The Authority to Forgive Sin
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በማርቆስ መፅሀፍ ዉስጥ ለኢየሱስ አንድ ቃላችን አገልጋይ ነው ማር(10፡ 45) እንድንረዳዉ ለመርዳት፡ “ እንዲሁ የሰዉ ልጅም ሊያገለግል እና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም ፡፡” በማርቆስ 1 የኢየሱስ ስኬት ሰዎች ፈዉስን እና የአጋንንት መዉጣትን በመፈለግ በበሩ ላይ በመታየት ቀድሞ ጀመረ ፤ ይሁን እንጂ በሞደስ እና በስኬት ብዙ ጊዜ ተቃርኖ ይመጣል ፡፡ በማርቆስ 2 ያ ተቃርኖ ይጀምራል ፡፡
ትምህርት
ማርቆስ (2፡ 1-4)፡ ኢየሱስ ለጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ወደ ዋና መምሪያዉ ተመለሰ (ቁጥር 1) ፤ ቤት ዉስጥ ብቻዉን እንደ ነበር ብዙ ሰዎች የኢየሱስን ትምህርት ለመስማት ተሰበሰቡ (ቁጥር 2) ፡፡ ከዚያም “ ሽባ ጓደኛቸዉን ወደ ኢየሱስ ለማምጣት ተጨነቁ ኢየሱስም የሚፈዉስላቸው “ አራት ሰዎች ደረሱ ፤ ስለ ህዝቡ አልተጨነቁም ጓደኛቸዉም ከኢየሱስ ራስ በላይ በጣሪያዉ በኩል የሚያስገቡበት መንገድ አገኙ (ቁጥር 4) ፡፡ ማክአርቱር ብዙዎቹ የመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ቤቶች በቀን ጊዜ የሚያርፉበት እና በሞቃት ምሽት ላይ ደግሞ ሊተኙበት የሚችሉት በዉጨኛ ደረጃ የሚደረሰባቸው ጠፍጣፋ ጣሪያዎች እንደ ነበሩ ገልፃል ፡፡ ጣሪያው ከሚመጣዉ ዝናብ ጣሪያዉን ለማሸግ በደረቅ ሸክላ አፍር ወለል በላይ ቀዝቃዛ ሸክላ አፈሩን ይሰራል ፡፡ “ የሽባዉ ጓደኞቹ በእዚህ አይነት ቤት አናት ላይ ወሰዱት የላይኛዉን የሸክላዉን ድራብ ቆፈሩት …. ወደ ኢየሱስ መገኛ ወደ ታች ለማዉረድ እስኪበቃ ድረስ የሚበቃ ክፍት ቦታ ሰሩ ፡፡” አራቱ ጓደኞቹ ስለ ሽባዉ በጣም ተጨንቀዉ ነበር እንጂ ምን ያክል ስራ እንደሚወስድ እና ወደ ኢየሱስ ጓደኛቸዉን ሲያመጡ ምን ያክል ጉዳት እንደሚፈጠር የተጨነቁ አልነበረም ፡፡ ዋይርስቤ ጓደኞች ለጓደኞቻቸዉ ብቻ አይፀልዩም “ ተስፋ እንዲያስቆርጣቸው አሰቸጋሪ ሁኔታዎችን አይፈቅዱም “ በማለት ተናግሮአል፡፡
ማርቆስ (2፡ 5-7)፡ ጓደኞቹ በጣሪያዉ በኩል በመስበር ወደ ኢየሱስ ሽባዉን ወደ ታች አወረዱት ፤ በእርሱ ፊት የወደቀዉን ሰዉ ወደ ታች በመመልከት “ አንተ ልጅ ኃጢዓት ተሰረየችልህ “ አለው (ቁጥር 5) ፡፡ አይሁዶች ምንኛዉም በሽታ ወይም መቅሰፍት በአንዳንድ ኃጢዓት ምክንያት እንደሆነ ያምናሉ ፤ ነገር ግን በዮሐ (9፡ 1-3) ይህ እምነት ትክክል እንዳልነበር ኢየሱስ በግልፅ ጠቅሶአል ፡፡ ንስሀ የሚገቡ ኃጢዓተኞችን እንዴት እግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ ይቅር ይላል ? ማክአርቱር እግዚአብሄር ምን ያክል ኅጢዓትን ይቅር ማለት እንደሚችል የሚያሳዩ አምስት ጥቅሶችን ይሰጣል፡
- መዝ (103፡ 12)፡ ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ እግዚአብሄር መተላለፍን ያስወግዳል ፡፡
- ኢሳ (38፡ 17)፡ እግዚአብሄር ኃጢዓትን ወደ ኃላ ይጥላል ፡፡
- ኢሳ (43፡ 25)፡ እግዚአብሄር ኅጢዓትን አያስብም ፡፡
- ሚክ (7፡ 19)፡ ኃጢዓትን ወደ ባህር ጥልቅ ይጥለዋል ፡፡
- ቆላ (2፡ 13-14)፡ እግዚአብሄር የእዳዉን ፅፈት “ሙሉ በመክፍል “መስቀሉ ላይ ጠርንቆ አስወገደው ፡፡
ከእኛ ዉስጥ ጥቂቶቻችን እግዚአብሄር በሙሉ ኃጢዓታችንን እንዳስወገደው አናምንም ምክንያቱም ብዙዎቹ በጣም የያዙ ናቸው ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ሁሉንም ይቅር ብሎአል !
ፃፎች (ህግ አዋቂዎች) እነዚህን አዲስ ትምህርቶች እንደ መፅሀፍ ቅዱስ ትክክል እንደነበሩ እርግጠኛ ለመሆን የማረጋገጥ ኃላፊነት ነበረባቸው ፡፡ የሽባዉን ኃጢዓት ይቅር ሲለዉ እና ስም ሲያጎድፍ ሰምተዋል ፤ ኢየሱስን እንደ መሲህ አላወቁትም ወይም መሲህ ኃጢዓትን እንደሚያሰረይ አያምኑም ፡፡ ኮንስታብል የጠቀሰው ቆይተው ፃፎች እና ፈሪሳዉያን “ ስም እንዳጎደፈ ስለወሰዱ ኢየሱስን ለሞት እንደ ሚፈርዱበት “ ፤ ማር (14፡ 61-64) ፤ የስም ማጉደፍ ክስ ሁልጊዜ ወደ ችግር ይመራል ፡፡
ዋይርስቤ የሚለው ኢየሱስ በሽባዉ ሰዉ ሰዉነት ላይ ወደ ታች ተመለከተ፣ ለመሰለል መጥተዉ የነበሩትን ፃፎች እና ፈሪሳዉያን ላይ ዙሪያ ተመለከተ ከዚያም “ ወደ ዋና የልባቸዉ መንፈስ ተመለከት በስም ማጥፋትም እየከሰሱት እንደ ነበር አወቀ ፡፡“ ኢየሱስ “ ሁሉን በሚያዉቅ አዳኝ ሀሳብ “ ምን እያሰቡ እንደ ነበር ተረዳ (ቁጥር 8) ፤ በቁጥር 9 ኃጢዓት ተሰረየችል ከማለት ወይም ፍራሽህን አንሳ ከማለት የትኛዉ እንደ ሚቀልል ኢየሱስ ጠየቃቸው ፡፡ በአንዳንድ አሳቦች ኃጢዓት ተሰረየችል ማለት ቀላል ይሆናል ምክንያቱም ማረጋገጥ ስለ ማይቻል ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ኃጢዓትን የማስተሰረየት ስልጣን እንደ ነበረዉ ለማረጋገጥ ሽባዉን ፍራሹን እዲያነሳ እና ወደ ቤቱ እንዲሄድ ነገረው(ቁጥር 10-11) ፡፡ ኢየሱስ ማን እንደሆነ በማረጋገጥ ዉጥረት አለ ፤ ሌሎች እያዩት ሽባው ወዲያዉኑ ተነሳ ከክፍሉም ወጣ (ቁጥር 12) ፤ በዚያ አብዛኛዎቹ ሰዎች ከእግዚአብሄር ታምራትን ማየት ይፈልጋሉ ፡፡
ማርቆስ (2፡ 13)፡ ኢየሱስ እንደ ገና በባህር አጠገብ ሄደ ህዝቡም ወደ እርሱ መጡ አስተማራቸውም ፡፡ ምን ታያላችሁ ሁሉም ነገር ለመነሻነት የሚቀጥል ነው ፡፡
በቁጥር 10 የሰዉ ልጅ የሚለዉ ርዕስ እንደ አገልጋይ ወደ ኢየሱስ ስዕል ያመለክታል ፤ ማክአርቱር የሚጠቅሰው “ ዝቅ (መዋረዱን) ለማብራራት ኢየሱስ ይህን ቃል ለራሱ ተጠቀመ ፡፡“ የሰዉ ልጅ በሚለዉ ርዕስ ኢየሱስ ከአድማጮቹ ጋር እንደ ነበር እና የእነርሱ አካል እንደ ነበር እያለ ነበር ፤ ርዕሱ ኢየሱስ መለኮታዊ መሲህ እና የሰዉ ወካይ ሁለቱንም እንደነበር ይገልፃል ፡፡ በማርቆስ መፅሀፍ ብቻ የሰዉ ልጅ የሚለዉን 14 ጊዜ ተጠቅሞበት ነበር ፤ ብዙ ጊዜ የሰዉ ልጅ የእርሱን ስቃይ ያሳያል (ማር 2፡ 28; 8፡ 31, 38, 13፡ 26, 26) ፡፡
መዝጊያ
“ ስለዚህ ገና ከታሪኩ መጀመሪያ ኢየሱስ በአስቸጋሪ ነገር ይጓዛል በቋሚ ማስፈራት ስር - እናም እስከ ትክክለኛዉ ጊዜ ከእዉነተኛ ወንጀል ክስ ያመልጣል ፤ በታሪኩ ቀድሞ ከእንደዚህ አይነት ከባድ ክስ (ስም ማጥፋት/ማጉደፍ) ጠባብ ማምለጫዉ በዚህ ግጭት ለዉጥረት እና ለመጠረጠር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል ፡፡” ኢየሱስ በቋሚነት በሰዉነቱ እና በመለኮታዊነቱ እየሰራ ነበር ፤ በዚህ በሽባዉ ታሪክ ኢየሱስ ስለ አካለዊ ፈዉስ ማምጣት እሚችልበት እንዲሁም መንፈሳዊ ግን የሚታደስበት አካባቢ ዉስጥ ራሱን አስቀመጠ ፡፡ የሰዉ ልጅ በምድር ላይ የሰዉን ኃጢዓት ይቅር የማለት ስልጣን አለው ፤ ሰዎች ነፃ ሊያወጣቸዉ በሚችለዉ በሰዉ ልጅ በአገልጋዩ ዙሪያ ዙሪያ መሆን ፈለጉ ፡፡
ለዚህ ትምህርት ይህ ጥያቄዬ ነው፡ በዚህ ታሪክ ሽባ ከሆናችሁ ወደ ጓደኞቻችሁ በመድረስ እርዳታ እንደሚያስፈልጋችሁ እንዲዉቁ ፍቀዱላቸው ፤ በዚህ ታሪክ ጓደኞች ከሆናችሁ ወደ ተጎዱት በመድረስ ለእነርሱ እዚያ መሆናችሁን እንዲያዉቁ ፍቀዱላቸው ፡፡ የሰዉ ልጅ እንዳገልጋይ መረዳት የምንጀምረው እንደዚያ ነው ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expositional (Study) Notes: Mark, p. 43; available online at www.soniclight.ocm.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1200.
Warren Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 115.
MacArthur, p. 1201.
Constable, p. 44.
Wiersbe, p. 115.
MacArthur, p. 1201.
MacArthur, p. 1201.
David M. Rhoads and Donald M. Michie, Mark as Story: An Introduction to the Narrative of a Gospel (Philadelphia: Fortress Press, 1982), p. 187.
ጥያቄዎች
-
አራቱ ሰዎች በጣሪያዉ ላይ ቀዳዳ ሰሩ በዚህም ሽባዉን ሰዉዬ ወደ ኢየሱስ ማዉረድ ቻሉ (ማር 2፡ 3-5) ፤ ተፈዉሰሀል በማለት ፋንታ ኢየሱስ ኅጢዓትህ ተሰረየችለህ ለምን አለዉ ? ይህ ማለት ቀጥሎ ከኋላ ተመሳሳይ ነገር እንዳለ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
-
ቀረጥ ሰብሳቢዎች እና ተግባረ ብልሹ ኃጢዓተኞች ለምን ተመሳሳይ መጥፎ ስም እንደ ተሸከሙ ምን ታስባላችሁ ? አሁንም እንደዛ ናቸው ?
-
ማር (2፡ 21-22) አንብቡ ፤ ከእነዚህ ምሳሌዎች ጋር በራሳችሁ ህይወት የሚገናኝ ማንኛዉንም ምሳሌ ማሰብ ትችላላችሁ ?
-
በማር (2፡ 27) ላይ አሰላስሉ ፤ ለእናንተ ይህ ምን ይላችኋል ? ይህን ጥቅስ እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
-
በማርቆስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Mark 2:17
“When Jesus heard this, He told them, ‘Those who are well don’t need a doctor, but the sick do need one. I didn’t come to call the righteous, but sinners.’”
ሌዊ ለኢየሱስ እና ለደቀመዛሙርቱ በቤቱ እራት አዘጋጀ፡፡ የእራት ግብዣው ቀራጮችን እና ኃጢያተኞችን− በሌላ ቃላት፥ የእግዚያብሔርን ህግ በተለይ የተላለፉትን ሰዎች ጨምሮ ያካተተ ነበር፡፡ ጻፎች እና ፈሪሳውያን ኢየሱስ ከዚህ አይነት የማህበረሰብ ክፍል ጋር አንድነት ለማድረግ የነበረውን ውሳኔ ሲጠይቁ፥ ኢየሱስ የመጣበትን ዓላማ አስታወሳቸው፡፡ ኢየሱስ የጠፉትን ለመፈለግ መጣ፡፡ ኢየሱስ የመጣው ሰዎችን ከኃጢያታቸው ለማዳን እንጂ ፥ እነርሱን ዝቅ አድርጎ ለመመልከት አይደለም፡፡ ኢየሱስ በኃጢያተኞች መካከል ሊያድር መጣ፡፡
በክርስቶስ እንደሚያምን ሰው፥ ለኃጢያተኞች የኢየሱስ ፍቅር እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፡፡ እንደ እግዚያብሔር ልጆች፥ እንድትወጡ ተጠርታችኋል፡፡ በኃጢያተኞች መካከል እንድትኖሩ እና የኢየሱስን ፍቅር እንድታንፀባርቁ ተጠርታችኋል፡፡ ምስክሩ ሆናችሁ ስትወጡ፥ ብቁ ሊያደርጋችሁ፣ ብርታት ሊሰጣቸሁ እና የምትናገሩትን ቃላት ሊሰጣችሁ ቃል ገብቷል፡፡ ዛሬ፥ በማህበረሰባችሁ ውስጥ ያሉትን " ኃጢያተኞችን እና ቀራቸጮችን" የምታዩበትን አይኖች እንዲሰጣችሁ ጌታን ጠይቁት፡፡ ከዚያም በተለምዶ ተቀምጣችሁ ከማታውቁት ሰው ጋር ተቀመጡ፡፡ ወደ ቤተክርስቲያናችሁ የማይሄድን ቤተሰብ ወደ ቤታችሁ ጋብዙ፡፡ እንደ ኢየሱስ ሰውን ለመውደድ ከመንገዳችሁ ውጡ፡፡ እናንተ በዓለም ውስጥ ብርሃን ናችሁ፡፡
“ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።’”
—ማርቆስ 2:17
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ማቴዎስ 1:21 — “ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። ”
- ዮሐንስ 1:14 — “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።”
- የሐዋርያት ሥራ 13:47 — “እንዲሁ ጌታ፦ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ አዞናልና አሉ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 30
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።