The Gospels Mark

Facing Opposition in Ministry

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 141 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ከማቴዎስ ጥናት እና እንደ ንጉስ ከኢየሱስ መልክ ወደ ማርቆስ ጥናታችን እንደ አገልጋይ ወደ ኢየሱስ መልክ ተጉዘናል ፡፡ በማርቆስ 3 ኢየሱስ ሳይፈራ እንዴት ከሰዎች ጋር መስተጋብር እንደሚያደርግ እናያለን ፤ ምክንያቱም ብዙዎች እርሱን መከተል ስለጀመሩ በሰዎች መሀከል ስለሄደ ፡፡

ትምህርት

ማርቆስ (3፡ 1-6)፡ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ጥቅሶች ኢየሱስ ወደ ምኩራብ ተመልሶ ሄደ ሽባ እጅ የነበረዉንም አንድ ሰዉ አየ ፤ ኢየሱስም የሰዉየዉን እጅ መለሳት ፡፡

ማርቆስ (3፡ 7-12)፡ ኢየሱስ አገልግሎት ማድረጉን ስለቀጠለ የትም ቦታ ሰዎች ተከተሉት ፡፡ ከይሁዳ፣ ከገሊላ እና ከሁሉም ቦታ ትምህርቱን የሚያዳምጡ እና ህመምተኞችን መፈወሱን እና ክፉ መንፈስን ሲያስወጣ የተመለከቱ ኢየሱስን የተከተሉ ታላቅ ህዝብ አለ ፡፡

ማርቆስ (3፡ 13-19)፡ ኢየሱስ 12ቱን መጥራት እና ሐዋሪያትን መሰየም ጀመረ፡ ስምዖን ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ (የነጎድጓድ ልጅ)፣ እንድሪያስ፣ ፊልጶስ እና በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ እና ቶማስ፣ የዕልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታድዮስ፣ ቀነናዊዉ ይሁዳ እና አስቆርቱ ይሁዳ ፡፡ ከእርሱ ጋር ይሆናሉ ወንጌልን ይሰብካሉ አጋንንትንም የማስወጣት ስልጣን አላቸው ፡፡ ሰይጣን እዉነት ከሆነ (እርሱ እንደሆነ ካመንን) ከዚያም የእርሱ ጭፍራዎች አሁንም አሉም ይሰራሉም ፡፡ እኛ ልክ እንደ ደቀ መዛሙርቱ (ቁጥር 15) አጋንንትን የማስወጣት ስልጣን አለን ፤ ለሚመጣዉ ለእነዚህ ጥቅሶች ይህ ዉጥረት በመልካም እና በክፉ ያለ መነሻ ነው (ኤፌ 6፡ 12) ፡፡ ማቴ (10፡ 2) የኢየሱስን ትዕዛዝ መዝግቧል፡ “ ድዉዮችን ፈዉሱ ፤ ሙታንን አስነሱ ፤ ለምጻሞችን አንጹ ፤ አጋንንትን አዉጡ ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ በከንቱ ስጡ ፡፡ “

ማርቆስ (3፡ 20-21)፡ ኢየሱስ ቤት ተመለሰ አሁንም በህዝቡ ተከተሉት በዚህም ምክንያት ኢየሱስ እንኳን መብላት አልቻለም (ቁጥር 20) ፡፡ ኮንስታብል ለእነዚህን ጥቅሶች ኢየሱስን የገጠሙት ሁለት የተለዩ ቦታዎች ተቃርኖ እንደ “ ሳንዱች” የመለየት ተቃርኖን ይገልፃል ፡፡ የመጀመሪያዉ “ የሳንዱች “ አካል ከኢየሱስ ቤተሰብ የሆነዉን ተቃርኖ የሚወክለዉ የታችኛዉ ዳቦ ነው (ቁጥር 21) ፤ ቤተሰቡ ኢየሱስን “ ለመገደብ “(ያ ማለት የማሳደግ ኃላፊነት እና ግዴታን መዉሰድ ወይም የሚያስር እና ገደብ ዉስጥ ያስቀምጣል) ይፈልጋሉ ምክንያቱም “ ከሀሳቡ በላይ ስለሆነ ፡፡” ለእርሱ ከመጨነቅ ዉጭ ቤተሰቦቹ ከኢየሩሳሌም 30 ማይል ተጉዘዉ ነበር - ከፍቅር እና ከአለማወቁ ከሁለቱም ዉጪ (ሐዋ 26፡ 24; 2ቆሮ 5፡ 13) ፡፡ በህግ መፅሀፍት በአራት ወር ጥናታችን ሁሉም አይሁዶች ህጉን እና በዙሪያዉ ያሉትን ልምዶች ተረድተዉት ነበር እናስታዉሳለን ፤ ኢየሱስ ከህጉ መረዳታቸዉ ጋር ያልተጣጣመ ነገሮችን እያደረገ እና እያስተማረ ነበር ፤ እናም ህዝቡ ምን እንደሚናገር ለመስማት እና የሚያደርገዉን ለመመልከት ከምኩራብ እየወጡ ነበር ፡፡ የእምነትን ዝላይ(ፍጥነት) ለመዉሰድ በምንቀጥል ጊዜ በብዙ ከቤተሰቦቻችን ተቃርኖ መጠበቅ አለብን ፡፡

ማርቆስ (3፡ 22-26)፡ ወደ ሳንዱቹ “ስጋ” አካል ስንሄድ ኮንስታብል ይህን ከጠላቶች የሆነ ተቃርኖ ብሎ ጠርቶታል ፤ ይህ ተቃርኖ ቀጥታ ለመጉዳት(ለማጥቃት) ይሄዳል - ኢየሱስን በመጥራት ግላዊ ማድረግ ፡፡ ፃፎች ኢየሱስን ሰይጣን (ብዔል ዜቡል) በእርሱ እንደ ነበረበት ተናገሩ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በአዲስ ኪዳን ስምንንት የጣዖት አምላኮችን የዘረዝራል ፡፡ ብዔል ዜቡል “ የሚበልጥ ክፉ መንፈስ እንደሚሆን በአይሁዶች የሚታሰብ የጤነኝነት አምላክ ነበር “ ፤ እንደ መጨረሻ ክፉ መንፈስ ኢየሱስን እየጠሩት ነበር ፡፡ ከአዲስ ኪዳን ሌሎች ጣዖት አምላኮች፡

  • ዲያና፡ “ የጨረቃ፣ የማደን፣ የዱር እንስሳት እና የድንግልና “ ሮማዉያን ጣዖት ፡፡
  • ሄርመስ፡ “ የግሪክ የንግድ፣ የሳይንስ፣ የፈጠራ፣ የብልጥ፣ የንግግር እና የሌባ አምላክ ፡፡ ”
  • ማሞን፡ “ ለሀብታሞች የአረማይክ ቃል እንደ ሀሰተኛ አምላክ በኢየሱስ የተመሰሉ ፡፡ “
  • ሞሎክ፡ “ ልጅ በመሰዋት የሚሰገድለት የአሞራዊያን አምላክ ፡፡ “
  • ረምፋን፡ “ በምድረበዳ በእስራኤል የተመለከ ጣዖት ፡፡ “
  • መንትያ ወንድሞች፡ “ በግሪክ አፈታሪክ የዙዊስ መንታ ልጆች ፡፡ “
  • ዙዊስ፡ “ የጥንታዊ ግሪኮች ታላቅ አምላክ ፡፡ “

ፃፎችም የኢየሱስን አጋጋንንት ማስወጣት ከሰሱት ምክንያቱም የአጋንንት መሪ ስለነበር ፤ ኢየሱስ ይህ የማይረባ ክስ እንደ ነበር ስለሚያዉቅ ጠየቃቸው፡ እንዴት ሰይጣን ሰይጣንን ማስወጣት ይችላል (ቁጥር 23) ? ቀጥሎም ኢየሱስ አንድ መንግስት በራሱ ላይ ከተከፋፈለ እና አንድ ቤት በራሱ ላይ ከተከፋፈለ መቆም እንደማይችል በመናገር ሀሳቡን ያደርጋል (ቁጥር 24-25) ፡፡ ሰይጣን በራሱ ላይ የሚቀዋወም እና የሚከፋፈል ከሆነ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ መቆም አይችልም (ቁጥር 26) !

ማርቆስ (3፡ 27-30)፡ ከዚያም ኢየሱስ ከተለያዩ አቅጣጫ ኃይማኖቱን ቀረበ ፤ መጀመሪያ ኃይለኛዉን ሳያስር የአንድን ኃይለኛ ሰዉ ቤትን መዝረፍ የሚችል ማንም የለም አለ (ቁጥር 27) ፡፡ ኃይለኛዉ ሰዉ ሰይጣን እንደሆነ እና ሊያስረዉ እና የሰይጣንን ስራ ሊያጠፍዉ ኢየሱስ እዚህ መሆኑን ባወቃችሁ ጊዜ ይህ ንግግር ትርጉም አለው ፡፡ 1ዮሐ (3፡ 8) የሚለው፡ “ ኃጢዓትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል ኃጢዓትም ዓመፅ ነው ፡፡ ስለዚህ የዲያብሎስን ስራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሄር ልጅ ተገለጠ ፡፡ “ ሁል ጊዜ የኢየሱስ ሚና ከሰይጣን በኋላ ይሄዳል ፡፡

በቁጥር 28 ኢየሱስ ፃፎችን “ ለሰዉ ልጆች ኃጢዓት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ እንደ ሚሰረይላቸው “ ነገራቸው ፤ ቀጥሎም ኢየሱስ ስለ እርሱ ብለዉት ስለ ነበረው በመጥራት፡ “ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢዓት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም “(ቁጥር 29) - ምክንያቱም “ ክፉ መንፈስ አለበት “ እያሉት ስለ ነበር (ቁጥር 30) ፡፡ ለፃፎች ኢየሱስ እያለ የነበረው ስለ እርሱ ብለዉት የነበሩት ዘላለማዊ ኃጢዓት አድርገዉ ስለነበር ነበር ፤ ፃፎች ይሉ የነበረው ኢየሱስን ሰይጣን እንደ ተቆጣጠረወሱ ነበር ፡፡ ኢየሱስም በእርሱ ዉስጥ እና በእርሱ ላይ መንፈስ ቅዱስ እንደ ነበረበት መለሰላቸው ነገር ግን ፃፎች ያ ርኩስ መንፈስ እንደ ነበር ተናገሩ ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ላይ በመሳደብ ይቅር የማይባል ኃጢዓት አድርገዉ ነበር ፤ እነዚህ ፃፎች ለእግዚአብሄር አክብሮት ያለሰጡ በመሆን በፍቃዳቸዉ መርጠዉ ነበሩ ፡፡ አንድ ሀተታ ሰጪ ስም ማጉደፍን “ ለእግዚአብሄር ጥላቻ፣ ተንኮል፣ ጎጅ እና ክብርን የሚነካ በይበልጥ በንግግር እንደ ኃጢዓት አይነት “ መረዳት እንደምንችል ይናገራል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ላይ በዚህ ስም ማጉደፍ ላይ ለመመልከት ሌለኛዉ መንገድ “ ለብርሃን የተጋለጠ ቢሆንም እንኳን ለጨለማ አንዱ መነሻ ነው (ዮሐ 3፡ 19) ፤ በፍቃድ ያለማቋረጥ አለማመን በይቅርታና በንስሀ ወደ ሚያጠነክር ሁኔታዎች ዉስጥ በእግዚአብሄር መንፈስ ሁለቱንም በማሰላሰል ቀላል(የሚቻል) አይሆንም (ማቴ 12፡ 31-32; ዕብ 10፡ 29) ፡፡

በማር (1፡ 10) በኢየሱስ ጥምቀት ላይ ኢየሱስ ቶሎ ከዉሃዉ ዉስጥ ወጣ “ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርደበት አየ “ ፤ በዚህም ፃፎች በኢየሱስ ላይ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሄር ወይም ከጠላቶቹ እንደነበሩ ይወስናሉ ፡፡

ማርቆስ (3፡ 31-35)፡ የቀረዉ “ የሳንዱች “ ተቃርኖ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ የሚገኝ ነው ፡፡ በመጨረሻም የኢየሱስ እናት እና ወንድሞቹ በቅፍርናሆም ደርሰዉ ነበር ፤ ለእርሱ ቃል በመላክ ጠሩት (ቁጥር 31) ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ለምን እዚያ እንደ ነበሩ ያውቃል - ሊያስተጓጉሉት እንደሆን ፡፡ ኢየሱስም በዙሪያዉ የነበሩት ሰዎች ተመለከተና እናቱ እና ወንድሞች መን እንደነበሩ ጠየቀ (ቁጥር 33) ፤ ከዚያም ኢየሱስ ቤተሰቦች የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርጉ ናቸው አለ (ቁጥር 35) ፡፡ ማለትም የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከማድረግ ቃሉን ከማስበክ እና አጋንንት ማስወጣት ከማስቆም አይሞክሩም …..ቤተሰቦችም ነበሩ ፡፡

መዝጊያ

አገልግሎት እየሰራችሁ ከሆነ ተቃርኖ መጠበቅ ይጠበቅባችኋል ፤ በእርግጥም ተቃርኖ የገጠማችሁ ኳልሆናችሁ ምናልባትም አገልግሎት እያደረጋችሁ አይደለም ፡፡ ወንጌልን እየሰበካችሁ እና አጋንንትን እያስወጣችሁ ከሆነ ተቃርኖ መጠበቅ ይጠበቅባችኋል ምክንያቱም ይህ በሚሆን ጊዜ የሰዎችን የተሳሳተ መንገድ ታስለቅቃላችሁ ፤ ሮሜ (8፡ 14) የሚለው “ በእግዚአብሄር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሄር ልጆች ናቸውና ፡፡” እነዚህን ነገሮች ስናደርግ የእግዚአብሄር ቤተሰቦች አካል ነን ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Mark, p. 62; available at www.soniclight.com.

  2. Constable, p. 62.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 1999), p. 1212.

  4. Radmacher, Allen, and House, eds., p. 1212.

  5. John D. Grassmick, “Mark,” The Bible Knowledge Commentary: New Testament (Wheaton: Scripture Press, 1983), p. 117; quoted in Constable, p. 65.

ጥያቄዎች

  1. በማር (3፡ 6) የፈሪሳዉያን ሴራ ኢየሱስ ለምን ሰዎችን “ለሌሎች ስለ እርሱ እንዳይናገሩ “ ማዘዝ መቀጠሉ የተሸለ መረዳት ይሰጣችኃል (ማር 3፡ 12) ? ኢየሱስ ሰዎችን ስለ እርሱ ለሌሎች እንዳይናገሩ ለምን አዘዘ ? (ማቴ 9፡ 30; ማር 1፡ 43-44)
  2. ማር (3፡ 11) በተግባር የሚመሰለዉን ምንድን ታስባላችሁ ? ሌሎች እንደ እግዚአብሄር ልጅ መቀበል ያልቻሉትን ክፉዉ መንፈስ ኢየሱስ ማን እንደሆነ እንዴት አወቀ ? (ሐዋ 19፡ 15)
  3. ደቀ መዛሙርቱ እንዲሆኑ 12ቱን ኢየሱስ እንዴት እንደ መረጣቸዉ ምን ታስባላችሁ (ማር 3፡ 13-14) ? “ በመጥራት “ እና “ በመሾም “ መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው ?
  4. አጋንንትን የሚያስወጣ የምታዉቁት አለ ? በማር (3፡ 21-22) የህግ መምህራን ኢየሱስን እንደከሰሱት ተመሳሳይ የሆነን ሰዉ የከሰሱ የምታዉቁት አላችሁ ወይስ አለ ?
  5. አጋንንትን በኢየሱስ ስም ማስወጣት በሰይጣን ያስወጣዉን አካል እንዴት መለየት ትችላላችሁ ?
  6. “ በመንፈስ ቅዱስ ላይ መሳደብ “ ማለት ምን ማለት ነው (ማር 3፡ 29) ? ይህን ጥቅስ ለሌላ አካል እንዴት ትገልፁታላችሁ ? የሆኑ ሰዎች ክርስቶስን ከመቀበላቸዉ በፊት በመንፈስ ቅዱስ ላይ ቢሳደቡ ይቅር ሊባሉ ይችላሉ ?
  7. በማርቆስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 3:21

“When His family heard this, they set out to restrain Him, because they said, ‘He’s out of His mind.’”

ኢየሱስ ሲሰብክ፣ ሲፈውስ፣ እና አጋንንትን ሲያስወጣ ካዩ በኋላ፥ ብዙ ሰዎች እርሱን መከተላቸውን ቀጠሉ፡፡ ወደ ተራራ ወጣ እና ከእርሱ ጋር አጋር ሆነው እንዲሰብኩ እና አጋንንትን የማስወጣት ስልጣን እንዲኖራቸው አስራ ሁለት ሐዋርያትን ሾመ፡፡ ከዚያም፥ ወደ ቤቱ ተመለሰ፥ አሁንም ሕዝቡ ተከተሉት፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ብዙ ስለነበር በጣም ተፈላጊ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ተልዕኮውን የሚያራምድ ቡድን በዙሪያው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፥ ኢየሱስ ወደ ቤት ሲመለስ፥ "አበደ" በማለት የገዛ ቤተሰቦቹ ሊይዙት ሞከሩ፡፡ የኢየሱስ ቤተሰቦች ተቀብለው "እንኳን ደህና መጣህ እና እግርህን አሳርፍ" አላሉትም፡፡ " የሰማያዊውን አባትህን አስደናቂ ስራ እየሰራህ ነው እና እኛም እንደግፍሀለን፡፡" በጭራሽ ፥ የእግዚያብሔር አገልጋይ፥ ኢየሱስ ራሱ ስለ አገልግሎቱ ክሶችን እና ተቃውሞን ከገዛ ቤተሰቡ ተቀብሏል፡፡

እናንተ መዛመድ ትችላላችሁ? የእግዚያብሔርን ቃል በምታጠኑበት እና ለክርስቶስ ህይወታችሁን በምትኖሩበት ጊዜ ፥ በቅርባችሁ ያሉ ሰዎች ከባድ ጊዜ ሲሰጧችሁ አግኝታችኋል? ከኢየሱስ ጋር ስትራመዱ ተቃውሞ እንደሚገጥማችሁ ቃል ተገብቶላችኋል፡፡ ስለዚህ ዛሬ፥ በርቱ፡፡ በክርስቶስ ማን እንደሆናችሁ እና ለምን እንደተጠራችሁ አስታውሱ፡፡ ከእናንተ ጋር ያለው በአለም ካለው ይበልጣል፡፡

“ዘመዶቹም ሰምተው፦ አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።”

— ማርቆስ 3:21

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ሮሜ 8:31-32 – “እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ”
  • ኤፌሶን 6:12 – “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”
  • ፊልጵስዩስ 1:27-29 – “ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ።በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 31