The Gospels Matthew

The Last Shall Be First

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 130 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በምዕራፍ 20 ንጉሱ ኢየሱስ ለአገልግሎት ከትክክለኛው እሳቤ አንፃር ደቀመዛሙርቱን አዘዛቸው ፤ በቃል ኢየሱስ ልክ እንደ ክርስቶስ እንዲሆኑ አዘዛቸው ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (20፡ 1)፡ ስራተኞች ስለ ሚያስፈልጉት የመሬት ባለቤት በምሳሌ ይጀምራል ፡፡ የመጀመሪያዉ ቃል “ስለ” ይህን ምሳሌ ከምዕራፍ 19 መጨረሻ ከጴጥሮስ ጥያቄ በቁጥር 27 ጋር ያገናኛል ፤ ኢየሱስ በዚህ ምሳሌ ለጴጥሮስ ከማቴዎስ (19፡ 28-30) ምላሹን ቀጠለ ፡፡ ይህ ምሳሌ “ ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞች ደግሞ ፊተኞች ይሆናሉ “ በሚለዉ ፅሁፍ ዉስጥ የታቀፈ ነው (ማቴ 19፡ 30; 20፡ 16) ፡፡

ማቴዎስ (20፡ 2-7)፡ መኸሩ በፍጥነት መሰብሰብ ያስፈልገዋል እነዚህ ቁጥሮች ሚገልፁት በመኸሩ ዙሪያ የተለየ አስቸኳይነትን ነው ፡፡ የመሬቱ ባለቤት “ የሚገባዉን “ ከፍሎ የሚያሰራቸዉ ለመፈለግ ወደ ገበያ መመለሱን ቀጠለ ፤ ቆይቶ ሰራተኞቹ ተቀጠሩ በቀን ከሙሉ ቀን ደሞዝ በጣም ያነሰ ክፍያ እንደሚቀበሉ ይጠብቃሉ ፡፡ በኢየሱስ ጊዜ የስራ ቀን በግምት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6፡00 ስዓት ነበር እናም ስዓቱ በ12 ዉስጥ አንድ ይቆጠር ነበር ፤ ያ ማለት ሰዎስተኛው፣ ስድስተኛው፣ ዘጠነኛው እና አስራአንደኛው ስዓታት ቀን 9 ሰዓት፣ ቀትር ሰዓት፣ ምሽት 3 ሰዓት፣ ፀሀይ ከመግባቷ በፊት አንድ ስዓት ወይም ምሽት 5 ሰዓት በቅደም ተከተል ነበሩ ፡፡ የመሬቱ ባለቤት ለሙሉ ቀን ሰራተኞች ለእያንዳንዳቸዉ አንድ ዲናር ሊከፍላቸዉ ተስማማ ፤ እነዚህ ሙሉ ቀን ሰራተኞች ወይም ከሌሎቹ የሰራተኞችን ቡድን ማንኛውም (ለምሳሌ በኑሮአቸዉ ክርስቶስን በጣም ያወቁት ወይም በጣም አማኞች ካልሆኑት በተቃራኒ በተለየ አማኞች የሆኑትን መወከሉን) ለመለየት በሙከራችን መጠንቀቅ በታም አስፈላጊ ነው ፡፡

ማቴዎስ (20፡ 8-12)፡ የአይሁድ ህግ አስተዳደር ሰራተኞች በሰረት ቀን ተመሳሳይ ይከፈላቸዋል እናም ደሞዙ ብዙ ጊዜ ለዚያ ቀን ፍላጎት ብቻ በቂ ነበር (ዘዳ 24፡ 14-15) ፡፡ የስራዉ ቀን ባለቀ ጊዜ የመሬቱ ባለቤት ተቆጣጣሪዉን በመጨረሻ ተቀጣሪዉ ጀምሮ በመጀመር ተቀጣሪዉ ላይ በማብቃት እንዲከፍላቸው አዘዘው ፤ መጨረሻ ላይ የተቀጠሩት የሙሉ ቀን ደሞዝ አንድ ዲናር ተቀበሉ ፤ ከቀኑ 6 ስዕት ላይ ጀምረዉ የነበሩት ሰራተኞች ፤ አንድ ዲናር ተቀበሉ በጣም ዘግይተዉ መጥተዉ ከነበሩት ጋር ተመሳሳይ ተክፍሎዐቸዉ ስለነበር አጉረመረሙ(ቅር ተሰኙ) ፡፡

እዉነተኛ ምዘና፡ ምንያክላችን ነን ደስተኞች የምንሆነው ሙሉ ቀን ሰርተን የመጨረሻ ስዓቷን ብቻ ሰርተው ካደረግነዉ ጋር ተመሳሳይ ክፍያ ቢቀበሉ ? ሰራተኞቹ ቅሬታ ያቀረቡት ዘግይተዉ ለመጡት ተመሳሳይ መከፈሉ ተገቢ አይደለም ነበር ፡፡ “ እነዚህ ኋለኞችም አንድ ሰዓት ሰሩ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልካቸው ! “ (ቁጥር 12) ፤ ቅሬታቸው ንፅፅርንና ብልጫን ሁለቱንም ያሳያል ልክ በማቴዎስ (19፡ 27) “ እኛስ ?” ይህ ትክክል አይደለም “ ያለዉን የጴጥሮስን ንግግር የሚመስል ነው ፡፡

ማቴዎስ (20፡ 13-16)፡ምይሮን ኦግስበርገር የሚለው “ ወዳጅ “በማቴዎስ ኢየሱስ ሰዎስት ጊዜ የተጠቀመበት ገለፃ ነበር እናም በእያንዳንዷ ጊዜ ሰዉየዉ የደረሰዉ በስህተት ነበር (ማቴ 22፡ 12; 26፡ 50) ፡፡ የናስብ እትም ቁጥር 15 እንደ “ ወይስ በለጋስነቴ አይናችሁ ቀናን ?” ይተረጉመዋል ኢየሱስ የችግሩ ስር የሰራተኞቹ እይታ እንደሆነ ለማሳየት ይህን ተጠቀመ ፤ ስህተት ነበር ምክንያቱም በቅድሚያ ስለ ክፍያው መጠን ስምምነት አድርገዉ ስለ ነበር፡፡ ዋይርስቤ የሚለው “ የሚገመት(የሚበቅ) ሽልማት ለመቀበል አናገለግለዉም በተጨማሪም የምናገኘዉን በማወቁ ሙጭጭ ማለት የለብንም ፡፡ ” ክርስቶስ ለጥቅም ብቻ የምናገለግለዉ ከሆነ(ለጊዜያዊን ዘላለማዊ ጥቅም) ለእኛ ያለዉን ምርጡን በረከት እናጣዋለን ፡፡ ኦግስበርገር በምሳሌዉ ያለዉ ሀሳብ የመጀመሪያውን ፍላጎት በግልፅ ለማብራራት ይረዳልም ወደዛ ማጠቃለያ እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል ብሎ ገልፆአል፡ 1) ለአገልግሎት ጥሪዉ ከፍላጎት ጋር በቀጥተኛ ግንኙነትነው; 2) ለአገልግሎት ሽልማቱ የፍላጎቶቻችን ሞቅ ያለ ስብሰባ ነው እና 3) የአገልግሎት አንድነት በስብሰባ ፍላጎቶቻችን በእኩል የአንድነትን ፀጋ ያከብራል ፡፡

ማቴዎስ (20፡ 17-19)፡ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ስለ ሞቱ እና ስለ ትንሳኤዉ ቀድሞ ነገራቸው ፡፡ “ የሰዉ ልጅ “ የሚለው ርዕስ ከስቅላት ጋር ከመሲሁ ጋር ይዛመዳል ፤ “ ይዘባበቱበታል፣ ይገርፉታል፣ ይሰቅሉታል “ (ቁጥር 19) ፡፡ የሰዎስቱም ግስ የግሪክ ቴንስ(ጊዜ) ያልተጠበቅ እዉነት እንደነበር ያሳያል ፡፡

ማቴዎስ (20፡ 20-28)፡ዋይርስቤ “ የዘብድዮስ ልጆች እናትን “ ሳሎም ብሎ ለይቶአታል ፤ ሳሎም ልጆቿን በማስተዋወቅ ከጥያቄዉ ኃላ የነበረች ነች ፤ በማር (10፡ 35-45) ወንድማማቾቹ ጥያቄ አቀረቡ ፡፡ በኢየሱስ መንግስት ልጆቿ በግራና በቀኝ እንዲሆኑ ጠየቀች ፤ ኢየሱስ በዙፋን ላይ ስለሚቀመጡት ሰጥቶ የነበረውን ተስፋ ለማመን አዳፈኑ (ማቴ 19፡ 28) በዚህም ድረጊታቸዉ አንድ እምነት ነበር ፡፡ ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ሲናገር በዘዉዱ እና በተለየ ዙፋኑ ላይ የጓጉ(የፈለጉ) ነበሩ ፡፡

ዋይርስቤ በጥያቄው ስህተት የነበሩትን ብዙ ነገሮችን ፅፎአል ፤ መጀመሪያ በድንቁርና የተወለደ ነበር ምክንያቱም ምን እየጠየቁ እንደ ነበር አያዉቁትም ፤ ያዕቆብ መጀመሪያ የሚሰዋ የመጀመሪያዉ ደቀመዝሙር ነበር ዮሐንስ ደግሞ በፍጥሞ ከባድጊዜ ይደርስበታል ፡፡ ሁለተኛ የሰማያዊ አቅጣጫ እጥረት ነበረበት በዚህም ለራሳቸው ክብር በመፈለግ አለማዊ እና በእራስ ወዳድነት አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ነበር ፡፡ ሰዎስተኛ በኩራት በመነሳሳት ጥያቄዉ በስጋ ነበር ኢየሱስን በዙፋኑ ላይ ለማስቀመጥ የሰይጣንን ግብዣ ያስታውሳል (ማቴ 4፡ 8-11) ፡፡ ኢየሱስ ሰማዕትነቱን በማመልከት መለሰላቸው ፤ የሌሎቹ ደቀመዛሙርት ምላሽ ኢየሱስን ስለ መምራት አንዱን አንዱን በማገልገል የማስተማሪያ ቅፅበት ሰጡት ፡፡

ሳሎም ኢየሱስ በተሰቀለበት ጊዜ መስቀሉ ጋር ነበረች ሀዘኑን እና ህመሙን ተካፍላለች ፤ ከቀኙ እና ከግራዉ ዙፋኑ ይልቅ በመስቀሉ ላይ ሁለቱን ሌቦች አየች ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ምን እንደሆነች ለማየት እንድንጀምር ለእኛ ወደ ሰዉ ልብ ዉስጥ የመለኮታዊ ልብ ጠብታ ይወስዳል(ያስፈልጋል) ፡፡

ማቴዎስ (20፡ 29-34)፡ እነዚህ ቁጥሮች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከመግባቱ በፊት የርህራሄ ፈዉስን ይይዛል ፡፡ ኢየሱስ ለሁለቱ ለተገፉ እዉር ለማኞች እንደ አገልጋይ እንደመታ ለደቀመዛሙርቱ ግምቱን አሳያቸው ፤ እንዲፈዉሳቸዉ ብቻ ጠየቁት በጥያቄአቸዉ ግልፅ(የተለዩ) ነበሩ ( ያዕ 5፡ 13-16) ፡፡

በእኛ ልምድ ከሚከተሉት አንዱ እስኪ ከሰት ድረስ ለፈዉስ እንቀባለንም እንፀልያለን፡ 1) በዚህ ህይወት ፈዉስ አግኝተዋል; 2) ኢየሱስ ሲመለስ አነድ 3) በሰማይ ተፈዉሰዋል ፡፡ በኢየሱስ የተሰራ ህይወት ማይክ ብሪን የተናገረው ቢያንስ ኢየሱስ ሲመለስ ፈዉስ ካልሆነ እንድናደርግ የነገረንን እንድናደርግ ይፈልጋል ፤ ይህ የጦርነት አዋጅ ነው ! የዚህ ተዓምራት መሲሀዊ አስፈላጊነቱ የኢሳያስን ትንብያ መፈፀም ነው (ኢሳ 29፡ 18-19; 35፡ 5-6) ፡፡

መዝጊያ

ዋይርስቤ ይህ ምዕራፍ ለመቀበል እና ለማድረግ አስቸጋሪ የሆኑ ነገሮችን ይዞአል ይላል፡

  • የዚህን አለም ነገሮች የምንወድ ከሆነ እግዚአብሄርን አስበልጠን መውደድ አንችልም ፡፡
  • ለፈቃዱ በሙሉ የተሰጠን(የተጠመድን) ካልሆንን በግልፅ ልናከብረዉ አንችልም ፡፡
  • ለራሳችን ክብር የምንፈልግ ከሆነ ወይም እራሳችንን ከሌሎች አማኞች ጋር የምናነፃፅር ከሆነ እርሱን ከፍ ማድረግ አንችልም ፡፡

አስበልጠን እርሱን ካልወደድን፣ በግልፅ ካልታዘዝነው እና ሙሉ ለሙሉ ካላከበር ነው በቀር ኢየሱስን እንደ ንጉስ እዉቅና መስጠት አንችልም ፡፡ ንጉሱ አሁን እና ቀጥሎ ለአገልግሎት ከትክክለኛ አመለካከት አንፃር አዘዛቸው ፡፡ ኢየሱስ አልፈፀመም - ነገ እንደ ንጉስ በዉርንጭላ ላይ ተቀምጦ የፋሲካ ጠቦት ተመርጦ በሚሰዋበት ቅርበ ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ይገባል (ማቴ 21) ፡፡

  1. D. A. Carson, The Expositor’s Bible Commentary: Matthew, v. 8; ed. Frank E. Gaebelein (Grand Rapids, MI: Zondervan Publishing, 1984), p. 428.

  2. Myron Augsburger, The Preacher’s Commentary: Matthew (Nashville, Thomas Nelson Publishers, 1982), n.p.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 74.

  4. Augsburger, n.p.

  5. Wiersbe, p. 75.

  6. Wiersbe, pp. 74-75.

  7. Augsburger, n.p.

ጥያቄዎች

  1. ማቴዎስ 20 በቁጥር 1-6 በሰራተኞች ምሳሌ ይጀምራል ፤ ይህን ባነበባችሁ ጊዜ በቁጥር 21 የመጀመሪያ ዙር ሰራተኞች እንደ ተሰማቸዉ በተመሳሳይ መንገድ ይሰማችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አይሰማችሁም ? በእነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ ያቀርብ ስለ ነበረው ምን ታስባላችሁ ?
  2. የሆኑ ሰዎች በልጅነት እድሜአቸው ወደ ሚያድነው የክርስቶስ እዉቀት በሚመጡ ጊዜ በህይወታቸዉ ዘግይተዉ ክርስቶስን ከሚቀበሉት ሽልማቶቻቸዉ የሚበልጥ ነው ? ለምን ወይስ ለምን አይበልጥም ?
  3. ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ብዙ ጊዜ እንደሚሰዋ እና እንደሚሰቀል ለምን እንደ ነገራቸዉ ምን ታስባላችሁ ? በደቀ መዛሙርቱ ቦታ ብትሆኑ ምላሻቹሁን የሚሆነዉን እንዴት ታስቡታላችሁ ?
  4. በማቴዎስ (20፡ 22) ኢየሱስ ስለ ፅዋ አወራ ፤ ይህ የምን ስዕል እንደሆነ ምን ታምናላችሁ ? ከዚያም በቁጥር 23 እንዳደረገው ተመሳሳይ ፅዋን እንደ ምንጠጣ ተናገረ ፡፡ ለእናንተ ይህ ምን ማለት ነው ?
  5. ማቴ (20፡ 26-27) ኢየሱስ ስለ መጀመሪያ እና ስለ መጨረሻ በተጨማሪም ስለ አገልጋይነት ተናገረ ፤ በህይወታችሁ ይህ እንዴት በትክክል ምደል እንደ ነበር እና ትክክል ባልሆነ ሞዴል እንደ ነበር ምሳሌ አስቡ ፡፡
  6. በማቴዎስ 20 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 20:31

“There were two blind men sitting by the road. When they heard that Jesus was passing by, they cried out, ‘Lord, have mercy on us, Son of David!’ The crowd told them to keep quiet, but they cried out all the more, ‘Lord, have mercy on us, Son of David!’”

ኢየሱስ ከኢያሪኮ ሲወጣ፥ ሁለት ዕውሮች ምህረትን በመጠየቅ አይኖቻቸውን እንዲከፍትላቸው ወደ ኢየሱስ ጮሁ፡፡ ኢየሱስ ወደ ቀጣዩ የአገልግሎት ቦታ እየሄደ ቢሆንም ለመቆም ጊዜ ወስዶ ምን እንደሚፈልጉ ጠየቃቸው፡፡ ርኅራሄን በማሳየት፥ ያዩ ዘንድ አይኖቻቸውን ዳሰሰ፡፡

በተመሳሳይ መንገድ፥ ለእናንተ ካለው ትልቅ ፍቅር የተነሳ፥ ቆም ብሎ ርኅራሄውን አሳይቶአችኋል፡፡ በህይወታችሁ ላለው ፍቅሩ እና ምህረቱ አይኖቻችሁ ከተከፈቱ፥ በመንገዳችሁ ለሚያልፉ ሰዎች ርኅራሄን ማሳየት ትችላላችሁ፡፡ ዛሬም፥ ኢየሱስ ለዕውሮቹ ያሳየውን ምህርት እና ርኅራሄ ለአንድ ሰው ለማሳየት ጊዜ ውሰዱ፡፡

“ አነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው ፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ የዳዊት ልጅ ማረን በለው ጮሁ፡፡ ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሰጿቸው፤ እነርሱ ግን ፦ጌታ ሆይ የዳዊት ልጅ፥ ማረን እያሉ አብዝተው ጮሁ፡፡’”

— የማቴዎስ ወንጌል 20:30-31

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • 2ኛ ቆሮንቶስ 1:3 – “ የርኅራኄ አባት የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይባረክ፡፡”
  • ወደ ቲቶ 3:5 – “ እንደ ምህረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብ እና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ስራ አይደለም፡፡ ”
  • 1ኛ ጴጥሮስ 2:10 – “ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእጊዚያብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምህረትያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምህረትን አግኝታቸኋል፡፡ ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 20