ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የክርስቶስ ተከታይ ለመሆን ራሳችሁን ክዳችሁ መስቀሉን በመሸከም ተከተሉት ፡፡ ይህን የሞት መሽከርከሪያ እንደሆነ ካሳባችሁ በእዉነቱ የህይወት መሽከርከሪያ ነው ፡፡ እነዚህን ባህሪዎች ምሳሌ ስትሆኑ የክርስቶስ እዉነተኛ ደቀ መዛሙርት ናችሁ ፡፡ ማር (10፡ 45) ጠቅላላ የማርቆስ ወንጌል ቁልፍ ጥቅስ ነው ዛሬ በዚህ እንጨርሳለን ፡፡ ማርቆስ 10 ስለ ፍቺ በመወያየት(ቁጥር 1-12) ይጀምራል ከዚያም በመቀጠል ወደ ልጆች በረከት ይጓዛል (ቁጥር 13-16) ፡፡ ከዚያም ማርቆስ በማቴዎስ ቀድመን የሸፈነዉን በኢየሱስ እና በወጣቱ ሀብታም ጋር መገናኘትን ያቀርባል (ቁጥር 17-22) ፤ ማርቆስም በእግዚአብሄር መንግስት ያለዉን ሀብት ይሸፍናል (ቁጥር 23-31) ፡፡
ትምህርት
ማርቆስ (10፡ 32-34)፡ ይህ በማርቆስ ወንጌል ኢየሱስ ስለሚመጣዉ ሞቱ የሰጠዉ ሰዎስተኛዉ ትንብያው ነው ፤ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄዱ መንገድ ላይ ነበሩ ፡፡ ቁጥር 32 “ የተከተሉትም ፈሩ “ ይላል ፤ ኢየሱስ 12 ደቀ መዛሙርቱን ለብቻቸዉ በመዉሰድ ስለ ሚመጣዉ ሞቱ ይነግራቸዉ ጀመር ፡፡ በቁጥር 33 በኢየሩሳሌም ምን እንደሚሆን ገለፀ፡ “ የሰዉ ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል “ ፤ ከዚያም ዝርዝሩን ሰጠ ፤ “ ይዘብቱበትማል፣ ይተፉበትማል፣ ይገርፉትማል፣ ይገድሉትማል በሰዎስተኛዉም ቀን ይነሳል አላቸው “ (ቁጥር 34) ፡፡ ይህን መልዕክት ኢየሱስ የሰጣቸዉ ለሰዎስተኛ ጊዜ ነው ፤ ማር(10፡ 33) እንደ መጀመሪያዎቹ ሁለቱ ተመሳሳይ ቋንቋ ይጠቀማል ፡፡
የመጀመሪያዉ ትንብያ በማር (8፡ 31) ነበር፡ “ የሰዉ ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል ሊገደልም ከሰዎስት ቀንም በኋላ ሊነሳ እንዲገባው ያስተምራቸዉ ጀመር ፡፡”
ሁለተኛዉ ትንብያ በማር (9፡ 31) ነበር፡ “ ደቀ መዛሙርቱን ያስተምር ስለ ነበር ማንም ያዉቅ ዘንድ አልወደደም ፤ ለእነርሱም ፡፡ የሰዉ ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጣል ይገድሉትማልም ተገድሎም በሶስተኛው ቀን ይነሳል ፡፡”
ማር (15፡ 17-20) በማር(10፡ 34) የተጠቀሰዉ መዘባበት ማረጋገጫ ነው፡ “ ቀይ ልብስም አለበሱት የእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት ፤ የአይሁድ ንጉስ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር ፤ ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም ተንበርክከዉም ሰገዱለት ፡፡ ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት ፡፡ “ በተጨማሪም ይህ ቀድሞ በብሉይ ኪዳን ተነግሮ ነበር (መዝ 22፡ 6-8 ፤ ኢሳ 50፡ 6) ፡፡
ማርቆስ (10፡ 35-37)፡ እዚህ ጋር ማርቆስ የተለየ ሽግግር ይሰጣል ፡፡ በማቴ (20፡ 20) የያዕቆብ እና የዮሀንስ እናት ስለ ተለየ ነገር ልትጠይቀዉ ኢየሱስን ቀረበችዉ ፤ በማርቆስ አገላለፅ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ በመሄድ “ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት “ (ቁጥር 35) ፤ ኢየሱስም “ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ ? አላቸው (ቁጥር 36) ፡፡ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም የሚደርሰበትን ከገለፀ በኋላ ያንን “ክብር” ለማግኘት በቀኙ እና በግራ እጆቹ ላይ እንዲቀመጡ ጠየቁት (ቁጥር 37) ፡፡
ማክአርቱር የፃፈው “ ይህ አጋጣሚ የኢየሱስን ትምህርት በትህትና ላይ ለመያዝ እንደገና የደቀ መዛሙርቱ ዉድቀት ይገልፃል ፤ ለመሞት ወደ ኢየሩሳሌም እየሄዱ እንደነበር የአምላክን የተደጋገመ ትዕዛዝ በመተዉ አሁንም ደቀ መዛሙርቱ የመንግስቱ አካላዊ መታየት ስለ መገለጡ ያስቡ ነበር በተጨማሪም በዚህ መንግስት ስለ እዉቅና ቦታ በማቀድ ተጠምደዉ ነበር ፡፡”
ይሁን እንጂ ለማወቅ ዋጋ ከምንሰጣቸዉ በላይ ደቀ መዛሙርቱ ያውቃሉ ፤ በማቴ 919፡ 28) ኢየሱስ ለእነርሱ የተናገራቸው “ እዉነት እላችኋለሁ እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት የሰዉ ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአስራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ ፡፡” በማቴ (20፡ 20-22) ደቀ መዛሙርቱ ተዘጋጅቶላቸዉ የነበረዉን መቀመጫ ይጠይቁ ነበር ፡፡ ዮሐ (14፡ 13) የሚለው “ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ ፡፡” ደቀ መዛሙርቱ እየጠየቁ ያሉት መንግስቱ በመጨረሻ ጊዜ ምንድን እንደምትመስል እና በዚህ ዉስጥ ሚናቸዉ ምን እንደሚሆን ይሆናል ፡፡
ማርቆስ (10፡ 38-39)፡ ኢየሱስ እየጠየቁት የነበረዉን እንደማያዉቁ ገለፀ ፡፡ ስለ ሰዉ ልጆች ኃጢዓት የተሸከመዉን የእግዚአብሄር የቁጣ ፅዋ ሊጠጡ ይችሉ ነበር ? በገጠመዉ ሙሉ መከራ ራሳቸዉን ለማስገባት ዝግጁ ነበሩ ? ሁለቱ ወንድማማቾች “ እንችላለን “ (ቁጥር 39) ብለዉ መለሱ ፤ ኢየሱስም ኢየሱስ እንደተጠመቀዉ ተመሳሳይ ጥምቀት እና ፅዋዉን እንደ ሚጠጡ መለሰላቸው ፡፡ በሐዋ (12፡ 2) ንጉስ ሄርዶስ ያዕቆብን በሰይፍ ገድሎታል ፤ ያዕቆብ ስለ ወንጌል ፅዋዉን ጠጥቷልም በጥምቀት ችግሮች(መከራ) አካላት ዉስጥ ተከትቶአል(ገብቷል) ፡፡ ዮሐንስ በወንጌል ምክንያት በፍጥሞ ደሴት ላይ ወደ ግዞት ተላከ (ራዕ 1፡ 9) ፡፡ ለኢየሱስ መልሳቸዉ ትክክል ነበር ፡፡
ማርቆስ (10፡ 40-41)፡ ኢየሱስም የተዘጋጀዉን ስፍራ መስጠት የእርሱ እንዳልሆነ መለሰ ፡፡ ማክአርቱር የሚለው “ በመንግስቱ ክብሮች የሚሸለሙ እንጂ በራስ ጉጉት መሰረት አይደለም በሉዓላዊ መለኮት ፍቃድ ምክንያት እንጂ ፡፡” ይህ ለእግዚአብሄር እንደሆነ እንዴት እግዚአብሄር አመቻቸ (ቁጥር 40) ፡፡ በያዕቆብ እና ዮሐንስ ቅድሚያ ስለ መቀመጫ በመጠየቃቸው ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ተበሳጩ (ቀኑ) (ቁጥር 41) ፡፡
ማርቆስ (10፡ 42-45)፡ አለም በግለሰቦች ላይ ስልጣን የነበራቸዉን መሪዎች እንደነበሯት እና ሰዎች በሌሎች ላይ ስልጣን እንደሚፈልጉ ይገልፃል ነገር ግን የእግዚአብሄር መንግስት በተቃራኒ ስፍራ መሰረት ነበር፡ በትህትናና በአገልጋይነት ፡፡ ክርስቲያን ለእነዚህ ስፍራዎች አይጠይቅም (ቁጥር 42) ፡፡ ለወሲባዊ ኃጢዓት እና ሴቶችን በመዝለፍ ሰዎች ከስልጣናቸዉ ስር ላሉ የተጠሩትን በከፍተኛ ተፅዕኖ በአሜሪካ ያሉትን ሁሉንም ሰዎች ስናስብ ፤ ያ የአለም መንገድ እንጂ የእግዚአብሄር መንግስት መንገድ አይደለም ፡፡
በክርስቲያን አገልግሎት በራስ ኃይል የተሳባችሁ ላለመሆን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው ነገር ግን ለመንፈስ ቅዱስ በመፍቀድ በኃላፊነት(በስራ) አንዶቹ ትሆናላችሁ ፡፡ ኢየሱስም “ በእናንተስ እንዲህ አይደለም ፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን ፤ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን “ አለ (ቁጥር 43-44) ፡፡ አንድ ሀተታ ሰጪ የተናገረው በክርስቶስ አካል ዉስጥ ለኃይለኛ መሪዎች ቦታ የለም ፡፡
ጎዉልድ የፃፈው “ የእግዚአብሄርን መንግስት ተፃራሪ አለ ፤ ጌቶች ከመሆን ይልቅ አገልጋዮች መሆን ታላቅ ነው በተጨማሪም አለቆች የሁሉም በነፃ አገልጋዮች ናቸው ፡፡ ” ማር (9፡ 35) የሚያረጋግጠው “ ተቀምጦ 12ቱን ጠርቶ ፡፡ ሰዉ ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን አላቸው ፡፡ “ (1ጴጥ 5፡ 3-6 ለእናንተ ስለተሠጡት በኃይል ስላለማስተዳደር ያወራል) ፡፡
በ 3ዮሐ (1፡ 9-10) ዮሐንስ የቤተ ክርስቲያን አባላት በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ለራስ ክብር እየተጉ የነበረበትን ሁኔታ ገልፃታል፡ “ ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም ፡፡ ስለዚህ እኔ ብመጣ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈየሚያደርገውን ስራዉን አሳስባለሁ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም ሊቀበሉአቸዉም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል ፡፡ “ በኢየሱስ የተጣራን በምንሆን ጊዜ መያዝ እና ቃሉን መሆን እንጀምራለን ፤ አገልጋይ መሆን ማለት ምን እንደሆነ መኖር እንጀምራለን ፡፡ ኢየሱስም “ እንዲሁ የሰዉ ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣምና “ አላቸው (ቁጥር 45) ፡፡
“ ቤዛ በነፃ ለባሪያ እና ለአስረኛ የሚከፈልን ዋጋ ይገልፃል ፤ ማለትም በቦታዉ በመተካት በእርሱ እምነታቸዉን ስላስቀመጡት በክርስቶስ የተተካዉን ሞት በጣም የተከበረ ነው በሁሉም መፅሀፍ የተባረከ እዉነት ነው “ ፤ እነዚህ ሁሉ ክርስቶስ ስለ እኛ በቦታችን እንደ ቤዛ ህይወቱን ስለ መስጠቱ ነው ፡፡ ሮሜ (4፡ 25) የሚለው “ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠዉን እኛን ስለ ማፅደቅ የተነሳዉን ” ፤ ሮሜ (5፡ 6-8) ይህን በዚህ መንገድ ያጠቃልለዋለል፡ “ ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢዓተኞች ሞቶአልና ፡፡ ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና ፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል ፡፡ ነገር ግን ገና ኃጢዓተኞች ሳላን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሄር ለዕኛ ያለዉን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ! “
መዝጊያ
የእኛ ቤዛ በመሆን ይህን ሀሳብ ለማግኘት ለክርስቶስ ብቸኛዉ መንገድ ለእርሱ እንደ አገልጋይ ህይወቱን ለመስጠት ፍቃደኛ መሆኑ ነበር (ሮሜ 6፡ 3; 1ቆሮ 15፡ 3; 2ቆሮ 5፡ 21; ገላ 1፡ 4; 1ዮሐ 2፡ 6) ፤ እግዚአብሄር በጠየቃችሁ ምክንያት ከግል እርካታ ዉጪ ለማገልገል ፍቃደኞች በምትሆኑ ጊዜ ማር (10፡ 45) መረዳት ጀማሪዎች ናችሁ ፡፡
3 Ezra P. A. Gould, “A Critical and Exegetical Commentary on the Gospel According to St. Mark,” International Critical Commentary series. (Edinburgh: T. & T. Clark, 1896), p. 202; quoted in Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Mark, p. 160; available at www.soniclight.com.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1233.
MacArthur, p. 1233.
MacArthur, p. 1233.
ጥያቄዎች
-
ኢየሱስ ተመልሶ ሙሴ ያዘዛቸዉን ለምን ጠቀሰ (ማር 10፡ 3) ? ሙሴ ስለ ፍቺ አስተምሮት የነበረዉ ኢየሱስ ካስተማረዉ ጋር እንዴት ነበር እሚለያየው ? (ዘዳ 24፡ 1)
-
እንደ ህፃን የእግዚአብሄርን መንግስት እንዴት ትቀበሉታላችሁ ? (ማር 10፡ 14-15)
-
ጎበዙ ኃብታም ሰዉዬ ኢየሱስን “ ቸር መምህር ሆይ “ ብሎ እንዲጠራዉ ለምን አልፈለገም (ማር 10፡ 17-18) ? ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት ለሀብታም እንዴት አስቸጋሪ ነው ?
-
ኢየሱስ ስለ ሞቱን ሲናገር ደቀ መዛሙርት ሆናችሁ ቃሉን ስትሰሙ ምንድን ተሰማችሁ ? (ማር 10፡ 32-34)
-
በማር (10፡ 35-45) ያዕቆብ እና ዮሐንስ ኢየሱስን የጠየቁትን የሚመስል ነገር መቼ ጠየቃችሁ ? ይህን ለመጠየቅ ፍላጎታቸዉ ምን ነበር ? በእርሱ ፍቃድ ያልሆነ ነገር ለማድረግ በጠየቃችሁት ጊዜ ኢየሱስ እንዴት አድርጎ መለሰላችሁ ?
-
በማርቆስ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Mark 10:43b-45
“On the contrary, whoever wants to become great among you must be your servant, and whoever wants to be first among you must be a slave to all. For even the Son of Man did not come to be served, but to serve and to give His life—a ransom for many.”
ያዕቆብ እና ዮሐንስ ኢየሱስ በክብሩ ጊዜ በቀኙ እና በግራው እንዲያስቀምጣቸው ጠየቁት፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ እንዲሆን፥ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ስለ ሀይል እና የክብር ሥፍራን በመፈለግ ስላለው ትግል ትምህርት አስተማራቸው፡፡ በከፍታ ሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በሌሎች ላይ ሀይልን መለማመድ እንደሚወዱ ጠቀሰ፡፡ በተቃራኒው፥ የኢየሱስ ተከታይ ታላቅ የሚሆነው አገልጋይ በመሆን ነው፡፡ እንደ ንጉስ ከመገልገል ይልቅ፥ ስለሌሎች ነፍሳችሁን እስከመስጠት ድረስ፥ ሌሎችን ማገልገል ማለት ነው፡፡ የኢየሱስ ህይወት አላማው ይሄ ነበር− ሊያገለግል እና ነፍሱን በመስጠት ሌሎች የዘላለምን ህይወት እንዲያገኙ መጥቷል፡፡
በተመሳሳይ መንገድ፥ እናንተም ለዝና፣ ለሀብት፣ ለሀይል እና ለሥልጣን አልተጠራችሁም፥ ነገር ግን ለማገልገል ተጠርታችኋል፡፡ እንዴት የቤተሰብ አባልን መውደድ እንደምትችሉ፣ የትዳር አጋርን እንዴት እንደምትይዙ ወይም የስራ አጋሮቻችሁን እንዴት እንደምትባርኩ፥ ራሳችሁን እየጠየቃችሁ ከሆነ፥ እንዴት እንደምታገለግሏቸው ጌታን በመጠየቅ ጀምሩ፡፡ እናንተ ይገባኛል ብላችሁ የምታስቡት ምንም ይሁን ምን፥ ራሳችሁን እንደ ኢየሱስ በማዋረድ እግዚያብሔር በህይወታችሁ ያስቀመጣቸውን ሰዎች በማገልገል ጀምሩ፡፡ ይህን በማድረግ፥ ጌታን ታከብሩታላችሁ፡፡
“በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
— ማርቆስ 10:43-45
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6-8 — “ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ”
- 1ኛ ጴጥሮስ 5:3-6 — “ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ”
- 1ኛ ዮሐንስ 2:6 – “በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 38
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።