The Touch of the Servant
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ማርቆስ 4 በማዕበሉ ጊዜ የደቀ መዛሙርቱን እምነት ማጣት ኢየሱስ በማመልከቱ እና ኢየሱስ ሲያደርግ አይተዉት በነበረዉ መደነቃቸው ያበቃል ፡፡ ማርቆስ 5 ኢየሱስ እንዴት ከሰዎች ጋር መስተጋብር እደፈጠረ ያተኩራል ፡፡
ትምህርት
ማርቆስ (5፡ 1-20)፡ በምዕራፍ 4 ከማዕበሉ በኋላ ጀልባዋ “ በባህሩ በሌላኝዉ በኩል “ ዳርቻ ላይ መጣች ፤ ወዲያዉኑ ኢየሱስ ከጀልባዋ ወረደ አንድ ክፉ መንፈስ ያለበትም ሰዉ ወደ እርሱ መጣ ፤ ምናልባትም ኢየሱስ በቂ እረፍት አላገኘም ነበር ነገር ግን የሚያስፈልገዉን አግኝቶ ነበር ፡፡ ቶሎ እረፍት ስናገኝ ብዙ አገልግሎት ለመሰረት የተዘጋጀን እንሆናለን ፡፡ ኢየሱስ ርኩስ መንፈሶቹን ወደ ታች ሮጠዉ ወደ ባህር ዉስጥ ገብተዉ ሰመጡት 2,000 አሳማ(እሪያዎች) መንጋዎች ዉስጥ አሰገባቸው ፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት አልቆመም ፡፡
ማርቆስ (5፡ 21)፡ የምዕርፍ 5 ቀሪዎቹ ሁለት በጣም ከተለያዩ ሰዎች ጋር የኢየሱስን መስተጋብር መዝግቧል -
ለመስራት ታዋቂ የነበረዉ በጣም አሰፈላጊ የነበረዉ የምኩራቡ ሰራተኝ ኢያኢሮስ እና ስሟ ህክምና በመፈለግ
ልትሞት የነበረችዉ ሴት ፡፡ በእነዚህ በሁለቱ ኢየሱስ ሁለት ታአምራት አደረገ አድሎም እንደማያሳይ አሳየ ፡፡ ወንጌል
ማለት ለሁሉም ነው !
ማርቆስ (5፡ 22-24)፡ ኢያኢሮስ ለእርዳታ ወደ ኢየሱስ በመምጣት “ በእግሩ ላይ ወደቀና አጥብቆ ለመነው “
(ቁጥር 22-23) ፡፡ ኃይማኖታዊ መሪዎች እንዴት ወደዚህ ሀሳብ እንዴት ያገኛሉ ? በግልፅ ኢያኢሮስ ስለ ልጁ ተስፋ
መቁረጥ ተሰማው ኢየሱስ ህይወት ሊሰጣት እንደሚችል ያውቃል ፡፡ ኬንት ሁግህስ ተስፋ መቁረጥ ለምህረት
የመጀመሪያ ድርጊት እንደሆነ አመልክቷል ፤ ተስፋ መቁረጥ ከእኛ የሚበልጥ ነገር እንደሚያስፈልገን እንድናዉቅ
ይፈቅድልናል ፡፡ ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ሄደ እንደገና ኢየሱስን በመግፋት ብዙ ህዝብ ተከተለው ፤ የምታስታዉሉት እንደ
አገልጋይ ኢየሱስ ከኢያሮስ ጋር በመሄድ ከእርሱ ጋር ጊዜ አሳለፈ ፡፡
ማርቆስ (5፡ 25-32)፡ ለ 12 አመታት ደም ይፈሳት የነበረች አንዲት ሴት ኢየሱስን ተጠጋቸው ፡፡ በደሙ ምክንያት
በስርዕቱ እንደረከሰች ትታያለች በተጨማሪም ማንኛዉም እርሷን የነካም እንደ እርኩስ ይታያል (ዘሌ 15፡ 25-27) ፡፡ “ በብዙ ዶክተሮች ስር ብዙ ታግሳ(ደክማ) ነበር “ (ቁጥር 26) የዳነች ለመሆን ሁሉንም ነገር ሞክራ ነበር ፤ በኬንትሁግህስ መሰረት የለመደቻቸው አንዳንድ የመዳኒት ህክምናዎች የሚያካትቱት ፡
- በአንድ ነጭ አህያ ፈንዱያ ዉስጥ የሚገኝ የገብስ ፍሬን ቁራጭ መሸከም ፡፡
- የሆኑ ሰዎች ከኃላዋ ሲመጡ እንዲፈሯት የተለየ መጠጥ ትይዛለች ፡፡
ከባህላዊ የህክምና ተግባር ይልቅ በተለያየ መንገድ ለመፈወስ ይህ የኢየሱስ ፍላጎት ምሳሌ ነው ፡፡
ሴቲቱ ኢየሱስን ወደ ከበበዉ ህዝብ ዉስጥ ተጭና ገባች ፤ ሴቲቱ ምንድን ነካች ? በኢየሱስ ቀሚስ ላይ ከአራቱ አንዱን ዘርፍ ነካች (ዘኁ 15፡ 37-40) ፡፡ እምነቷ ኢየሱስን እንድትፈልግ አነሳሳት፡ “ ልብሱን ብቻ የዳሰሰሁ እንደ ሆነ እድናለሁ ብላለችና “ (ቁጥር 28) ፤ እምነቷ ለድርጊት አነሳሳት ፡፡ በክርስቶስ እምነት በሚኖረን ጊዜ የሚያስቅ ነገር እንቀመጣለን ነገር ግን ሁልጊዜ እምነት ወደ ድርጊት ይመራል ፤ እምነት የኃጢዓት ይቅርታ ማለት ብቻ አይደለም በእምነታችን ስንጓዝም እንጂ ፡፡ ኡጉስቲን “ ስጋ ይጫናል ነገር ግን እምነት ይነካል “ ብሎ ፅፏል ፡፡ ቁጥር 29 ሴቲቱ ከ12 አመታት በኋላ በአንድ መነካት ብቻ ወዲያዉኑ እንደተፈወሰች መዝግቧል ፡፡ ለልጁ ለፈዉስ ኢያኤርስ ስለጠየቀ ሌላይቱም ተፈወሰች ፡፡
ያ ለእኛ አስፈላጊ ስዕል ነው ፤ በሪቫይቭ ት/ቤት ወይም በስራ ላይ ወይም በአገልግሎት በእምነታችን ስንጓዝ ወደ ኢየሱስ በምናመጣቸዉ ሰዎች መካከል ያለማቋረጥ እየተጓዝን ነው ፤ በተጨማሪም ይህን ለማድረግ ዘጠኝ የቅርብ ጓደኞችን እስክናገኝ ድረስ መጠበቅ የለብንም ፡፡ አንድ ሰዉ በጊዜው….. አንድ ቀን በጊዜው ኢየሱስ ተስፋ ቆርጠዉ እርሱ የሚያስፈልጋቸውን ወደ እርሱ ፈልገን እንድናመጣችዉ ይፈልገናል ፡፡
አንድ ጊዜ ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል ወጥቶ እንደ ነበር አወቀ (ቁጥር 30) ፤ ማን ነክቶት እንደ ነበር ጠየቀ የሚያዉቀዉ አስደናቂ ጥያቄ ፡፡ ፈዉሱን እዉቅና ለመስጠጥ ሲቲቱን ፈለጋት ፤ እንዲህ አይነት ጥያቄ በመጠየቁ ደቀ መዛሙርቱ ሊያምኑት አልቻሉም ምክንያቱም የተጨናነቀዉ ህዝብ በጣም ትልቅ ስለ ነበር (ቁጥር 31) ፡፡
ማርቆስ (5፡ 33-34)፡ ኢየሱስ በህዝቡ ላይ ሲመለከት የምትንቀጠቀጠው ሴት መጥታ በኢየሱስ እግር ላይ ወደቀች (ቁጥር 33) ፤ የስግደት ድርጊቷ እንደ ኢያርኤስ ድርጊት ተመሳሳይ ነበር ፡፡ ሁለቱም ኢየሱስ እንደሚያስፈልጋቸዉ አዉቀዋል ፡፡ ሴቲቱ ኢየሱስን ታሪኳን ነገረቸው ፡፡
ኢየሱስ በጉድፈቻ ስነ ስርዓት አይነት መለሰ ፤ ለሁሉም ኢየሱስ እንደ “ሴት ልጅ “ የጠቀሰበት እና በእምነቷ ምክንያት ወደ እግዚአብሄር ቤተሰብ በሰላም እንድትመጣ ያደረገበት ብቸኛው ጊዜ ነበር ፡፡ “ በሰላም “ እንድትሄድ ነገራት ፤ “ ሰላም “ የሚለው ቃል በእስራኤል በጣም የተለመደዉ ቃል “ሻሎም “ ነው ፤ በኮንስታብል መሰረት ሻሎም እንደ “ ከዉስጥ ጭንቀት ነፃነት ብቻ አይደለም ነገር ግን ከእግዚአብሄር ጋር ባለ ትክክለኛ ግንኙነት የመጣ የህይወት ጠቅላላነት እና ሙሉነት “ የተገለፀ ነው ፡፡ ኢየሱስ በማር (3፡ 35)፡ “ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ ነው እህቴም እናቴም አለ ፡፡ ”
ማርቆስ (5፡ 35-43)፡ አሁንም ኢየሱስ እየተናገረ ከኢያኢሮስ ቤት ሰዎች ልጁ እንደሞተች በዚህ ዜና ደረሱ ፤ ኢያኢሮስ መምህሩን ለምን ማስጨነቅ እንደሚቀጥል ጠየቁት (ቁጥር 35) ፡፡ ኢየሱስ ቃላቸዉን ሰምቶ “ አትፍራ እመን ብቻ “ ብሎ መለሰለት (ቁጥር 36) ፡፡ እምነት ሁልጊዜ ፍራትን ያሸንፋል - በእምነት መጓዝ እንጂ በፍርሀት አለመጓዝ ፡፡ ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብ እና ከዮሐንስ ጋር ብቻ ወደ ኢያኢሮስ ቤት ተጓዘ ፤ ከማቴ (17፡ 1-2) እና ማቴ (26፡ 37) በተለወጠበት ተራራ ላይ እና በጌተሰማኔ ጋርደን ከኢየሱስ ጋር እነዚህ ተመሳሳይ ደቀ መዛሙርት እንደ ነበሩ እናውቃለን ፡፡ ኢየሱስ ከእርሱ ጋር በሚቀርቡት አደረገ ስለዚህም የተለየ ነገር ማየት ይችላሉ ፡፡
በኢያኢሮስ ቤት የተከፈሉ አዘንተኞች “ እየተንጫንጩ እና በሀይል እያለቀሱ ነበር “(ቁጥር 38) ፡፡ ሚስቱ በሞተች ጊዜ እንዲያለቅሱ ድሀ ባል እንኳን ሁለት ዋሽንት ተጫዋቾች እና አንድ ሴት ይቀጥራል ፡፡ በሞቱ ላይ እንዲህ አይነት ሁከት ለምን እያደረጉ እንዳለ ኢየሱስ ጠየቀ ምክንያቱም ልጅቱ ተኝታ ስለ ነበር (ቁጥር 39) ፤ ሰዎቹ መሳቅ ጀመሩ ስለዚህ ኢየሱስ ሁሉንም ወደ ዉጪ ላካቸው ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ፣ ደቀ መዛሙርቱ እና ኢያኢሮስ ልጂቱ ወደ ነበረችበት ገቡ ፤ ኢየሱስ በእጁ ልጂቱን አነሳት - አገልጋዩ ኢየሱስ እርኩሱን፣ አጋንንት የያዘዉን ወይም ህይወት የሚያስፈልገዉን የታመመ እና የተቀሰፈዉን ለመንካት አልፈራም ፡፡ ኢየሱስ ልጂቱን “ ጣሊታ ቁሚ አላት !” ትርጉሙም “ አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው ! “ (ቁጥር 41) ፤ ልጂቱም ተነስታ ተመላለሰች ፤ 12 አመቷም ነበር ፡፡ አስደናቂ አጋጣሚ ……. ሴቲቱ ለ 12 ዓመታት ደም ሲፈሳት ነበር ልጂቱም 12 ዓመቷ ብቻ ነበር ? እግዚአብሄር ትንሽ ወይም ትልቅ ወይም ምን ያክል ጊዜ ህመም ወይም ችግር ደርሶበት ቢሆንም ችግር እንደሌለው ያሳያል አሁንም ኢየሱስ መፈወስ ይችላል ፡፡ ህዝቡ ባያት ጊዜ በፍፁም ደንግጠዉ ነበር ወይም “ በታላቅ ማስገረም ከአይምሮአቸዉ ዉጪ ሆኑ “ ፤ በቁጥር 43 ኢየሱስ ምስክሮቹን ሆኖ የነበረዉን ለማንም እንዳይነግሩ እና ምግብ እንደሚያስፈልጋት ነገራቸው ፡፡
ኢየሱስ አገልግሎቱን መስራት ለመቀጠል እና በመካከላቸዉ ከእነርሱ ጋር መጓዝ ፈለገ ፤ የኢያኢሮስ ሴት ልጅ ከተነገረ የሚሆነዉን ችሎታዉን እንኳን ለማንቀሳቀስ በጣም ያስቸግራል ፡፡
መዝጊያ
አንድ አባት ሴት ልጁ እንድትፈወስለት ብቻ የሚፈልገዉን ወይም በማያቋርጥ መቅሰፍት(በሽታ) ስር በመኖር በጣም ደክማ የነበረችን የአንዲት ሴት ፈዉሳቸዉን ለማየት በመፈለግ ብቻ ምንድን እናደርጋለን ? መልሱ ቀላል ነው፡ ኢየሱስ ብቸኛው መንገድ ነው ! የሰይጣን አላማ በልጁ በኩል ከአባቷ ቦኃላ መሄድ እና ለ 12 ዓመታት ተመትታ ከነበረችዉ ሴት በኋላ እንድንሄድ ነበር ፤ ዮሐ (10፡ 10) የሚለው “ ሌባው ሊሰርቅ እና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸውእንዲበዛላቸውም መጣሁ ፡፡ “ ዮሐንስ 11፡ 25-26 ኢየሱስ ህይወት እንደሆነ ያረጋግጣል !
p. 86; available atwww.soniclight.com.)
5 John D. Grassmick, In The Bible Commentary: New Testament, eds. John F. Walvoord and Roy B. Zuck (Wheaton, IL: Scripture Press/Victor Books, 1983) p. 126; quoted in Dr. Constables Expository (Study) Notes: Mark, p. 88; available at www.soniclight.com.)
R. Kent Hughes, Mark: Jesus, Servant and Savior (Wheaton, IL: Crossway, 2015), p. 125.
R. Kent Hughes, pp. 123-124..
Hugh Anderson, The Gospel of Mark (Greenwood, SC: Attic Press, 1976), p. 154; quoted in Dr. Constables Expository (Study) Notes: Mark, p. 85; available at www.soniclight.com.)
H. Van der Loos, The Miracles of Jesus, Novum Testamentum series, v. VIIII (Leiden, Netherlands: E. J. Brill, 1965), p., 568; quoted in Dr. Constables Expository (Study) Notes: Mark,
ጥያቄዎች
-
በማር (5፡ 6) አጋንንት የተቆጣጠረዉ ሰዉዬ ኢየሱስን ባየዉ ጊዜ ወዲያዉኑ ባደረገው ምንድን ታስታውላላችሁ ? የኢየሱስን ስልጣን በአጋንንት ላይ እንዴት ታዩታላችሁ ? (ፊል 2፡ 10)
-
አጋንንት ያለበት ሰዉ መፈወሱን ካዩ በኋላ ሰዎቹ ለምን አመኑ ብቻቸዉን ትቷቸዉ እንዲሄድ ኢየሱስን ለመኑትስ (ማር 5፡ 17); ሉቃ (8፡ 37) ?
-
በማር (5፡ 22-23) በኢያኤሬስ ያለዉን ትህትና እና እምነት እንዴት ታዩታላችሁ ? ኢየሱስ ጥያቄዉን ያከበረበት በዚህ እንደ ነበር ታምናላችሁ (ያዕ 4፡ 10; 1ጴጥ 5፡ 5) ? ሴት ልጁ በፍጥነት በመፈወስ ፋንታ ሴቲቱን ለመፈወስ ኢየሱስ ባቆመ(በዘገየ) ጊዜ ኢያኤሬስ የተሰማዉን እንዴት ታስቡታላችሁ ?
-
በህይወታችሁ እናንተ ወይም የምታዉቁት ሌላ ሰው በእናንተ እምነት ምክንያት የተፈወሰበት ጊዜ አለ ? በተመሳሳይ እምነት ኢየሱስ አለመፈወሰን የመረጠበት ጊዜስ ? እንዴት አስተናገዳችሁት ?
-
በማር (5፡ 40) በኢየሱስ ላይ ሳቁበትም ተሳለቁበትም ነገር ግን የአባቱን ፈቃድ ከማድረግ አልራቀም ፤ እግዚአብሄርን ስለ መከተላችሁ በተሳቀባችሁ ወይም በተንጓጠጣችሁበት(በተዘለፋችሁበት) ሁኔታ ዉስጥ ነበራችሁ ? በዚያ ሁኔታ ዉስጥ እግዚአብሄር እየሰራ እንደ ነበር ከዚያ በኋላ ማስረጃ ነበር ? እያፌዙ የነበሩት እንዴት አድርገዉ መለሱ ?
-
በማርቆስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Mark 5:33-34
“Then the woman, knowing what had happened to her, came with fear and trembling, fell down before Him, and told Him the whole truth. ‘Daughter,’ He said to her, ‘your faith has made you well. Go in peace and be free from your affliction.’”
ለአስራ ሁለት አመት ደም ሲፈሳት የነበረች አንዲት ሴት ኢየሱስን ብዳስሰው ብቻ ደህና እሆናለው የሚል እምነት ነበራት ደግሞም አመነች፡፡ በእምነት እንዳመነች ሁሉ፥ ልክ እንደነካችው ፥ ሰውነቷ ተፈወሰ፡፡ ኢየሱስ በብዙ ሕዝብ ቢከበብም እንኳን፥ ኃይል ከእርሱ እንደወጣ ተሰማው፡፡ ሴቲቱ እንደዳሰሰችው ተገንዝቦ፥ " ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል ፥ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ" አላት፡፡
የዚህችን ሴት ህመም እና ትግል ተረዳችሁ? በስቃይዋ ምክንያት ለዓመታት የማትነካ ሴት ነበረች፡፡ አሁን ግን በእምነቷ እና ኢየሱስን በመዳሰሷ ምክንያት ፥ ተፈወሰች፡፡ ዛሬ በኢየሱስ መነካት ትፈልጋላችሁ? በእምነት ኢየሱስን ለመንካት መዘርጋት ለእናንተ ምን ይመስላል? ራሳችሁን ዝም አሰኙ እና ፀልዩ፡፡ በትህትና ንሰሐ ግቡ እና ህመማችሁን ወስዶ ነፃ እንዲያወጣችሁ ጌታን ጠይቁት፡፡ ለሚታመን ሰው ስቃያችሁን እና ሸክማችሁን አካፍሉ፡፡ የኃጢያት ጥልቀት ወይም ይህን ሸክም የተሸከማችሁበት የዓመታት ርዝመት ምንም ያክል ቢሆን፥ ዛሬውኑ ልቀቁት፡፡ ዘርጉ እና ኢየሱስን ንኩት፡፡ የእርሱ ኃይል ከፍርሃታችሁ እና ከጥርጣሬያችሁ ሁሉ በላይ ነው፡፡ ለእናንተ ስላለው ፍቅር እና በእርሱ ስላላችሁ ተስፋ እምነት ይኑራችሁ እና ጌታን አመስግኑት፡፡
“ሴቲቱ ግን የተደረገላትን ስላወቀች፥ እየፈራች እየተንቀጠቀጠችም፥ መጥታ በፊቱ ተደፋች እውነቱንም ሁሉ ነገረችው። እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ አላት።”
—ማርቆስ 5:33-34
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ትንቢተ ኤርምያስ 17:14 — “አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ ለዘላለምም በማታውቃትም ምድር ለጠላቶቻችሁ ባሪያ አደርግሃለሁ፤ ለዘላለም የሚነድደውን እሳት በቍጣዬ አንድዳችኋልና። ”
- ፊልጵስዩስ 4:7 — “አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ”
- የያዕቆብ መልእክት 5:15-16 — “የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 33
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።