለኢየሱስ ጴጥሮስ “ አንተ ሰይጣን ወደ ኋላዬ ሂድ “ ለምን አለው ? ከዚያም ኢየሱስ እራሳቸዉን እንዲክዱ መስቀላቸዉን እንዲወስዱና እንዲከተሉት ነገራቸው ፤ ይህ ጥቅስ እንዴት ይናገራችኋል ?
  5. በማቴ (16፡ 25-26) እንደገና ደግማችሁ ህይወታችሁን እንዴት ታጡታላችሁ ? ሙሉ አለምን አግኝተዉ ነፍሳቸዉን በሚያጡ እንዴት ታስቡታላችሁ ?
  6. በማቴዎስ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 16:15

“‘But you,’ He asked them, ‘who do you say that I am?’”

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ሰዎች እርሱ ማን እንደሆነ እንደሚሉ ጠየቃቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱን ለአገልግሎት ልኳቸው ስለነበር፥ ለጥያቄው መለስ ነበራቸው፡፡ በመቀጠል ኢይሱስ ደቀመዛሙርቱን ተመልክቶ በቀጥታ ጠየቃቸው፥ አላቸውም፥ "እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?" ደቀመዛሙርቱ ሁሉን ትተው ኢየሱስን ተከተሉ፡፡ በተአምራቱ ሰዎችን ሲፈውስ፣ የጠፉትን ሲመልስ እና ለሰዎች ሲሰጥ አይተዋል፡፡ ከእርሱ ጋር አብረው ተራምደዋል፡፡ ጴጥሮስም መለሰ፥ " አንተ ክርስቶስ የህያው እግዚያብሔር ልጅ ነህ፡፡ "

ዛሬም ይህንን ጥያቄ ራሳችሁን ጠይቁ፡፡ ኢየሱስን በህይወታችሁ ተቀብላችሁ ከእርሱ ጋር ስትራመዱ፥ ኢየሱስ ማን ነው ትላላችሁ? መልሶቻችሁ ከሚገጥሟችሁ ነገሮች የተነሳ ከቀን ወደ ቀን ሊለያዩ ይችላሉ ፥ ኢየሱስ አዳኛችሁ፣ ጓደኛችሁ፣ ሀይላችሁ፣ ረዳታችሁ፣ ሸክማችሁን የሚሸከም፣ ደስታችሁ ወይም ተስፋችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ዛሬም ለሌሎች ለመመስከር ዝግጁ ሁኑ፡፡ በህይወታቸው ያላችሁት ብቸኛ ምስክር እናንተ ብቻ ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ይብራ፡፡

“‘ እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደሆንኩ ትላላችሁ? አላቸው፡፡’”

— የማቴዎስ ወንጌል 16:15

ተጨማሪጥቅሶች

  • የዮሐንስ ወንጌል 15:27 – “እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋር ኖራችኋልና ትመሰክራላችሁ፡፡ ”
  • የሐማርያት ሥራ 22:15 – “ባየኸው እና በሰማኸው በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆንለታለህና፡፡”
  • Iኛ ጴጥሮስ 3:15 – “ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት፡፡ በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየኋነት እና በፍርሃት ይሁን፡፡”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 16