The Gospels Mark

Teaching With Authority

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 139 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የወንጌል ጥናታችንን ስንቀጥል ወደ ማርቆስ ወንጌል እንሄዳለን ፡፡ ይህ እንደ አገልጋይ የኢየሱስ መልክ ነው ፡፡ ወንጌሉ በማርቆስ ተፅፎአል በተጨማሪም በሐዋ( 12፡ 12) የዮሐንስ ማርቆስ እናት ቤት እንደ ፀሎት ቦታ ሆኖ ታይቷል ፤ ስለሆነም ማርቆስ ለወንጌሉ በፀሎት ላይ የተለየ አመለካከት አመጣ ፡፡ የምትፀልይ እናት ስትኖር ይህ ወደ ልጇቿ ላይ እንዲሸከሙት ያቀርባል(ያስጠጋል) ፡፡ በመጀመሪያዉ ተልዕኮ ጉዞ ላይ በርናባስ እና ሳዖል (ጳዉሎስ ተብሎ የተጠራው፤ ሐዋ 13፡ 9) ከእነርሱ ጋር ዮሐንስ ማርቆስን ወስደዉታል (ሐዋ 12፡ 25) ፤ በተጨማሪም ዮሐንስ ማርቆስ የበርናባስ የአጎት ልጅ ነበር (ቆላ 4፡ 10) ፡፡ ዮሐንስ ማርቆስ ሀብታም መንፈሳዊ ቅርስ(ዉርስ) ነበረው ፡፡

ዮሐንስ ማርቆስ ጥቂት ችግሮችም ነበሩበት ፤ የአግልግሎት ጉዞዉን መጨረስ አልቻለም ቀድሞም ወደ ቤት በመመለስ በበርናባስ እና በጳዉሎስ መሀከል መከፋፈልን ፈጥሮአል ( ሐዋ 13፡ 13; 15፡ 38-40) ፡፡ ዮሐንስ ማርቆስ ጳዉሎስ ላይ የተንጠለጠለ ቢሆንም እንደ ጳዉሎስ አብሮ ሰራተኞች የተለየ (ፊል 24) እና በአገልጉሎቱም አስፈላጊ ነበር (2ጢሞ 4፡ 11) ፤ በተጨማሪም ዮሐንስ ማርቆስ እና ጴጥሮስ ቅርብ የደቀመዝሙርት ግንኙነት ነበራቸው (1ጴጥ 5፡ 13) ፡፡

ዮሐንስ ማርቆስ ከትንሳኤ በኋላ ለሰዎስት አስርት አመታት ሁለተኛዉን የእርሱን ወንጌል ምናልባትም ከሮም ፅፎአል ምክንያቱም አህዛብ ለነበሩ ሮማዉያን አማኞች የተፃፈ ነበር ፡፡ በማርቆስ ወንጌል ዉስጥ ኢየሱስ እንደ “ መከራ አገልጋይ “ የሰራ ነው ፤ “ እንዲሁ የሰዉ ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣምና “ (ማር 10፡ 45) ፡፡ በዚህ ወንጌል ዉስጥ የኢየሱስ የሰዉ ስሜቶች ታይተዋል (ማር 1፡ 41) ፤ እንደ መከራ አገልጋይ ኢየሱስ ለህዝቡ በርህራሄ ተንቀሳቀሰም ከእነርሱም ጋር መገናኘት ቻለ (ማር 1፡ 41; 3፡ 5) ፡፡ ኢየሱስ የሰዉ ስሜት እና አካላዊ እጥረት ሁለቱም ነበሩት፡ ደክሞታል (ማር 4፡ 38)፣ ተርቧል(ማር 11፡ 12) እና ተስፋም ቆርጧል (ማር 8፡ 12) ፡፡

ትምህርት

ማርቆስ (1፡ 1-8)፡ 8ንቱ መጀመሪያ ጥቅሶቹ በትንቢት(ቁጥር2-3) እና በመጥምቁ ዮሐንስ መንገድን በማዘጋጀት በኩል የመሲሁን መምጣት ያበስራል (ቁጥር 4-8) ፡፡ በማቴዎስ ካነበብነዉ የማርቆስ ዮሐንስ ታሪኮች በብዙ ያነሱ ናቸው ፡፡

ማርቆስ (1፡ 9-15)፡ ማርቆስ ዮሐንስ የኢየሱስን በመጥምቁ ዮሐንስ (ቁጥር 9-11) እና በምድረ በዳ የኢየሱስን ፈተናዎች (ቁጥር 12-13) መዝግቧል ፤ ከዚያም ማርቆስ ዮሐንስ መጥምቁ ዮሀንስ መታሰሩን እና ኢየሱስ አገልግሎቱን ለመጀመር ወደ ገሊላ መሄዱን ጠቅሷል (ቁጥር 14) ፡፡

ማርቆስ (1፡ 16-20)፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን መጥራት ጀመረ ፡፡

ማርቆስ (1፡ 21-22)፡ ኢየሱስ አገልግሎቱን በገሊላ ቅፍርናሆም ጀመረ ፤ በማርቆስ መፅሀፍ ዉስጥ አንዱ የተለመደ ቅደም ተከተል ሁል ጊዜ ኢየሱስ ለማስተማር ወደ ምኩራብ መሄዱ ነው ፡፡ (ማር 2፡ 13; 4፡ 1-12; 6; 10-12; 14) ቅፍርናሆም ጠቃሚ እና በሰሜን ምዕራብ ገሊላ ባህር ዳርቻ በዋናዉ መንገድ ላይ የምትገኝ በአሳ የበለፀገች አካባቢ ነበረች ፤ መገኛዉ ለኢየሱስ ዋና መምሪያ አስፈላጊ አካል ሆኗል ፡፡ በምኩራብ የነበሩት በትምህርት ተደነቁ ምክንያቱም “ እንደ ባለ ስልጣን “ ስለአስተማረ (ቁጥር 22) ፤ አይሁዶች የቃል ልምዶችን በመጠቀም ሌሎች የህግ መሪዎችን ለህግ አዋቂዎቹ ተጠቅመዉበት ነበር ፡፡ ኢየሱስ ራሱን እንደ እዉነት ተናገረ ፤ ለሚሰሙት መልዕክቱ አድስ ገፅታ ነበረው ፡፡ አንድ ሀተታሰጪ ኢየሱስ ግላዊ በመሆን በቀጥታና በኃይል እንደ ተናገረ ተናግሯል ፡፡ በእርግጥ የማርቆስ ወንጌል 42 ፐርሰንት በዝርዝር ትምህርቱን የሚጠቅስ ነው ፡፡

ማርቆስ (1፡ 23-24)፡ ከዚያም አንድ ርኩስ መንፈስ ያለበት ሰው ምኩራቡ ገባ ፤ ሰይጣኑ(ክፉዉ መንፈስ) ሁለቱንም እንደ ሰዉ እና እንደ መለኮት “ የእግዚአብሄር ቅዱስ !” ብሎ አሳወቀዉ ማክአርቱር የሰይጣኑን ጥያቄ “ ለምን በእኛ ጣልቃ ትገባለህ ? “ በማለት ተርጉሞታል የኔልሰን ማብራሪያ የኢየሱስ 20 ፐርሰንት ታዓምራቶች “ በሰይጣን የተቸገሩትን በመርዳት እንዳጠነጠኑ “ ይጠቅሳል ፡፡ ወንጌልን ለመናገር በመቀጠል ሁሉንም ቀን አገልግሎትን ስታደርጉ የሰይጣን ድርጊት ይገጥማችኋል ፤ ኢየሱስ ሩብ የሚሆነውን ጊዜዉን ከሰይጣን ጋር በማድግ አሳልፏል ምክንያቱም በክፉ ለተጠቁት ሰዎች ርህራሄ ስለነበረው ፡፡

አንድ ምኩራብ ሁል ጊዜ ሲጀመር ቢያንስ በማህበሩ ውስጥ አስር ሰዎች ነበሩ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን በምኩራቦች ምንድን እንደሚገኙ ይገልፃል፡

  • ሽማግሌዎች፡ የምኩራቦችን ፖሊሲ የሚቆጣጠሩ ፡፡
  • አንድ አስተዳዳሪ፡ በህንፃዉ ላይ እና አገልግሎትን በማቀድ ጥንቃቄ እንዲወስድ በሽማግሎዎቹ የተሸሞ፡፡
  • አንድ ኃለፊ፡ በተጠቀለለዉ ህግ ያዘነበለ፣ ጠቦቶቹን የሚከታተል እና ህንፃዉን በንፅሃና የሚያስቀጥል እንዲሁም እንዲያነቡ ልጆችን የሚያስተምር እና የጅራፍ ቅጣትን የሚያስተዳድር ፡፡
  • አንድ ተወካይ፡ በአገልግሎት ፊት መፅሀፍን እንዲያነብ፣ ፀሎት እንዲመራ እና ለተሰበሰበዉ ጉባኤ እንዲሰብክ በመሪ የተመረጠ የሚችል ሰዉ (ጊዜያዊ ሰራተኛ) ፤ በናዝሬት ምኩራብ ኢየሱስ እንደ ተወካይ አገለገለ (ሉቃ 4፡ 16-30) ፡፡
  • አንድ ተርጓሚ፡ ብዙ አይሁዶች አረማይክ ተናጋሪ ስለሆኑ የእብራዉ መፅኀፍትን መተርጎም የሚችል አንድ ሰው ፡፡
  • እርዳታ ሰብሳቢዎች፡ የድሆችን ፍላጎት ለማሟላት ገንዘብ ተቀብለዉ የሚወስዱ ሁለት ወይም ሰዎስት ሰዎች ፡፡

ኢየሱስ በምኩራቦቹ በጣም ብዙ ጊዜ በማስተማር ስላሳለፈ በእነዚህ ሁሉ ቦታ ካሉት ሰዎች ጋር ይገናኝ እና መስተጋብር ይፈጥራል ፡፡

ጳዉሎስም ሁሉም ማህበር ዉስጥ በመግባት በቀጥታ ወደ ምኩራቦች ሄደ ፤ በኃይማኖት ባለስልጣናት ጋር መስተጋብሩ ብዙ ጊዜ በምኩራቦች ይካሄዳል ፡፡ አገልግሎቱ ሼማዉን(የህግ ዋናዉን) በማንበብ ይጀምራል (ዘዳ 6፡ 4-9)፣ አንዱ ተናጋሪ ኢየሩሳሌምን በገጠማቸዉ እጆቻቸዉን በመዘርጋት በፀሎት ጊዜ ይመራቸዋል ከዚያ በመቀጠል የተመረጠዉ ተናጋሪ በመነሳት ተርጓሚዉ የተረጎመዉን የህጉን ክፍል እና የተተረጎመዉን የነቢያት ክፍል ያነባል ፤ ቀጥሎም ተወካዩ ማብራሪያዉን እና ትምህርቱን ይሰብካል ፤ ከዚያም በኋላ ካህኑ ቡራኬዉን ያሳዉቃሎ ጉባኤዉም “አሜን “ በማለት ይጠቀልላሉ ፡፡ በማርቆስ ዉስጥ ይህ ዋና(የተሰመረበት) አድማጭ ይሆናል ፡፡

ማርቆስ (1፡ 25-28)፡ ርኩስ መንፈስ ያለበት ሰዉዬ የኢየሱስን ትምህርት አስተጓጎለ ፤ ኢየሱስም “ዝም በል !” ወይም “ የተዘጋ እንዲሆን !” በማለት ገሰፀዉ ሰዉየዉንም እንዲለቅቀዉ አዘዘው (ቁጥር 25) ፡፡ ክፉዉ መንፈስም ወጣ ሰዉየዉም በመንዘፍዘፍ መንቀጥቀጥ ጀመረ (ቁጥር 26) ፡፡ ከክፉዉ መንፈሶች ጋር መነጋገር ዝብርቅርቅ ያደርጋል ! በምኩራብ የነበሩት ሰዎች አይተዉት በነበረዉ ተደነቁ ሆኖ ስለነበረዎ እና ስለ ኢየሱስ በስልጣን ማስተማር መከራከር ጀመሩ (ቁጥር 27) ፡፡ በምኩራብ አይተዉት በነበረው መሰረት ቃል ተሰራጨ - ምክንያቱም ኢየሱስ በቀላሉ ሰይጣኑን አሰወጥቶት ስለ ነበር (ቁጥር 28) ፤ በስልጣን እና በኃይል በምትጓዙ ጊዜ የኃይማኖት መንፈስ ወደኃላ ይመልሳል ነገር ግን ህዝቦች መልዕክቱን ለመስማት የተራቡ ይሆናሉ ፡፡

ማርቆስ (1፡ 29-34)፡ ከምኩራብ በኋላ ኢየሱስ፣ ስምዖን፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ እና እንድሪያስ ወደ ስምዖን እና እንድሪያስ ቤት ሄዱ ፤ በህግ የስምዖን ጴጥሮስን እናት በመፈወስ ኢየሱስ አገለገለ (ቁጥር 29-31) (አዎ ስምዖን ጴጥሮስ አግብቷል ፤ 1ቆሮ 9፡ 5) ፡፡ በዚያን ምሽት በፍጥነት ሰዎች የታመሙትና እና ክፉ የተቆጣጠራቸውን ለፈዉስ ወደ ኢየሱስ ማምጣት ጀመሩ ፤ በፍጥነት እየመጡ ሙሉ ከተማይቱ በበር ተሰበሰቡ (ቁጥር 32-33) ፤ ኢየሱስ ክፉዎችን አስወጣቸው ነገር ግን “ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አዉቀዉ ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም “ (ቁጥር 34) ፡፡ ከዚያ ቦኃላ የምንሆነው ይህ የአገልጋይ ትክክለኛ ስዕል ነው ፡፡

መዝጊያ

ለማርቆስ መፅሀፍ በመንዴስ አስደናቁ ስዕላ ላይ ተመልከቱ ፤ አስታዉሱ በመፅሀፍ ቅዱስ ለእያንዳንዱ መፅሀፍ አንድ ስዕል አለው ፡፡ በተለይም በእጅ ላይ ተመልከቱ - የታመመን በመፈወስ እና አጋንንቶቹን በማስወጣት በኩል የክርስቶስ ኃይል መጣ ፤ በህግ የስምዖን ጴጥሮስን እናት ነካት ደህናም ሆነች ፡፡ የችግር አገልጋዩ ክርስቶስ ማንኛዉን እና ሁሉንም በማንኛዉም ጊዜ ላይ ወደ እርሱ ለመሳብ ፍቃደኛ ነው ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1208.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1199.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., p. 1209.

  4. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., p. 1208.

  5. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., p. 1208.

ጥያቄዎች

  1. ኢየሱስ ለ 40 ቀናት ወደ ምድረበዳ ለምን ሄደ ? በሰይጣን ለምን ነበር የተፈተነዉ ? ይህ አስፈላጊ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አያስፈልግም ?
  2. የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርቱ ስምዖን እና እንድሪያስን ኢየሱስ እንዲከተሉት እና ሰዉ አጥማች እንደሚያደርጋቸዉ በተናገራቸዉ ጊዜ አሳ እያጠመዱ ነበር ፤ የማታዉቁትን ሰዉ ለመከተል ሁሉንም ነገር እንደጣላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አልሆነም ?
  3. በማር (1፡ 25) ኢየሱስ ማን እንደ ነበር አጋንንቱን ከማዉራት አስቆመው ፤ ከዚህ ጀርባ የነበረዉ ምክንያት ምን እንደሆነ ታስባላችሁ ? ኢየሱስ በአጋንንት ላይ ስልጣኑን አሳየ (ማር 1፡ 27 ፤ ሉቃ 4፡ 36) ፡፡ ይህ ተመሳሳይ ስልጣን አለን ? (ሉቃ 10፡ 17 ፤ ዮሐ 14፡ 12)
  4. በቁጥር (40-45) ኢየሱስ በርህራሄ በመንቀሳቀስ ለምፅ ያለበትን አንድ ሰዉ ፈወሰዉ ፤ የተፈወሰዉን ሰዉ በካህናቱ ፊት እንዲሄድ እና እንዲያሳይና መስዋዕቱን እንዲከፍል ነገረው ፤ ለሁሉም እንዲናገር ኢየሱስ ለምን አልፈለገም ? በኢየሱስ ተፈዉሳችሁ ከነበር ፀጥ(ዝም) ብላችሁ መቆየት ችላችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አትችሉም ?
  5. በማርቆስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 1:38

“And He said to them, ‘Let’s go on to the neighboring villages so that I may preach there too. This is why I have come.’”

የዕለቱ ቃል- ከላውራ ማርቲን

ኢየሱስም፥ እውነት ተፈፀመ፤ የእግዚያብሔርም መንግስት ቀርባለች እንዲሁም ሁሉም ንሰሐ መግባት እና በወንጌል ማመን አለበት የሚለውን የእግዚያብሔርን መልካም ዜና መስበክ ተልዕኮው እንደሆነ ያውቅ ነበር፡፡ በሙሉ ስልጣን እየሰበከ ወጣ፡፡ በአንድ ወቅት፥ በማስተማር፣ በመፈወስ እና አጋንንትን በማስወጣት መካከል ሆኖ፥ በማለዳ ለመፀለይ ብቻውን ወጣ፡፡ ደቀመዛሙርቱም ወዲያው አገኙት እና " ሁሉ ይፈልጉሃል!" አሉት፡፡ ኢየሱስም መለሰ፥ "እንሂድ፥ ስለዚህ መጥቻለሁና፡፡"

ኢየሱስ በሰው መልክ አምላክ ነው፡፡ ፍፁም ሰው መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ ተልዕኮውን እና ጥሪውን ያውቃል ፥ እናም ይህንኑ ተልዕኮ እና ጥሪ ለህይወታችሁ ወስኗል፡፡ ልክ እንደ ኢየሱስ፥ በስራ የምትጠመዱበት ወቅቶች ይኖሯችኋል፡፡ ሁሉም ሰው እናንተን የሚፈልግበት አስገዳጅ ጊዜያቶች ይኖሯችኋል፡፡ ስለዚህ፥ ኢየሱስ ለመጸለይ ከእንቅስቃሴዎች ሁሉ የመራቅን አስፈላጊነት በምሳሌነት አሳይቷል፡፡ ወደ ተልዕኮ የመመለሻ ጊዜ ሲደርስ ደግሞ " እንሂድ" የሚል አዎንታዊ ምልከታም ምሳሌ ነው፡፡ ዛሬ፥ ለመጸለይ እና እግዚያብሔርን ለመፈለግ ጊዜ ውሰዱ፡፡ ወደ ሥራ የመመለሻው ጊዜ ሲደርስ ደግሞ፥" እንሂድ! እግዚያብሔር ለዚህ ነው የጠራኝ" ማለትን ተለማመዱ፡፡ በራሳችሁ ብርታት ሳይሆን፥ በእያንዳንዱ እርምጃ ለተልዕኮ በሚያስታጥቃችሁ፥ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እና ብርታት ስሩ፡፡

“እርሱም፦ በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ ስለዚህ ወጥቻለሁና አላቸው።”

—የማርቆስ ወንጌል 1:38

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ፊልጵስዩስ 2:13 — “ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።”
  • ቆላስይስ 1:28-29 — “እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ። ”
  • 2 ጢሞቴዎስ 1:9 — “ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 29