The Gospels Matthew

Jesus' Lamentations Over Jerusalem

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 23 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 133 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እንደ ቅዱስ ሳምንት በምናውቀዉ በማቴዎስ አካዉንት ላይ ነን ፤ ኢየሱስ በመቅደሱ አደባባይ እያስተማረ ነበር ፡፡ በትንሳኤ ጥያቄ ላይ ሰዱቃዊያንን ዝም አሰኝቶአቸው ነበር በተጨማሪም በታላቂቱ ትዕዛዝ እና በመሲሁ ላይ ከፈሪሳዉያን ጋር ተከራክሮ ነበር ፤ አሁን በመጨረሻ የጉባኤ መልዕክቱ ኢየሱስ የኃይማኖት መሪዎች ግብዝነታቸዉን ሲያስጠነቅቅ እናያለን ፡፡ እነዚህ እንደ ኃይለኛ ትቸታ እና በቁጣ በመንቀፍ (ከባድ ግሰፀ) በመግለፅ ኃይለኛ ማስጠንቀቂያዎች ነበሩ ፤ እርሱን ከመስማት ይልቅ ኢየሱስን ለማጥመድ ለግብዝነት ጥያቄአቸዉ ተገቢ ምላሽ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ለፅድቅ በማሰብ መደንዘዛቸዉ እና አሁንም እንዳዘኑ ቀጥታ አመልክቶአቸዉ ነበር ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (23፡ 1-3)፡ ኢየሱስም ቀጥሎ ለህዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው ፤ ዋይርስቤ “ ሀሰት የፅድቅ ፅንስ ሀሳብ እንደ ነበራቸው “ ፅፎአል (ቁጥር 2-3) ፡፡ 6,000 ያክል ፈሪሳዉያን ነበሩ ከብዙ ተጨማሪ “ ተከታዮቻቸው “ ጋር ፤ “ ፈሪሳዊይ “ የሚለው ስም “መለየት “ ማለት ነው ፤ በህጉ ትንሽ ጥልቀት በትንሹ የተጨነቁ ነበሩ ፡፡ በዘሌ 21 እና 22 ከመጣ ትክክል ባልሆነ ትኩረት ላይ ህጋዊ እሆነ ወጥመድ ዉስጥ ይወድቃሉ ፡፡

ለፈሪሳዉያን ቅድስና ማለት ለእግዚአብሄር ህግ ዉጫዊ ማረጋገጫ ማነት ነው ፤ የልብን ዉስጣዊ ሁኔታ ገፍተዋል ፡፡ ኢየሱስ በፈሪሳዊያን በዋነኝነት አትኩሮ ነበር ምክንያቱም ለእዉነት ዝግ ነበሩ ብዙዎቹም ኢየሱስ በተለመደ የሚያስተራቸዉ ነበሩት ፡፡ የቶራው ትዕዛዝ እና የኢየሱስ ዋነኛ ትኩረት የነበሩት የተወሰኑ የክፉ መሪዎች ግብዝነትን በህጋዊነት መመልከት ነበር ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 4-6)፡ ዋይርስቤ ፈሪሳዉያንን “ የአገልግሎት ሀሰተኝ ፅንስ ሀሳብ እንደ ነበራቸው “ ተናግሮአል (ቁትር 4) ፤ ለፈሪሳዉያን አገልግሎት ማለት የያዙዓቸዉን ህጎች የራሳቸዉን ቀምበር በመጨመር ወደ ህዝቡ ማውረድ ማለት ነው ፡፡ ኢየሱስ የሰዎችን ቀምበር ሊያቀል መጣ (ማቴ 11፡ 28-30) ፡፡ ህጋዊ ኃይማኖተኝነት ሁልጊዜ ቀንበርን ማክበድ የሚያደርግ ይመስላል ፡፡

ዋይርስቤ ደግሞም ፈሪሳዉያን “ የታላቅነት ሀሰተኛ ፅንስ ሀሳብ እንደ ነበራቸው “ ፅፎአል ፡፡ በአዲስ ኪዳን አሸንክታብ (በእጃቸዉ እና በራሳቸዉ ላይ የሚቀመጠውን ሸክም ያስረዝማሉ) እዚህ ጋር ብቻ የተጠቀሰ ነው ፡፡ መነሳንሶቻቸው ሰማያዊ እና በዉጨኛው ልብሶቻቸው ነጭቅ የተቀመቀመ ጠርዝ ነበር (ዘኁ 15፡ 36; ዘዳ 22፡ 12) ፡፡ ግብዞች ዘርፋቸዉን ያስረዝማሉ ምክንያቱም በደንብ የሚታይ ዘርፍ በጣም መንፈሳዉ ይመስላቸዋል ፤ ለእነርሱ ስኬት ከሰዎች እዉቅና እና ክብር ማግኘት ነው ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 7-10)፡ ራቢ ማለት በግልፅ “ የእኔ ታላቅ “ እና በተጨማሪም “ የኔ ማስተር “ ወይም “የኔ መምህር “ ብሎ መጠቀም ይቻላል ፤ በሁሉም ለህጉ ምሁራን የሚጠቀሙት የክብር ማዕረግ ሆኗል ፤ በተጨማሪም ይህ ማዕረግ ከታላቅነት ጋር የተዛመደ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከሚለዩዓቸው ወይም ከማህበሩ እምነት በላይ የሚሆኑ ማዕረጎችን እንዲያስወግዱ አስጠነቀቃቸው ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 11-12)፡ ማቴዎስ (23፡ 11) በጣም አንድ አይነት ከሆነው ከማቴዎስ (20፡ 26-28) ቃል ጋር አነፃፅሩት ፤ ታላቅ ሌሎቹን ያገለገለ ሰዉ ነው ፡፡ ግብዞች እንዲገለገሉ እና እንዲከበሩ ይፈልጋሉ ፤ ፈሪሳዉያን ለእግዚአብሄር እዉነት እና ለራሳቸዉ ኃጢዓት እዉሮች ሰለ ነበሩ የኢየሱስ አመለካከት አንዱ የሚያም ሀዘን ነበር ፡፡

ዋይርስቤ “ ምናልባት በእነዚህ ሰባት(ወይም ስምንት) “ አሳዛኞች ” ለማውራት በማቴዎስ (5፡ 1-12) ላይ ከሚገኙት ብፁእ ጋር ማነፃፀር ምርጡ መንገድ ነው ፤ በተራራው ስብከተ ላይ ጌታ እዉነተኛ ፅድቅን ገልፆአል ፤ እዚህ ደግሞ ሀሰተኛ ፅድቅን ገልፆአል ፡፡ “

ማቴዎስ (23፡ 13-14)፡ በመንፈስ ድሆች መንግሰተ ሰማይ ይገባሉ ግን በመንፈስ ኩራተኞች ራሳቸዉንም ሌሎችንም ያስወጣሉ ፡፡ በራሳቸዉ ኃጢዓት ላይ ከማዘን ይልቅ በመበለቶች ያዝናሉ እነርሱን ለመዝረፍ ፈሪሳዉያን የእነዚህን ሰዎች ጥቅም ወሰዱ ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 15-22)፡ ፈሪሳዉያን በራሳው ህጋዊ ዘዴ ሌሎችን ለማሳመን ይጥራሉ ፤ በዙሪያቸው ላሉት ህያው እግዚአብሄርን እንዲያዉቁት አያደርጉም ፡፡ ፈሪሳዉያን ለእዉነተኛ ህይወት ዋጋ እዉሮች ነበሩ ፤ የእነርሱ ቅድሚያ መደናገር ነበር ፡፡ ፈሪሳዉያን መሀላ ይቀበላሉ ከዚያም ያን መኃላ ለማረጋገጥ አስፈሪ ነገሮችን ይጠቀማሉ - በመቅደሱ ያለ ወርቅን፣ ወይም በመሰዊያው ስጦታ ፤ ከቅድሚያ ነገራቸው እግዚአብሄርን አስወጥተውታል ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 23-24)፡ ፈሪሳዉያን አስፈላጊ ነገሮችን በማስወገድ እንኳን ለሁሉም አካባቢ የህይወት ህግ ነበራቸው ፡፡ ከሁሉም ነገር ከጓዳቸው ሳንቲም፣ ከእንስላል እና ከከስሙን አስራት ያወጣሉ ፤ አስራታቸው የሚጨስ መሸፈኛ ብቻ ነበር ከገፉዓቸው በጣም አሰፈላጊ ነገር ከሆኑት ህጎች ከማስታዋል ህዝቡን ያመናታሉ - ፍትህ, ምህረትን እና እምነትን (ዘዳ 10፡ 12-13; ሚክ 6፡ 8) ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 25-28)፡ ኢየሱስ ሁለት ሁለት ማሳዮችን ፅዋን እና ወጭትን እና መቃብርን ተጠቀመ ፤ እነዚህ ማሳዮች ሁለቱም በዋናነት ተመሳሳይ ነገር ይናገራሉ ፡፡ በዉጪ የነፃ መሆን ቀላል ነበር በተመሳሳይ ጊዜ ውስጣቸዉ እረክሶአል ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 29-33)፡ እባቦች(እፉኝቶች) ብሎ በመጥራት ኢየሱስ ከሰይን ጋር እያስተካከላቸው ነበር ፡፡ እዚህ ጋር ገሀነም “ ሲዖል “ከሚለው ቃል ጋር የሚተካካ ነው ፡፡ ገሃነም የቀድሞዉን የኢየሩሳሌም ከተማ ከምዕራብና ከደቡብ የሚከብብ ሸለቆ ነው በአሁኑ ጊዜ በሄኖም በመባል ይታወቃል ፤ የይሁዳ ንጉሶች ልጆቻቸውን በእሳት የሚሰዉበት ቦታ ነበር በፅኑ ተረግሟል (ኤር 7፡ 31; 19፡ 2-9) ፡፡ በራቢኒክ ስነፅሁፍ እና መፅሀፍ ገሃነም የእርግማን(የክፉዎች) መድረሻ ነው ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 34-36)፡ ሁሉም የፃድቅ ደም በፈሰሰው ለፈሪሳዊያን እዳ ይሆናል በቃየል እጅ ከሞተው ከአቤል (ዘፍ 4፡ 8) በእብራዊ መፅሀፍ እስከ መጨረሻው ሰማዕት ዘካሪያስ ያለው ፡፡ የዕብራዊ ብሉይ ኪዳን ዘካሪያስን እዚህ (2ዜና 24፡ 20-22) በተጠቀሰው የመጨረሻ ሰማዕት በማድረግ ከእኛ ከእንግሊዘኛዉ ብሉይ ኪዳን ቅደም ተከተለ በተለየ ያስቀመጠ ነው ፡፡

ማቴዎስ (23፡ 37-39)፡ ኢየሱስ በእስራኤል ጥፋት አዘነ ፡፡ “ ማዘን “ ታላቅ ሀዘንን ወይም ፀፀትን የሚገልፅ ወይም የሚሰማ ግስ ነው ፡፡ ስቶርት ብሪስኮ “ በሀዘኑ የማቴዎስ ማጠቃለያ የኢየሱስ ትንቢት በመደገፍ (በማዳን) መንፈስ እንዳልተሰጠ በሙሉነት ለማሳየት ነው “ ፅፎአል ፤ የፍቅር፣ የደግነት ጥበቃ መልክ እና እስራኤልን በማካተት ለአለም ሁሉ ኃጢዓት ለመሞት ፍቃደኝነት ነው ፡፡

ስቶርት ኬ. ወቤር “ ግን ፍቃደኞች አልነበሩም ፤ ኢየሱስም እንዲያሟሉት አያስገድድም ፡፡ ለዚህ ሀዘን ምክንያት የሆነው ፤ የፍቅር ማሳያ፣ ለፍቃዳችን ስሜቱን ይሰጣል፣ በእኛ የፍቃድ አመፅ ላይ መከራን እና ስቅለትን ለመቅመስ ራሱን መፍቀዱ ፤ ያም እዉነተኛ ፍቅር ነው ፡፡”

መዝጊያ

ኢየሱስ ከመቅደሱ ተመልሶ ተጓዘ ነገር ግን ቃሎቹ በደቀመዛሙርቱ ጆሮ ውስጥ ያቃጭላሉ ፡፡ ለመጠየቅ ቀርበው “ ይህ መቼ ይሆናል የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው ?” አሉት (ማቴ 24፡ 3) ፡፡ ኢየሱስም ከኢየሩሳሌም ዉጭ ከደብረ ዘይት ተራራ ላይ በሰፊዉ ንግግሩ ለመጥራት ስንቀርብ ጥያቄአቸዉን መለሰላቸው ፤ ያ እርዕስ ነገ ይመጣል ፡፡

ዛሬ ንጉሱ ለእናንተ ያ ፅድቅ በዉስጠኛው ሰው መጀመር እንደሚገባ እንጂ በዉጨኛው መታዘዝ ብቻ እንዳልሆነ እንድታውቁ ይፈልጋል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Expository Commentary New Testament: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 83.

    Stuart Biscoe, The Preacher’s Commentary Series, Volumes 1-35: Genesis-Revelation (Nashville, TN: Thomas Nelson, Inc., 1987), n. p.

  2. Wiersbe, p. 83.

    Stuart Weber, Holman New Testament Commentary: Matthew (Nashville. TN: Broadman & Holman, 1999), p. 382.

  3. Wiersbe, p. 83.

  4. Wiersbe, p. 84.

ጥያቄዎች

  1. ኢየሱስ የኃይማኖት መሪዎች የተናገሩት እንድናከብር ነገር ግን ምሳሌአቸዉን እንዳንከተል ያፀናዉ ለምን ነበር ? (ማቴ 23፡ 2-7)
  2. በማቴዎስ 23 ኢየሱስ ብዙ “ ለእናንተ አሳዛኝ “ መግለጫዎችን ሰጠ ፤ እነዚህን ነገሮች ለፃፎች እና ለፈሪሳዉያን የተናገረበት ምክንያቶች ምን ነበሩ ? (ማቴ 23፡ 13-16; 23, 25, 27, 29)
  3. ማቴዎስ 23፡ 12 አንብቡ ፤ ይህ ጥቅስ ለእናንተ ምን ማለት ነው ? ይህ ለዘላለማዊነት እዚህ በምድር ላይ ወይም ሁለቱም ላይተስፋ ነው ? (መዝ 138፡ 6; ምሳ 29፡ 23; ኢሳ 57፡ 15; ያዕ 4፡ 6)
  4. ኢየሱስ ከዉጨኛዉ መልካችን ይልቅ በልባችን ላይ በጣም የሚያተኩር ነው (1ሳሙ 16፡ 7; መዝ 15፡ 2; ማቴ 5፡ 8) ፤ ከእግዚአብሄር ይልቅ የሰዉን ትኩረት በማግኘት ማሳት የሚችሉ ነገሮች ምንድን ናቸው ? ይህን እንዴት ማስተካከል እንችላለን ?
  5. እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ልጆቹ ወደ እርሱ እንዲመለሱ ፈልጓል አሁንም ይፈልጋል ነገር ግን ብዙ ጊዜ ወደ ሌላ ነገሮች እንዞራለን ፤ በማቴ (23፡ 37) የእግዚአብሄርን ፍቅር እና ርህራሄ እንዴት ትሰሙታላችሁ ? ኢየሱስ በኢየሩሳሌም እያዘነ ነበር ይሁን እንጂ ተስፋን ሰጠ ፤ በዚህ ምዕራፍ በቁጥር 39 ያለው ተስፋ የት ነው የሚገኘው ?
  6. በማቴዎስ 23 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 23:11-12

“The greatest among you will be your servant. Whoever exalts himself will be humbled, and whoever humbles himself will be exalted.”

ኢየሱስ ለሕዝቡ እና ለደቀመዛሙርቱ ስለ ጻፎች እና ፈሪሳውያን ነገራቸው፡፡ ውጫዊ ገጽታቸውንና እና ሀይማኖተኛ ለመምሰል የነበራቸውን ፍላጎት አስረዳ፡፡ በምሳ ላይ የከበሬታ ስፍራ ይወዳሉ፡፡ ክብር እንደሚገባቸው በማሰብ፥ መምህር ሆይ ተብለው ሰላም መባልን ይወዳሉ፡፡ ኢየሱስ አሰፈላጊ የሆኑት ነገሮች እነዚህ እንዳልሆኑ ጠቅሷል፡፡

ከጻፎች እና ከፈሪሳያን ጋር በተመሳሰለ መልኩ፤ የእናንተም በደንብ የተስተካከሉት ዘመናዊ ልብሶች ጥቅም የላቸውም፡፡ ያላችሁ ማዕረግ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ባማሩ የቤት ዕቃዎች ያጌጠው ቢሮአችሁ አይጠቅምም፡፡ ኢየሱስ ልባችሁን ይፈልጋል፡፡ ትኁታን ክፍ እንደሚሉ እነዳስተማረ ልባችሁ ለእርሱ እንዲገዛ ይፈልጋል፡፡ በመንፈስ ድሆች የሆኑብጹአን ናቸው፥ የእግዚያብሔር መንግስት የእነርሱ ናትና፡፡ በጣም መሞከርን አቁሙ፡፡ ቁጭ ብላችሁ ልባችሁን አንፁ፡፡ በትህትና ቦታ ላይ ቆዩ፡፡ ጌታም ልባችሁን ሲያይ በእግዚያብሔር መንግስት ከፍ ከፍ ትላላችሁ፡፡

“ከእናንተ የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል፡፡ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድም ሁሉ ከፍ ይላል፡፡”

— የማቴዎስ ወነጌል 23:11-12

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የማቴዎስ ወንጌል 5:3 – “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብጹአን ናቸው፥ መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡ ”
  • የማቴዎስ ወንጌል 23:37 – “ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርሰዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደደኩ!”
  • የያዕቆብ መልዕክት 4:10 – “በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል፡፡”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 23