ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና የአምስት ሺህ ሰዎች መመገብ ላይ ተመልክተናል ፡፡ ተሸፍኖ የማናገኘው ክስተት የኢየሱስ የዉሃው ላይ ጉዞ ነበር ፤ በማርቆስ 7 በሽማግሌዎቹ ባህል ላይ የምንመለከት ይሆናል ፡፡ ጉባኤውን በእኔ በተቀረፀ ህይወት አሳድጌዋለሁ እግዚአብሄርም ወደ እርሱ በፍጥነት እኔን ለመጥርት ተጠቀመበት ፤ ያን ጉባኤ አላንኳኳም ነገር ግን በአደግንባቸው እንጂ ከመፅሀፍ ያልተወሰደ ብህሎች ነበሩ ፡፡ በማርቆስ ሰባት 23ቱ ቁጥሮች በባህል ከመደረጋቸዉ ይልቅ ነገሮች ስለ ምን በተለያዬ መንገድ እንደተፈፀሙ በጥያቄ ያወራል ፤ በቁጥር 24 ኢየሱስ ክፉ መንፈስ ከነበረባት አንዲት ወጣት ሴት ጋር ማዉራት ጀመረ ፡፡
አካታቾቹ ወንጌላት እያንዳንዳቸዉ ኢየሱስን በተለያዩ እይታዎች በኩል ያሳያሉ ፡፡ በማርቆስ በሌሎች ወንጌላት ያልተካተቱ ስለ ፈዉስ እና ታሪክ ብዙ ምሳሌዎች አሉ ፤ ለምሳሌ ማር (4፡ 26-29) የአደገዉን ዘር ምሳሌ ይዟል ፤ የዛሬዉ የማይሰማዉ እና የማይናገረዉ ሰዉ ፈዉስ ታሪክ በማርቆስ ወንጌል ላይ ብቻ ነው ፡፡ በማር (8፡ 22-26) የተፈወሰዉ አንድ እዉር ሰው ሌለኛዉ ሲሆን የመጨረሻው በማር (13፡ 34-37) የሚገኘው የቤቱ ባለቤት አለመኖርን ምሳሌ ነው ፡፡
ትምህርት
ማርቆስ (7፡ 31-32)፡ ብዙ ጊዜ የኢየሱስ መስተጋብር ከአይሁዶች ጋር ነበር ስለዚህ በማንኛዉም ጊዜ ከአህዛብ ጋር መገናኘት ነበረው ይህም ሁልጊዜ የተለየ ነበር ፤ ኢየሱስ ሳምንታት ወይም ወራት ሊወስድ የሚችል መንገድ ጉዞ ላይ ነበር ፡፡ ጢሮስን ትቶ ወደ ገሊላ ባህር በሲዶና አጠገብ በአስር ከተማ መካከል (በምስራቅ ዮርዳኖስ አስር ከተማ) ሄደ ፤ ይህ ቀላል ጉዞ እና ቀጥያለ መንገድ አልነበረም ፡፡ በአስር ከተማ ሰዎች አንድ የማይሰማ መናገር የማይችል ሰዉ (መስማት የማይችል እና መረዳት የማይችል) አመጡለት ፤ “ በእርሱ ላይ እጁን እንዲያስቀምጥበት” ለመኑት (ቁጥር 32) ፡፡ ቤን ዊዘሪግተን “ አንዱን እጁን ማስቀመጡ የአይሁዶች ልምድ ስለነበር አይሁዳዊ እንደ ነበር ያመለክታል “ ይላል ፡፡ ግራስማይክ የጠቀሰዉ “ ብዙ ጊዜ የተበላሸ ንግግር ከአካላዊ እና መንፈሳዊ ከሁለቱም የተበላሸ አሰማም ዉጤት ነው ” ፤ ይህ ምናልባት ተከስቶ ይሆናል ፡፡
ማርቆስ (7፡ 33)፡ ኢየሱስ ሰዉየዉን ከህዝቡ ራቅ አድርጎ ወሰደው ፤ ማርቆስ ኢየሱስ ሰዎችን ሲፈዉስ ይህን ደጋግሞ እንዳደረገ መዝግቧል ፤ ይህ በአሜሪካ ከተያዝንበት መንገድ ተቃራኒ ይሄዳል ፤ ትኩረት ስንፈልግ ፡፡ ኢየሱስ እንደ አገልጋይ ሙሉ ተቃራኒ ነበር ፤ ለነፃነት ይህን ሰዉ ለይቶ ወሰደው ፡፡ ትናትና ሁልጊዜ እንዴት ርህራሄ ወደ ድርጊት እንደሚመራ አዉርተናል ፤ የአገልጋይ አስተሳሰብ ካላችሁ ርህራሄ ይኖራችኋል ፡፡ ይህ አረፍተ ነገር ማንም ተነክቶበታ ባልነበረዉ ቦታ ይህን ሰዉ የነካው አገልጋዩ ኢየሱስ የተሟል ስዕል ነው ፤ ኢየሱስ የሰዉየዉን ጆሮዎች ነካ ምናልባትም የጆሮዉን ኩክ ሙሉዉን ከዚያም ቀጥሎ የሰዉየዉን አንደበት ነካው ፡፡ ኢየሱስ ስላደረገው የሚያረጋግጥ ምንም የለም ፤ ሙሉ በሙሉ የረከሰ ነበር ፤ ይህ ሰዉየዉ ስለ ማይሰማ ጆሮዉን በመንካት ኢየሱስ እያደረገ የነበረዉ የምልክት ቋንቋ ቅርፅ ነበር ፡፡
ሉቃ (5፡ 12) በለምፅ የጠሸፈነዉን አንድ ሰዉን ኢየሱስ እንደነካዉ መዝግቧል ፤ በኢየሱስ ቀላል መንካት ህይወትን ወዲያዉኑ መቀየር ይችላል ፡፡ የሆነን ሰዉ ፈገግታን እንዴት እንደሚመስል እንደለበሰ ወይም በንቅሳት የተሸፈኑ ቢሆኑም የምንፈራቸዉ ልንሆን አንችልም ፤ ችግር የለዉም ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰዉ በእግዚአብሄር መልክ ነው የተሰሩት ፡፡
ማርቆስ (7፡ 34)፡ ወደ ሰማይ መመልከት ኢየሱስ በሰማይ አምላክ ላይ መደገፉን የሚያሳይ ሌላ የምልክት ቋንቋ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ለሰዉየው ሸክሙን በመሸከም ወይም ለጫናው በመጠንቀቅ በጥልቅ ቃተተ ፤ ከዚያም ኢየሱስ “ ኤፍታህ “ አለዉ ትርጉሙም “ ተከፈተ ! “ ሲሆን ኢየሱስ ሰዉየዉን በመፈወስ ሂደት ዉስት ተጓዘ ከዚያም ሁለት ቃሎች ብቻ ተናገረ - “ ተከፈተ “ ኬንት ሁግስ ይህ ለአገልግሎት ሞደል እንደሆነ ይጠቅሳል፡ በእግዚአብሄር ላይ በመደገፍ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለከተ (ቁጥር 34) ፤ በርህራሄ ቃተተ (ቁጥር 34) ፤ ሰዉየዉን በመንካት ድርጊት ወሰደ (ቁጥር 33) ፤ ከዚያም በስልጣን ተጓዘ ምክንያቱም ሰዉየዉን እግዚአብሄር እንደሚፈዉሰዉ አምኗል (ቁጥር 34) ቃሉ እግዚአብሄር በማንኛዉም ጊዜ ሊገለጥ እንደሚችል ይናገራል ፡፡ ትናትና፣ ዛሬ እና ነገ ተመሳሳይ ነው ፤ የሚፈዉሰዉን የክርስቶስን እጅ መዉሰድ፣ መጓዝ እና ምን ማድረግ እንደምንችል ማየት ያስፈልገናል ! ጆሮቹ ሲሰሙ ፤ በእዉነቱ አፉ ለመናገር መጀመሩን እናያለን ፡፡
ማርቆስ (7፡ 35)፡ ሰዉየዉ ወዲያዉኑ ተፈወሰ ፤ መስማት ቻለ ፤ የመናገር አስቸጋሪነቱም ተወገደ ፤ በግልፅ መናገር ጀመረ ፡፡
ማርቆስ (7፡ 36)፡ ከዚያም ኢየሱስ “ ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸዉ መጠን እጅግ አወሩለት ፡፡ “ ስለዚህ አስቡ ….. መናገር ይቸግረዉ የነበረዉ ሰዉዬ አሁን ዝም ማለት አይችልም ነበር ! ማክአርቱር “ የኢየሱስ አገልግሎት ለአህዛብ የሚያስፈልጋቸዉን በማንቀሳቀስ ቢሆንም ሀሳቡ በእነርሱ መሀከል የህዝብ አገልግሎት እንዲኖረው አልነበረም ፡፡ “
ማርቆስ (7፡ 37)፡ “ ያለ መጠንም ተገረሙና ሁሉን ደኅና አድርጎአል ! ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል አሉ ! “ ሁሉንም ደህና አድርጎአል ! የሚለዉ ሀረግ ወደ ዘፍ (1፡ 31) መልሶ ይወስደኛል፡ “ እግዚአብሄርም ያደረገዉን ሁሉ አየ እነሆም እጅግ መልካም ነበር ፡፡ ”
ይህ እዉነተኛ ንግግር ነበር ፤ ኢየሱስ በደህና በአስደናቂነት ያደርግ ነበር ፡፡ ማቴ (15፡ 31) የሚለው፡ “ ፈወሳቸውም ስለዚህም ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ ጉንድሾችም ሲድኑ አንካሶችም ሲሄዱ ዕዉሮችም ሲያዩ አይተዉ ተደነቁ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ ፡፡ “ ኢየሱስ በእግዚአብሄር ላይ ተደገፈ፣ ለሌሎች ርህራሄ ነበረው፣ ድርጊት ወሰደ በስልጣንም ተጓዘ ፡፡ አህዛቦች ማወቅ እና ለእስራኤል አምላክ ክብር መስጠት ጀመሩ ፡፡
ይህን እንዴት በመንፈሳዊነት እንወስደዋለን ? ” ጆሮ ያለዉ ይስማ “ ወደ ሚለው መመለስን እይዛለሁ(እጠብቃለሁ) ፡፡ አንድ ሀተታ ሰጪ ሁልጊዜ ኢየሱስ ባለጆሮዎችን እንዳደረሰ ተመልክቶአል ምክንያቱም ቃሉን ይሰጣቸዉ ስለነበር ነበር ፤ ለእነርሱ እየተናገራቸዉ ስለነበር ቀጥሎም እየሰሙት እንደነበር ይጠይቃቸዋል ፡፡ የመናገር እና የመስማት አካላዊ ጎኑን አይደለም የማወራው ነገር ግን የመንፈሳዊ ጎኑን እንጂ ፤ ኢየሱስ “ ጆሮ ያለዉ ይስማ “ (ማቴ 11፡ 15; ማር 4፡ 9; 23) ! ኢየሱስ እንድንሰማ እና ከሚናገረው ጋር የተጣበቅን እንድንሆን እፈልጋለሁ ነዉ የሚለው ፡፡
የዘሪዉ ምሳሌ ያልተማርንበት ምሳሌ ነው ፤ www.GotQuestions.com ድህረ ገፅ ስለዚህ ምሳሌ፡ “ አንዳንዶች ይሰማሉ ነገር ግን ስር እንዲሰድድ አይፈቅዱም ፤ አንዳንዶች ይሰማሉ ነገር ግን በመሳደድ እና በችግሩ ምክንያት አይቀበሉትም ፤ አንዳንዶች ቃሉን ይሰማሉ ለመረዳት እና ለመቀበል በራሳቸዉ ይፈቅዳሉ ይህም ሊቀይራቸዉ እና ፍሬ እንዲያፈሩ ያስጀምራቸዋል ፡፡ ” ቃሉን የምትሰሙት እና የምትቀበሉት እንዴት ነው በእዉነት ከቃሉ እንደምታገኑት ነው ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሙሉ በሙሉ ከመንፈስ ቅዱስ መገናኘት እንደምትችሉ እና በፍፁም ለእናንተ እንዲናገራችሁ ይፈቅዳል ይላል ፡፡
የእግዚአብሄርን ቃል እየሰማችሁ በእርሱ ካልተቀየራችሁ በራዕይ ሰባቱን አብያተክርስቲያንን በብዙ የምትመስሉ ናችሁ ፡፡ ሁልጊዜ በራዕይ የሚያበረታታ ቃል አለ “ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለዉን ጆሮ ያለዉ ይስማ “ የሚል ትዕዛዝ አለ (ራዕ 2፡ 29) ፡፡ ይቅር የማይባል ኃጢዓት መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ነው ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እየተናገራችሁ መንፈሱን እምቢ እያላችሁ ነው ከእግዚአብሄር ለመስማት ይህ ከባድ ነው ፤ በእያንዳንዱ ጊዜ ለእነዚህ ቤተ ክርስቲያናት ተመሳሳይ ንግግር የተደረገ ነው(ራዕ 2፡ 11, 17, 29; 3፡ 6, 13, 22) ፡፡ ዮሐ (10፡ 27-28) የሚለው “በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ እኔም አዉቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል ፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ ለዘላለምም አይጠፉም ከእጄም ማንም አይነጥቃቸዉም “ ፤ በተጨማሪም ማር (4፡ 24) የሚለው “ አላቸዉም ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ ፡፡ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል ለእናንተም ይጨመርላችኋል ፡፡ “
መዝጊያ
መስማት የማይችለው ሰዉ ክርስቶስን በመልመድ አንደበቱን ማንበብ፣ መነካቱን መረዳት እና በመጨረሻም ድምፁን መስማት ችሎ ነበር ፤ በመንፈሳዊነት ለእኛ መንፈስ ቅዱስ እያለን(እየተናገረን) ላለዉ በንቃት መሆን ያስፈልገናል ፡፡
Ben Witherington, The Gospel of Mark: A Socio-Rhetorical Commentary (Cambridge, UK: Wm. B. Eerdmans Publishing, 2001), p. 234.
John D. Grassmick, “Mark,” in The Bible Knowledge Commentary, eds. John F. Walvoord and Roy B. Zuck (Wheaton: Scripture Press Publications, 1983), p. 136.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p.1223.
ጥያቄዎች
-
ፃፎች እና ፈሪሳዉያን ኢየሱስን ስለ ምን ደቀ መዛሙርቱን የሽማግሌዎቹን(የአባቶቻቸዉን) ልምድ ለምን እንደ ማያደርጉ ጠየቁት ለእነርሱ ኢየሱስ መንድን የብሉይ ኪዳን ጥቅስ ጠየቀሰላቸው ? (ማር 7፡ 6-7; ኢሳ29፡ 13)
-
እግዚአብሄርን በከንፈራችዉ ማክበር ነገር ግን ልባቸዉ ከእርሱ የራቀ ነበር ማለት ምን ማለት እንደሆን ምንድን ታስባላችሁ ?
-
በማር (7፡ 9) ኢየሱስ ፃፎችን እና ፈሪሳዉያንን በምንድን ከሰሳቸው ? ሀሳቡን ለመስራት(ለማድረግ) ምንድን ምሳሌ ተጠቀመ ? (ማር 7፡ 10-13)
-
በማር (7፡ 20-23) መሰረት ኢየሱስ ሰዉን ከየት የሚመጣዉ እንደ ሚያረክስ አስተማራቸዉ ? ምንድን ምሳሌዎችን ዘረዘረ ?
-
በማር (7፡ 33-34) የማይሰማ እና የማይናገር የነበረዉን ሰዉዬ ለመፈወስ ኢየሱስ ምንድን ድርጊት አደረገ ? ለእናንተ እነዚህ እንግዳ ይመስላችኋል ?
-
ማር (7፡ 34) ፅሁፍ ላይ የማይሰማው ሰዉዬ ጆሮዎች እንዲከፈትለት በተናገረ ጊዜ ኢየሱስ በጠለቀ መቃተት ወደ ሰማይ ለምን እንደተመለከተ ምን ታስባላችሁ ?
-
በማርቆስ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Mark 7:33-34
“So He took him away from the crowd privately. After putting His fingers in the man’s ears and spitting, He touched his tongue. Then, looking up to heaven, He sighed deeply and said to him, ‘Ephphatha!’ (that is, ‘Be opened!’).”
ኢየሱስ የአገልጋይነት ምሳሌ ነው፡፡ ለሰዎች ያለውን ርህራሄ በተግባር አሳይቷል፡፡ ደንቆሮ እና ኮልታፋ የሆነውን ሰው ወደእርሱ ሲያመጡ፥ ኢየሱስ አልሸሸም፡፡ እንዲያውም ኢየሱስ አገልግሎት እንዴት እንደሚሰራ ለደቀመዛሙርቱ ምሳሌ ነው፡፡ በመጀመሪያ በጌታ ላይ ይታመን ነበር፡፡ ከዚያም፥ ይህን ሰው ይወድ እና ለዚህ ሰው ይራራ ነበር፡፡ ኢየሱስ እርሱን በመዳሰስ እርምጃ ወሰደ እና ከጌታ በተሰጠው ስልጣን አገለገለ፡፡ በጌታ አገልግሎት እና ሀይል፥ ደንቆርው ተፈወሰ፥ ጆሮዎቹ ተከፈቱ ደግሞም አጥርቶ ይናገር ጀመረ፡፡
ወዳጆች፥ የሌሎችን ፍላጎቶች ስታዩ፥ ሸክማቸውን እና ህመማቸውን በራሳችሁ እንደማትሸከሙ አስታውሱ፡፡ ጌታን ለሀይሉ፣ ለስላጣኑ እና ለርህራሄው ፈልጉት፡፡ በእናንተ ውስጥ በሚሰራው ሀይሉ ሁሉን ማድረግ ትችላላቸችሁ፡፡ አገልግሎትን በራሳችሁ አቅም እና በስጋችሁ ለመስራት ከሞከራችሁ ትደክማላችሁ፡፡ በዚህ ሰአት አገልግሎት እና የሰዎች ፍላጎቶች እየከበዳችሁ ከሆነ፥ በረጅሙ ተንፍሱ እና ወደሰማይ ተመልከቱ፡፡ ጌታን እርዳታ ጠይቁት፡፡ ርህራሄያችሁን ወደ ተግባር ለውጡት እና የእግዚያብሔር ፀጋ በቂ ሲሆን ተመልከቱ፡፡
“እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑት። ከሕዝቡም ለይቶ ለብቻው ወሰደው፥ ጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ፤ ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና፦ ኤፍታህ አለው፥ እርሱም ተከፈት ማለት ነው።”
—ማርቆስ 7:33-34
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ትንቢተ ኢሳይያስ 49:10 — “የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፥ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፥ አይጠሙም፥ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።”
- የማቴዎስ ወንጌል 11:28 — “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ”
- 2ኛ ቆሮንቶስ 12:9 — “እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 35
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።