Go and Tell of the Risen Lord!
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 28 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በማቴዎስ ይህ የመጨረሻዉ ትምህርታችን ነው ፡፡ ትናትና ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ስለቻለዉ ከባድ ስቃይ ተመልክተናል ነገር ግን ዛሬ በትንሳኤዉ ምክንያት ታሪኩ እንዴት በደህና እንዳበቃ እናያለን ፡፡ ሐዋሪያው ጳዉሎስ ስለ ኢየሱስ ትንሳኤ ብዙ ፅፎአል ከትንሳኤ ዉጭ ኢየሱስ ሌላ ሰዉ እንደሆነ ጠቅሶታል (ሮሜ 6፡ 4) ፤ ትንሳኤዉ ለእርሱ እንደ ንጉሳችን፣ እንደ መሲሀችን፣ እንደ አዳኝቻን ቦታዉን ለመውሰድ አስፈላጊ ነበር ፡፡ ክርስቶስ በመቃብር ስላልሆነ መታመን እንችላለን (ሮሜ 8፡ 34) ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (28፡ 1-4)፡ “ ከሰንበት በኋላ “ በቅዳሜ ፀሀይ መጥለቅን ያመለክታል ወይም ጥቂጦች የጠቀሱት የእሁድ ጥዋት መክፈቻን አመልክተዋል ፡፡ ይህ ማለት ከአርብ ፀሀይ መጥለቅ እስከ እሁድ ፋሲካ መክፈቻ ድረስ ያለዉን ጊዜ እንመለከታለን ፤ ኮንስታብል የሚጠቅሰዉ ሁለቱ ማሪያሞች “ መቃብሩ ጋር የጥበቃዉ አለቃዉ ቆሞ እንደነበር ብግልፅ አያዉቁም “ ፤ የኢየሱስን ሰዉነት በመቀባት ተግባራቸዉ ላይ አትኩረዉ ነበር ፡፡ መለዓኩ በድንገት ሲገለጥ ሀይለኛ መሬት መንቀጥቀጥ ነበር ከመቃብሩም መግቢያ ላይ ድንጋዩን አንከባሎ በላዉ ላይ ተቀመጠ (ቁጥር 2) ፡፡ ሉቃ (24፡ 4) ሁለት መልዓክት እንደ ነበሩ ያሳያል ፡፡ በማቴ (27፡ 51) የመሬት መንቀጥቀጡ በክርስቶስ ሞትም ላይ በግልፅ ታይታል ፤ በትንሳኤዉም ጊዜ እንደገና የመሬት መናወጥ ነበር ፡፡ በቁጥር 3 መልዓኩ የቅድስና መልክ ነበረው ፤ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነበር ( ማቴ 17፡ 2; ሐዋ 1፡ 10) ፡፡ አንድ ማብራሪያ ጥበቃዎቹ በጣም ተንቀጥቅጠዉ ስለ ነበር እንደ ሞቱ ያመለክታል (ቁጥር 4) ፡፡
ማቴዎስ (28፡ 5-10)፡ መለዓኩ የተሰቀለዉን ኢየሱስን ለመመልከት መጥተዉ እንደ ነበር ሰለሚያውቅ አትፍሩ (ቁጥር 5) ! መልዓኩም “ እንደ ተናገረ ተነስቷል በዚህ የለም ! ”(ቁጥር 6) ብሎ በማሳወቅ ሴቶቹን ነገራቸው ፡፡ ይህን ኢየሱስ መቼ ተናገረ ? ማቴ( 12፡ 40; 16፡ 21; 17፡ 9, 23; 26፡ 32) ሁሉም ወደ ኢየሱስ ሞት፣ መቀበር እና ከሰዎስት ቀናት በኋላ መነሳት ያመለክታሉ ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የክርስቶስን መነሳት መልካም ዜና መያዝ ለመቻል የመሰቀሉን መጥፎ ዜና እና ሞቱን ከልክ በላይ ያስባሉ (ቁጥር 7) ፡፡ ክርስትና በትንሳኤ ላይ እንጂ በሞት ብቻ ላይ የተደገፈ አይደለም ፤ ነገር ግን እዉነተኛ ህይወት ለመፈለግ ሞትን መለማመድ ይገባናል (ማቴ 10፡ 39; 16፡ 25; 28፡ 6) ፡፡
መለዓክቱ ደቀ መዛሙርቱን ለመንገር ከመሄዳቸዉ በፊት(ቁጥር 8) ባዶዉን መቃብር መጥተዉ እንዲያዩ እና በግላቸዉ ትንሳኤዉን እንዲቀምሱት ሴቶቹን ጋበዙዓቸው (ቁጥር 6) ፡፡ እኛ ሁላችንም በግላችን ስለ እርሱ ሄደን ከመመስከራችን በፊት ትንሳኤዎን ለንለምደዉ ይገባናል ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ኢየሱስን መስሎ ለመኖር መጠጋት አሁንም በመቃብሩ ነዉ አልወጣም ፤ ይሁን እንጂ መጥተን “ አዚህ አለመኖሩን !” በምናይ ጊዜ ሄደን ለሌሎች ስለ እርሱ መናገር እንችላለን ፡፡
ከዚያም መለዓኩ ሄደዉ አድሱን ዜና ደቀ መዛሙርቱን እንዲነግሩዓቸዉ ሴቶቹን ነገራቸው (ቁጥር 7) ፤ ሴቶቹ “ በፍርሀት እና በታላቅ ደስታ “ ወጡ (ቁጥር 8) ፡፡ ኢየሱስ በመንገዳቸዉ ላይ በተለመደ ሰላምታ “ ደስ ይበላችሁ !“ በማለት ተገናኛቸው (ቁጥር 9) ፤ ሴቶቹም የኢየሱስን አግር በመያዝ ሰገዱለት ፡፡ ሰዉነቱን ለመመልከት መጡ ወዲያዉኑ ለደቀ መዛሙሩቱ ኢየሱስ መነሳቱን ለመናገር ሄዱ ፤ ለእነርሱ የኢየሱስ መልክ አስፈላጊ አልነበረም ምክንያቱም በእምነት ድርጊት ቀደመዉ በመንገዳቸዉ ላይ ነበሩ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ በመገኘቱ ሊባርካቸዉ መረጣቸዉ ሰገዱለትም ፡፡ ኢየሱስ ሴቶቹን ለደቀ መዛሙርቱ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ እና እርሱን በዚያ እንደሚያዩት
እንዲነግሩዓቸዉ ነገራቸው ፡፡ ያም ቀላል ጉዞ አልነበረም 100 ማይል ርቀት ነበር ፤ በማቴ (26፡ 32) ኢየሱስ ነግሮአቸዉ የነበረበት ስፍራ ነበር ፡፡
ይህ ከትንሳኤ በኋላ የኢየሱስ መልክ መታየት ጀመረ ፤ ለሴቶቹ ታየ ፤ በኢየሩሳሌም እና በይሁዳ ታየ ፤ በገሊላ ታየ ፤ በኢየሩሳሌም እንደገና ታየ ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ታሪኩን በሰሙ ጊዜ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ሴቶቹ አይተዉት የነበረውን ለማየት ተመልሰዉ ወደ መቃብሩ ሮጡ (ዮሐ 20፡ 4-7) ፡፡ የኢየሱስን የቀብር ልብስ መፈለግ ልክ “ የእጭ ሽፋን “ እንደ መፈለግ ነበር ፤ ልብሶቹ በትክክል ተጠቅልለዉ ነበር ነገር ግን እሱ አልነበረም ፡፡
ማቴዎስ (28፡ 11-15)፡ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ገሊላ መንገዳቸዉ ላይ እያሉ ጠባቂዎች ለካህናት አለቃ የሆነዉን ሁሉ ተናገሩ (የመሬት መናወጥ፣ መለዓክቱን፣ የሞቱ መሆናቸዉን) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ያመለከተው ለጠባቂዎቹ ይህ ትክክለኛ ተግባራቸዉ እንደነበር ነው ፡፡ የኃይማኖት መሪዎች ወታደሮቹ ተኝተዉ ሳሉ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አካሉን ሰረቁት በማለት በእቅድ መጡ እናም ስለ እዉነቱ ዝም እንዲሉ ወታደሮቹን መደለያ ገንዘብ ተከፈላቸው (ቁጥር 12) ፡፡ እቅዱ ትርጉም አይሰራም (አይሰጥም) ምክንያቱም በስራ ቦታዉ የሚተኛ አንድ ጥበቃ እንዲሞት ይፈረድበት ስለ ነበር (ሐዋ 12፡ 19; 16፡ 27) ፤ በተጨማሪም ተኝተዉ ከነበር ምንድን ተፈጥሮ እንደ ነበር እንዴት አወቁ ? ደግሞስ ደቀ መዛሙርቱ ድንጋዉን ለማከባለል ይችሉበት ጥንካሬ መቼ አገኙ ? በቁጥር 14 ስለ ጠፋዉ አካል ገዢዉ መረጃ ቢያገኙ እንካን የኃይማኖት መሪዎች ለወታደሮቹ ሚስጥሩን እንደሚሸፈኑላቸዉ ቃል ገቡላቸው፡፡ ወታደሮቹ ገንዘቡን ወሰዱ የኢየሱስ አካል እንደተሰረቀ ወሬዉን አሰራጩ ፤ በቁጥር 15 መሰረት አሁንም ወሬዉ በአይሁድ ተሰራጭቶአል ፡፡
ማቴዎስ (28፡ 16-17)፡ሁገስ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ብዙ አስደናቂ ጥያቄዎችን ይጠይቃል ፤ መጀመሪያው ለምን 11 ብቻ ወደ ገሊላ ሄዱ ? በመፅሀፍ መሰረት ቁጥር 11 ፍፁም አይደለም በጣም የሚያስደንቀዉ ደቀ መዛሙርቱ ለምን ሌላ አለመጨመራቸዉ ጠቅሷል ፤ “ ምናልባት የነበረው ለመልካም ኢየሱስ እንደ መሲህ ባቡር ማበረሩ ቆሞ እንደነበር ማሰባቸዉን “ ያመለክታል ፡፡ በተጨማሪም ሁገስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ተልከዉ የነበረው ይህ የ100 ማይል ጉዞ መታመን የሚያመጣ “ የእምነት ጉዞ “ እንደ ነበር አመልክቷል ፡፡ ሌላዉ ደግሞ አሁንም ተቀብለዉት ስላል ነበር ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ አለመፈለጉ ነው ፡፡ ሰዎስተኝዉ ጥያቄ ሁገስ የጠየቀው ኢየሱስ በተራራዉ ላይ ደቀ መዛሙርቱን ለምን አገኛቸዉ የሚል ነበር ፤ ሁገስ ኢየሱስ አገልግሎቱን በተራራው ስብከት እንደጀመር ያብራራል(ማቴ 4፡ 12) ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ የትንሳኤዉን ኢየሱስ ባዩት ጊዜ ሰገዱለት (ቁጥር 17) ፤ ነገር ግን ይህ ባዩት በ11 ብቻ አልነበረም ፤ ጳዉሎስ በአንድ ጊዜ 500 ሰዎች እንዳዩት መዝግቧል (1ቆሮ 15፡ 6) ፡፡ ምናልባትም ይህ መጥተዉ የተጠራጠሩትን ነው (ቁጥር 17) ፡፡
ማቴዎስ (28፡ 18-20)፡ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ጠፉት እስራኤል በጎች መላካቸዉ ነገር ግን ተቀብለዉት እንዳልነበር እናስታውሳለን ፤ አሁን አዲስ ተልዕኮ ሰጣቸዉ ፡፡ መጀመሪያ “ ስልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ “ ብሎ አፅዕኖት ሰጠ (ቁጥር 18) ፤ እግዚአብሄር ሰብዓዊነቱን እና መለኮታዊነቱን ሁለቱንም እያወጀ ነበር ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ “ እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ አድርጉ “ ብሎ ነገራቸው ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ እንዴት ነበር ደቀ መዛሙርት የሚያደርጉት ? መጀመሪያ በመሄድ ፤ ወደ እነርሱ ከመሄድ ዉጪ ደቀ መዝሙር ማድረግ አንችልም ፡፡ ሁለተኛ በማጥመቅ ፤ ጥምቀት የሆነ ሰው በክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ባመነ ጊዜ በየትኛዉም ጊዜ እና የትኛዉም ቦታ መሆን ይችላል ፡፡ አዲስ አማኞችን ለማጥመቅ መለየት(ለአገልግሎት መለየት) አስፈላጊ አይደለም ፡፡ ሁልጊዜ አዲስ አማኞችን በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማጥመቅ ይገባናል ፡፡ ሰዎስተኛ ክርስቶስ እንድናስተምራቸዉ ያዘዘንን ትዕዛዝ በማስተማር ፤ በዚህም ኢየሱስ እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ከእኛ ጋር እንደሆነ ማስታወስ እንችላለን ፡፡
መዝጊያ
አሁን ንጉሱ ኢየሱስ በኑሮአችን ላይ እያስተዳደረ እና እየገዛ ነው ፤ እምንሄድበት ሁሉ ስለ ኢየሱስ የምናወራው ተልዕኮ አለን ፡፡
6 O’Donnell and Hughes, p 907.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Matthew, p. 478; available on-line at www.soniclight.com.
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 105.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1202.
Douglas Sean O’Donnell and R. Kent Hughes, Matthew: All Authority in Heaven and on Earth (Wheaton, IL: Crossway, 2013), p. 906.
O’Donnell and Hughes, p. 907.
ጥያቄዎች
-
ከሰማይ የመጣዉን እና ከመቃብሩ ላይ ድንጋዩን ያንከባለለዉን መለዓክ ግለፁ (ማቴ 28፡ 3) ፤ ይህን በማቴዎስ (17፡ 2) ከኢየሱስ ገለፃ ጋር አወዳድሩ ፤ ለምን ተመሳሳይ እንደሆኑ አብራሩ ፡፡
-
ጠባቂዎቹ መለዓኩን በመፍራት እንደ ሞተ ሰዉ ነበሩ ነገር ግን ወደ መቃብር የመጡት ሴቶች እንዳይፈሩ ተነግሮአቸዋል (ማቴ 28፡ 4-5) ፤ ሴቶቹ እንዴት መለሱ ? (ማቴ 28፡ 8)
-
መለዓኩ ሴቶቹን ኢየሱስ እንደ ተናገረዉ መነሳቱን ነገሩዓቸው ፤ ኢየሱስ ይህን መቼ ተናገረ ? (ማቴ 12፡ 38-41; 16፡ 21; 17፡ 23; 20፡ 19; 26፡ 32)
-
በማቴ (28፡ 9-10) ኢየሱስ ለሴቶቹ በታየ ጊዜ እንዳይፈሩ ነገራቸው ፤ መለዓኩ ኢየሱስ ተነስቶ እንደ ነበር ቢነግራቸዉም የእርሱ መልክ እንዳስፈራቸዉ ታስባላችሁ ? ፈርታችኋል ?
-
ኢየሱስ በሴቶቹ በኩል እንዳዘዛቸውደቀ መዛሙርቱ ወደ ገሊላ በሄዱ ጊዜ ወደ ህይወት በእርግጥ እንደ ተነሳ እምነታቸዉን እንደሚያሳይ ታስቡታላችሁ ? አዎ ከሆነ እርሱን እያዩት ጥቂቶች ተጠራጥረዉ እንደነበር ቁጥር 17 እንዴት ይገልፀዋል ?
-
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አህዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርቱ እንዲያደርጉአቸው ሲነግራቸዉ ታላቅነቱ ምን ነበር ? (ማቴ 10፡ 5-6)
-
በማቴዎስ 28 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 28:17, 19-20
“When they saw Him, they worshiped, but some doubted . . .‘Go, therefore, and make disciples of all nations, baptizing them in the name of the Father and of the Son and of the Holy Spirit, teaching them to observe everything I have commanded you. And remember, I am with you always, to the end of the age.’”
"ኑና ኢየሱስ እንደተናገረው ከሞት መነሳቱን፥ ተመልከቱ!" በማለት መላዕክት አወጁ፡፡ መግደላዊት ማርያምን እና ሌላኛይቱን ማርያምን ያዩትን እና የሰሙትን እንዲናገሩ አዘዟቸው፡፡ ሴቶቹም መንገዳቸውን ሲሄዱ ፥ ኢየሱስን ተገናኙት፡፡ በእግሩ ስር ወድቀው ከሰገዱ በኋላ እርሱም ሄደው እንዲናገሩ አዘዛቸው፡፡ ከዚያም ደቀመዛሙርቱ አስቀድሞ ኢየሱስ እንደተነበየው ከሞት ተነስቶ አይተዋል፡፡ ቢሰግዱለትም፥ አንዳንዶች ያዩትን ይጠራጠሩ ነበር፡፡ በእውነት ኢየሱስ ከሞት ተነስቷልን
ልክ እንደ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ በእናንተ ውስጥ ህያው ነው! ሄዳችሁ ስለታላቅ ፍቅሩ ለሌሎች እንድትናገሩ ነግሯችኋል፡፡ አምልካችሁት ትሄዳላችሁን ወይስ ኢየሱስ በህይወታችሁ ሕያው እንደሆነ መጠራጠር ትቀጥላላችሁን? ዛሬ ከጥርጣሬ ወደ እምነት ተሸገሩ እና ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ እንዳዘዛቸው ለእርሱ ኑሩ፡፡ ኢየሱስ እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር እንደሚሆን ቃል ገብቷል፡፡
“’” ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ።… እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።"
— የማቴዎስ ወንጌል 28:17, 19-20
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 96:3 — ".ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።”
ወደ ገላትያ ሰዎች 2:20-21 — “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።"
የዮሐንስ ራእይ 14:6-7 — “’ምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ በታላቅ ድምፅም፦ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 28
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።