Giving Everything to Jesus
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ስለ መጨረሻው ጊዜ መረጃ ላይ በሰፊ ምልከታ በመንሸራተት የመጨረሻዎቹ ጥቂት ትምህርቶች የተወጠሩ ናቸው፡፡ ዛሬ በእነዚህ ክስተቶች በሰዉ በኩል በትንሹ እንመለከታል ፤ ማቴዎስ 26 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እርሱን ለመግደል ሴራ እንደሚኖር በመናገር ይጀምራል (ቁጥር 1-5) ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (26፡ 6-9)፡ ቢታኒያ የእነ አልአዛር፣ ማሪያም እና ማርታ አባት የስምዖን ቤት ይገኝበት የነበረ በደበረ ዘይት ተራራ ላይ ያለች ትንሽ ሰፈር ነበረች ፡፡ ሰሞዖን በከባድ “ የቆዳ በሽታ “ በለምፅ ተመቶአል ፤ ለለምፅ ብቸኝዉ መዳኛ በእግዚአብሄር መነካት ነበር ፤ ለንጉሱ በመዘጋጀት የሚሆን አስደንጋጭ የቅባት መነሻ ነው ( ማር 14፡ 3-9; ዮሐ 12፡ 1-8) ፡፡ እዚያ እያሉ አንዲት ሴት(በሌሎች አመዘጋገብ መሰረት የማርታና የአልዓዛር እህት ማሪያም ነበረች) ውድ ከሆነ ብልቃት ዘይት ጋር መጣች ፤ በዮሐ (12፡ 3) መሰረት ማሪያም “ ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቶ “ ነበራት ፤ ሽቶዉ 300 ድናር ዋጋ ይገባው ነበር (ዮሐ 12፡ 5) ፡፡ የመፅሀፍ ቅዱስ አዋቂዎች 300 ዲናር ብዙ ሰራተኞች በአንድ አመት የሚያገኙት እነደ ነበር ያመለክታሉ ፤ ደቀ መዛሙርቱ መስዋዕቱአን ቢጠይቁም ማሪያም በኢየሱስ ራስ እና እግር ላይ አፈሰሰችዉ ፡፡
ማሪያምን ባሰብናት ጊዜ “ ፈጣን ስብራት “ የሚለውን ቃል መጠቀም እንችላለን ፡፡ ዋይርስቤ በመፅሀፍ ውስጥ ሰዎስት ጊዜ ማሪያምን ሁል ጊዜም በኢየሱስ እግር ስር መጠቀሷን አመልክቷል፡ 1) ማሪያም በእግሩ ስር ተቀምጣ የሚያስተምረዉን አዳመጠች - ሉቃ (10፡ 38-39); 2) ከወንድሟ ሞት በኋላ በእግሩ ስር ተምጣ አዘነች (ዮሐ 11፡ 28-32) እና 3) በሽቶ ቀብታው እግሩ ላይ ሰገድች (ዮሐ 12፡ 3) ፡፡ የተሰበሩ ሰዎች ወደ እዉነት የተሳቡ ናቸው - ወደ ኢየሱስ እግር ስር ፤ ማሪያም የኢየሱስን ራስ እና እግር በመቀባት በፀጉሯ እግሩን ጠረገች (ዮሐ 12፡ 3) ፡፡ ሙሉ ገንዘቧን ሰጠች ከዚያም ቀጥሎ በንጉሱ ፊት “ ክብሯን “ ሰጠች (1ቆሮ 11፡ 13) ፤ ንጉሱን በማዘጋጀት የነበራትን ሁሉንም ነገር ሰጠች ፡፡
ሁልጊዜ ጥያቄአችን መሆን ያለበት “ ለንጉሱ ለማዘጋጀት ምን ማድረግ እችላለሁ ? “ ይሁን እንጂ ደቀ መዛሙርቱ ሙሉ ለሙሉ ተቃራኑ ነበሩ በማሪያም ድርጊት የተበሳጩ ሆኑ ፡፡ በዮሐ (12፡ 4-5) ስለ ሽቶዉ ዋጋ በጣም ነገሩ የሆነዉ የተለየው አንዱ ይሁዳ ነው ፤ ለምን ይሁዳ አሰበ ? በገንዘብ ኅላፊነት ላይ ነበር ያሰበዉም ኢየሱስ የፖለቲካ ንጉስ እንደሚሆን እና በእርሱ በስልጣን ከፍ እንደሚል ነበር ፡፡
በዮሐ (17፡ 12) ኢየሱስ ይሁዳን “ የጥፋት ልጅ “ ብሎ ጠራው ይህም ደግሞ “ ይብክነት ልጅ “ ነው ፡፡ ይሁዳ ህይወቱን ወደ ዙሪያዉ የመመለስ ሁሉም አድሎች ነበሩት ነገር ግን በዚያ ፋንታ ለሰይጣን ክፍት ሆነ (ዮሐ 13፡ 2) ፡፡ ይሁዳ እንደ ደቀ መዝሙር ሰዎስት አመታትን ቆይቷል በሂደቱም ስልጣን ተሰጥቶት ነበር ነገር ግን የሆነ ቦታ ላይ ከመንገድ ዞር አለ እዉነቱንም ተወ ፤ የራሱን ስሜት እና ሀሳብ መግለፅ በጀመረ ጊዜ ወደ ኅይማኖታዊ ስልጣኖች እንጂ ወደ ኢየሱስ አይስዳቸው ፡፡ ምንም ነገር አልሰጠም ነገር ግን ትንሽ 30 ብር ተቀብሎአል ፤ “ ቁራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት ፡፡ እንግዲህ ኢየሱስ የምታደርገዉን ቶሎ ብለህ አድርግ አለው “ (ዮ 13፡ 27) ፤ ይህ ማለት ይሁዳ ሰምኣት ነበር ማት አይደለም ምክንያቱም አይሆንም ማለት ይችላል ፡፡ ትንቢቱ ራሱን መስዋዕት ስለሚያደርገዉ ወደ መሲሁ ወደ ሚቀርበዉ ሰዉ ማመልከቱን ቀጠለ (መዝ 41፡ 9; 55፡ 12-14) ፤ ይሁዳ ወደ እግዚአብሄር ስብራቱን ለመመለስ ምርጫ ነበረው በዚያ ፈንታ ወደ ሰይጣን ዞረ ፡፡
ማቴዎስ (26፡ 10-13)፡ ኢየሱስም ለመቃብር እርሱን በማዘጋጀት መልካም እንዳደረገች መለሰላቸው ፤ ለአንድ አመት የሚገባ ደሞዟን በመስጠት እና ፀጉሯ ወደ ታች በኢየሱስ እግር ላይ ለመጠቀም በመፍቀድ ማሪያም ለንጉሱ በእዉነት መንገዱን አዘጋጀች ፡፡ ማር (14፡ 3)፡ “ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችዉ “ ይህ ገለፃ አለው ፡፡ ሁላችንም እንዴት ወደ እግዚአብሄር መምጣት እንደሚገባን ያ ስዕል ነው - በፍርሃት ሳይሆን በድፍረት ለኢየሱስ ሁሉንም ነገር ለመስጠት መዘጋጀት አለብን ፡፡
አንዴ ጠርሙሱ ስለተሰበረ ጠርሙሱን መልሱ መክደን ወይም መተቀም አይቻልም ፡፡ ማሪያም አዉቃም ይሁን ሳታዉቅ ያደረገችዉ ነገር ከብሉይ ኪዳን ስዕል ነው ፤ 2ነገ (9፡ 6) የሚለው፡ “ ዘይቱንም በራሱ ላይ አፍስሶ እንዲህ አለው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል በእግዚአብሄር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ንጉስ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ ፡፡ “ ወጣቱ ነቢይ በንጉሱ ራስ ላይ አፈሰሰው ፤ በራሱ ላይ ባለዉ ዘይት ምክንያት ኢዩ በንጉስ መንገድ የተዘጋጀ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ የተናገረው ማሪያምን የኢየሱስን ትምህርት ሰምታ ስለነበር በቀርብ እንደሚሞት ታውቃለች በዚህም “ ሰዉነቱ ለሞተ የሚሰጥ የባህል እንክብካቤ አያስፈልገዉም ምክንያቱም ሰዉነቱ መበሰበስን አያይም (መዝ 16፡ 1); ሐዋ 2፡ 22-28) ፡፡”
ሁለት አይነት ሰዎች አሉ - የማሪያም አይነት እና ይሁዳ ፤ በማቴዎስ 25 መሰረት ማሪያም በግ ነች ይሁዳ ደግሞ ፍየል ፡፡ ማሪያም እርሱን ትንከባከብ ነበር ይህም የወንድሞቹ እንክብካቤ ጥላ ነው ፤ ይሁዳ ለራሱ ጥንቃቄ ወሰደ ፡፡ ኢየሱስ ስለ ሞቱ የሚሰሙ ሁሉም ለሞቱ ኢየሱስን ለማዘጋጀት እንዴት ሁሉንም ነገር እንደሰጠች ስለ ማሪያምም ይስሙ ብሎ ተናገረ (ቁጥር 13) ስለ እርሷ ድርጊት ሌሎች ሲያስተምሩ ተጨንቃ እንደ ነበር ማሰብ ትችላላችሁ ?
ማቴዎስ (26፡ 14-16)፡ ይሁዳ ወደ ካህናት አለቃ ሄደ ከኢየሱስም ሲመለስ ምንድን እንደሚሰጡት ጠየቃቸው ፤ ሰላሳ ብር ከፈሉት ከዚያም ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት አማራጮችን መመልከት ጀመረ ፡፡ የይሁዳ አሳልፎ የመስጠት ተግባር በቀረዉ በማቴ (26፡ 47-51) ላይ ነው ፡፡ ማሪያም በአምልኮ ንጉሱን ሳመችዉ ፤ ይሁዳ ንጉሱን በአሳልፍ መስጠት ሳመው ፡፡ ማሪያም በስብራቷ መንገዱን አዘጋጀች ፤ ይሁዳ በኩራቱ መንገዱን አዘጋጀ ፡፡
መግቢያ
ዳግላስ ሰን ኦ ዶንነል የፃፈው፡ “ ማሪያም ኢየሱስ ከሁሉም በላይ ትወደዋለች …… በተጨማሪም ማሪይም ኢየሱስን ዉድ በሆነ ፍቅር ትወደዋለች …… ማሪያም ኢየሱስ በተናገረው ነበር የወደደችዉ ፡፡ ” ፅሎቴ ይህ ነው፡ እግዚአብሄር እንድታደርጉት የጠያቃችሁን በራሳችሁ መንገድ ለመስራት እንዳትሞክሩ ፤ ያን ይምታደርጉ በይሁዳ መንገድ ትሄዳላችሁ ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew––Galatians (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 94.
Wiersbe, p. 94.
Douglas Sean O’Donnell and R. Kent Hughes, Matthew: All Authority in Heaven and on Earth (Wheaton, IL: Crossway, 2013), pp. 766-768.
ጥያቄዎች
-
በኢየሱስ ላይ የጠርሙሱን ሽቶ ያፈሰሰችበት ሴት ማን ነበረች (ማቴ 26፡ 7; ዮሐ 12፡ 3) ? ጥቂት ደቀ መዛሙርቶች ስለዚህ ለምን ነበር የተበሳጩት (ዮሐ 12፡ 4-6) ? ኢየሱስ ለእርሱ ስላደረገችለት እንዴት ተሰማው ?
-
በማቴ (26፡ 21) ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ የፋሲካ እራት እንደ ነበራቸዉ ከእነርሱ አንዱ እርሱን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጠው ኢየሱስ ጠቀሰላቸው ፤ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት 30 ብር ከተቀበለ በኋላ ይሁዳ እንዱ እሆንን ብሎ ለምን እንደጠየቀ ምን ታስባላችሁ (ማቴ 26፡ 25) ? ኢየሱስ በመልሱ ለንስሀ ይሁዳን እድል ሰጥቶታል ?
-
በፋሲካ እራት ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱን ያስተዋወቁዉ አዲሱ ኪዳን ምን ነበር (ኤር 31፡ 31; 33-34; ሕዝ 36፡ 26-27; 2ቆሮ 5፡ 21; ዕብ 9፡ 14-15) ? ይህ ከአሮጌዉ ይልቅ እንዴት ነዉ የሚሻለው ?
-
ከመሰቀሉ በፊት በምሽቱ ላይ ኢየሱስ ያደረገዉን ምንድን ታውቃላችሁ (ማቴ 26፡ 30) ? ለእርሱ ምስጋና ለእግዚአብሄር ብሎ መዘመራችሁ እንዴት ያስፈልገዋል(ይጠቅመዋል) (መዝ 100; 113) ? በህይወታችሁ ተጨንቃችሁ እና በብስጭት ተሞልታችሁ የነበረበትን ጊዜ አስቡ ፤ በእነዚያ ሁኔታዎች ጊዜ ለእግዚአብሄር ምስጋና መዘመር ችላችሁ ነበር ? አስቸጋሪ ጊዜዎች ቢመጡ አሁን ታደርጉታላችሁ ?
-
ኢየሱስ ጴጥሮስ እንደሚክደዉ ያውቃል ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ይበተናሉ ይሁን እንጂ አሁንም ለእርሱ እንዲፀልዩለት ፈለገ ፤ ስለ ፀሎት ሊያስተምራቸዉ የሞከረው ምን ነበር (መዝ 43፡ 5; ማቴ 6፡ 13; 26፡ 38, 41) ? ኢየሱስ አባቱን እግዚአብሄርን ይች ፅዋ ከእርሱ እንድታልፍ ስንት ጊዜ ጠየቀው ? በፅሎት ሂወታችሁ እንዴት የፀናችሁ ናችሁ ?
-
በማቴዎስ 26 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 26:13
“I assure you: Wherever this gospel is proclaimed in the whole world, what this woman has done will also be told in memory of her.”
ኢየሱስ በስምዖን ቤት በማዕድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፡፡ ሽቱውንም ወስዳ በራሱ ላይ አፈሰሰችው፡፡ ደቀመዛሙርቱ ምን ለማለት እንደፈለገ በጊዜው ባይረዱትም፥ ኢየሱስ ግን ይህን መስዋዕት ለቀብሩ የሚዘጋጅበት መንገድ አድርጎ ተቀብሎታል፡፡ ደቀመዛሙርቱ ሁኔታውን በአመክኗዊ እይታ በማየት ሴቲቱ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነን ሽቱ በማባከኗ አዘኑ፡፡ ኢየሱስ ግን የሴቲቱን ልብ ተረድቶ ነበር፡፡ ብልቃጡን ሰብራ ሽቱውን በማፍሰሷ አከበራት፡፡ ለንጉሱ ኢየሱስ የሆነ የፍቅር እና የመሰጠት ተግባር እንዲሁም በመጻሕፍት የተጻፈው የተፈጸመበት ክስተት ነበር፡፡
ልባችሁን ለጌታ በምትሰዉበት ጊዜ ፥ አንዳች የምታስቀሩት ነገር አለን? ልቆጣጠር ይገባል የምትሏቸውን ነገሮች ፦ ወደፊታችሁን፣ ልጆቻችሁን፣ ገንዘባችሁን፣ ጤናችሁን፣ ወይም ለቀኑ ያላችሁን አቅድ፥ ከእጆቻችሁ ልቀቁ፡፡ ዛሬ የተሰበረውን ልባችሁን በጌታ ፊት አፍስሳችሁእንዲህ በሉ፥ " ኢየሱስ፥ ሁሉንም ውሰደው!" ትርጉም እንኳን ባይሰጥ እናንተነታችሁን እና ያላችሁን ነገር በሙሉ በእምነት ለጌታ ሰዉ፡፡ በተሰበረ ልብ ንጉሱን ኢየሱስን ስታመለኩት ጌታ ይባርካችኋል፡፡
“ እውነት እላችኋለው፥ ይህ ወንጌል በአለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርሷ ያደረገችው ደግሞ ለእርሏ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል፡፡”
— የማቴዎስ ወንጌል 26:13
ተጨማሪ ጥቅሶች
- 2ኛ ነገስት 9:6 — “ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ገባ፤ ዘይቱንም በራሱ ላይ አፍስሶ እንዲህ አለው፦የእስራኤል አምላክ እግዚያብሔር እንዲህ ይላል፦ በእግዚያብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ንጉስ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፡፡’”
- መዝሙረ ዳዊት 51:16-17 – “ መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፤ የሚቃጠለው መስዋዕት ደስ አያሰኝህም፡፡ የእግዚያብሔር መስዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፡፡”
- መዝሙረ ዳዊት 62:8 – “የህዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚያብሔር ረዳታችን ነው፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 26
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።