The Gospels Mark

A Servant of All

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 147 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የክርስቶስ ተከታይ ለመሆን ረሳችሁን መካድ ይጠበቅባችኋል፣ መስቀሉን መሸከም ይጠበቅባችኋል ከዚያም እርሱን መከተል ፡፡ ይህን የሞት መሽከርከሪያ አድርጋችሁ ካሰባችሁ በእዉነቱ የህይወት መሽከርከሪያ ነው ፡፡ እነዚህን ባህሪያት ከመሰላችሁ የክርስቶስ እዉነተኛ ደቀ መዛሙርት ናችሁ ፡፡

ትምህርት

ማርቆስ (9፡ 2-13)፡ ተከታዮቹን ራሳቸዉን እንዲኪዱ፣ መስቀሉን እንዲሸከሙ እና እርሱን እንዲከተሉን ከነገራቸዉ ከስድስት ቀናት በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን እና ያዕቆብን “ ወደ ረጅሙ ተራራ ብቻቸዉን አወጣቸው “ (ቁጥር 2) ፡፡ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ እና ያዕቆብ የኢየሱስ የቅርብ ደቀ መዛሙርቶቹ ነበሩ ፡፡ በዚህ ተራራ ላይ እነዚህ ሰዎስት ደቀ መዛሙርቶች የኢየሱስን መቀየር መስክረዋልም ከሙሴ እና ከኤልያስ ጋር ሲያወራ አይተዋል ፡፡ በቀደመዉ ትምህርት በማቴዎስ ይህን ክስተት ሸፍነነዋል ስለዚህ በዚህ ጊዜ አልፈነዉ እንሄዳለን ፡፡

ማርቆስ (9፡ 14-29)፡ እነዚህ ቁጥሮች ሌላ ሰይጣናዊ መስተጋብርን መዝግበዋል ፤ አጋንንት እንዲያስወጡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንደላካቸዉ እናስታዉሳለን እዚህ ደግሞ ራሱ ሲያደርገዉ እናያለን እንደ ሰይን ወይም ብኤልዘቡል አይደለም ምክንያቱም ያ ትርጉም አይሰራም( አይሰጥም) ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሄር ነዉ እንጂ ደግሞም ሰዎችን ነፃ የማድረግ ስልጣን ከእግዚአብሄር አለው፡፡

ማርቆስ (9፡ 30-32)፡ በማር(8፡ 34) ከትዕዛዙ የቀደመ ኢየሱስ ይሞት እንደነበርበማርቆስ የመጀመሪያዉን ትንብያ አይተናል ፡፡ በማርቆስ ወንጌል በአጠቃላይ ሰዎስት ትንብያዎች አሉ ይህ ሁለተኛዉ ነው ፡፡ በቁጥር 30 ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ “ መንገዳቸዉን በገሊላ በኩል አደረጉ “ ፤ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ብቻ ይህ መልዕክት ነበረው ፤ “ የሰዉ ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጣል ይገድሉትማል ተገድሎም በሰዎስተኛዉ ቀን ይነሳል ይላቸዉ ነበር “ (ቁጥር 31) ፤ ደቀ መዛሙርቱ ንግግሩን ባይረዱትም እንኳን ስለ ንግግሩ ለመጠየቅ ፈሩ ፡፡

ማርቆስ (9፡ 33-34)፡ ከዚያም ወደ ቅፍርናሆም መጡ ፡፡ ቀደ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር በቤት በተሰበሰቡ ጊዜ (በዝርዝር የተጠቀሰ ቤት አልነበረም ነገር ግን የጴጥሮስ ቤት ሊሆን ይችላል ወይም ኢየሱስ “የተከራየዉ” ቤት) በጉዞዉ ላይ እየተከራከሩ ስለ ነበረዉ ኢየሱስ ጠየቃቸዉ በቃለ ምልልሳቸዉ እርሱን አካትተዉት እንዳልነበር ሙሉ በሙሉ ያውቃል ፡፡ “መነጋገር ወይም መከራከር” ማለት ዋና ችግር ነበር - ሀይለኛ ንግግር ማለት ነው ፡፡ ዝም አሉ ምክንያቱም ይከራከሩ የነበረው ማን ታላቅ እንደሚሆን ስለ ነበር ፤ የትህትናን ጠቅላላ ሀሳብ ስተዋል ፡፡ በማቴ (5፡ 3) ኢየሱስ “ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና ” ብሎ ተናገረ ፡፡

ማርቆስ (9፡ 35)፡ መቼም ቢሆን ኢየሱስ ሲቀመጥ ለመናገር አስፈላጊ ነገር ነበረው ፤ “ ማንም ሰዉ ፊተኛ ለመሆን የሚወድ ከሁሉ በኃላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን ፡፡ “ በማር (8፡ 34) እንደ ተገለፀዉ ክርስቶስን መከተል ማለት ለሌሎች አገልጋይ መሆን ነው ፤ የክርስቶስ ተከታይ መሆን ባህል ማዞር ነዉ ፡፡ ሀተታ ሰጪ ሄነሪይ ስዊት የተናገረው “ የአገልግሎት መንፈስ በእግዚአብሄር መንግስት ለመታወቅ ፓስፖርት ነው ለዚህ ራሱን ዳቆን ፓንቶን ያደረገዉ (የሁሉም አገልጋይ) የመንፈስ አለቃ ነው “ ፤ ወደ እግዚአብሄርን መንግስት አቅርቦት መድረስ ከፈለጋችሁ አገልግሉ ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታዮች አማኞች ራሳቸዉን መካድ አለባቸዉ፣ መስቀላቸዉን መሸከም እና እርሱን መተል አለባቸዉ ፡፡

ሁሉንም ለማገልገል መጨረሻ መሆን የሚለው ይህ የራስ አስተሳሰብ ቦታ ያስፈልገዋል ፤ የእኛ አንድ ቃል ለማርቆስ ወንጌል አገልጋይ ነው ፡፡ ኢየሱስ እንደ አገልጋይ መጣ እንዲኖረን የሚፈልገዉ አኗኗር ይህን ነው ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው፡ “ እርሱ ሊልቅእኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል “ (ዮሐ 3፡ 30) ፤ ይህ ባህላችን ካስተማረን ሁሉም ነገር በተቃሪኒ የሚሄድ ነው ፡፡ ህይወት ስለ እኛ አይደለም ስለ እርሱ እንጂ ፡፡ ያደረጋችሁትን ማንም ካላወቀዉ አሁንም ታደርጉታላችሁ ምክንያቱም ኢየሱስ ለእናንተ ጠይቋችኋል ? ይህን ጥቅስ ከማር (10፡ 45) ጋር አወዳድሩ ፤ እዚያ ቦታ ላይ ኢየሱስ ያወድሳችሁ ይጀምራል ፡፡

የተጠቀምነዉ ቃል “አገልጋይ” የግሪክ ቃል ዲያቆን ነው ማለትም ሳይገደድ በራሱ ፍቃድ የሚያገለግልን የሆነን አካል(ሰው) ይገልፃል ፡፡ ታስመስመስሉት ይሆናል ነገር ግን እግዚአብሄር በሙሉ ልባችሁን እና ፍላጎታችሁን ያውቃል (መዝ 139፡ 2) ፤ ፀሎታችሁን ይህን አድርጉ “ ሌሎችን መጀመሪያ እንዳስቀምጥ እግዚአብሄር ልብ ስጠኝ “ ፡፡ በ 1ዜና (28፡ 9) መሰረት እግዚአብሄር ልባችንን ይመረምራል ሀሳባችንንም ያውቃል ፡፡ እንድናገለግል ኢየሱስ ይጠይቃል በደንብ እንድናገለግል ፡፡

ኮሊን ስሚዝ የእግዚአብሄራዊ አገልጋይ ሰባት ባህሪያትን ገልፃል ፡፡

  1. አገልጋይ የዋህ ነው ፊል (2፡ 3-8) የሚለው ኢየሱስ “ ራሱን አዋረደ ለሞትም ይኸዉም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ ፡፡“ የትህትና አገልጋይ ምሳሌአችን ነው ፡፡
  2. አገልጋይ ይዘጋጃል ፤ በጢሞ (4፡ 7) ጳዉሎስ የተናገረው “ እግዚአብሄርን መምሰል ራሳችሁን አስለምዱ “ ፤ እንዴት ማድረግ እንችላለን ? ጳዉሎስ የተናገረዉን ለማየት ወደ ቁጥር 15 ስንዘልል ፤ “ ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ ይህንም አዘዉትር ፡፡ “
  3. አገልጋይ ተግቶ ይሰራል ፤ በሉቃ (12፡ 35-36) አገልጋዮቹ ለአገልግሎት ምንም እንኳን ጌታቸው መቼ እንደሚመለስ ባያዉቁም ዝግጁ ሆነዉ ይጠብቃሉ ፤ በተመሳሳይ ጌታን ለማገልገል የተዘጋጀን እና የምንጠብቅ እንሆናለን ፡፡
  4. በሚያስፈልግበት አገልጋይ ያገለግላል ፤ በ 1ቆሮ (9፡ 19) ጳዉሎስ የተናገረው “ የሚበልጡትን እንድጠቅም እንደ ባሪያራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ ፡፡ ” የትም በሚያስፈልግበት በምናገለግልበት ጊዜ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት(ለመማረክ) እድል ይኖረናል ፡፡
  5. አገልጋይ እግዚአብሄር እንዳዘዘዉ ያገለግላል(አያገለግል) ፡፡ ሮሜ (8፡ 28) የሚለው ለተጠሩት እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር በአንድ ላይ ይሰራል ፤ ከተጠራችሁ ሂዱ ፡፡ ትርጉም አይኖረዉም ፤ እግዚአብሄር እንደ ሚመራዉ ስሩ ፡፡
  6. አገልጋይ መከራ ይጠብቀዋል ፡፡ ማቴ (10፡ 24-25) እና ማር (8፡ 34) እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች የሚለው ስለ እምነታችን ችግር ሲገጥመን የምንገረም መሆን የለብንም ፡፡
  7. አገልጋይ አይፈራም ፤ በ 2ጢሞ (2፡ 15) ጳዉሎስ የተናገረው “ የእዉነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሰራተኛ ሆነህ የተፈተነዉን ራስህን ለእግዚአብሄር ልታቀርብ ትጋ ፡፡” እግዚአብሄር እንደንሰራዉ የሰጠንን ስራ በምንሰራበት ጊዜ የእዉነትን ቃል በትክክል የምናስተምር ከሆነ ዝም ማለት ወይም የአፈርን መሆን የለብንም ፡፡

በእነዚህ ነገሮች ላይ እንዴት እንደምትሰሩ እንዲያሳያችሁ ለእግዚአብሄር ፀልዩ በዚህ ምክንያት የእግዚአብሄር አገልጋይ ባህሪያትን ማሳየት ትጀምራላችሁ ፡፡ 1ጴጥ (5፡ 6) ስታነቡ በሁሉን ቻዩ እግዚአብሄር እጅ ስር ራሳችሁን እንዴት እንዳዋረዳችሁ አስቡ ፡፡

መዝጊያ

በማር(9፡ 37) ኢየሱስ አንድ ልጅ በእጆቹ ወሰደና “ እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል “ ፤ ይህን ድንገተኛ ንፅፅር ለምን አደረኩ ? በአረማይ ቋንቋ “ህፃን” እና “አገልጋይ” የሚለዉ ቃል ተመሳሳይ ቃል ነው ፡፡ ሌሎችን በሚገባ ለማገልገል የህፃን ልብ ሊኖራችሁ ይገባል ፤ ምንም አድሎ ባለማሳየት በፍቃደኝነት ማንኛዉንም ሰዉ ታገለግላላችሁ ፡፡ ከራሳችሁ በፊት ሌሎችን በፍቃደኝነት በምታስቀምጡ ጊዜ፣ ራሳችሁን በምትክዱ ጊዜ፣ መስቀሉን ስትሸከሙ እና ኢየስሱን ስትከተሉት “ የሁሉም አገልጋይ “ አስተሳሰብ በሚኖራችሁ ጊዜ ኢየሱስ ክብር ያገኛል ፡፡

  1. Henry Barclay Swete, The Gospel According to St. Mark (London: Macmillan, 1905), p. 205; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Mark, p. 140; available at www.soniclight.com.

  2. Colin Smith, “Seven Marks of a Godly Servant”; available from https://unlockingthebible.org/2016/05/seven-marks-of-a-godly-servant/.

ጥያቄዎች

  1. ማር (9፡ 1) አንብቡ ፤ ምን ይገልፃል ባላችሁ ታስባላችሁ ?
  2. መልኩ በተቀየር ጊዜ ሙሴና ኤልያስ ሁለቱም ከኢየሱስ ጋር አዉርተዋል ፤ እንዲሁም ህጉ እና ነቢያቱ ሁለቱም እዚህ ተወክለዉ ነበር እግዚአብሄር ደቀ መዛሙርቱን ምንድን እንዲያደርጉ አዘዛቸው ? (ማር 9፡ 7; ዕብ 1፡ 1-2)
  3. በማር (9፡ 17-24) ልጅ ያለዉ ሰዉዬዉ ለእርዳታ ኢየሱስን በጠየቀዉ ጊዜ “ ቢቻልህ ግን እዘንልን እርዳንም የሚለዉን “ ቃል ተጠቀመ ፤ ይህ ድምፅ ሰዉየዉ ኢየሱስ ልጁን መፈወስ እንደሚችል እምነት እንደ ነበረዉ ይመስላል ? ለአባትዬዉ ኢየሱስ እንዴት አድርጎ መለሰለት ? ቀጥሎ ኢየሱስ ለጠየቀዉ ሰዉዬዉ ምን አደረገ ?
  4. የሆነ ሰዉ መጀመሪያ መሆን ቢፈልግ ምንድን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ ? (ማር 9፡ 35; 10፡ 43-45)
  5. እጃችሁ፣ እግራችሁ ወይም አይናችሁ ሊያደናቅፋችሁ እንዴት ይችላሉ ? ወደ “ ህይወት ለመግባት “ የሰዉነታችሁን ክፍል ለማጣት ትመርጣላችሁ ? (ማር 9፡ 43, 45)
  6. በማርቆስ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 9:35

“Sitting down, He called the Twelve and said to them, ‘If anyone wants to be first, he must be last of all and servant of all.’”

ደቀመዛሙርቱ በመንገዳቸው ሲሄዱ ሳለ፥ ተከራከሩ፡፡ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ባይሆንም፥ ስለምን እየተከራከሩ እንደነበረ ጠየቃቸው፡፡ በዝምታ ቆይተው መልስ ባይሰጡም፥ ኢየሱስ ግን ያውቅ ነበር፡፡ ከማሰባቸው በፊት ሀሳባቸውን ያውቅ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱ ማን ከሁሉ እንደሚበልጥ ሲከራከሩ ነበር፡፡ ኢየሱስ ልጆቹን እንደሚያናግር ወላጅ ቁጭ አደረገ እና በግልፅ ተናገራቸው፡፡ ከሁሉ መብለጥ የምትፈልጉ ከሆነ፥እርስ በእርሳችሁ አገልግሉ፡፡ ፊተኛ ለመሆን አትፈልጉ ፥ ኋለኛ ለመሆን ፈልጉ፡፡

እንደ ክርስቶስ ተከታይ፥ ከራሳችሁ ይልቅ ስለሌሎች ትልቅነት በማሰብ ፥ በትህትና እንድትራመዱ ተጠርታችኋል፡፡ ሌሎችን ስታገለግሉ፥ ሌሎችን ወደ ኢየሱስ እንጂ ወደ እናንተ አትጠቁሙም፡፡ ደግሞም የሁሉም ነገር ዋና ነጥብ፥ ኢየሱስን እና በእናንተ ውስጥ የሚሰራውን ሀይሉን እና ብርታቱን ማክበር ነው፡፡ በቀጣዩ ጊዜ መጀመሪያ የመሄድ እድል ሲገጥማችሁ፥ ለሰከንድ ቆም በሉ እና ሌላ ሰው ከእናንተ በፊት እንዲሄድ ፍቀዱ፡፡ ይህን በማድረጋችሁ፥ ጌታ ያከብራችኋል፡፡ ልባችሁን ያያል ደግሞም ሀሳባችሁን ያውቃል፡፡

“ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠርቶ፦ ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን አላቸው።”

— ማርቆስ 9:35

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 139:1-3 — “አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፤ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ ”
  • የዮሐንስ ወንጌል 3:30 — “እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።”
  • የያዕቆብ መልእክት 4:10 — “በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 37