The Gospels Matthew

Fulfillment of the Crucifixion Prophecies

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 27 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 137 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ማቴዎስ በሙሉ ስለ ንጉሱ ነው ፤ ትናትና ማሪያም እና ይሁዳ ሁለቱም እንዴት ለንጉሱ መንገድ አዘጋጅተዉ እንደነበር ተመልክተናል ፡፡ ዛሬ ስለ ስቅለቱ እንመለከታል ፡፡ ማቴዎስ 27 66 ቁጥሮች አሉት ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (27፡ 1-10)፡ ኢየሱስ ለጲላጦስ ተላልፎ ተሰጠ ይሁዳም ለካህናቱ አለቃ እና ሽማግሌዎች 30 ብሩን መለሰ እና ህይወቱን አጠፋ ፡፡ ቁጥር 4 በይሁዳ ልብ ቆሻሻ እንደ ነበር እንዳወቀ ያሳያል ፡፡ የካህናቱ አለቃ 30 ብሩን የደም ገንዘብ እንደ ነበር ቢያዉቅም የእርሻ መሬትን በብሩ ገዙበት (ቁጥር 6-7) ፡፡

ማቴዎስ (27፡ 11-14)፡ ኢየሱስ በገዢዉ “ የአይሁድ ንጉስ አንተ ነህ “ ተብሎ ተጠየቀ ኢየሱስም “አንተ አልክ “ ብሎ መለሰ ፡፡ በማቴዎስ 1 ከመወለዱ እስከ ማቴዎስ መጨረሻዉ ኢየሱስ እን አይሁድ ንጉስ ነዉ የቀረበው ፡፡

ማቴዎስ (27፡ 15-26)፡ ጲላጦስ እንዲለቅላቸዉ የሚፈልጉት ኢየሱስን ወይስ በርባንን እንደሆነ ህዝቡን ጠየቃቸው ፤ ህዝቡም “ እርሱን ስቀለው “ እያሉ ተጣሩ ጲላጦስ ተጨማሪ ጥያቄ በጠየቃቸው ጊዜ በእነዚያ ቃላቶች መጮሀቸዉን ቀጠሉ ፡፡ ጲላጦስ እጁን ታጠበና ከኢየሱስ ደም ንፁህ እንደሆነ ተናገረ (በቁጥር 4 ከኃይማኖት መሪዎቹ ጋር ይሁዳ ከነበረዉ ጋር ተመሳሳይ ቃለ ምልልስ) ፤ ህዝቡም “ ደሙ በእኛ እና በልጆቻችን ላይ ይሁን !“ ብለው መለሱ ፡፡

ማቴዎስ (27፡ 27-31)፡ ጲላጦስ ኢሱስን እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው ፡፡ ምንድን ይመስላል ?ማክአርቱር የሚለው ለሮማዉያን በፋሪሳዊያን፣ በቀድሞ ሴሜቲክ በነበሩት ሰዎች እና በቀድሞ ካርቴጅያዊን ተጀምሮ የነበር የስቅላት አይነት ነበር ፡፡ አላማው በተቻለ መጠን(ለቀናት በማቆየት) ተጎጂዉን ሳይሞት ማሰቃየት ነበር ፤ በተጨማሪም እግሮቹ ይደክማሉ ስለዚህ ተጎጂዉ(ተጠቂዉ) መተንፈስ አይችልም ስለሆነም እግሮቹ መስበር ሞቱን በፍጥነት ያመጣዋል ፡፡ ሚስማሮቹ በእግሩ ጉብታ እና የእጅ አንጓዉ ዉስጥ ይገባሉ ይህም አደገኝ ብቻ አልነበረም ኅይለኛ ህመምም እንጂ ፡፡ (ዮሐ 19፡ 31) ፡፡

ገላ( 3፡ 13)፡ “ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከህግ እርግማን ዋጀን ፡፡ “

ማቴዎስ (27፡ 32-34)፡ በህመም 200 ፓዉንድ መስቀሉን በመሸከም በጣም በመድከም መልመዱ ይህ የኢየሱስን ትህትና ያሳያል (ዕብ 4፡ 15) ፤ ስምዖን ከቀሬና ለኢየሱስ መስቀሉን እንዲሸከምለት ተገደደ (ቁጥር 32) ቆይቶም አማኝ ሆኗል ፡፡ ጎልጎልታ (የራስ ቅል ቦታ) ከከተማዋ በሮች ዉጪ የሚገኝ ነበር ፡፡ ህመሙን እንዲቀንስለት ከሀሞት ጋር በመቀላቀል ወይን ለኢየሱስ በሰጡት ጊዜ ኢየሱስ መስቀሉ ላይ ነበር (ቁጥር 34) ፡፡ ይህ በመዝ (69፡ 21) የተተነበየ ነበር ፤ ኢየሱስ አልተቀበለውም ፤ ለምን ? ሁለት የሚሆኑ ምክንያቶች፡

  1. ሉቃ (23፡ 43) ኢየሱስ ከሌሎቹ አንዱን እንዳገለገለ መዝግቧል ስለዚህ ምናልባት በግልፅ ያልምንም አካላዊ እንቅፋት ያንን ማድረግ እንዲችል ስለፈለገ ፡፡
  2. ምሳ (31፡ 6) ምናልባት ኢየሱስ ህመሙን ለመያዝ መፈለጉን ይመክራል(ያመለክታል) ፡፡

ማቴዎስ (27፡ 35-37)፡ ወታደሮቹ ለልብሶቹ እጣ አዘጋጁ የተከሰሰበትንም ከራሱ በላይ ምልክትን አስቀመጡ፡ የአይሁድ ንጉስ ኢየሱስ ነው ፤ በሌሎች አካታች ወንጌላት ላይ በማስረጃ ባጣመርነው ጊዜ (ማር 15፡ 26; ሉቃ 22፡ 3; ዮሐ 22፡ 38) የሚነበበዉም ምልክት፡ የአይሁድ ንጉስ የናዝሪቱ ኢየሱስ ነው ፤ ይህ የክርስቶስን ሰብዓዊነት እና መለኮታዊነትን ሁለቱንም ያሳያል ፡፡

ማቴዎስ (27፡ 38-44)፡ ኢሳ (53፡ 12) በመስቀሎቹ ላይ በሁለት ሌቦች መካከል እንደሚሆን ትንቢት አለ ፤ ባጠገቡ ሚሄዱት ሰዎች፣ ህዝቡ፣ የካህናቱ አለቃ፣ ፃፎች እና ሽማግሌዎቹ የእስራኤል ንጉስ እያሉ አፌዙበት ፤ ወንጀለኞቹም እንኳን እንደነሱ አንጓጠጡት ፡፡

7ቱ የመሰቀል ትንቢቶች ኢየሱስ ሊፈፅማቸዉ የመጣዉ እነዚህ ትንቢቶች፡

እግዚአብሄር የገዛ ልጁን በስቃዩ ጊዜ ይተወዋል (መዝ 22፡ 1; ማቴ 27፡ 46; ማር 15፡ 34) ፡፡

ክርስቶስ የተናቀና መሳለቂያ ይሆናል (መዝ 22፡ 7, 8; ማቴ 27፡ 39-44; ሉቃ 23፡ 35) ፡፡

የክርስቶስ እጆች እና እግሩ የተወጋ ይሆናል (መዝ 22፡ 16; ዮሐ 20፡ 25, 27; ሐዋ 2፡ 23) ፡፡

ለክርስቶስ ልብሶች ሌሎች ይቆምሩበታል(ይከፋፈሉታል) (መዝ 22፡ 18; ማቴ 27፡ 35, 36) ፡፡

ከክርስቶስ አጥንቶች አንዲቷ አትሰበርም (መዝ 34፡ 20; ዮሐ 19፡ 32, 33, 36) ፡፡

ክርስቶስ በጓደኞቹ ተላልፎ ይሰጣል (መዝ 41፡ 9; ዮሐ 13፡ 18) ፡፡

ክርስቶስ ሆምጣጤ እና ሀሞት ይሰጠዋል (መዝ 69፡ 21; ማቴ 27፡ 34; ዮሐ 19፡ 28-30) ፡፡

መዝጊያ

እነዚህ ሁሉ እንዴት ወደ መሲሁ እንደሚያመለክቱ የሚያሳዩ ናቸው ፡፡ ብሉይ ኪዳን ወደ መሲሁ ያመለክታል ፡፡ አዲስ ኪዳን ወደ መሲሁ ያመለክታል ፡፡ ማቴዎስ 27 የክርስቶስ እየቀጠለ ያለዉን የትንቢቱን መፈፀም ያሳያል ፡፡ ንጉሱ እኛ ነፃ እንድንሆን መከራ ያያል (ይሰቀላል) ፤ ፀሎቴ ህይወት እንዲኖረን ለእኛ ኢየሱስ ያለፈበትን ህመም እንዳነረሳ ነው ፡፡ የኢየሱስ መፈፀም በመስቀሉ ላይ አያልቅም ፤ ነገ ማለት ነው !

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1182.

ጥያቄዎች

  1. በማቴ (27፡ 1-2) የኢሳ (53፡ 3) ትንቢት የተፈፀመ ሆኖ ማየት ትችላለሁ ? ለምን ወይስ ለምን አልቻላችሁ?
  2. በማቴ (27፡ 5-10) ይሁዳ ለካህናት አለቃ 30 ብሩን መለሰ ፤ ይህን ገንዘብ መቅደሱ ግምዣ ቤት ዉስጥ ለምን አላስቀመጡም ? በዘካ (11፡ 12-13) በዚህ አዲስ ኪዳን ፅሁፍ ዉስጥ ምንድን መሲሀዊ ትንቢት ነዉ የተፈፀመው ?
  3. ማቴ (27፡ 12-14) አንብቡ ፤ በኢሳ (53፡ 7) የተነገረው ምንድን ትንቢት ነዉ የተፈፀመው ? በማይገባ የተከሰሳችሁ ብትሆኑ ዝም ትላላችሁ ?
  4. በማቴዎስ 27 የተፈፀሙ በሰዎስት የተለያዩ ብሉይ ኪዳን መፅሀፍት ዉስጥ ቢያንስ 12 መሲሀዊ ትንቢቶች አሉ ፤ ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ በምታነቡበት ጊዜ እዉነቱን ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑን አሳምኖናል ብላችሁ ታስባላችሁ ? (መዝ 22፡ 1, 7-8, 16, 18; 31፡ 5; 38፡ 11; 69፡ 21; ኢሳ 50፡ 6; 53፡ 1-3, 7, 9, 12; ዘካ 11፡ 12-13)
  5. በኢየሱስ ላይ የእሾክ አክሊል ተቀመጠበት (ማቴ 27፡ 29) ፤ በዘፍ (3፡ 18) እሾክ በኃጢዓት ምክንያት የእርግማን አካል ነበር ፤ ይህ አክሊል ለእኛ ኢየሱስ እርግማን እንደሆነ ምልክት እንደነበር ታስባላችሁ ? (ገላ 3፡ 13)
  6. ማቴ (27፡ 51) የመቅደሱ መጋረጃ ከላይ ወደታች ለሁለት መቀደዱብ ይናገራል ፤ ይህ መጋረጃ ምንድን ይወክላል (ዕብ 10፡ 20) ? የኢየሱስ ሞት ወደ ዕብ (10፡ 19-21) መንገድ ምንድን ነው የከፈተው ? በዚህ በራስ መተማመን ትሄዳላችሁ ?
  7. ወደ እግዚአብሄር በጮኸ ጊዜ ኢየሱስ ለምን ጥሎት እንደነበር ለመጠየቅ ከመዝ (22፡ 1) ጠቀሰ ፤ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሄር በእዉነት ተትቶ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ማቴ 28፡ 7; ሉቃ 1፡ 33; ኤፌ 1፡ 19-21)
  8. በማቴዎስ 27 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 27:54

“When the centurion and those with him, who were guarding Jesus, saw the earthquake and the things that had happened, they were terrified and said, ‘This man really was God’s son!’”

ኢየሱስ በመስቀል ላይ በግፍ ሞተ፡፡ "የአይሁድ ንጉስ፥ ኢየሱስ ይህ ነው" በማለት ሕዝቡ ቢጮህም፥ በጊዜው ከነበረው ህግ አንጻር ኢየሱስ እንዲሞት መወሰን ትርጉም የማይሰጥ ነበር፡፡ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት ይኖረው ዘንድ፥ የኢየሱስ ሞት፥ አንድያ ልጁን አሳልፎ የሰጠው የእግዚያብሔር አብ ፈቃድ ነበር፡፡ ኢየሱስ በአካላዊ ስቃይ ውስጥ አልፎአል፡፡ ተዘብቶበታል፡፡ ስለበደላችሁ ቆስሏል፥ ስለመተላለፋችሁ ደቋል፡፡ አካላዊ እና ስሜታዊ ስቃይ ውስጥ አልፏል፡፡ በመጨረሻዎቹ ሰአታት፥ ስለኢየሱስ መሞት የተነገሩ ትንቢቶች ተፈጸሙ፡፡ ነጻ ወጥታችሁ የዘላለምን ሕይወት እንድታገኙ፥ እርሱ በብዙ ተሰቃየ፡፡

ዛሬ፥ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የተሰቃየውን ስቃይ በማሰብ አመስግኑ፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ በኃጢያት ምክንያት የተሰቃየውን ሰቃይ እያሰቡ መቅረት ይከብዳል፡፡ አዎን፥ ኢየሱስ ተነስቷል! ወደ ሚለው እውነት መሻገሩ ይቀላል፡፡ ቢሆንም የተሰቃየው ስቃይ አያምልጣችሁ፡፡ ትክክለኛ ነበር፡፡ ህመሞቻችሁን እየረሳችሁ ደስ ወደሚሉ ጊዜያት ማለፍ ትወዱ ይሆናል፡፡ እውነታው ግን፥ ሁሉም ሰው በስቃይ ውስጥ ያልፋል፡፡ ሁሉም ሰው በህመም ይጸናል፡፡ የነገስታት ንጉስ ኢየሱስ አዳኛችሁ ነው፡፡ በህመማችሁ ሊያዝንላችሁ እና ሊራራላችሁ ይችላል፡፡ የተወደድክ የእግዚያብሔር ልጅ ሆይ፥ ኢየሱስ መከራ እና ሞትን የታገሰው ለአንተ ነው፡፡ ኢየሱስ ያሳለፈውን ስቃይ እና በህይወታችሁ የሚያለፈውን ህመም ስታስቡ፥ ጌታ ከእናንተ ጋር ለመሆን ቃል እንደገባ አስቡ፡፡ በህመሙ እንድትጸኑ ይረዳችኋል፡፡ ክህመሙ በኋላ ያለውን የትንሳኤ ተስፋ አስቡ፡፡ ተስፋችሁ የሚገኘው በክርስቶስ ብቻ ነው፡፡

“ የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና እና የሆነውን ነገር አይተው፦ይህ በእውነት የእግዚያብሔር ልጅ ነበር ብለው እጅግ ፈሩ፡፡”

— የማቴዎስ ወንጌል 27:54

ተጨማሪም ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኢሳያስ 53:5 — “ እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለ፥ ስለበደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችን ተግሳፅ በእርሱ ላይ ነበር፥ በእርሱም ቁስል አኛም ተፈወስን፡፡”
  • የዮሐንስ ወንጌል 3:16 — “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላላም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚያብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለምን እንዲሁ ወዷልና፡፡”
  • ዕብራዊያን 4:15-16 — “ ከኃጢያት በቀር በነገር ሁሉ እንደኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀካህናት የለንም፡፡ እንግዲህ ምሀረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ፡፡”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 27