Signs of the End Times
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በማቴዎስ 24 ኢየሱስ የመመለሱን ምልክት ደቀመዛሙርቱን ጋር ተጋራ ፤ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ ብዙ አመለካከቶች አሉ ፡፡ ከእነርሱ ዉስጥ በጥቂቶቹ እንነጋገራለን ፡፡ መፅሀፍትን እናገላብጣለን የእግዚአብሄር ቃል ስለ ራሱም እንዲናገር እንፈቅዳለን ፤ የዚህ ክፍል መጨረሻ ለንጉሱ መመለስ ለእናንተ የተዘጋጃችሁ እንድትሆኑ ነው ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (24፡ 1-2)፡ ኢየሱስ የመቅደሱን ግንብ መፈረስን አመጣ ( አ.አ 70) ፤ ይህ የመቅደሱን መፍረስ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በኢየሱስ ሞት ስለ ሚቀደደዉ መጋረጃም እንጂ ፡፡
ማቴዎስ (24፡ 3-8)፡ ቆይቶ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን እነዚህ ነገሮች መቼ እንደሚሆኑና ምንድን ምልክቶች እንደሚያዩ ጠየቁት ፤ ኢየሱስም የሚያታልሉዓቸውን እንዲያስታዉሉዓቸው አስጠነቀቃቸው - ሀሰተኛ መሲሆችን (ቁጥር 5) ፡፡ ብዙዎቹ መሲሁ ነኝ እያሉ በቀደመዉ ጊዜ መጥተዋል ፤ ኢየሱስም እነዚህ ሀሰተኛ መሲሆች ብዙዎችን ያስታሉ አለ ፡፡ በተጨማሪም ጦርነት እና የጦርነት ወሬ ይሆናል ነገር ግን መጨረሻዉ አሁንም አይመጣም አለ (ቁጥር 6) ፤ እንደገናም ርሀብ እና የመሬት መናወጥ ይሆናል (ቁጥር 7) ፡፡ እነዚህ ሁሉ የምጥ ህመም ይሆናል (ቁጥር 8) ፡፡ እነዚህ ሁሉ ምልክቶች እንድንዘጋጅ ይነግሩናል ፡፡
ማቴዎስ (24፡ 9-14)፡ ቀጥሎም የደቀመዛሙርቱ ስቃይ እና ሞት ይመጣል ፤ በኢየሱስ ስም የተጠሩት ሁሉ የሚጠሉና የሚከዱ ይኖናሉ ፡፡ ሀሰተኛ ነቢያት የሚያዳምጧቸዉን ወደ ስህተት የሚመራ ሀሰተኛ ትንቢቶች ያመጣሉ ፤ ህግ የለሽነት እና መመሰቃቀል የሚጨምሩ እና የሚስፋፉ ይሆናል ፡፡ “ እስከ መጨረሻ የሚፀና ግን ይድናል ፡፡“ እስከ መጨረሻ ስለምንፀና በዚህ እንቀጣለን ! የእግዚአብሄር መንግስት መልካም ዜና በአለም ዙሪያ ይነገራል ፡፡
እዚህ ወደ መጨረሻዉ ጊዜ እንሂድ፡ በዚህን ጊዜ 144,000 መልዕክቱን የሚያደርስ ይሆናሉ ፤ የአይሁድ ወንጌላዊያን ይሆናሉ (ራዕ 7፡ 4) ፤ ያም ከእያንዳንዳቸው ከ12 ነገድ 12,000 ነው ፡፡ በግልፅ አላማቸው የእግዚአብሄርን መንግስት መስበክ ይሆናል ፤ የፀኑትም እነዚህ አይሁዳዊ ወንጌላዊያንን መርዳት ይችላሉ ፡፡
ማቴዎስ (24፡ 15-22)፡ ቁጥር 15 ልክ እንደ ቦንብ የወደቀ ነው ፤ ወንጌል መሄድ በመጀመሩ “ ለብቸኝነት ምክንያት የሆነው ጥላቻ “(ፀረ ክርስቶስ) በመምጣት እና በሁለተኛዉ ግማሽ የሰላም ሰባት አመት ላይ ከፍ ይላል(ይቆጣጠራል) ፤ ለእግዚአብሄር ቅዱስ ታ በሆነው ይቆማል ፡፡ ዳን(9፡ 24-27) በማቴዎስ 24 ስለ ተወያየንባቸው ምልክቶች ያወራል ፤ በእነዚህ ጥቅሶች አንድ ሳምንት ለ7 አመታት ይቆማል ፡፡ ለ490 አመታት የጊዜ ሰለዳው ወደ ሰዎስት ክፍል የተከፋፈለ ነው በዚህም ይህን ይመስላል፡
የመጀመሪያዎቹ 7 ሳምንታት (49 አመታት)፡ የኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ትገነባለች ፡፡
ቀጣዩ 63 ሳምንታት (434 አመታት)፡ መሲሁ መጥቶ ለአለም ሁሉ ኃጢዓት ይሞታል ፡፡
የመጨረሳው ሳምንት (7 አመታት)፡ ለመጀመሪያዎቹ ሰዎስት እና ግማሽ አመታት ለሰላም ጊዜ ልዑሉ ከአይሁዶች ጋር ስምምነት ያደርጋል ከዚያ በመቀጠል የዓመፅ ሰው በመምጣት ከፍይላል (ይቆጣጠራል) (2ተሰ 2፡ 3-4) ፡፡
የዓመፅ ሰዉ በእግዚአብሄር መቅደስ በመቀመጥ እግዚአብሄር እንደሆነ ይናገራል ፡፡ በእስራኤል የሰባት አመታትን የሰላም ስምምነት ስናይ ያን ስምምነት ያነሳሳው ከመሪዎቹ አንዱ እራሱን በእግዚአብሄር መቅደስ ያስቀምጣል እግዚአብሄርም እንደሆነ ያዉጃል እስከዚያ ኢየሱስ ተመላሶ እንዳልመጣ እናውቃለን ፡፡ በአመታቱ ሰዎስተኛው ክፍል ምንም አናይም ፡፡ ይህ በሆነ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ሁሉ የራሳቸዉን ነገር እንኳን ምንም ሳይዙ ወደ ተራራ ይሸሻሉ(ቁጥር 16-18) ፤ ለእርጉዝ ሴቶች እና ለህፃን ልጅ እናቶች አስቸጋሪ ያሆናል (ቁጥር 19) ወይም በክረምት እና ሰንበት ላይ ላለ (ቁጥር 20) ፡፡ ያ የሰላም ስምምነት በተደረገ ጊዜ ለማወቅ የመጨረሻዉን ጊዜ ለመጠበቅ መጀመር እንችላለን ፡፡ እስካሁን አለም አይቶት የማያውቅ ምንም ነገር የማይመስል ዉጣ ውረድ ይኖራል በተመረጡት ምክንያት የመከራው ቀናቶች ባያጥሩ ኖሮ ማንም አይድንም (ቁጥር 21-22) ፡፡
ማቴዎስ (24፡ 23-28)፡ በመከራዉ ጊዜ ሀሰተኛ መሲሆች እና ሀሰተኛ ነብያቶች እንደገና ይገለጣሉ (ቁጥር 23-24)፡፡ ኢየሱስ በእነዚህ ሀሰተኛ መልዕክተኞች የተታለሉ እንዳይሆኑና እንዳይሳቡ አብራራላቸው(በደንብ ገለጠላቸው) (ቁጥር 25-26) ፡፡ የመሲሁን መምጣት ጥቂቶች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ያዩታል በድንገት በማንኛዉም ጊዜ ይመጣል (ቁጥር 27) ! የሆነ ጊዜ ላይ አርማጌድዮን ላይ ለመዋጋት የሰዎች ክምችት(ስበስብ) ይኖራል እልቂቱም አሰፈሪ ይሆናል (ቁጥር 28) ፤ የሰዉ ልጅ ከመምጣቱ በፊት ከባድ ጦርነት ይኖራል ፡፡
ማቴዎስ (24፡ 29-31)፡ ከመከራው እብደት ቦኃላ ፀሀይ፣ ጨረቃ እና ከዋክብት ይቀየራሉ ከዚያም “ በኃይልና በክብር “ በሰማይ የሰዉ ልጀ ይታያል (ቁጥር 29-30) ፤ በሐዋ 1 ትቶ እንደሄደበት መንገድ በተመሳሳይ በደመና ላይ ይታያል ፡፡ የአለም ህዝብ ሲያዩት ያዝናሉ ፤ መለዓክቶቹ ከአለም ዙሪያ የተመረጡትን ለመሰብሰብ በመለከት ይወጣሉ (ቁጥር 31) ፡፡
- የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ በሆነ ጊዜ ላይ ይካሄዳል ፤ በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ መሆን ይበቅብናል ፡፡
- የአስር አዎሮፓዉያን አገር መሪ ከእስራኤል ጋር የሰባት አመት የሰላም ስምምነት ያደርጋሉ ፤ ያ መሪ የአመፅ ሰዉ ሊሆን ይችላል (ዳን 9፡ 26-27) ፤ ያ ሲሆን ዝግጁ መሆን ይተበቅብናል ፡፡
- ከሰዎስት አመት በኋላ የአመፅ ሰዉ ( የመለየት(የብቸኝነት) ከፍተኛ ጥላቻ) ስምምነቱን ይሰብራል (ዳን 9፡ 27) ፡፡
- የአመፅ ሰው ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ በመቅደሱ ምስሉን ይተክላል (2ተሰ 2፡ 4) ፡፡
- የአመፅ ሰዉ እንዲያመልኩት አለምን መቆጣጠር ይጀምራል በዚያን ጊዜ እግዚአብሄር ታላቅ መከራ ይልካል፡፡
- ህዝቦች አርማጌድዮን ላይ ይሰበሰባሉ የአመፅ ሰዉን ይዋጋሉ ፤ የሆነ ጊዜ ላይ በእስራኤል ላይ የአመፅን ሰዉ ለመዋጋት የክርስቶስ መምጣትን መልክቶች እናያለን ፡፡
- ንጉስ ኢየሱስ ወደ ምድር ይመለሳል ጠላቱን ያሸንፋል በአይሆዶች የተቀበለ ይሆናል መንግስቱን ይመሰርታል
- ከዚያም ኢየሱስ ለ 1,000 አመታት ይገዛል ፡፡
መዝጊያ
በግልፅ ይህ በጣም ግልፅ ማጠቃለያ ነው ፡፡ አስፈላጊነቱ በምታመልጡበት በመነጠቅ ስበት ላይ ካልቆለላችሁ(ካልቆማችሁ) በዚህ ምክንያት መከራውን እንደ ማትቋቋሙት እንድታውቁት ነው ፤ ለእኛ አስፈላጊው እስከመጨረሻው መቋቋም እንድንችል የተዘጋጀን መሆን ነው ፡፡
ጥያቄዎች
-
ማቴ (24፡ 36) እና 42 ተመልከቱ ፤ “ ጊዜዉን ባለማወቅ “ እና “ ጊዜዉን በመጠበቅ “ መካከል ያለው ማስተካከያ(መጠን) ምንድን ነው ? (ማቴ 25፡ 1-13; ሉቃ 12፡ 56)
-
የመሲሁን ተመልሶ መምጣት ምንድን ክስተት/ነገሮች ይቀድሟሉ ? በሂደቱ ክስተት የት ነን ?
-
በማቴ (24፡ 45-51) ያለዉን ትዕዛዝ ወደ ራሳችሁ ህይወት በተግባር እንዴት ለተገብሩት ትችላላችሁ ?
-
በራሳችሁ ልብ ዉስጥ ማቴዎስ 24 እንዴት አስቸኳይነትን ያስነሳል በዚያ አስቸኳይነት ላይ እንዴት አክት ታደርጋላችሁ ?
-
በማቴዎስ 24 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 24:6b,8
“See that you are not alarmed, because these things must take place, but the end is not yet. . . . All these events are the beginning of birth pains.”
ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን፥ " የመምጣትህ እና የአለም መጨረሻ ምልክት ምንደነው?" ኢየሱስም አለ፦ ሰደት፣ ሕገወጥነት፣ ሀሰተኛ ክርሰቶሶች፣ ሀሰተኛ ነቢያት፣ ጦር እና የጦር ወሬ፣ ረሀብ፣ የምድር መናወጥ፣ ህዝብ በህዝብ ላይ መንግስትም በመንግስት ላይ ይነሳል እንዲሁም ብዙዎች እርስ በእርስ አልፈው ይሰጣጣሉ ደግሞም ይጠላላሉ፡፡ ህፃን ልጇን ለመውለድ ማማጥ እንደ ጀመረች እናት፥ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡
ኢየሱስም ከመመለሱ በፊት ይህች አለም በተመሳሳይ ምጥ ውስጥ ታልፋለች፡፡ እነዚህ ሁሉ ሊሆኑ የግድ ነውና፥ በመሆናቸው አትደንግጡ ይልቁንም የጌታ መምጫ መቅረቡን አስተውሉ፡፡ በፍርሃት አትኑሩ፡፡ የምጥ ጣር ውስጥ እያለፋችሁ እንደሆነ በማሰብ፥ በክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ ኑሩ፡፡
ዛሬ፥ ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት እየተዘጋጃችሁ የእግዚያብሔርን ፍቅር ለአለም ለመናገር ያሏችሁን እድሎች ሁሉ ተጠቀሙ፡፡
“ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ. . እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡”
— የማቴዎስ ወንጌል 24:6፣8
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የማቴዎስ ወንጌል 24:14 — “ ለአሕዛብ ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል፡፡”
- የማርቆስ ወንጌል 13:32 — “ ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላዕክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም፡፡”
- 2ኛ ጴጥሮስ 3:10 — “ የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምጽ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርሷ ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል፡፡ ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 24
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።