The Gospels Mark

Walk in Faith and Not Fear

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 142 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በማርቆስ 3 አገልግሎቱን እያደገ በነበረበት ጊዜ ኢየሱስን ከራሱ ቤተሰብ እና ከጠላቶቹ የገጠመዉ ተቃርኖ ላይ ተመልክተናል ፡፡ ስላስተማረ እና አጋንንትን ስላስወጣ የህዝቡ ጭንቅንቅ ተከተሉት ፤ ይሁን እንጂ ቤተሰቦቹ ከአይምሮዉ ዉጪ እንደነበር አሰቡ ሊያስተጓጎሉትም ፈለጉ ፡፡ ፃፎች ኢየሱስ ያደርግ የነበረዉ ወደ እነርሱ ኃያማኖታዊ ሳጥን ዉስጥ እንዳልተጣጣመ ተሰማቸው ስለዚህም ከሰይጣን ነዉ በማለት ከሰሱት ፤ ኢየሱስ ሰይጣን ራሱን ማስወጣት እንደማይችል ገለፀላቸው በዚህም ፃፎች በመንፈስ ቅዱስ ላይ መሳደባቸዉን አመለከታቸዉ - ይቅርታ የሌለዉን አንዱ ኃጢዓት ፡፡ ምዕራፉ ቤተሰቦቹ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርጉ እንደነበር በኢየሱስ ንግግር ያበቃል ፤ ለምዕራፍ 4 ያ አስፈላጊ መነሻ ነው ምክንያት ህዝቡ ለማደግ ስለቀጠሉና ከእርሱ ብዙ ስላስፈለጋቸው ፡፡ ይደክመዋል ነገር ግን ቀጠለ ፡፡

ትምህርት

ማርቆስ (4፡ 1-9)፡ ብዙ ህዝብ በዙሪያዉ በተሰበሰቡ ጊዜ ኢየሱስ ባህሩ አጠገብ ማስተማር ጀመረ ፤ ኢየሱስ ወደ መርከቡ በመንቀሳቀስ አንዱን በጣም የሚታወቀዉን መሳሌዉን አስተማራቸው - የዘሪዉን ምሳሌን ፡፡ ኢየሱስ በጥብቅ በተለያየ ዉጤት በተለያዬ አይነት መሬት ላይ ዘሪዉ የወረወረውን ዘር ገልፆታል ፤ ከዚያም ሰዎች ወንጌልን የሚቀበሉበት መንገድ እንዴት አፈሩ ዘሩን እንደሚቀበል በጣም ተመሳሳይ እንደሆነ ገለፀ ፡፡

ማርቆስ (4፡ 10-20)፡ የእግዚአብሄርን መንግስት በዚህ መንገድ በመግለፅ ምሳሌዎችን ለምን እንደሚጠቀም ኢየሱስ ተናገረ ፤ አንዳንድ ሰዎች እንደሚረዱት እና አንዳንዶች እንደማይረዱት ተናገረ ፡፡ በምሳሌዎች መንፋሳዊ ምልከታን ለማድረግ እና ከሚያምኑት እና ከማያምኑት ጋር ለመነጋገር ኢየሱስ ሁሉንም ቀን ነገሮችን ተጠቀመ ፤ ከዚያም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የምሳሌዎችን ትርጉም ይሰባብርላቸዋል ፡፡

ማርቆስ (4፡ 21-32)፡ በዚህ ምዕራፍ ማርቆስ ሰዎስት ተጨማሪ ምሳሌዎችን አካትቷል ፡፡ የመጀመሪያው በመቅረዙ ላይ መብራትን ስለማስቀመጥ ነበር በዚህም ብርሃኑ ይታያል (ቁጥር 21-25) ፤ ሁለተኛው ስለ ሚያድገዉ ዘር እና ስለ መከሩ ነበር (ቁጥር 26-29) ፤ ሰዎስተኛው ስለ ትንሽ ሰናፍጭ ዘር ተፅዕኖ ነበር (ቁጥር 30-32) ፡፡

ማርቆስ (4፡ 33-34)፡ ኢየሱስ ህዝቡን ምሳሌዎችን በመጠቀም ብቻ ያስተምራቸዋል ነገር ግን ለደቀ መዛሙርቱ ሁሉንም ነገር ያብራራላቸዋል ፡፡

ማርቆስ (4፡ 35-41)፡ ዋይርስቤ ያመለከተው “ የእግዚአብሄር አገልጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም ሁኔታ እና የሁሉም ጠላት አሸናፊ ማስተር ነው ፡፡ ከአንድ ቀን ትምህርት በኋላ ምናልባትም ከህዝቡ ራቅ በማለት ጥቂት ጊዜ ለማግኘት ኢየሱስ በባህሩ ላይ ጀልባዋን በመዉሰድ እንዲሄዱ ደቀ መዛሙርቱን ነገራቸው (ቁጥር 35-36) ፡፡ የገሊላ ባህር ስምንት ማይል የሚሰፋ፣ 700 ጫማ ከባህር ወለል በታች እና ከ3,000 እስከ 4,000 ጫማ ከፍ ባሉ ተራራዎች የተከበበ ነው ፤ ባህሩ በቀዝቃዛ ምሽት የጠለመደ ነው ፡፡ ጀልባዋ ባህሩን ማቋረጥ እንደጀመረች ሌላ ጀልባዎች ተከተሉ ፤ ማዕበል ሲመጣ (ቁጥር 37) ሁሉም ጀልባዎች ይድናሉ ፡፡ እርሱን በብዙ የምንወደዉ እንድንሆን እኛን ለማጥራት ኢየሱስ አንዳንድ ጊዜ በማዕበል ዉስጥ እንድንሄድ ይፈልጋል ፡፡

ቁጥር (37-38) ጀልባዋ እንኳን በዉሃ መሙላት ስትጀምር በማዕበሉ ጊዜ በሚገባ ተኝቶ መቀጠሉ የኢየሱስን ሰብአዊነት ያሳያል ፤ ኢየሱስ ተኝቶ ደቀ መዛሙርቱ ለእርዳታ እየጮሁ ነበር ፡፡ ሀይበርት የደቀ መዛሙርቱን ምላሽ “ ያለመታመን ጩኸት ነበር ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በአስቸጋሪ ሁኔታ በአማኞች እግዚአብሄር እንደ ተዋቸዉ ከሚሰማቸው ጋር እንደሚዛመድ “ ገልፆታል ፡፡ ደቀ መዛሙርቶቹ በገሊላ ላይ ማዕበልን የሚያዉቁ አሳ አጥማጆች ስለነበሩ ኢየሱስ ነገሮችን እንዲያስተካክል ጠበቁ ፡፡ በማዕበሉ ጊዜ ኢየሱስ ስለተኛ ፈሩ ፤ አለማመን ፍራትን መፍጠር ይጀምራል ፡፡ ሰዎች ፍራትን በሚለምዱ ጊዜ የደነዘዙ ይሆናሉ ፤ የደነዘዙ በሆኑ ጊዜ ቀጥሎ በእምነት አይጓዙም ፤ በእምነት መጓዝ ባቆሙ ጊዜ እምነታቸዉ የማያድግ እና የሞተ ይሆናል ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እምነት እንዳልነበራቸው ነገራቸው (ዕብ 3፡ 12) ፡፡

በቁጥር 39 ኢየሱስ ማዕበሉን “ ገሰፀዉ ” ፤ አንድ ሀተታ ሰጪ “ በማዕበሉ ፀጥ ማለት (ቁጥር 4፡ 35-41) የንፋስ ግሳፄዉ እና የማዕበሉ መታፈን አጋንንትን በማስወጣት ቋንቋ ዉስጥ በፍጥረት መዘበራረቅ ላይ የእግዚአብሄርን ኃይል እንደገና በመጥራት የተነገሩ ናቸው ፤ ሁለቱም ክፍል በቃል ብቻ እንደተደረጉ “ ፅፏል ፡፡ ኢየሱስ ሁሉንም ድርጊት እንዲያቆሙ በመናገር ብቻ ያስቆም ነበር ፤ ኢየሱስ ፈጣሪዉ ለባህሮቹ መናገር ይችላል ምክንያቱም ፈጥሮአቸዉ ስለነበር (ዕብ 1፡ 2) ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው (ቁጥር 40) “ እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምንድን ነው ? እንዴትስ እምነት የላችሁም ? “ ደግመዉ ደግመዉ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ፍርሀትን እና የእምነት ማጣትን አሳዩ ፤ ያ ተስፋ ይሰጠናል ፡፡ ከሰዎች ጋር አገልግሎትን ስናደርግ፣ ወደ ማህበረሰቡ ስናፈስ፣ የሰንደይ ትምህርት ክላስን፣ የደቀ መዝሙርነት ቡድኖች፣ ጥቂት ቡድኖች እና ቤተሰቦቻችን በዚህም በመደነቅ እንዴት እንዳላገኙት ደቀ መዛሙርቱ አንዱንም እንዳላገኙት እናስታውሳለን (ማር 7፡ 18; 8፡ 17-21) ፡፡

ሽባ ሰዎችን መፍራት ፤ ኢየሱስ ማን እንደሆነ ጤነኛ አመለካከት ከሌላችሁ ከማዕበሉ የሆነዉ ፍርሀት ይቆጣጠራችኋል ፤ ነገር ግን የማዕበሉ እና ኢየሱስ በእነርሱ ማን እንደሆነ ትክክለኛ አመለካከት ባላችሁ ጊዜ ማዕበሉን በሰላም ትቀበሉታላችሁ ምክንያቱም እግዚአብሄር በመቀጠል በብዙ እያጠራችሁ ስለሆነ ፡፡ ለክብሩ እርሱን የምንመስል ለማድረግ እግዚአብሄር እነዚህን ክስተቶች ይጠቀማል ፡፡

በቁጥር 41 ደቀ መዛሙርቱ ፈሩ ነፋስ እና ባህሮች እንኳን የሚታዘዙለት ኢየሱስ ማነዉ ብለዉ ጠየቁ ፤ ኢየሱስ ማን እንደ ነበር ወይም ምን ማድረግ እንደሚችል ግንዛቤዉ የላቸውም ፡፡ በማዕበሉ ኢየሱስ ተፈጥሮን መቆጣጠሩን እስኪያዩ ድረስ በብዙ ፈርተዉ ነበር ፤ በማዕበል ዉስጥ በምንሄድ ጊዜ እግዚአብሄር እንዴት ትልቅ እንደሆነ እና እንዴት እንደሚቆጣጠር ማየት እንችላለን ፡፡ መዝ (89፡ 8-9)፡ “ አቤቱ የሰራዊት አምላክ እንደ አንተ ያለ ማን ነው ? አቤቱ አንተ ብርቱ ነህ እዉነትህም ይከብብሀል ፡፡ የባህርን ኃይል አንተ ትገዛለህ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ ፡፡ “ ኢየሱስ እግዚአብሄር(አብ) እንደሚያደርገዉ ይህን ማድረግ ይችላል ፤ የኢየሱስ መለኮትነት ያሳያል በተጨማሪም በማዕበልም ዉስጥ በእርሱ መታመን እንደምንችል ያረጋግጣል ፡፡

ማይክ ኳይር በእምነት ለምን እንደማንሄድ ምክንያቶቹን ያቀርባል፡

  1. እንፈራለን (ዘጸ 3፡ 11) ፤ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር እሆናለሁ ብሎ ይመልሳል (ቁጥር 12) ፡፡
  2. ወደኋል መገፋት እናገኛለን (ዘጸ 3፡ 13) ፤ እግዚአብሄር ይህ የእናንተ እንዳልሆነ ይመልሳል (ቁጥር 14-15) ፡፡
  3. ሰዎቹ ችግሮች ናቸው (ዘጸ 4፡ 1) ፤ እግዚአብሄር እኔ ከሰዎች እበልጣለሁ ብሎ ይመልሳል (ቁጥር 2-9) ፡፡
  4. በሚገባ በቂ አይደለሁም ማለት (ዘጸ 4፡ 10) ፤ እግዚአብሄር ለሚያጥራችሁ ሁሉ እሰራለሁ በማለት ይመልሳል (ቁጥር 11-12) ፡፡

መዝጊያ

በማዕበሉ ላይ ከሆኑት ደቀ መዛሙርቶች ብዙ እንማራለን ፤ በእምነት እንድንጓዝ እና እንዳንፈራ በእነርሱ የጠራን እንድንሆን ሁሉም ስለ ማዕበሉ አስተሳሰብ ነው ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), 124.

  2. D. Edmond Hiebert, Mark: A Portrait of the Servant (Chicago: Moody Press, 1974), p. 115; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Mark, p. 78; available at www.soniclight.com.

  3. James R. Edwards, “The Authority of Jesus in the Gospel of Mark,” Journal of the Evangelical Theological Society, 37:2 (June 1994): p. 223; quoted in Constable, p. 78.

ጥያቄዎች

  1. ኢየሱስ ለምንድን ምሳሌዎችን ተጠቀመ ? በማርቆስ 4 ምሳሌዎቹን ተረድተናችዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ወይስ ደቀ መዛሙርቱ እንደ ጠየቁዓቸዉ አይነት ጥያቄዎች ጠይቃችኃል ?
  2. ማር (4፡ 24-25) ላይ ተመልከቱ ለእናንተ ይህ ምን ማለት ነው ? ምሳሌ ወይም ይህን ያያችሁበትን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ?
  3. በማር (4፡ 35) ወደ ሌለኛዉ ጫፍ ለመሄድ ኢየሱስ ጀልባዋ ዉስጥ ገባ ፤ በዚህ አገላለፅ ወደ ሌላኛዉ ጫፍ ለምን እንደሄደ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በማር (4፡ 39) ኢየሱስ ማዕበሉን ፀጥ አደረገው ፤ ይህ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሄር እንዴት ያመለክታል ? (መዝ 89፡ 8-9; 104፡ 7)
  5. በቁጥር 40 ኢየሱስ እምነት አለመኖርን ጉዳይ ደረሰ ፤ የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከቱ፡ ማቴ 15፡ 28; 21፡ 21; ማር 5፡ 34; 2ቆሮ 5፡ 7; ዕብ 11፡ 6 ፡፡ ሁሉም እነዚህ ጥቅሶች በጋራ የሚያደርጉት ምንድን አላቸው ? እናንተ ስላላችሁ የእምነት መጠን እንዴት ይሰማችኋል ?
  6. በማርቆስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 4:39-40

“He got up, rebuked the wind, and said to the sea, “Silence! Be still!” The wind ceased, and there was a great calm. Then He said to them, “Why are you fearful? Do you still have no faith?”

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ሕዝቡን ትተው በገሊላ ባሕር ላይ ወደነበረ ታንኳ ገቡ፡፡ በድንገት፥ ብርቱ አውሎነፋስ በላያቸው መጣ እና ታንኳቸው በውሃ ሞላ፡፡ ደቀመዛሙርቱም አውሎነፋሱን በመፍራት ኢየሱስ ስለእነርሱ ግድ እንደማይሰጠው በመቁጠር ከሰሱት፡፡ ኢየሱስም በቀላሉ ተነስቶ፥ ነፋሱን ገሰፀው እና ባህሩንም ፥ "ዝም በል! ፀጥ በል!" አለው፡፡ ወዲያውኑ፥ አውሎነፋሱ ቆመ፡፡

በህይወታችሁ በሆነ ጊዜ ላይ፥ ራሳችሁን ባልተጠበቀ "የባሕር ላይ ማዕበል" ውስጥ ታገኙታላችሁ፡፡ ድንገተኛ የመኪና አደጋ፣ የገንዘብ ቀውስ፣ የልጃችሁ ወይም የምትወዱት ሰው መታመም ወይም የማይሄድ ድብታ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ደቀመዛሙርቱ በፍርሃት ወይስ በእምነት መልስ ትሰጣላችሁ? ፍርሃት በእግዚያብሔር ላይ አመኔታ ማጣት ሲሆን፥ እምነት ግን በእግዚያብሔር ላይ መታመን ነው፡፡ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ጠየቃቸው ፥ "ለምን ትፈራላችሁ? እስከአሁን እምነት የላችሁምን?" በቀውስ መካከል እንኳን፥ ኢየሱስ አውሎነፋሱን ማረጋጋት እና ለእናንተ ሰላምን ማምጣት ይችላል፡፡ ከባድ ነገሮችን ይበልጥ ማቅለል ይችላል፡፡ ለሀዘናችሁ ደስታን ማምጣት ይችላል፡፡ ሁልጊዜም ያዘጋጃል፡፡ አዕምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላምን ማምጣት ይችላል፡፡ በወጀብ መካከል እርሱ ከእናንተ ጋር እንዳለ እና ሰላም እንደሚሰጣችሁ በማመን ወደርሱ ተመለሱ፡፡

“ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? አላቸው።”

—ማርቆስ 4:39-40

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 46:1-2 – “አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም። ”
  • መዝሙረ ዳዊት 107:28-30 – “በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።ዐውሎንም ጸጥ አደረገ፥ ሞገዱም ዝም አለ።ዝም ብሎአልና ደስ አላቸው፤ ወደ ፈለጉትም ወደብ መራቸው። ”
  • 2ኛ ተሰሎንቄ 3:3 – “ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 32