Getting Rid of Distractions
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ማቴዎስ ከሌዊ የተጠራ ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር ለእርሱ ገንዘብ ልክ የሚወደዉ እርዕስ የሚመስለዉ ነበር ፡፡ ዛሬ ገንዘብ ላይ እንመለከታለን ምክንያቱም ኢሱስን እየተከተላችሁ በገንዘብ መተግበር(መስማማት) አስቸጋሪ ስለሆነ ፡፡ ማቴዎስ 19 በፍች ላይ ያለን ጥያቄ በመመለከት (ቁጥር 1-12)፣ ልጆችን በመባረክ (ቁጥር 13-15) ይጀማራል ከዚያም በመቀጠል ወደ ዛሬዉን ምንባባችን አንድ ጎበዝ ወጣት ለኢየሱስ መንግስተ ሰማይ ስለመግባት ሲነግረዉ እናገኛለን ፡፡ የወጣቱ ጎበዝ ሀብታም ታሪክ በሁሉም ወንጌል የተካተተ ነው፡ ማቴ19፡ 16-22; ማር 10፡ 17-22; ሉቃ 18፡ 18-23 ፤ ያ ማለት ሁሉም ሰዎስቱም ከተለያየ አንፃር ያዩታል ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (19፡ 16-20)፡ ማቴዎስ “ የሆነ ሰዉ “ወደ ኢየሱስ መጣ ብሎ ፃፈ ፤ ሌሎቹ ወንጌላት እንዳደረጉት ሰዉየዉን እንደ ጎበዝ ወጣት ሀብታም አልለየውም ነገር ግን በዚያ ፈንታ ሰዉየዉን በትሁትንት አቅርቦታል ፡፡ ሰዉየው የዘላለም ህይወት እንዲኖረዉ ላደርገዉ የሚያስፈልገኝ መልካም ምንድን ነው ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው (ቁጥር 16) ፤ የዘላለማዊ ህይወት በእግዚአብሄር መገኘት ለዘላለም መቀጠል ማለት ነው ፤ የዘላለማዊ ቅጣት ተቃራኒ ነው ፡፡ “ መልካም “ የሚለው ቃል ፍፁም የሆነ ስርዓት የለውም ስለዚህ መልካም ለማድረግ ማንኛውም በእዉነቱ እንዴት ማወቅ እንችላለን ፤ ሞሪስ የተናገረው “ ጥያቄዉን መመለስ የሚችል የተለመደ መምህር አልነበረም “ ፤ ኢየሱስም መልሶ “ ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ ? መልካም የሆነ አንድ ነው ፤ ወደ ህይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዝትን ጠብቅ ”(ቁጥር 17) ፡፡ ይህ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ህይወት ለመግባት በስራ በኩል እንደሚመስል እያመከተ ነበር ፡፡ ከዚያም ወጣቱ ሰዉየ የትኛዉን ትዕዛዝ መጠበቅ ያስፈልገኛል ብሎ ጠየቀ ( የእግዚአብሄር ትዕዛዝን የሆኑትን ሁሉ አስደናቂ ሀሳብ ነው) ፡፡ ኢየሱስ ስድስተኛውን ትዕዛዞች መጥቀስ ጀመረ - አትግደል፣ ሰባተኛው ትዕዛዝ ዝሙት እትፈፅም፣ ስምንተኛው ትዕዛዝ - አትስረቅ፣ ዘጠነኛው ትዕዛዝ - በሀሰት አትመስክር፣ አምስተኛው ትዕዛዝ - አብትህንና እናትህን አክብር እና በመጨረሻ ብልጀራህን እንደራስህ አድርገህ መዉደድ ያስፈልግሀል - ከዋናው አስዕርቱ ትዕዛዙ አንዱን አላለም ( ቁጥር 18-19) (ዘሌ 19፡ 18; ዘዳ 6) ፡፡ እነዚህን ትዕዛዞች ባለመጣሱ ምክንያት በቁጥር 20 ወጣቱ ሰዉየ አሁንም ምንድን እንደ ቀረው ጠየቀ (ሮሜ 3፡ 20-22; ያዕ2፡ 10) ፡፡
ማቴዎስ (19፡ 21)፡ ኢየሱስም ሰዉየውን ፍፁም መሆን ከፈለክ የነበረዉን ሁሉንም ነገር በመሸጥ ለድሆች መስጠት እንደሚያስፈልገው ከዚያም በሰማይ ሀብት ይኖርሀል አለው (ቁጥር 21) ፡፡ ማቴዎስ (9፡ 9) ኢየሱስን ለመከተል ከሁሉም እርቆ ስለተጓዘ ፤ የወጣቱን ሰዉየ ፈተና ይረዳል ፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን መጥፎዉ ነገር ኢየሱስን መከተል እንፈልጋለን ነገር ግን ሁሉንም ነገር እንዲኖረን እንፈልጋለን ፤ እርምጃችንን በሁለቱም አለም እንፈልገዋለን - የኢየሱስ አለም እና የተመቻቸ አኗኗር ዘዴ፡፡
ማቴዎስ (19፡ 22)፡ ወጣቱ(ጎበዙ) ሰዉየ በማዘን ኢየሱስን ትቶት ሄደ ምክንያቱም ብዙ ሀብት ስለነበረው ፤ ቢያንስ ማድረግ ስላልቻለዉ ታማኝ ነበረ ፤ ምላሹ ማስመሰል አይደለም ፡፡ ሉቃ( 9፡ 57-62) ኢየሱስን መከተል የሚፈልጉ ሰዎስት አይነት ሰዎች ምሳሌን ይሰጠናል ነገር ግን የቁርጠኝነትን ዋጋዉን መክፈል ያልቻሉ ፡፡ የእቃዎች(የነገሮች) ጊዜ ማሳለፊያነት የአሜሪካን ቤተ ክርስቲያን እየገደለ ነው ፤ ሁላችንም በኑሮአችን ከኢየሱስ አርቀዉ የሚስቡ ጊዜ ማሳለፊያዎች ነገሮች አሉን (ሮሜ 8፡ 7; 1ዮሐ 5፡ 3) ፡፡
ማቴዎስ (19፡ 23-24)፡ ኢየሱስ ወደ ደቀመዛሙርቱ ዞሮ ለሀብታሞች ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት ከባድ እንደነበር ገለፀላቸው ፤ ሀብታሞች ወደ እግዚአብሄር መንግስት ከሚገቡ ይልቅ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ማሾለክ ቀላል እንደሚሆን ነገራቸው (ቁጥር 23-24) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ለመርፌ ቀዳዳ” ብዙ ትርጓሚዎችን ይሰጣል ፤ አንዱ ትርጓሜ የግመል ፀጉር ገመድን በመሪፌ ቀዳዳ ዉስጥ ማስገባት አስቸጋሪነቱን ያመለክታል ፤ ሌለኛው ምልከታ በኢየሩሳሌም ቅጥር ከተማ ዉስጥ “ የመርፌ ቀዳዳ “ በሚባለዉ ትንሽ በር ግመልን ለማሳለፍ መመኮርን ፤ ሰዎስተኛዉ ትርጋሜ ኢየሱስ ትግግለኛ ግመል በፍልስጤም ትልቅ እንስሳት በትንሽዬ የመርፌ ቀዳዳ ተጨናንቆ ለማለፍ መሞከርን የገለፀው ነው ፡፡ ሰዎስቱም ትርጓሜዎች አንድ ሀብታም ሰው ለማድረግ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ትኩረት ይስባል ፡፡
ማቴዎስ (19፡ 25-26)፡ ደቀመዛሙርቱ ተደነቁ ምክንያቱም አንድን ኃብታም ሰዉ በመንፈሳዊ በረከት እንደተባረከ ያዩ ስለነበር ፤ “ እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል “ (ቁጥር 25) ብለው ጠየቁ ፡፡ በቁጥር 26 ኢየሱስም ለአማኞች በትክክለኛ የተስፋ ቃል መለሰላቸው፡ “ይህ በእግዚአብሄር ዘንድ እንጂ በሰዉ ዘንድ አይቻልም “ (ማር 10፡ 27) ፡፡
ማቴዎስ (19፡ 27-30)፡ ጴጥሮስ ኢየሱስን ለመከተል ከሁሉም እርቀዉ እየተጓዙ እንደ ነበር ተናገረ ፤ መልሶም “ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን ?” (ቁጥር 27) ፡፡ ኢየሱስም የሰዉ ልጅ በክብር ዙፋኑ ላይ ከአጠገቡ በነበሩት በ12 ዙፋኖች ላይ ከተቀመጡት ጋር በተቀመጠ ጊዜ በመሲሁ ዘመን እንደሚሸለሙ መለሰላቸው (ቁጥር 28) ፤ ከዚያም ኢየሱስ እርሱን ለመከተል ቤታቸዉን፣ ቤተሰባቸዉን እና እርሻቸዉን የሚተዉ ከዘላለም ህይወት በተጨማሪ 100 እጥፍ እንደሚቀበል አመለከተ (ቁጥር 29) ፡፡ ኢየሱስም “ ነገር ግን ብዙዎች ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ አለ “ (ቁጥር 30) ፡፡ ማቴዎስ (20፡ 16) ለዚህ ትምህርት በማቴዎስ 19 የተመዘገበ ነው፡ “ እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ ፡፡”
መዝጊያ
ማርክ ትዋይን የተናገረው “ ስለ ሚያስቸግረኝ መረዳት አልችልም እነዚህ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች የኔ ሳላልሆኑ የምረዳዉ ክፍሎች ይህ ነው ፡፡”
ለህይወታችሁ በፍጥነት እግዚአብሄርን በታመናችሁ ጊዜ፣ ኢየሱስን ለመከተል በህይወታችሁ ሁሉንም ነገር ስትሰጡ ነፃ ትሆናላችሁ ፡፡ ሚሽነሪይ ሁድሰን ታይለር የተናገረው “ ለእግዚአብሄር መስዋዕት በማድረግ በፍፁም ተሳክቶለት አልነበረም ፤ ሁልጊዜ ለእግዚአብሄር ሁሉንም ነገር ይሰጣል የነበረዉን ሁሉንም ነገር በመስጠቱ መጥፎነት ከሚያሰማው ይልቅ የተሻለ የሚያሰማዉ ብዙ በረከት ተቀበለ ፡፡”
የምወስደው፡ በፍጥነት ኢየሱስን እንዳልከተለው የሚከለክለኝ የያዝኩት ሽፋን ምንድን ነው ? ሁሉንም ነገር ለመስጠት ፍቃደኛ በምሆንበት ጊዜ በህይወቴ እግዚአብሄርን በመለኮታዊ አድስ መንገድ እለምደዋለሁ ፡፡
Leon Morris, The Gospel According to Matthew (Grand Rapids, MI: Wm. B. Eerdman Publishing, 1992), p. 490.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1177.
ጥያቄዎች
-
በማቴ (19፡ 14) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለምን ገሰፃቸዉ ? ይህን በአባታችን ላይ ያለለን መደገፍ እንደሚያመለክት ታዩታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታዩትም ?
-
በቁጥር 21 ኢየሱስ ጎበዙን ሰዉዬ የነበረዉን ሁሉ እንዲሸጥ በሰማይም ሀብት እንደሚኖረው ነገረው ፤ ላመኑት የሚጠብቃቸዉን ሀብት ምንድን እንደሆነ ታምናላችሁ ? በዘጸ (19፡ 5); በዘዳ (28፡ 12) እና ምሳ (2፡ 4) ከተጠቀሱት ሀብት ጋር እንዴት ይወዳደራል ?
-
በማቴ (19፡ 23-24) ስለ ሀብታም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ በነበረበት ጊዜ በገንዝብ ያ ማስጠንቀቂያ በገንዘብ ሀብታም ለሆኑት ወይስ በሌላ ቦታ ሀብታም ለሆኑት እንደሆነ አስባችሁታል ? ለምን ?
-
በቁጥር 29 ኢየሱስ ያላችሁን ሁሉ የተው - ቤተሰብ ወይም እና እርሻ - 100 እጥፍ ይቀበላል አለ ፤ ይህ ለእናንተ እንዴት ይነግራችኋል ? ያለው ሽልማቱ በዚህ በምድር ላይ ወይስ በሰማይ ላይ እንደሚሆን ታስባለችሁ ? ለምን ?
-
በማቴዎስ 19 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 19:24, 26
“‘Again, I tell you, it is easier for a camel to go through the eye of a needle than for a rich person to enter the kingdom of God’…but Jesus looked at them and said, ‘With men this is impossible, but with God all things are possible.’”
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ማስተማሩን በመቀጠል፥ ባለጠጋ ወደ እግዚያብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብታልፍ እንደሚቀል አስረዳ፡፡ ባለጠጋ ወደ እግዚያብሔር መንግስት ለመግባት ለምን ይከብደዋል? ምድራዊ በሆነ ውጫዊ እይታ ካየነው ባለጠጋ ህይወቱን በራሱ አቅም እና ሀይል መኖር ይችላል፡፡ እግዚያብሔር ግን በፍቅር እና በፀጋ የተሞላ አምላክ ነው ኢየሱስም በሰው የማይቻል በእግዚያብሔር እንደሚቻል ቃል ገብቶላቸዋል፡፡
እግዚያብሔር ልብን ስለሚያይ፥ አንድ ሰው ኢየሱስን እንደ ጌታው እና አዳኙ መታመኑን ያውቃል፡፡ ስለዚህ፥ በምድር ላይ የቱን ያህል ባለጠጋ ብትሆኑም እንኳን ልባችሁ በክርስቶስ ላይ ከሆነ ወደ እግዚያብሔር መንግስት መግባት ትችላላችሁ፡፡ ኢየሱስ ልባችሁ በእርሱ ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲታመን ይፈልጋል፡፡ ዛሬስ፥ ከእግዚያብሔር በላይ የምትታመኑት ነገር አላችሁ? የእግዚያብሔር ፍላጎት ልባችሁን ሙሉ ለሙሉ ለንጉሱ ኢየሱስ እንድትሰጡት እና የነገራችሁ ሁሉ አምላክ መሆኑን እንድታረጋግጡ ነው፡፡ የምትመኩ ከሆነ በኢየሱስ ተመኩ!
“‘ዳግመኛ እላችኋለው ፥ባለጠጋ ወደ እግዚያብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል፡፡ …ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚያብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው፡፡’”
— የማቴዎስ ወንጌል 19:24, 26
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 20:7 – “እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚያብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላላን፡፡”
- ኤፌሶን 2:8-9 – “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚያብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም፡፡”
- ቆላስይስ 3:2 – “ በላይ ያለውን እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 19
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።