The Gospels Matthew

Hearing the Voice of the Holy Spirit

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 131 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለማጠቃለል ለእያንዳንዱ መፅሀፍ እስካሁን ቃላቶችን መስርተናል፡ ዘፍጥረት -ዘር; ዘጸዓት - ነፃ አዉጪ; ዘሌዋዉያን - አስተሰሪይ; ዘኁልቁ - አለት እና ዘዳግም - ነቢይ ፤ እነዚያ አምስት ቃላቶች የህግን መፅኀፍ ይሸፍናሉ ፡፡ ለማቴዎስ ያ አንድ ቃል ንጉስ ነው ፤ ከምዕራፍ 21 በላይ ኢየሱስን እንደ ንጉስ የሚያብራራ በማቴዎስ ሌላ ምዕራፍ የለም ፤ በዚህ ምዕራፍ ኢየሱስ ለራሱ ትኩረት ለመስጠት ክስተት ያስቀመጠበት ብቸኛው ጊዜ ነው ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (21፡ 1-5)፡ ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ከኢያሪኮ ወደ ኢየሩሳሌም 17 ማይል ጉዞ አደረጉ ፤ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ኢየሱስ አንድ አህያ ለመፈለግ ወደ ሰፍር እንዲሄዱ ሁለት ደቀመዛሙርት ላካቸው ከዚያም ታስራ ታገኛላችሁ ለእርሱም እንወስዳቸዋለን በሉዓቸው አላቸው ፡፡ አስተዉሉ ኢየሱስ እነዚህን ደቀ መዛሙርት “ አንዴ “ የሚያያት እንስሳት ነገራቸው ፤ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ እንዲታመኑ ፈጣን የሆነ መንገድ ኢየሱስ መስጠት ጀመረ፡፡ ዮሐ (10፡ 14-16) የሚለው፡

“ መልካም እረኛ እኔነኝ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደ ማውቀው የራሴን በጎች አዉቃለሁ የራሴም በጎች ያዉቁኛል ነፍሴንም ስለ በጎቼ አኖራለሁ ፡፡ ከዚህም በረት ያልሁኑ ሌሎች በጎች አሉኝ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛዉም አንድ ፡፡”

የመቀደስ ሂደት መጀመሪያ ነው - በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በእግዚአብሄር ማደግ ነው ፤ ቀድሞ ኢየሱስ የባለቤቱን ልብ ለደቀመዛሙርቱ እንስሳይቱን እንዲወስዱ እንዲፈቅድላቸው ልቡን አዘጋጅቶ ነበር (ቁጥር 3) ፡፡

የመንፈስ ቅዱስ ድምፅን መታመን እንችላለን፡ “ ወደ ምኩራቦችና ወደ መኳንንቶችም ወደ ገዢዎችም ሲጎትቱአችሁ እንዴት ወይም ምን እንድትመልሱ ወይም እንድትናገሩ አትጨነቁ ፤ መንፈስ ቅዱስ በዚያች ሰዓት ልትናገሩት የሚገባችሁን ያስተምራችኋለውና “ (ሉቃ 12፡ 11-12) ፡፡

እንዲሁም ምንድን መናገር እንዳለብን አቅጣጫ እንደሚሰጠን እግዚአብሄርን መታመን እንችላለን፡ “ እግዚአብሄርም የሰዉን አፍ የፈጠረ ማነው ? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕዉርስ ያደረገ ማን ነው ? እኔ እግዚአብሄር አይደለሁምን ? እንግዲህ አሁን ሂድ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ የምትናገረውንም አስተምርሀለሁ አለው “ (ዘጸ 4፡ 11-12) ፡፡

ማቴዎስ (21፡ 4-5)፡ ዝግጅቱና ትዕዛዝ በኢሳ (62፡ 11) እና በዘካ (9፡ 9) በሁለቱም ትንቢት ደቀ መዛሙርቱን እንዲጓዙ ይመራቸዋል ፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ በሰማችሁ ጊዜ እንድታደርጉ ለላካችሁ ቀድሞ ያዘጋጃችኋል ፤ ድምፁን ታመኑትም ተጓዙበትም ፡፡ ቁጥር 5 በቀጥታ ወደ ኢየሱስ እንደ ንጉስ ያመለክታል ፤ አንድ ንጉስ በአህያ ላይ ተቀምጦ መምጣት ትህትናን ይወክላል ፤ አንድ ንጉስ በፈረስ ላይ ተቀምጦ መምጣት ስልጣንን ይወክላል ፡፡ እንደ ንጉስ በነጭ ፈረስ መመለስ ከመቻሉ በፊት(ራዕ 19፡ 11) ኢየሱስ እንደ ንጉስ በትህትና ይመጣል (1ነገ 1፡ 33; ዘካ 9፡ 9) ፡፡

ማቴዎስ (21፡ 6-8)፡ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው በትክክል አደረጉ ፤ የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ሰሙ በእምነትም መለሱ ፤ ምንድን እንደሚያደርጉ ለማስቀመጥ መሰብሰብ አላስፈለጋቸውም ፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ በመከተል ላይ ነፃነት አለው ፤ አቅጣጫዉን በመከተል ለንጉሱ መንገድ ማዘጋጀት ድርሻቸዉን የሚጫወቱትን ሁለት እንስሳት ይዘዉ ተመለሱ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንድናደርገዉ የጠየቀንን ማንኛውንም ነገር አስፈላጊነት ማሳነስ የለብንም ፡፡ እግዚአብሄር ፈቃዱን ለመፈፀም ምንኛችንንም በየትኝዉም ጊዜ ሊጠቀም ይችላል፡፡

በእንስሳቶቹ ላይ የራሳቸዉን ካፓ አስቀመጡ ፤ በአህያይቱ ላይ እንዲቀመጥ ለእርሱ ሁሉንም ነገር ሰጡ - የዱር ያልተጋለበች እንስሳ (መዝ 8፡ 6-7; ማር 11፡ 7; ዮሐ 12፡ 14) ፡፡ ኢየሱስ በሁሉም ነገር ቁጥጥር ነበር የዱሯ እንስሳ እንኳን በፍፁም ተጋልባ አታውቅም ፡፡ ህዝቡ ኢየሱስ በላው ላይ እንዲሄድበት ልብሶቻቸውን በመንገዱ ላይ ማንጠፍ ጀመሩ ፤ ሁለቱ ልብሶቻቸዉን ስለሰጡ በህዝቡ ዉስጥ ሁሉም አደረገው (ቁጥር 8) ፡፡ ይህ ሁሉ ተጀመረ ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ቃል ስለታመኑ፣ በትንቢት ተጓዙ፣ በመታዘዝ ሄዱም ሁሉንም ነገር ሰጡ….ምክንያቱም ንጉሱ እየመጣ እንደ ነበር ስላመኑ ፡፡ ከህዝቡ ሰዎች በኩል ኢየሱስን የፖለቲካ ንጉስ እንዲሆን ፈለጉ ፡፡

ማቴዎስ (21፡ 9-10)፡ ህዝቡ ለኢየሱስ ከመዝ (118፡ 25-26) ምስጋናና እየጠቀሱ ከኢየሱስ ፊት እና ኋላ ሄደ ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በሚፈፀምበት ቀን ላይ እንደ ሚሆነው የሺህ አመት መምጣትን ተስፋ በማድረግ የዘንባባ ቅርንጫፎችን በመንገዱ ላይ ተነጠፈ ፡፡ ህዝቡ ኢየሱስ የንጉስ ዳዊት ዘር አካል እንደ ነበር አዩ (ማቴ 1፡ 1) ፡፡

“ ሆሳዕና ” የሚለው ቃል “አሁን አድነን !“ ማለት ነው ከነበሩበት የፖለቲካ ሁኔታ ያድነናል ብለዉ ስለጠበቅ ህዝቡ ለእርሱ ጮኹ ፤ እንደ መሲህ አልተመለከቱትም ፡፡ ከማቴዎስ 10 እና በማቴዎስ 28 ውስጥ ደቀ መዛሙርቱ ሄደዉ የእስራኤልን የጠፉ በጎችን እንዲፈልጉ ተነግሮአቸዉ ነበር ነገር ግን በመንገዳቸዉ ያለዉ ሁሉ አልተቀበላቸውም ፡፡ በማቴዎስ 28 ለዚያ ነው ሙሉ ተልዕኮዉ የተቀየረው ሁሉም አህዛብ እጠፉት በጎች ላይ የተጨመሩት ፡፡ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ብዙዎች ለመስዋዕት በግ ወደ ኢሩሳሌም ይመጣበት በነበረው የበግ በር አልፎ ይሄዳል ብለው ያምናሉ ፤ ያ እንደ መጨረሻ መስዋዕት የኢየሱስን አስገራሚ ስዕል ይፈጥራል ፡፡

በቁጥር 10 “ ሻካናይ ” የሚለው ቃል እንደ፡ የተንቀሳቀሰ፣ በሚሆነው ተደነቁ (ምንድን ነዉ እየሆነ ያለው ?) ወይም በሀይል ተረበሹ መተርጎም ይቻላል ፤ ሰዎስተኛው ትርጓሜ በደንብ ተስማሚ የሚሆን ነው ምክንያቱም የኢየሩሳሌም ህዝብ ኢየሱስ ምን እንደነበር ጠየቁ ህዝቡም “ ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው ! “ማለት ቀጠሉ ህዝቡ ተጨነቀ ምክንያቱ ከየት እንደ ሚመጣ ስለሚያውቁ ፡፡ ህዝቡ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ በሚሰሙ ጊዜ፣ በትዕዛዞቹ በተጓዙ ጊዜ፣ ወደ ከተማዋ በሚገቡ ጊዜ የኢሱስን ስም ይጠሩታል ከተማዋም ትንቀጠቀጣለች !

መዝጊያ

ለንጉሱ መንገድ ለማዘጋጀት ስራችን ነው ፡፡ የምፀልየው ቀጣዩን እርምጃዉን እንዲያሳየን መንገዱን ለማዘጋጀት ለእያንዳንድችን ማድረግ የሚያስፈልገንን መንፈስ ቅዱስ ማሳየት እንዲጀምር ነው ፡፡ ዛሬ ለምንሰማው መልዕክት ታዛዥ መሆን ይሆናል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ኢየሱስ እንዲያገላቱት፣ እንዲገርፉት እና እንዲሰቁሉት ለሮማዉያን ተላልፎ እንደ ሚሰጥ ያውቃል (ማቴ 20፡ 19) ፤ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አሸናፊነ እና ህዝባዊ ለማድረግ ለምን መረጠ ? (ዘካ 9፡ 9)፣ ማቴ (21፡ 2-5)
  2. ኢየሱስ አህያይቱን እና ዉርንጫዋን ስለ ማግኘት ለደቀ መዛሙርቱ በጣም ዝርዝር የሆነ ትዕዛዝ ሰጣቸው ፤ ለማድረግ ለምን ጠይቀዉ እንደ ነበር ደቀ መዛሙርቱ ተረድተዉታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ይህ እግዚአብሄርን ስለመታዘዝ ምን ያስተምራችኋል ?
  3. ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ ኢየሱስ የተበሳጨዉ ለምን ነበር (ኢሳ 56፡ 7; ኤር 7፡ 11; ማቴ 21፡ 21፡ 12-13) ? ኢየሱስ ትኩረቱ በሚገዙት፣ በሚሸጡት ወይም በሁለቱ ላይ ነበር ትኩረቱ ? ይህ ከሆነ በኋላ አገልግሎቱን ከመቀጠል አስተጓጉሎታል (ማቴ 21፡ 14) ? ሌሎችን ከማገልገል መረበሽን የሚያመጡባችሁ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?
  4. የካህናት አለቃዉ እና የፃፎች የኢየሱስን አስደናቂ ተዓምራት በማየታቸዉ ምላሾቻቸዉ ምንድን ነበሩ (ማቴ 21፡ 15) ? ስለ ነበረዉ ምንድን አበሳጫቸው ኢየሱስስ እንዴት መለሰላቸው ?
  5. ኢየሱስ መፅሀፍትን አስካሁን እንብበዉ እንደ ነበር በጠየቃቸዉ ጊዜ የካህናት አለቆች እና የእስራኤል ሽማግሌዎች ምላሽን እንዴት ታስቡታላችሁ (ማቴ 21፡ 42) ? ሳይጠቅስ ትንቢቱ የተፈፀመዉ እርሱን በተመለከተ እንደነበር በምሳሌ ስለ እነርሱ እየተናገር እንደ ነበር ባወቁ ጊዜ አፀፋቸዉ ምን ነበር ?
  6. በማቴዎስ 21 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 21:6-7

“The disciples went and did just as Jesus directed them. They brought the donkey and the colt; then they laid their robes on them and He sat on them.”

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲቀርቡ እና ደብረዘይት ተራራ ላይ ወደሚገኘው ወደ ቤተፋጌ ሲመጡ፥ ኢየሱስ ሄደው ስለሚያደርጉትን የተወሰኑ ተግባሮች ደቀመዛሙርቱን ያወራ ጀመር፡፡ ደቀመዛሙርቱም በንግግሩ ታመኑ፡፡ ሄደው የሰው ንብረት የሆኑትን አህያ እና የአህያይቱን ውርንጭላ አንዲያመጡ የሚለውን ቀላል የሚመስል ትእዛዝ ሁሉ ይሰሙ ነበር፡፡ ሁሉን በመተው ፤በጀርባቸው የነበረውን ልብስ እንኳን በመግፈፍ፤ የኢየሱስን ስም በማወጅ " ሆሳዕና በአርያም" ይሉ ነበር፡፡ በመታዘዛቸው ምከንያት ንጉሱ ኢየሱስ በውርንጫይቱ ሲመጣ ከተማዋ ተናወጠች፡፡

ይህ የመታዘዝ ተግባር የኢየሱስን መንገድ በማዘጋጀት ወስጥ ደቀመዛሙርቱ የነበራቸው ድርሻ ነበር፡፡ እናንተም የኢየሱስን መንገድ በማዘጋጀት ውስጥ ድርሻ አላችሁ፡፡ ዛሬም፥ ኢየሱስ ሊመለስ ባለበት ጊዜ ውስጥ ድርሻችሁ ምን እንደሆነ ጌታን ጠይቁት፡፡ ድምጹን ሰምታችሁ በመታዘዝ ሂዱ፡፡ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ በክብር እንዲመጣ ሚና እንደነበራቸው፤ እናንተም የእግዚያብሔርን ድምጽ በመታመን እና በመታዘዝ ስትወጡ ተፅእኖ ይኖራችኋል፡፡

“ ደቀመዛሙርቱ ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው፥ አህያይቱን እና ውርንጫዋንም አመጡለት ”

— የማቴዎስ ወንጌል 21:6-7

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የማቴዎስ ወንጌል 21:10 — “ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ መላ ከተማ ፦ ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ’”
  • የሉቃስ ወንጌል 9:23 – “ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡’”
  • የዮሐንስ ወንጌል 10:27 — “ በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 21