All Are Invited; Few Will Accept
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የእግዚአብሄር ቃል የማይታየው ነገር ግን በዚያ መንግስት ለምንጓዝበት ለኛ የሚታይ ለሆነው የሚመጣዉ የእግዚአብሄር መንግስት መገለጥ ነው ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ መንግስቱ እየመጣ እንደነበር ሰብኳል የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ብቻ አልነበረም ይሰብክ የነበረው ነገር ግን መንግስቱንም እንጂ ፡፡
ማንኛውም መንግስት የተወሰነ ክልል፣ መንግስት (ንጉስ)፣ ህጎች እና ህጎቹን አስፈፃሚ ሊኖረዉ ይገባል (ኤፌ 6፡ 12) ፤ ሁሉም መንግስት የራሱ ቋንቋ እና ባህል እንዲሁም አመለካከት አለው ፤ ስለሆነም እነዚህን መርሆች በመጠቀም በእግዚአብሄር መንግስት ላይ መመልከት መጀመር እንችላለን - ምንድን እንደሚመስል፣ ድንበሩ የት እንደሆነ እና የስልጣኑ ቦታ የት ነው የሚለውን ፡፡ የመንግስቱ ዜጋ በመሆን እንማራለን ይህ ስልጣን ምን እንደ ሚመስል ፤ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በእግዚአብሄር ቃል ተገልጠዋል ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ምንዛሬ ጊዜ እንደሆነ አምናለሁ ይህም በእርሱ ጊዜ እንድንሰራ የጠራበት ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (22፡ 1-4)፡ ኢየሱስ ሰርግን በመጠቀም ስለ መንግስተ ሰማይ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው ፡፡ በስልጣኑ ስር ያሉትን እና ትዕዛዙን ያከብራሉ ብሎ ተስፋ ያደረጋቸውን ንጉሱ ግብዣ አዘጋጀ ፤ ነገር ግን አልመጡም (ቁጥር 1-3) ፤ ንጉሱ ለሰርጉ ሁሉንም ስራ እና ዝግጅት ፈፅሞ ነበር ፡፡ ተጨማሪ አገልጋዮችን ላከ ግን ተጋባዦቹ “ አቃለሉት(ቸል አሉት) “ ፤ ምላሻቸው ለንጉሱ ልባቸዉን አንፀባረቀዉ ፡፡
ማቴዎስ (22፡ 5-7)፡ ተጋባዦቹ በራሰቸዉ መንገድ ሄዱ (ቁጥር 5) ፤ የቀሩትም ተጋባዦች አገልጋዮቹን ያዙዓቸው “አንገላቱዓቸዉም ገደሉዓቸዉም “(ቁጥር 6) ፤ ንጉስም በወታደሮቹና በቅጣት መለሰላቸው (ቁጥር 7) ፡፡
ንጉሱ በግብዣ አገልጋዮቹን ላከ ግብዣዉን አልተቀበሉትም ነበር ስለዚህ እንደ ገና አገልጋዮቹን ላካቸው ፤ አገልጋዮቹን በመጥፎነት አንገላቱዓቸዉም ገደሉዓቸውም ፡፡ ይህ ምንድን ይወክላል ? ምንድን እንደተፈጠረ ለማየት ቀላል ነው ፡፡ መልክ በተቀየረበት ተራራ ላይ እግዚአብሄር የእግዚአብሄርን መንገድ ያመጣዉን - ህጉን ሙሴን ላከ በተጨማሪም ነቢያትን የሚወክለውን ኤልያስን ላከ ፤ አይሁዶች፣ ተጋባዦች ግብዣዉን አልተቀበሉም ፡፡ ዘዉዱን እንደ እሚታይ ወርቅ እና እንደ ሚያምር መሳል እንፈልጋለን ነገር ግን በዘዉዱ ፋንታ አንዱ እሾክ እና መከራዉ ነበር ፤ የዘብድዮስ ልጆች እናት ለልጇቿ ከኢየሱስ አጠገበ በዙፋን ላይ በመቀመጥ ክብር እንዲኖራቸው ጠየቀች ፤ ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ “የአይሁድ ንጉስ “ በሚል ርዕስ ከሁለት ሌቦች መሀከል ተሰቅሎ ነበር ፤ ኢየሱስን አይሁዳዊ እንደ ነበር ለማያዉቁት ፡፡
ማቴዎስ (22፡ 8)፡ ለሰርጉ ንጉሱ ያልተገቡ ሆነዉ ያገኛቸዉን ለንጉሱ ባለቸው ዋጋ የሚገባቸዉን ይለካላቸዋል ፤ እዉነታው የግብዣቸዉን ዋጋ ባያዩም ወይም ለመንግስቱ የእነርሱ መገኘት ተገቢ ስለ ነበር ንጉሱ ልካቸዉን ይመጠንላቸዋል ፡፡
ማቴዎስ (22፡ 9-14)፡ ንጉሱ አገልጋዮቹን መፈለግ የሚችሉትን ሁሉንም እንዲጋብዙ ላካቸው “ መጥፎዎቹን እና ጥሩዎቹኑ ሁለቱንም “ ፤ ሁሉም እንግዶች የሚያደርጉት መምጣት ነበር ምክንያቱም ዝግጅቱ አልቆ ስለነበር ፡፡ ንጉሱ በገባ ጊዜ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰዉ አየ ፤ ንጉሱ ለምን እንዳለበሰ ሲጠይቀዉ እንግዳዉ አልተናገረም ነበር ፡፡
በቁጥር 14 ኢየሱስ ብዙዎች “ተጠረተዋል” ነገር ግን ጥቂቶች “ተመርጠዋል “ ብሎ ገለፀ ፤ መግለጫው(ንግግሩ) በግሪክ ቃል ላይ የምንመለከተው ከሆነ ብቻ ትርጉም ይሰራል ፡፡ “ መጠራት” የሚለው ቃል “ ተጋባዥ” ከሚለዉ የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ መመረጥ” የሚለው ደግሞ “ አባል “ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ነው ፤ ስለዚህ ቁጥር 14 እንደ “ ብዙዎች ተጋብዘዋል ነገር ግን ጥቂቶች አባል ሆነዋል “ ምርጥ መረዳት ነው ፤ ይህ በድንበር፣ በህጎች እና በህግ አስፈፃሚዎች ከመንግስት አንፃር ባስቀመጥነው ጊዜ ትርጉም ይሰራል ፡፡ የመንግስቱን ጥቅም የምትፈልጉ ከሆነ የንጉሱን ትዕዛዝ ተከተሉ ፤ ንጉሱ አቅርቦት በነበረው ሙሉ ነገር ፍላጎት ይኑራችሁ ፡፡ በመንግስቱ የሚታወቁ ጥቅሞች ….. እኛን ለመከላከል ጦር፣ የጋራ ቋንቋ፣ ለመልካሞቻችን ህጎች፣ በአንድ ላይ ለኢኮኖሚያችን ፡፡ በዚህ ፅሁፍ ሰዎቹ በራሳቸዉ መንገድ እና በራሳቸዉ ጊዜ የራሳቸዉን ነገር ማድረግ ፈለጉ ፡፡ ኢየሱስ ለመስቀሉ እየቀረበ ነበር እናም መንግስቱ ምን እንደሆነች ተከታዮች እንዲረዱ ፈለገ ፡፡ በቀደሙት ቀናት ንጉሱ በነበረበት ግንቡ ላይ ባንድራ ይዉለበለብ ነበር ሲሄድ ደግሞ ተወርዶ ይወሰዳል ፤ የኢየሱስ መልዕክት ንጉሱ በቤቱ ተቀምጦ ሁሉም እንዲመጡ ጋብዦአቸዉ ነበር ነገር ግን ሁሉም አልተቀበሉትም የሚል ነበር ፡፡
ማቴዎስ (22፡ 23-32)፡ ሰዱቃዉያን አስቸጋሪ ጥያቄዎች ለማወሳሰብ ለመሞከር ወደ ኢየሱስ መጡ ፤ ኢሱስም ልጥያቄአቸው “ መፅሀፍትንና የእግዚአብሄርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ “(ቁጥር29) በማለት መለሰላቸው ፡፡ የግሪኩ ቃል ዱናሚስ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው ፤ ኢየሱስ ሰዱቃዉያን ምን ያክል የእግዚአብሄርን ኃይል እንዳልተረዱት ለመግለፅ ዱናሚስ የሚለውን ቃል ተጠቀመ ምክንያቱም በትንስኤ ሰላላመኑ ፡፡ በቁጥር 32 ኢየሱስ እግዚአብሄር የተናገረውን ጠቀሰ “ እኔ የአብርሃም የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሄር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን ? የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አይደለም ፡፡ “ ይህ የአብርሃም የይስሐቅ እና የያዕቆብ ልጆች ….ሰዱቃዉያን ለበሩት ሁሉ በቀጥታ ወደ ልባቸው ሄደ ፤ ስለዚህ እነዚህ ፓትሪያርኮች ሞተው ተቀብረው ነበር ? አዎ ከሆነ የእነርሱ ቅርስ መኖር ዉበቱ ምን ነበር ? ኢየሱስ እነዚህ ሰዎች አሁንም እንዳሉ እየተናገር ነበር ምክንያቱም እግዚአብሄር የህያዋን አምላክ ነው እናም እነዚህ ፓትሪያሪኮች እንዲመጣ የእግዚአብሄር እቅድ አካል ናቸው ፡፡
ማቴዎስ (22፡ 33-40)፡ ህዝቡ ኢየሱስ ሰዱቃዉያንን እንዴት ዝም በማሰኘቱ ተደነቁበት ፤ ፈሪሳዉይን የሆነዉን በሰሙ ጊዜ በአንድ ላይ ተቀላቀሉ ፤ ከእነርሱ አንድ ህግ አዋቂ ኢየሱስን ታላቂቱ ትዕዛዝ የትኛዋ ነበረች ብሎ ጠየቀው ፤ ኢየሱስም “ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ፡፡ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትዓዛዝ ይህቺ ናት ፡፡ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርስዋም ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት ፡፡ በእዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል ፡፡”
ማቴዎስ (22፡ 41-45)፡ በመቀጠል ኢየሱስ ፈሪሳዉያንን መሲሁ የማን ልጅ ይመስላችኃል ብሎ ጠየቃቸው ፤ “የዳዊት “ብለዉ መለሱለት ፤ ኢየሱስም መልሶ መዝ(110፡ 1) በመጥቀስ) “ እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል” ብሎ ጠየቃቸው ፡፡ የዳዊት ትንቢት ከፈሪሳዊያን(መፅሀፍትን ያውቃሉ ተብለዉ ከተቀመጡት) መረዳት በላይ የራቀ ነበር ፤ ፈሪሳዉያን ሊመልሱለት አልቻሉም ምክንያቱም ሁሉም ነገር ኢየሱስ ያስተምር የነበረው የራሳቸው መንገድ ስለነበራቸው ንጉሱን በማይቀበሉት በኃይማኖታዊ ሰዎች ላይ ያተኮር እንደ ነበር ያውቃሉ ፡፡
መዝጊያ
የንጉሱን አዋጅ ላለመከተል ስፍራችን ምክንያት በሆነብን ቦታ ብንመጣ በዚያ የሚፈረድብን እና እሚያሰጋዉ ሁኔታ ውስጥ የምንቀመጥ ነን እናም የሚመጣው አደገኛ(አስቸጋሪ) ፍርድ ይሆናል ፡፡
ጥያቄዎች
-
በታላቁ ግብዣ መጨረሻ ምሳሌ ላይ ኢየሱስ ለምን ብዙዎች ተጠርተዋል ነገር ግን ጥቂቶች ተመርጠዋል አለ (ማቴ 20፡ 16; 22፡ 14(ንከጂቭ); ራዕ 17፡ 14) ? ይህ ወደ ሰርጉ ግብዣ ላይ ላልመጡት እንግዶች ምርጫ ነበር ? ለምን ወይስ ለምን ምርጫ አልነበረም ? የንጉሱ መፍትሄ ምንድን ነበር ? (ማቴ 22፡ 9)
-
ኢየሱስ የኃይማኖት መሪዎችን ከሶ እና አጋልጦ ነበር (ማቴ 9፡ 4; 12፡ 3-8) ፤ በማቴ (22፡ 15-22) በኢየሱስ ላይ የተሴረዉ ምንድን ነበር ? ኢየሱስ እንዴት መለሰ ?
-
በፈሪሳዉያን እና በሰዱቃዉያን መካከል አንድ ልዩነት ጥቀሱ ፤ (ማቴ 22፡ 23; ገላ 1፡ 14) ፡፡
-
ሰዱቃዉያን በስነ መለኮታዊ ጥያቄዎች ለማጥመድ ሞከሩ ፤ ስለ እነርሱ ኢየሱስ ያመለከታቸዉ ሁለት ነገሮች ምንድ ናቸው ? (ማቴ 22፡ 24-29)
-
አምላካችሁን እግዚአብሄርን በፍፁም ልባችሁ፣ በፍፁም ነፍሳችሁ እና በፍፁም ሀሳባችሁ ዉደዱ ማለት ምን ማለት ነው ? (ዘዳ 6፡ 5; 8፡ 6; 10፡ 12; ሚክ 6፡ 8; ማቴ 22፡ 37; ሮሜ 12፡ 1)
-
በማቴዎስ 22 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 22:14
“For many are invited, but few are chosen.”
አንድ ንጉስ ለልጁ ሰርግ አደረገ፡፡ ነገር ግን፥ ወደ ሰርጉ የተጠሩት ለመምጣት አልወደዱም፡፡ ለሁለተኛ ጊዜም ቢጠሩም፥ ለጥሪው ትኩረት ስላልነበራቸው ወደ እርሻቸው እና ወደ ንግዳቸው ሄዱ፡፡ በመጨረሻም ፥ ንጉሱ ግብዣው በመንግስቱ ላሉ መልካም እና ክፉ ለሆኑ ሰዎች በሙሉ እንዲሆን አዘዘ፡፡ ሰርግ ቤቱ በእንግዶች ተሞላ፡፡ ከነዚያ ውስጥ አንድ ሰው የሰርግ ልብስ ባለመልበሱ ወደ ውጪ ተጣለ፡፡
በተመሳሳይ መልኩ፥ በልጁ በኢየሱስ በማመን ወደ መንግስቱ እንድትመጡ ጌታ እግዚያብሔር ይጋብዛችኋል፡፡ ለዚህ ጥሪ የምትሰጡት ምላሽ የልባችሁን ሁኔታ ይገልጻል፡፡ ንጉሱ ኢየሱስ በህይወታችሁ ያስፈልጋችኋል? ወይስ በራችሁ ነገር ተጠምዳችሁ በስራቸሁ መንግስታችሁን እየገነባችሁ ነው? ጥሪውን በትቀበሉም ልባችሁ ግን ጌታን የልባችሁ አዳኝ አድርጎ መቀበል የሚለውን ሀሳብ አይቀበልም? ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ "ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ እና በፍጹም ሀሳብህ ውደድ" ወደ እግዚያብሔር መንግስት ሁሉም ሰው ተጠርቷል፡፡ በልባችሁ እሺ ትላላችሁ?
“የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና፡፡”
—የማቴዎስ ወንጌል 22:14
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የማቴዎስ ወንጌል 22:29 – “ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መጻሕፈትንና የእግዚያብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላቸሁ፡፡’”
- ሮሜ 1:5-6 – “በእርሱም ስለስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሰሳ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤ በእነርሱም መካክል የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ፡፡”
- የዪሐንስ ራእይ 17:14 – “ እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገስታት ነጉሥ ስለሆነ እነርሱን ድል ይነሳል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩ እና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሳሉ፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 22
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።