The Gospels Mark

Take Up Your Cross

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 146 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኢየሱስ እንደ አገልጋይ ሰዎቹን ለመቅጠር እና ከሰዎቹ ጋር መስተጋብር ለማድረግ አልፈራም ፡፡ ይህ ምዕራፍ ለክርስቲያን ቁልፍ ጥቅስን ይዟል ፡፡ እዉነታው ኢየሱስን በምንከተል ጊዜ ቀላል አይሆንም ፡፡

ትምህርት

ማርቆስ (8፡ 1-10)፡ እንደገና በኢየሱስ ዙሪያ ተሰብስቦ የነበረዉ ታላቅ ህዝብ ለሰዎስት ቀናት ምንም አልበላም ነበር ፤ ይህም እንደገና እቅም እንጂ ችግር አልነበረም ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እንዲታመኑበት በማንኛዉም አገልግሎት ጉዞ ላይ በእርሱ ላይ እንዲደገፉ ፈለገ ፡፡ ይህ ህዝብ 4,000 ወንዶች ተቆጠሩ ኢየሱስም ሁሉንም ለመመገብ ሰባት እንጀራ እና ጥቂት ትንንሽ አሶሽ ተጠቀመ ሰባት ሞሰብ ምግብብም ተረፈ ፡፡ አምላክም ለህዝቦቹ እመኑኝ የህይወት እንጀራ ነኝ ማለቱን ቀጠለ ፡፡

ማርቆስ (8፡ 11-12)፡ ፈሪሳዉያን ከኢየሱስ ጋር ለመከራከር በጀመሩ ጊዜ ሊፈትኑት ምልክት ፈለጉ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ጀልባዋ ገብተዉ ወደ ሌላኛው አቅጣጫ ሄዱ ፡፡ ጀልባዋ ላይ እንደተሳፈሩ ኢየሱስ “ ተጠንቀቅ ! ከፈሪሳዉያን እና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ ብሎ አዘዛቸው “ (ቁጥር 15) ፡፡ በእጀራ አለመኖር እጥረታቸዉ ላይ ደቀ መዛሙርቱ ስላተኮሩ የኢየሱስን መልዕክት አልተረዱትም ፤ በሌላ ቃላት ፈሪሳዉያን እና ሄርዶስ ደቀ መዛሙርቱ መጠንቀቅ የሚያስፈልጋቸዉ አንዳንድ ጉዳዮች ነበራቸዉ ስለዚህ ኢየሱስ ከፈሪሳዉያን፣ ከኃይማኖተኞች እና ከተቃርኖ እንዲጠነቀቁ አስጠነቀቃቸው ፡፡

ማርቆስ (8፡ 22-26)፡ እነዚህ ቁጥሮች እዉሩን ሰዉዬ ኢየሱስ ሲፈዉሰዉ ይገልፃሉ ፤ ይህ ታሪክ በማርቆስ ወንጌል ላይ ብቻ የሆነ ነው ፡፡ በዚህ ምሳሌበሁለት ደረጃዎች ኢየሱስ ሰዉየዉን ፈወሰው ፤ ኢየሱስ ሰዉየዉን ከፈወሰው በኋላ ወደ አካባቢዉ ሳይገባ ቀጥታ ወደ ቤቱ እንዲሄድ ነገረው ይህም ማለት ተፈጠሮ የነበረዉን ለማንም እንዳይናገር ኢየሱስ አዘዘዉ ፡፡

ማርቆስ (8፡ 27-33)፡ እነዚህ ቁጥሮች በመሲሁ የጴጥሮስን ንስሀ ያወራሉ ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ ሰዎች እኔን ማን እንደሆንሁ ይላሉ ? ብሎ ጠየቃቸው (ቁጥር 27) ፤ ደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኤልያስ እንደነበር ወይም ከነቢያት አንዱ እንደ ምሳሌ ኢሳያስ፣ ኤርሚያስ ወይም ሙሴ እንደነበር ያስባሉ አሉት ፤ ጴጥሮስ ግን “ አንተ መሲህ ነህ !” ብሎ መለሰለት (ቁጥር 29) ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን መሲህ እንደነበር ለማንም መናገር እንደማይችሉ ነገራቸው ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ሞቱን፣ መቀበሩን እና ከሰዎስት ቀን በኋላ ስለ መነሳቱ አመለከታቸው (ቁጥር 31) ፤ ኢየሱስ እነዚህን ክስተቶች ከደቀ መዛሙርቱ አልደበቃቸውም ፡፡

ጴጥሮስ ወደ ጎን ሳበዉ እና ይገስፀዉ ጀመር ፤ በጣም በቅርብ የተጠቀሰዉ “ ግሰፃ “ በገሊላ ባህር ላይ በማዕበሉ ጊዜ በጀልባዉ ላይ እንደነበሩ ኢየሱስ ነፋሱን እና ዝናቡን የገሰፀዉ ነበር (ማር 4፡ 39) ፡፡ አሁን ጴጥሮስ ኢየሱስን ገሰፀዉ ፤ ለምን ? ኢየሱስ የሚነሳ እንኳን ቢሆንም ጴጥሮስ ይህ እንዲሆን አይፈልግም ፡፡ ከእኛ ዉስጥ እያንዳንዳችን እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ይጠበቅብናል፡ በመፅሀፍ ቅዱስ በእዉነቱ በዚህ ምዕራፍ አምናለሁ ? በኢየሱስ ሞት፣ መቀበር እና ትንሳኤ አምናለሁ ? በእዉነቱ እርሱ እንደጠራኝ አምናለሁ ?

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ተመለከተና ጴጥሮስን ገሰፀው (ቁጥር 33) “ ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን የሰዉን እንጂ የእግዚአብሄርን ነገር አታስብም አለው !” የጴጥሮስ ችግር በሰዉ ሀሳብ ላይ እንጂ በእግዚአብሄር ሀሳብ ላይ አለማተኮሩ ነበር ፡፡ ይህ በየቀኑ የሚገጥመን የሚቀጥል ጦርነት ነው ፡፡ ችግሩን ብቻ የምናይ ከሆነ በፍፁም አቅምን አናይም ፤ እምነትን በፍፁም አንለምድም ፤ በኑሮአችን የእግዚአብሄርን ስራ በፍፁም አንለምደዉም (አንቀምሰውም) ፤ የሁኔታዎችን ትንሳኤ በፍፁም አንለምድም ፡፡ ጴጥሮስ በዚህ ለመነጋገር አልፈለገም እግዚአብሄር ለዕኛ ያለዉን ትንሳኤ ለመልመድ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን መከራዉን መልመድ አይፈልጉም ፡፡ ዋይርስቤ የተናገረው ይህ ሰይጣን በኋላ የነበረው ነበር … ደቀ መዛሙርቱ “ የእግዚአብሄርን ፍልስፍና ከመከተል ይልቅ(ችግር ወደ ክብር ከመለወጥ) የሰይጣንን ፍልስፍና ተከትለዉ ነበር (ያለ መከራ(ዋጋ ሳያከፈል) ክብር) ፡፡

ማርቆስ (8፡ 34)፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ብቻ ሳይሆን ሙሉዉን ህዝብ ጠራቸውና “ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ “ አላቸው ፡፡

ለእናንተ “ተከታይ” ማለት ምንድን ማለት ነው ? ተከተይ ከሆነ በሚከተለዉ ሰዉ በኋላ ይሄዳል ፡፡ ኢየሱስ ከሄደ እናንተም ትሄዳላችሁ ፤ ተከታዮች ከሆናችሁ ኢየሱስ የሚያደርገዉን ታደርጋላችሁ ፡፡ ስለዚህ የምናደርገዉን ለምን እናነሳና እንመርጣለን ? ለምሳሌ ይህን የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል አነብበዋለሁ ነገር ይህ አይደለም ፤ ማር(8፡ 34) የማንይዝ ከሆነ ለመጨረሻዉ ዘመን የተዘጋጀን አንሆንም ፡፡ ለመጣዉ ለማንኛዉም ነገር በፍፁም ኢየሱስ እያዘጋጀን ነው ፤ የመጨረሻዉ ዘመን ጊዜ አካል እንደምንሆን አምናለሁ ፤ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ ይህን ከተናገረ እኛም እንደሱ ይህን እንናገራለን ፡፡

በዚህ ንግግር ተጨማሪ ጥናት የሚገባቸዉ ሰዎስት የተለዩ ትዕዛዞች ኢየሱስ ሰጠ ፤ የመጀመሪያዉ ትዕዛዝ “ ራስን መካድ “ ነበር ፤ ይህ ምን ማለት ነው ? ይህ ማለት የራስን ፍላጎት መካድ ወይም የዚህን አለም የራስ ነገሮች መካድ ማለት ሲሆን ፤ ራሳችሁን ጥሉ ማለት ግን አይደለም ፤ ለእርሱ ሙሉበሙሉ በማስገዛት ለኢየሱስ ሙሉ ቁጥጥር መስጠት ማለት ነው ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር ይህ አሰፍላጊ መንፈሳዊ እዉነትን ይገልፃል ብሎአል፡ “ የህይወትን ቀላሉን፣ ምቾቱን የሚከታተሉ እና በአለም የተቀበሉ ዘላለማዊ ህይወትና አያገኙም ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ክርስቶስ ኑሮአቸዉን የሰጡ ወንጌልም ይህን ይፈልግላቸዋል ፡፡ ” የዚህን አለም ነገሮች በእግዚአብሄር ፊት ማስቀመጥ አንችልም ፡፡

ሁለተኛዉ ትዕዛዝ “ መስቀሉን መሸከም “ ነበር ፡፡ ይህ ማለት የሆነ አይነት መሰዋእትነትን ማድረግ እና የራሳችንን ፍቃድ እንዲሞቱ በማድረግ የሚወስደዉን ማንኛዉንም ለማድረግ ፍቃደኝነትን ስናሳይ ነው ፡፡ ህይወቱን እንዴት እንደኖረዉ እና ክርስቶስን ለመከተል ለመከራ፣ የተገፋን ለመሆን እና ለመገደል… ፍቃደኞች መሆን አለብን ፤ የችግሩ እና የሞተ አካል በዚህ ይጣጣማል ፡፡ በዚህ ለመሄድ ፍቃደኛ ናችሁ ? የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትይህን በማድረግ ጨረሱ ፡፡ ባለ ምቹ ቤቱ ቀረጥ ሰብሳቢዉ ማቴዎስበኢትዮጲያ በስለት ተወግቶ ነበር ፤ ያዕቆብ (አንድ ጊዜ ታላቅ መሆን የፈለገው) ጉድጓድ ዉስጥ ተወርዉሮ እስኪሞት ተደበደበ ፤ ይሁዳ በፋሪስበሰብዓ ሰገል ተሰቀለ ፤ ዮሐንስ በሬንጅ ተቀቅሎ እና ወደ ፍጥሞ ደሴት ተሰድዷል ፡፡

ማቲያስ (የይሁዳን ቦታ የወሰደው ) በድንጋይ ተወግሮ እራሱን ተቆርጦአል ፤ ፊልጶስ በብረት መስቀያ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎአል ፤ ኢየሱስ እንዲገደል ያልፈለገዉ ጴጥሮስ በባህላቸዉ መሰረት በሮማዉያን ነገስታት ተዘቅዝቆ ተሰቀለ ፡፡ እነዚህ ሰዎች ኢየሱስ እንደነበር ይህን አላገኙትም ነገር ግን የእግዚአብሄር መንፈስ በመጣ ጊዜ የሆነ ነገር ሆነ መስቀላቸዉን ለመሸከም ፍቃደኞች ሆኑ ፡፡ እዉነት እዉነት ሲሆን በእዉነት ያስቸግራል በመጀመሪያም እንገፋዋለን ፤ ከዚያም የእግዚአብሄር መንፈስ ሲለጋን ለመቀበል እንመጣለን ፡፡ ተጠራጣሪዉ ቶማስ በህንድበስለት ተወግቷል ፤ ትንሹ ያዕቆብ በፍልስጤም አንገቱ ተቀላ ፤ ስምዖን በፋሪስ ተሰቀለ (ልክ እንደ ይሁዳ) ፤ እንድሪያስ በኤክስ ቅርፅ መስቀል ላይ በግሪክ ተሰቀለ ፤ በርተለሚዎስ በእስያ ንዑስ በጅራፍ እንዲሞት ተገረፈ ፡፡ እነዚህ ሰዎች በወንጌል ምክንያት ተሰቅለዉ(ተሰዉተው) ነበር ፤ ማር (8፡ 34) የያዙት ይህ መልዕክት በጣም ህይወት የሚያሰጥ እንደነበር አምነዋል ፤ ይህ መልዕክት አሁንም ይተገበራል ፡፡ በ 2ጴጥ (1፡ 16) ጴጥሮስ “ በብልሀት የተፈጠረዉን ተረት ሳንከተል….” ብሎአል ፤ ማናም ለአፈ ታሪክ ወይም ለተረት አይሞቱም ፡፡ በእዉነቱ ተከታይ መሆን ከፈለጋችሁ ኢየሱስን በመከተል መንገድ የምታገኙትን ሁሉንም ነገር አሳልፋችሁ መስጠት ይጠበቅባችኋል ፤ ስለ ወንጌል ለመሞት ፍቃደኞች መሆን ይጠበቅባችኋል ፤ ነገር ግን ሞት እስኪመጣ ይህን ማድረግ መቻላችሁን ወይም አለመቻላችሁን መገመት በእዉነቱ አስቸጋሪ ነው ፡፡

ሰዎስተኛዉ ትዕዛዝ “ ክርስቶስን መከተል “ ነበር ፡፡ ሁሉንም ነገር ለመስጠት እና በእርሱ እርምጃ ለመጓዝ ምን ያክል ጊዜ ተጠይቀናል ? እንዲከተለው በማር( 2፡ 14) ኢየሱስ ማቴዎስን ጠራው ( የዕልፍዮስን ልጅ ሌዊን ጠራው ፤ ማቴ (9፡ 19)) ፡፡ ኢየሱስን መከተል ማለት አሁንም መቀመጥ ማለት አይደለም ፤ ተነስታችሁ ወንጌሉን ማካፈል ነው ፡፡ ስለ ራሳችሁ የት መዉደቅ አትጨነቁ ፤ ስለ ሂሳባችሁ(ክፍያችሁ) አትጨነቁ ፡፡ በማር (10፡ 21) ኢየሱስ ጎበዙን ሀብታም ሰዉዬ ሁሉንም እንዲሸጥ እና ከዚያም እንዲከተለዉ ነገረው ፤ ኢየሱስን እንደ አዳኝ ከተቀበልነዉ በላይ የሚሰራ ብዙ አለ - ልንከተለዉ ይገባል ፡፡ ወደ ሚመራን ሁሉ ኢየሱስን በመከተል እምነታችንን እናስጉዝ(እናስኪድ) ፤ በግልፅ በእምነታችሁ እዚህ ሀሳብ ለመድረስ ጊዜ የሚወስድ ሂደት ነው ፡፡

ማርቆስ (8፡ 35-38)፡ ስለ ኢየሱስ ብቻ ኑሮአችንን ስናጣ ወንጌሉ ሊያድንልን ይችላል ፤ በኢየሱስ እና በቃሎቹ በምናፍር ጊዜ “ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላዕክት ጋር በመጣ ጊዜ “ (ቁጥር 38) በእኛም የሚያፍርብን ይሆናል ፡፡

መዝጊያ

ማር(8፡ 34) እየኖርንበት ከሆነ ይህ ሁሉ ርዕስ(ነገር) አይሆንም ፤ ዛሬ በዚህ ሁሉ የት ናችሁ ? ጴጥሮስ መጀመሪያ ችግር ነበረበት ፤ ከጌታ ይልቅ ይህ ሁሉ ስለ እርሱ ነበር ፤ ነገር ግን ስተወረዉሩት ይሰራል ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 140.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1225.

  3. MacArthur, p. 1225.

ጥያቄዎች

  1. ለሁለተኛ ጊዜ ኢየሱስ በጥቂት የገብስ እንጀራ እና በጥቂት አሳ ህዝቡን መገበ (ማር 6፡ 35-42; 8፡ 2-9) ፤ በሁለቱ ድርጊቶች ምን ተመሳሳይነት ነበሩ ? ምንድን ልዩነትስ ?
  2. ከእነዚህ ከሁለቱ ሁኔታዎች በኋላ መፅሀፍት ደቀ መዛሙርቱ ልባቸዉን ማደንደናቸዉን ይጠቅሳል ፤ ለእናንተ ይህ ምን ማለት ነው ?
  3. ኢየሱስ በጠነከረ ልባቸዉ የደቀ መዛሙርቱን የማየትን እና የመረዳታቸዉን እጥረት ለማገናኘት ይመስላል ፤ በህይወታቸዉ እግዚአብሄር ይሰራ የነበረዉን እንዳይረዱ ምክንያት የሆነ የጠነከረ ልብ ያላቸዉን ሰዎች አይታችኋል ? ለጠነከረ ልብ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ?
  4. በማር (8፡ 22-25) ያለዉን መግለጫ ባነበባችሁ ጊዜ በመጀመሪያ ኢየሱስ በነካዉ ጊዜ ሰዉዬዉ ለምን በተወሰነ ደረጃ መፈወሱ ለመረዳት አስቸጋሪ ሆኖ አግኝታችሁታል ? ኢየሱስ ሰዎችን ፈዉሶ እንደ ተፈወሱ የጠየቀባቸዉ ሌላ ምክንያቶች(መግለጫዎች) ታዉቃላችሁ ?
  5. በማር (8፡ 34) ህዝቡን ኢየሱስ በደረሰ ጊዜ መስቀላቸዉን እንዲሸከሙ እና እንዲከተሉት ጠራቸው ፤ ያ ምን ማለት እንደሆነ ተረድተዉታል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  6. በማርቆስ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 8:33

“But turning around and looking at His disciples, He rebuked Peter and said, ‘Get behind Me, Satan, because you’re not thinking about God’s concerns, but man’s!’”

ጴጥሮስ ኢየሱሰን ወደጎን ወስዶ፥ ኢየሱስ ሊመጣ ስላለው ሞቱ ለደቀመዛሙርቱ መናገር እንዲያቆም ሊያሳምነው ሞከረ፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስን ገሠጸው እና በጥብቀ "ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን" አለው፥ ከዚያም ነገሩ አበቃ፡፡ ጠላት ኢየሱስ መከራ እንዳይቀበል እና እንዳይሞት ለማሳመን የነበረው አላማ በእውነቱ በቀላሉ ተበታተነ፡፡

ከጌታ እንዳልሆነ በምታውቁት ሁኔታ ውስጥ ራሳችሁን ልታገኙት ትችላላችሁ፡፡ ፈተና እናንተን ለማሸነፍ እየገባ እንደሆነ ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ በአይምሮአችሁ ያሉት ሀሳቦች እና ውሸቶች በጣም እንደከበዱ ተሰማቷችሁ ጠዋት ከአልጋችሁ መነሳት እስካትፈልጉ ልትደርሱ ትችላላችሁ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ፀንታችሁ ቁሙ እና ጌታ አምላካችሁ ከእናንተ ጋር እንደሆነ እወቁ፡፡ በኢየሱስ ስም "ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን" የማለት ሥልጣን እንዳላችሁ አስታውሱ፡፡ ለጌታ ራሳችሁን አስገዙ፥ ጠላት ይሸሻል፡፡ በእግዚያብሔር የተስፋ ቃል እና በቃሉ እውነት ላይ ማተኮርን አስታውሱ፡፡ ኢየሱስ በስልጣኑ መራመድ ነበረበት፥ እናንተም እንደዚያው፡፡ በመተማመን ተራመዱ− ኢየሱስ በእናንተ ውስጥ እየሰራ ነው!

“እርሱ ግን ዘወር አለ ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሠጸውና፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና አለው።’”

— ማርቆስ 8:33

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ሉቃስ 10:19 — “እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ”
  • የያዕቆብ መልእክት 4:7 — “እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 2:14 — “አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 36