Sheep, Goats, and Brethren
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 25 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በማቴዎስ 24 ለትናትናዉ ትምሀርት አላማ ለመጨረሻዉ ጊዜ መዘጋጀት ነው ፡፡ ማቴዎስ (25፡ 1-13) የአስሩ ደናግልት ሴቶች ምሳሌ እና ግማሾቹ ስለተዘጋጁት እና ስላልተዘጋጁት የሚያወራ ነው ፤ ቁጥር (14-30) ስለ አስሩን ተሰጥኦ ምሳሌ ያወራል ፡፡ ጥያቄዉ ይህ ነው፡ ለክብሩ የተቀበልነዉን ተሰጥኦ እንዴት አድርገን ነዉ የምንጠቀመው ? ዛሬ ከምናወራዉ በላይ ሌላ ከባድ ርዕሳ የለም ፡፡
መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ሁለት ፍርዶች ያወራል፡
- የህዝቦች ፍርድ - በትንሳኤ የሚነሳን አይጠቅስም በዚህም በህይወት የሚኖሩት ፍርድ ነው ፤ በዚህ ዉስጥ ሰዎስት ቡድኖች ናቸው፡ በጎች፣ ፍየሎች እና ወንድሞች ፡፡
- የነጩ ዙፋን ፍርድ - ለማያምኑት እና ለተረገሙት ነው ይህንም ቆይተን እንሸፍነዋለን ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (25፡ 31)፡ ይህ የሚከሰተው ከመሲሁ መንግስት(ከ 1,000 አመት ዘመን) በፊት እና ከአርማጌድዮን ጦርነት በኋላ ፤ ይህ ፍርድ ከሰባት አመት የሰላማ ጊዜ እና ከአመፀ ሰዉ መምጣት በፊት ነው ፡፡
በቁጥር 31 የሰዉ ልጅ ከመለዓክቱ ጋር በሚመጣ ጊዜ (ዳን 7፡ 13-14) በክብሩ በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል ፡፡ የሁሉም ህዝብ ሰዎች በአንድ ላይ በፊቱ ይመጣሉ እረኛዉ መንጋዉን እንደለየው ( በጎቹን እና ፍየሎቹን ሁለቱንም ለይቶ በአንድ ላይ) ፡፡ በዚህ ሀሳብ በጉቹ አማኞች ናቸው ፍየሎቹ ደግሞ የማያምኑ ናቸው ፡፡ በሚከተሉት ጥቅሶች የበጎቹን መልክ መሳል እፈልጋለሁ፡
ማቴ (10፡ 16)፡ “ እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ ፡፡ ”
ዮሐ (10፡ 14)፡ “ መልካም እረኛ እኔ ነኝ ፤ የራሴን በጎች አዉቃለሁ የራሴም በጎች ያዉቁኛል ፡፡ “
ዮሐ (10፡ 16)፡ “ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ ፡፡ “
መዝ (79፡ 13)፡ “ እኛ ሕዝብህ ግን የማሰማርያህም በጎች ለዘላለም እናመሰግንኃለን ፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን ፡፡ “
ሕዝ (34፡ 17)፡ “ ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል እናንተም መንጋዬ ሆይ እነሆ በበግና በበግ መካከል በአዉራ በግና በአዉራ ፍየል ፍየልም መካከል እፈርዳለሁ ፡፡ “
በጎቹ በቀኙ በኩል ፍየሎቹ ደግሞ በግራዉ በኩል ይቀመጣሉ ፤ ቀኝ ሞከስን ሲወክል ግራ ደግሞ ሞገስ ማጣትን ይወክላል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በጎች እና ፍየሎች በአንድ ላይ ሊታጎሩ ይችላሉ ነገር ግን ያ የሆነ ጊዜ ላይ የሚለያዩ ይሆናሉ ሲል አመልክቶአል ፡፡
ማቴዎስ (25፡ 34)፡ በጎቹ በንጉሱ ለእነርሱ የተዘጋጀዉን መንግስት ይወርሳሉ ፤ መጀመሪያ ይመጣል በዋነኝነት በንጉሱ በበጎቹ እምነት ፡፡
ኤፌ (1፡ 4)፡ “ ዓለም ሳይፈጠር በፊት ቅዱሳንና ነዉር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን፡፡”
ሮሜ (8፡ 29)፡ “ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና ፡፡ “
ማቴዎስ (25፡ 35-40)፡ እነዚህ ቁጥሮች የበጎቹን አገልግሎት ወይም ፍሬአቸዉን ይገልፃል ፡፡ ይህ የሚሆንበት የጊዜ መዋቅር በመከራዉ ጊዜ ለሚኖሩ ሰዎች ነው እነዚህ ነገሮች ለወንድሞች ይደረጋሉ - ለሚያምኑ አይሁዶች ፡፡ በጎቹ እነዚህን ነገሮች መቼ እንደሚያደርጉ ይጠይቃሉ (ቁጥር 37-39) ፤ ንጉሱም “ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት “ ብሎ መለሰላቸው (ቁጥር 40) ፡፡ ሰዎስተኛው ቡድን ሰዎች ይህ ነው - ወንድሞቹ ፡፡
በጎቹ በመከራው ጊዜ ወንድሞቹን ያገለግላሉ፡ የሚያምኑት አይሁዶች በኑሮአቸዉ በኢየሱስ የታመኑትን የ144,000 ወንጌል አካፊዎች ተቀባዮች ናቸው ፤ ለመመገብ ወይም ቤተሰቦቻቸዉን ለመንከባከብ ገንዘብ ለመስራት መግዛት ወይም መሸጥ አይችሉም ምክንያቱም ይህ ቡድን የአዉሬዉ ምልክት በላያቸዉ ላይ የላቸውም ፡፡ ስለሆነም አሕዛብ ለኑሮአቸዉ በታላቅ ስጋት ለእነርሱ እንክብካቤ በማቅረብ በጉዳዩ ጣልቃ ይገባሉ ፤ አሕዛቦች እርዳታ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል ፡፡ “ መነሳሳታቸዉ ለሽልማት አልነበረም ለፍቅር ዋጋ መክፈል እንጂ “ ፤ ይህ ማለት መጨረሻዉ ጊዜ አካባቢ ድረስ ያሉ አማኞች የእነዚህን አይሁዶች እንክብካቤ ይወስዳሉ ፡፡
ማቴ (10፡ 40)፡ “ እናንተን የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል “ (ቁጥር 40) ፡፡ መጀመሪያ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ጠፉት እስራኤል በጎች ተላኩ ነገር ግን በደህና አልተቀበሉትም ፤ ስለዚህ መልዕክቱ ወደ አሕዛብ ሄደ ፡፡ አሁን እነዚህ አሕዛቦች በኢየሱስ ለማመን የመጡት ወንድሞቹን ጥንቃቄ የሚወስዱላቸው ናቸው ፡፡
ማቴዎስ (25፡ 41-45)፡ በግራ በኩል ያሉት የተረገሙ እና ወደ ዘላለማዊ እሳት የተላኩ ናቸው ፤ ወንድሞቹን ከመርዳት ይልቅ ስለ ራሳቸው እና ስለ ራሳቸዉ ፍላጎት የሚያስቡ ነበሩ ፡፡
ማቴዎስ (25፡ 46)፡ በቀኝ በኩል ያሉት ወደ ዘላለም ህይወት መቀበል ሲሄዱ እነዚያ በግራ በኩል ያሉት ወደ ዘላለም ቅጣት ይሄዳሉ ፡፡ “ የማያልቅ “ በፍፁም ከማያቆም ከዘላለማዊ ጋር እኩል ነው ፤ “ ዘላለማዊ ቅጣት “ ከዘላለማዊ ሲኦል ጋር እኩል ነው ፡፡ ሲኦል ትክክለኛ ቦታ አይደለም የሚል ሀሳብ እንዳትገዙ ፡፡
በመፅሀፍት የሲኦል መግለጫዎች፡
እሳት በፍፁም አይጠፋም (ማቴ 3፡ 12) ፡፡
እፍረት እና የዘላለም ጉስቁልና (ዳን 12፡ 2) ፡፡
ትሉ የማይሞትበት እና እሳቱ አይጠፉም (ማር 9፡ 44) ፡፡
ስቃይ…ጣር በነበልባ ዉስጥ ! (ሉቃ 16፡ 23-24) ፡፡
የአመፅ እሳት (2ተሰ 1፡ 8) ፡፡
የስቃያቸውም ጢስ በዘላለም ላይ ይሄዳል (ራዕ 14፡ 11) ፡፡
ሞትና ሲኦል በእሳት ባህር ዉስጥ ተጣሉ (ራዕ 20፡ 14) ፡፡
መዝጊያ
ፍየሎችን ፍየል ከመሆን እንከላከላቸው ፤ አሁን ንጉሱን ኢየሱስን እንወክል ስለዚህ ሰዎች በግ ለመሆን ይዘጋጃሉ ፡፡ ትንሳኤ፣ እዉነት እና ህይወት የሆነውን ንጉሱ ኢየሱስ እንያዝ ፤ በንጉሱ በኢየሱስ በኩል ብቻ በንጉሱ ቀኝ በኩል መኖር እንችላለን ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1192.
Warren Wiersbe, Exposition Bible Commentary: Matthew–Galatians (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 93.
Wiersbe, p. 93.
ጥያቄዎች
-
በሰነፎቹ ደናግልት እና በልባሞቹ ደናግልት/ ደንገጡሮች መካከል ልዩነት ምንድን ነበር (ማቴ 25፡ 1-13) ? እንዴት ነበርስ የሚመሳሰሉት ? ዝግጁ ለነበሩት ደንገጡሮች ሽልማቱ ምን ነበር ተዘጋጅተዉ ላልነበሩትስ ቅጣቱ ምን ነበር ?
-
በማቴ( 25፡ 14-28) በተሰጥኦዎቹ ምሳሌ ላይ ለእያንዳንዱ አገልጋይ ምን ያክል ተሰጥኦዎች ተሰጥቶአቸዉ ነበር ? ለተለያየዉ ዉጤት ጌታዉ እንዴት አፀፋ መለሰላቸው ? በአገልግሎትዉጤትን እንዳናወዳድር ኢየሱስ ምንድን ያስተምረናል ?
-
የመጨረሻው አገልጋይ በተሰጥዖዉ ያደረገዉን ጌታዉ ለምን አላወደደዉም (ማቴ 25፡ 24-30) ? እግዚአብሄር ስለ ስንፍና እንዴት ይሰማዋል (ምሳ 12፡ 27; 20፡ 4; ሕዝ 16፡ 49; ሮሜ 12፡ 11) ? ቅጣቱ በጣም አደገኛ እንደ ነበር ታስባላች ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
-
ኢየሱስ ለመሰቀል ነበር ፤ ስለ ማቴ (25፡ 31-34) ምንድን ነበር የተናገረው ? የእነዚህ ንግግሮች ትንቢት በብሉይ ኪዳን እና በወደፊት ትንቢት እንዴት ይገኛል ? (2ሳሙ 7፡ 12-13; ሕዝ 20፡ 38; ዳን 7፡ 13-14; 1ተሰ 4፡ 16)
-
ሌሎችን ስናገለግል በእዉነቱ እንዴት ክርስቶስን እናገለግላለን (ማቴ 25፡ 35-40) ? ሌሎችን በተገቢ ለማገልገል በጎረቤቶችችሁ ዙሪያ፣ በት/ቤታችሁ ዙሪያ ወይም በስራችሁ ዙሩያ ምን ማድረግ ትችላላችሁ ?
-
በማቴዎስ 25 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 25:13
“Therefore, be alert, because you don’t know either the day or the hour.”
ዳግም ለሚመለስበት ቀን እንዲዘጋጁ እና ንቁ እንዲሆኑ፥ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን አዝዟል፡፡ ስለተሰጣቸው ስጦታ፣ መክሊት አና መዝገብ ሳያጉረመርሙ ወይም ሳያወዳድሩ በታማኝነት እንዲኖሩ በግልጽ መክሮአቸዋል፡፡ ኢየሱስ አነዚህ ስጦታዎች ለእርሱ ክብር እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚመለስ ብታውቁ ኖሮ ሕይወታቸሁን እንዴት ትኖሩ ነበር? ከድንጋይ በታች ተደብቃችሁ፥ ቀናቶቹን በመተኛት ታሳልፏቸው ይሆን? በጭራሽ! የእግዚያብሔር ደስታ ሀይላችሁ ነው! ደቀመዛሙርቱን እንዳዘዛቸው እናንተም በእርሱ ባገኛችሁት የዘላላም ተስፋ ምክንያት ህይወታችሁን በማስተዋል እንድትኖሩ ያዛችኋል፡፡ ይህ ማለት ከእርሱ ጋር ለዘላላም ለመኖር የሚያዘጋጃችሁን እና የኢየሱስን ፍቅር የሚያስተምራቸሁን መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በፍርሀት ስሜት ሳትገደቡ፥ በክርስቶስ ያላችሁን ተሰፋ እና እምነት ለምትወዷቸው ማካፈልም ማለት ይሆናል፡፡ ሆን ብሎ መኖር ማለት፥ እንግዳ ለመቀበል፣ ለማስተማር፣ ወይም ያለእፍረት በእምነት ለማገልገል የተሰጣችሁን የፀጋ ስጦታዎች መጠቀም የሚለውን ይመስላል፡፡ ስጦታችሁን መደበቅ ወይንም በፍርሃት መኖር ዳግም አይሁንባችሁ፡፡ ጌታ በሰጣችሁ ነገር ሁሉ ህይወታችሁን በሙላት ስትኖሩ፥ ኢየሱስ እንደዚ ይላችኋል፥ " መልካም፥ አንተ በጎ እና ታማኝ ባርያ! በጥቂቱ ታምነሃል እና በብዙ እሾምሀለው!" በዛሬው ቀን ጊዜ አታባክኑ፡፡ ለንጉሱ ኢየሱስ ዳግም መመለስ እንድትዘጋጁ እና ህይወታችሁን በሙላት እንድትኖሩ፥ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራችሁ ጠይቁት፡፡
“ቀኒቱንና ሰአቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ፡፡”
— የማቴዎስ ወንጌል 25:13
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ገላቲያ 5:25 — “ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላላስ፡፡”
- ኤፌሶን 3:20 — “ እንግዲህ በእኛ እንደሚሰራው ሀይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፡፡”
- 1ኛ ጴጥሮስ 4:10 — “ ልዩ ልዩን የእግዚያብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደመሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በእርሳችሁ አገልግሉ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 25
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።