The Gospels Matthew

His Transformation Before Men

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 127 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የቀደሞው ቀረጥ ሰብሳቢ ማቴዎስ በኢየሱስ ስልጣን ላይ እና እንደ ንጉስ ተግባሩ ላይ አተኮረ ፡፡ በማቴዎስ 17 ለጠቅላላ ምዕራፉ አንድ ቃል መጠቀም እንችላለን፡ መለወጥ - የመልክ መቀየር፣ መቀየር ወይም ወደ አድስ መልክ መለወጥ ፡፡ ኢየሱስ በደቀመዛሙርቱ ፊት በተራራዉ ላይ ይህን አደረገ ፤ ስታንለይ ቶዩዝያንት ይህንን እንደ “ የወደፊቱ መንግስት እዉነተኛነት ማረጋገጫ “ ብሎ ገልፆታል ፡፡ በመለወጡ ዉስጥ ኢየሱስ ራሱን ከሞቱ፣ ከመቀበሩና ከመነሳቱ በኋላ ወደፊት የሚሆነውን አሳየ ፤ መለወጡ በሚገባ(በደንብ) በሚያዉቁት ፊት ለፊት ይመጣል ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (17፡ 1-3)፡ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ በደንብ የሚቀርቡትን ወደ ተራራው ላይ ወሰዳቸው፡ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ወንድሙ ዮሐንስ (ቁጥር 1) ፡፡ በኢየሱስ እያንዳንዱ ጠቃሚ ክስተት በተራራዉ ላይ ከሆነው ተመሳሳይ መሆኑን ያስታውሳል ፡፡ ምናልባት መለወጡ 9,400 ጫማ በሚረዝመው በአርሞኒየም ተራራ ላይ ተካሂዶአል ፡፡ የኢየሱስ መልክ ሙሉ በሙሉ ተቀይሮአል ፤ ዋይርስቤ መለወጡን ወደ አራት ነገሮች ያመለክታሉ ይላል፡ “ የሰዉነቱ ክብር - ፊቱ አንፀባረቀ አካላዊም መልኩ ተቀየረ (ቁጥር 2) ፤ የመንግስቱ ክብር (ቁጥር 4-5) ፤ የመስቀሉን ክብር (ቁጥር 8-9) ፤ የመታዘዙን ክብር (ቁጥር 12) ፡፡”

በቁጥር 3 ኢየሱስ ህግ ከሚወክለዉ ሙሴ እና ነቢያትን ከሚወክለው ኤልያስ ጎን ተቀላቅሎ ነበር ፤ ማቴ (5፡ 17) ተመልከቱ “ እኔ ግን ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈፅም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም ፡፡ “ የእነዚህ የሰዎስቱ በአንድ ላይ የሚታየዉ ስዕል በኢየሱስ መፈፀሙን የእግዚአብሄርን ማረጋገጫ ይገልጣል ፤ ቶይዝያንት የሚለው “ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከክርስቶስ ጋር በከበረ ሁኔታ መገኘት በብሉይ ኪዳን የመንግስቱ መርህ ታላቅ ማረጋገጫ ነው ፡፡ “

ማቴዎስ (17፡ 4)፡ ሁል ጊዜ ጴጥሮስ በግልፅ ይናገራል ፤ ለኢየሱስ፣ ለሙሴና ለኤልያስ ሰዎስት ድንኳን ለመስራት አቀረበ ፡፡ ምናልባትም ጴጥሮስ ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን መገኘት ጋር መቆየት ፈለገ ፡፡

ማቴዎስ (17፡ 5)፡ አሁንም ጴጥሮስ “ የመንግስቱን ክብር “ እየተነገረና እያሳወቀ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሄር አቋርጦ፡ “ የምወደዉ ልጄ እርሱ ነው ፤ በእርሱ ደስ የሚለኝ ፤ እርሱን ስሙት !” ማቴ (3፡ 17) በኢየሱስ ጥምቀት ላይ ተመሳሳይ ቋንቋ አለው ፡፡ መዝ (2፡ 7) ወደ እነዚህ የተለዩ ቃላቶች(ኢሳ 42፡ 1) የሚያመለክት መሲሀዊ ትንቢት ነው ፤ በተራራው ላይ ይህ መገናኘት የኢየሱስ ማንነትና የወደፊት መንግስቱ በመረጋገጡ ታላቅ ደረጃ ነበር ፡፡ ሁሉም ነገር ያጠናነው ወደ መሲሁ ያመለክታል ፡፡

ማቴዎስ(17፡ 6)፡ ይህንን አይተዉ የነበሩት በእግዚአብሄር መገኘት ዉስጥ እንደነበሩ ስላወቁ በመዉደቅ እግዚአብሄርን አከበሩ ፡፡

ማቴዎስ (17፡ 7)፡ “ ክብር “ ሚለው ቃል ክብደት ማለት ነው ፤ አይሁዶች በሚፀልዩ ጊዜ ያለሟቋረጥ በኃይል ይጓጓሉ ፤ ስለዚህ በቀላሉ በእግዚአብሄር መገኘት ያለው ክብደት አንገታችን ብቅ እንድናደርግ ይመራናል በተጨማሪም በጉልበቶችችን እንበረከካለን ፡፡ ኢየሱስ ወዲያዉኑ “ አትፍሩ “ በማለት አጽናናቸው ፤ በተራራዉ ላይ እያሉ የእግዚአብሄርን ድምፅ ሰሙ ፡፡

ማቴዎስ (17፡ 8-9)፡ ደቀመዛሙርቱ ሁለቱንም ኤልያስንና ሙሴን በሚመለከቱ ጊዜ ሄደዋል ፤ ኢየሱስ፣ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ብቻ ቀርተዋል ፡፡ ከተራራው እንደወረዱ ኢየሱስ “ የመስቀሉን ክብር “ ማቆም ጀመረ ፤ ኢየሱስም አይተዉት የነበረውን ትንቢቱ ወደ እዉነት እስኪመጣ ድረስ ያም “ የሰዉ ልጅ ከሞት እስኪነሳ” (ቁጥር 9) ለማንም እንዳይነግሩ ነገራቸው ፡፡ በማቴዎስ አምስት ጊዜ የእግዚአብሄር ጊዜ እስኪፈፀም ድረስ ስለ እርሱ ለማንም እንዳይናገሩ ደቀመዛሙርቱን አስጠነቀቃቸው፡ ማቴ 8፡ 4; 9፡ 30; 12፡ 16; 16፡ 20; 17፡ 9 ፡፡

ማቴዎስ (17፡ 10-12)፡ ደቀመዛሙርቱ ለምን ኤልያስ በመጀመሪያ እንደሚመጣ ጠየቁት (ቁጥር 10) ፤ ኢየሱስ ቀድሞ ኤልያስ ይመጣል ብሎ መለሰላቸው (ሚል 4፡ 5-6; ማቴ 17፡ 11) ፤ መጥምቁ ዮሐንስ የኤልያስ ቃል አመጣ አልተቀበሉትም ነበር ስለዚህ ኤልያስ መጥቶ ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ ኢየሱስ “ የመታዘዙን ክብር “ ይወስዳል (ቁጥር 12) ፡፡

የተወያየናቸዉ እያንዳንዱ ክብሮች - ሰዉነቱ፣ መንግስቱ፣ መስቀሉ የመታዘዙ የመጨረሻ ሚና ላይ ጥገኛ ናቸው ይህ ማለት የራሱ ባቻ የሆነዉን ስልጣን ለሌላ ይለቃል ፡፡ በእዉነቱ ኢየሱስ ህይወቱን በመስቀል ላይ እስኪ ሰጥ ድረስ የወደፊት መንግስት ሊሆን አይችል ፡፡ ከኢየሱስ ጋር በተራራዉ ላይ የነበረዉ ደቀመዝሙር ያዕቆብ ለመሞት የመጀመሪያው ነበር (ሐዋ 12፡ 1-2) ፤ ዮሐንስ በፈጥሞ ደሴት ታስሮ ነበር እፈላ ዘይት ላይ ተቀመጠ ፤ ከሌሎቹ ደቀመዛሙርት ረጅም ጊዜ ቢኖርም ዋጋ ከፍሏል ፡፡ ጴጥሮስ መከራ የተቀበለዉ በሮም ከላይ ወደ ታች በመሰቀል ሞተ ፡፡ እንደ መግለጫው “ ህይወትን ለመቅመስ ሞትን መቅመስ ይጠበቅባችኋል ፡፡ “

ኢየሱስ ለጴጥሮስ፣ ለያዕቆብና ለዮሐንስ ከእነርሱ ምንድን ሊሆን እንደሚያስፈልግ ስዕል እየሳለላቸዉ ነበር ፤ ሁሉም ለወንጌሉ ህይወታቸዉን ሰጡ ፡፡

ጴጥሮስ የኢየሱስን መለወጥ አስፈላጊነት በእነዚህ ቃሎች ገልፆታል፡ “ የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መምጣት አስታወቅናችሁ ፡፡ ከገናናው ክብር በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሄር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና ፤ እኛም በቅዱስ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን ፡፡ ከእርሱም ይልቅ እጅግ የፀና የትንቢት ቃል አለን ፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮኮብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ ፡፡ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመፅሐፍ ያለዉን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደለትም ፤ ትንቢት ከቶ በሰዉ ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሄር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተዉ ተናገሩ “ (2ጴጥ 1፡ 16-21) ፡፡

መዝጊያ

የመለወጡ ሂደት በፍጥነት ጴጥሮስን ቀየረው ለወንጌል ምክንያትም ህይወቱን ለመስጠት ወደ ሚዘጋጅበት ቦታ ወሰደው (አፈጠነው) ፡፡ ለምን ? ምክንያቱም ጴጥሮስ ሁልጊዜም ሞት ወደ ህይወት እንደሚመ ራ ስላወቀ ፡፡

  1. Stanley Toussaint, Behold the King: A Study of Matthew (Grand Rapids, MI: Kregel, 1980), pp. 210-211.

  2. Warrer W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), pp. 60-61.

  3. Toussaint, pp. 210-211

ጥያቄዎች

  1. “ መልኩ የተቀየረ(ተለወጠ) “ ሆነ ማለት ምንድን ነው ? ኢየሱስ በተቀየረ ጊዜ ምንድን ነገሮች ሆኑ ?
  2. ማቴ (17፡ 10-13) እንዴት ትገልፁታላችሁ ? የኤልያስ መምጣት እንዴት ወደ መሲሁ ያመለክታል ? (ሚል 4፡ 5)
  3. በማቴ (17፡ 3) ሙሴ እና ኤልያስ ለምን ታዩ ? (ማቴ 5፡ 17)
  4. እንፍርፍሪት (ጨረቃ) የያዘዉ ሰዉ ለእርሱ ደቀ መዛሙርቱ በፀለዩለት ጊዜ ለምን ነበር ያልተፈወሰው (ማቴ 17፡ 14-20) ? ስለ ሆነ ሰዉ የተፈወሰ እንዲሆን ምን ያክል እምነት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል (ሮሜ 12፡ 3) ? ለሆኑ ሰዎች ፀልያችኁልቸዉ ካልተፈወሱ ምንድ ታጠቃልላላችሁ (ትላላችሁ) ?
  5. በማቴ (17፡ 24-27) ለጴጥሮስ ስለ መቅደሱ ግብር ኢየሱስ ለማሳየት የሞከረዉ ምንድን ነበር ? “ ልጆች ንፁሀን ናቸዉ “ ማለት ምንድን ማለት ነው ? ዛሬ ለእናንተ ይህ እንዴት ነዉ አግባብ የሚሆነው ?
  6. በማቴዎስ 17 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 17:2a

“He was transformed in front of them, and His face shone like the sun.”

ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብን እና ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ወጣ፥ በዚያም የኢየሱስ መልክ በፊታቸው ሲለወጥ አዩ፡፡ አጋጣሚው በዚህ ሳያበቃ፥ ሙሴ እና ኤልያስ ተገልጠው ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩዋቸው፡፡ በድንገትም እግዚያብሔር አብ ከሰማይ ተናገረ በዚያም፥ ኢየሱስ እግዚያብሔር ልጅ ነው፣ እግዚያብሔር አብ ኢየሱስን ይወደዋል እና ሁሉም ኢየሱስን መስማት እና መታዘዝ አለባቸው ፥ የሚሉትን ሶስጥ ገላጭ ሀሳቦች አወጀ፡፡ እግዚያበሔር አብ ከተናገረ በኋላ ደቀመዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ ፥እጅግም ፈርተው ነበር፡፡ የኢየሱስ መልክ በፊታቸው ሲለወጥ ከእርሱ ጋር አብረው በመሆናቸው ፥ የጴጥሮስ፣ የያዕቆብ እና የዮሐንስ ሕይወትም ተለውጧል፡፡

እንደ ክርስቶስ ተከታይ በህልውናው ወስጥ ጊዜ ስታሳልፉ፥ እግዚያብሔር የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን በመስጠት ህይወታችሁን ይቀይራል፡፡ "ቆይ ግን፥ ኢየሱስን አውቀዋለሁ፥ ህይወቴ ግን እንደ ተለወጠ አይሰማኝም" ብላችሁ እያሰባችሁ ይሆናል፡፡ ለእናንተ ምሳሌ እንዲሆን፥ ኢየሱስ ሆን ብሎ ወደ ተራራ የሚወጣው ከአባቱ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ነው፡፡ ዛሬም ከግርግሩ ፣ ከልማዱ እና ከሚያጨናንቀው ቦታ ፈቀቅ በሉ፡፡ እሱን ወደ መምሰል እንዲያስጠጋችሁ እየጠየቃችሁት፥ ከጌታ ጋር ጊዜ አሳልፉ፡፡ ይህን ማድረግ ልማዳችሁ ስታረጉት፥ በመንፈሱ ልባችሁን ሊቀይር ቃል ገብቶላችኋል፡

“ በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ”

— የማቴዎስ ወንጌል 17:2

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 139:23-24 — “ አቤቱ ፥መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ ፤ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ፡፡”
  • ሮሜ 12:2 — “ የእግዚያብሔር ፈቃድ እርሱም በጎ እና ደስ የሚያሰኝ ፍፁምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን አለም አትምሰሉ፡፡ ”
  • ኤፌሶን 4:22-23 — “ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 17