The Gospels Mark

Producing Fruit

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 149 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና እንደሚሞት፣ እንደሚቀበር እና በሰዎስተኛዉ ቀን ላይ ወደ ህይወት እንደሚመጣ በኢየሱስ ትንብያ ላይ ተመልክተናል ፤ በእርግጥ ኢየሱስ ትንብያዉን በማርቆስ ወንጌል ሰዎስት ጊዜ አድርጎታል ፡፡ ያዕቆብ እና ዮሐንስ በክብሩ ቦታ በቀኙ እና በግራዉ ላይ መቀመጥ እንደሚችሉ በመጠየቅ ለኢየሱስ ትንብያ መለሱ ፤ ኢየሱስ ያንን ቦታ ማግኘት ከፈለጉ የታገሰዉን መከራ ለመታገስ ፍቃደኞች ፍቃደኞች እንዲሆኑ መለሰላቸው ፤ ኢየሱስም ይህ መጀመሪያ ስለመሆን እንዳልነበር ነገር ግን መጨረሻ ስለ መሆን እንደነበር አላቸው ፡፡ ማር (11፡ 1-11) የኢየሱስን በድል ጩኸት ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱን ቀድመን ስለ አወራነዉ ይሸፍናል ፤ ቁጥር 11 የሚለው “ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ ፡፡ “ ዙሪያዉን በመመልከት አረጋግጦ ወደ ቢታኒያ ሄደ ፡፡

ማርቆስ (11፡ 12-14)፡ ይህ የሌላዉ “ ሳንዱች “ ይዘት መጀመሪያ ነው ፡፡ በበለስ ዛፍ ላይ ከዚያም በመቅደሱ ክስተቶች ላይ ከዚያም በመቀጠል እንደገና በበለስ ዛፋ ላይ እንመለከታለን ፡፡ በቀጣይም ቀን ኢየሱስ ቢታኒያን ትቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ ተርቦም ነበር (ቁጥር 12) ፤ ይህ የኢየሱስን ሰዉነት ያጎላል ፡፡ ተርቦ ስለነበር ቅጠል ያላት አንድ የበለስ ዛፍ አየ በላዋ ላይ ፍሬ እንደነበራት ለማየትም ሄደ (ቁጥር 13) ፤ ይሁን እንጂ በዛፏ ላይ ፍሬ አልነበረም “ ምክንያቱም የበለስ ማፍሪያ ወቅት አልነበረም “ ፤ ኢየሱስም “ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላት ! “(ቁጥር 14) ፡፡ ለበለስ ወቅቱ ግንቦት ወይም ሰኔ ነበር ፋሲካ ደግሞ በመጋቢት ወይም ማዚያ ነበር ስለዚህ በትክክለኛዉ ወቅት አልነበሩም ፤ ይሁን እንጂ በመጋቢት በግልፅ የሚበሉ ብዙ እንቡጦች አሉ ፤ በሚያዚያ ቅጠሎች ይከሰታሉ ከዚያ ቆይቶም ፍሬ ይከሰታል ፡፡ ኢየሱስ ወደ በለስ ዛፏ በመጣ ጊዜ ጥቂት የሚበሉ እንቦጦች ለማግኘት ፈለጎ ነበር ነገር ግን ምንም አላገኘም ፤ ለመብላት የሆነ ነገር ፈለገ ምንም አላገኘም ፡፡

ብዙ ሀተታ ሰጪዎች ስለ እስራኤል እንደ መንፈሳዊ ማሳያ ያዩታል ፤ ኖርማሊይ የበለስ ዛፍ የእስራኤል ሰላም፣ ብልፅግና ስጦታ ምልክት ነው (ሚክ 4፡ 4; ዘካ 3፡ 10) ፡፡ አሁን ይህን ታሪክ በማቆም ተመልሰን እንመጣለን ፡፡

ማርቆስ (11፡ 15-16)፡ ኢየሱስ ወደ መቅደስ ተመልሶ “ በመቅደስ ይሸጡ እና ይገዙ የነበሩትን ያወጣ ጀመር “ (ቁጥር 15) ፤ “ ሁሉንም ነገር ዙሪያ ከመመልከቱ “ ምሽት በፊት እዚያ ነበር ከዚያም በመቀጠል በማግስቱ ምንድን እንደሚሰራ ወሰነ (ቁጥር 11) ፡፡ ኢየሱስ እንደደረሰ ወዲያዉኑ “ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ ፤ ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም “ (ቁጥር 15-16) ፡፡ መቅደሱ በጣም ቅዱስ ስፍራ ነበርና “ መቅደሱን በማንፃት ኢየሱስ መጀመሪያ ይህን ቦታ በክብር ከሞላዉ ከእግዚአብሄር እኩል በግልፅ ስልጣኑን ወሰደ “ ፤ ኢየሱስ በአድስ ስልጣን ተጓዘ (2ዜና 5፡ 13-14) ፡፡ በመቅደሱ ዉስጥ ተፈፅሞ የነበረውን ሁሉንም ነገር ኢየሱስ ወደላይ እና ወደታች መወርወር ጀመረ - እንስሳቶቹ ለመስዋዕትነት እንዲሸጡ ሆኑ፣ ገንዘቡ ወደ መቅደሱ ምንዛሬ ተቀይሮ መስዋዕት ለማድርግ እንዲችል እና በመቅደሱ የተጓጓዙት ሸቀጦችም እንኳን ለመስዋዕት ይሆናሉ ፡፡

ገንዘብ ቀያሪዎቹ በመቅደሱ ላይ አስፈላጊ ሚና ነበራቸዉ ምክንያቱም ገንዘባቸዉን መቀየር የሚያስፈልጋቸው ከብዙ ቦታዎች እና ባህሎች ሰዎች ይመጡ ስለነበር ፤ ለፍላጎት ገንዘብ የመስራት እድሉ ታላቅ(መልካም) ነበር ፡፡ እርግቦች ለመስዋዕት ለድሆይ ይሸጣሉ በተጨማሪም ድሀዎች በጣም ተሰብስበዉ የሚገናኙበት ነበር ፡፡ ሮድነይኮፐር የሚለው ኢየሱስ ሰዎች በመቅደሱ ዉስጥ እንደ አቋራጭ መንገድ እንዳያቋርጡ ይፈልጋል ምክንያቱም መቅደሱ ለእግዚአብሄር ለመስገድ የተለየ ቅዱስ ቦታ ስለ ነበር ፡፡

ልክ እንደ ምቹ ማጠራቀሚያ እያደረጉት ነበር ፤ መቅደሱን ኢየሱስ በግልፅ ካፀዳው በፊት እና በተለይም በኃላ የተደበላለቀ(የተዘበራረቀ) ሆኖ ነበር ፡፡

ማርቆስ (11፡ 17)፡ በዝብርቅርቁ መሀከል ሁለት የብሉይ ኪዳን ትንቢቶችን ኢሳያስን እና ኤርምያስን በመጠቀም ኢየሱስ ማስተማር ጀመረ ፡፡ ኢሳ (56፡ 7) የሚለው “ ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ ፤ ቤቴ ለአህዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለዉን መስዋዕታቸውንና ሌላ መስዋዕታቸዉን በመሰዊያዬ ላይ እቀበላለሁ ፡፡ “ አስታዉሉ፡ ቤቴ ለአህዛብ ሁሉ የፀሎት ቤት ይባላል ! ኤር (7፡ 11) የሚለው “ ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን ? እነሆ እኔ አይቻለሁ ይላል እግዚአብሄር ፡፡ “ የፀሎት ቤት ከመሆን ይልቅ የወንበዴዎች ዋሻ ሆኖ ነበር ፤ በቁጥር 17 ኢየሱስ እነዚህን ሁለት ሀሳቦች በአንድ በመሳብ የሚያዳምጡትን ከእግዚአብሄር ቤት ወደ ሌቦች ዋሻ እንደቀየሩት ከሰሳቸው ፡፡ አህዛቦች በዉጨኛው አደባባይ ብቻ ማምለክ ይችላሉ አይሁዶች ለመስዋዕት እየሸጡዓቸዉ በነበረዉ እንስሳቶች እና የገንዘብ ምንዛሬዎች ከዚያ ስፍራ እየጎተቷቸዉ ነበር ፡፡ በሮክስ የሚለው “ የአህዛቦች አደበባይ ከሁሉም ጩኸቱ ሽብር እና ግማት ጋር ወደ ባዛር በመቀየር በመቅደስ ማምለክ እሚችሉበትን ብቸኛ ቦታ ከለከሉ ፤ ንግዱን በማፅዳት በግልፅ እና በምልክት ኢየሱስ ለአህዛብ በእግዚአብሄር መቅደስ ቦታ ሰጣቸዉ ፡፡ “ አይሁዶች አህዛቦችን ጎትተዋቸው ነበር (ዮሐ 1፡ 10-12) ፤ ኢየሱስ አህዛቦችን ለመቀበል ከመንገዱ ዉጪ ሁሉንም ነገር አንቀሳቀሰ (ሐዋ 13፡ 46-47) ፡፡ ኮፐር የሚለው መቅደሱ የማይገባቸዉ ሰዎች መማፀኛ ይሆን ነበር አይሁዶች ደግሞ በእግዚአብሄር የመቀበል ሁኔታ ደህንነት ተሰምቶአቸዋል ምክንያቱም በስርዓት እና በህግ ፡፡ አይሁዶች እነማን በነበሩበት(የተለዩ ስለነበሩ) ምክንያት በሁሉም ነገር የሚፈልጉትን ማግኘት እንደሚችሉ ተሰምቷቸዋል ፤ ነገር ግን መቅደሱ ያለ ምንም ቅጠላ ቅጠል ልክ እንደ በለሷ ዛፍ እየሆነ ነበር ፡፡

ማርቆስ (11፡ 18-19)፡ አለቃ ካህናቶች እና ፃፎች በስልጣ የኢየሱስን ትምህርት ሰሙ ፈሩትም ሊያጠፉትም ፈለጉ ፤ ለደህንነት ምሽት ላይ ኢየሱስ ከተማዋን ይለቅቅ ነበር ፡፡

ማርቆስ (11፡ 20-22)፡ በቀጣዩም ቀን ጴጥሮስ ከቀኑ በፊት ኢየሱስ ረግሟት የነበረችዉ በለስ “ ከስርዋ ጠዉልጋ እንደነበር “ አስተዋለ ፤ ኢየሱስም “ በእግዚአብሄር እምነት እንዲኖራቸው “ ነገረው ፡፡

ይህ ሁሉ በአንድ ላይ እንዴት ይጣጣማል ?ኮፐር የሚለው ኃይማኖታዊ ዘዴ ብዙ ቅጠሎች አሉት ፍሬ ግን የለዉም የስርአት አጥባቂዎች ዉጪ በአስራት፣ በፀሎቶች እና በፆም የታየ ነበር ፡፡ ኃይማኖታዊ ኢሊቶችን ጥሩ እንዲመስሉ ለማድረግ ኃይማኖታዊ ስርዓቶች በሴቶች፣ በለምፃሞች፣ እዉር ለማኞች እና አጋንንቶች ባሉባቸዉ እየተጠበቁ ነበር ፡፡ ቅጠላ ቅጠሉ ብዙ ተስፋዎች አቅርቧል ነገር ግን ፍሬ(መፈፀም) የለውም ፤ የኢየሱስን ርሀብ ማርካት እንዳልቻለችዉ እንደ ትንሻ የበለስ ዛፍ የመንፈሳዊ ርሀባችንን የተኛዉም የኃያማኖት ዘዴ ማርካት አይችልም ፡፡ ዘዴዉ(ስርዓቱ) እንደተሰበረ የምናዉቀዉ መቼ ነው ? በግልፅ መቅደሱ ቀጠሎ የቆመ አይደለም ስለዚህ አይሁዶች በዚህ ትንሽ ፀጋ ያገኛሉ ፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን አስቡ ፡፡ የተሰበረዉ እና ፍሬ የማያመርተዉ የኃይማኖታዊ ስርዓት(ዘዴ) እንዴት እንሆናለን ?

ሮሜ (11፡ 11) የሚለው “ እንግዲህ የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነዉን ? እላለሁ ፡፡ አይደለም ፤ ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸዉ ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆን ፡፡ ”

ማርቆስ (11፡ 23-26)፡ የተሰበረን ስርዓት እንዴት እናስተካክላለን ? በቤተ ክርስቲያን በብዙ ፀሎት እና በምህረት፡፡

መዝጊያ

በአሁኑ ጊዜ ፍሬ እንዴት ማፍራት እንደ ምትችሉ ማወቅ ትፈልጋላችሁ ? በእምነት ፀሎታችን መልስ ይሆናል ፤ ያ በዚህ ቀላል ነው ፡፡

4 Cooper, Kindle location 4381.

5 Cooper, Kindle location 4400.

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson’s Publishers, 1999), p. 1228.

  2. Rodney Cooper, Holman New Testament Commentary: Mark (Nashville: Holman Publishers, 1991), Kindle location 4373.

  3. James A. Brooks, Mark: An Exegetical and Theological Exposition of Holy Scripture (Nashville: Holman Publishers, 1991), p. 186.

ጥያቄዎች

  1. ፈሪሳዉያን ለሁሉም ኢየሱስን ያዬ እንዲነግራቸዉ ተናገሩ በዚህም ምክንያት ሊያስሩት ይችላሉ (ዮሐ 11፡ 57) ፤ በዚህ ሁሉ ዛቻ በማር (11፡ 7-11) የኢየሱስን ድፍረት እንዴት ታዩታላችሁ ?
  2. እግዚአብሄር የፍሬ መልክ በሚኖረን ጊዜ ነገር ግን በትክክሉ ፍሬ ከሌለን አይደሰትም ፤ ፍሬ ባለማፍራት እና መጥፎ ፍሬ በማፍራት መካከል ያለዉ ልዩነት ምንድን ነው ? (ማቴ 7፡ 16-20; ማር 11፡ 13-14)
  3. ኢየሱስ መቅደሱ ምንድን ተብሎ እንደሚጠራ እና ለመቅደሱ ማን እንደ ነበር ምን ተናገረ (ኢሳ 56፡ 7) ? መቅደሱን ወደ ሌባዎች ዋሻ ቀየራችሁት ብሎ በማስታወል ኢየሱስ ምን ማለቱ ነበር ? (ኤር 7፡ 11)
  4. ስለ በለሲቱ ዛፍ ታዓምራት ኢየሱስ የተናገረበት ምክንያት ምን ነበር (ማር 11፡ 21-22) ? ሁልጊዜ የእምነታችን አላማ መሆን ያለበት ማነዉ (ሮሜ 3፡ 26; ገላ 3፡ 26; ዕብ 11፡ 6) ? ይህ ማለት በቂ እምነት የሚኖረን ከሆነ እግዚአብሄር የጠየቅነዉን ሁሉ ያደርጋል ማለት ነው (ማር 11፡ 23-24) ? ለምን ወይስ ለምን አይደለም ? (1ቆሮ 2፡ 5; 13፡ 2; 1ዮሐ 5፡ 14)
  5. በማር (11፡ 28-30) የኃይማኖት መሪዎች የጠየቁትን ጥያቄ ኢየሱስ እየሸሸ ነበር ? አይደለም ከሆነ ለምን በዚያ መንገድ መለሰላቸው ? ይህ ኅይማኖተኞቹ ስለ ኢየሱስ ማን እንደ ነበር እዉነቱን ለማወቅ ፈልገዉ ይመስላል ?
  6. በማርቆስ 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 11:12-13

“The next day when they came out from Bethany, He was hungry. After seeing in the distance a fig tree with leaves, He went to find out if there was anything on it. When He came to it, He found nothing but leaves, because it was not the season for figs.”

ኢየሱስ ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቁ አየ፥ በቀረበ ጊዜ ግን፥ ፍሬ እንደሌላት ተመለከተ፡፡ ውጪዋ ብቻ መልካም ይመስል ነበር፡፡ በተመሳሳይ መንገድ፥ ወደ ቤተመቅደሱ ግቢ በገባ ጊዜ ፥ የአምልኮ ሥፍራው ቅዱስ ቦታ ከመሆን ይልቅ ገበያ በመምሰሉ ኢየሱስ አዘነ፡፡ ሁለቱም የቤተመቅደስ ግቢ እና የበለሰ ዛፍ፥ ውጪያቸው መልካም ይመስላል፥ ነገር ግን በቅርበት ሲፈተሹ፥ በሁለቱም ውስጥ የፍሬያማነት ማስረጃ የለም፡፡

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን አላቸው፥ " በእግዚያብሔር እመኑ"፡፡ ዋናው ነገር ይህ ነው . . . እመኑ፡፡ በእግዚያብሔር ላይ እምነት ሲኖራችሁ፥ ከኢየሱስ ጋር ግንኙነት አላችሁ፡፡ በኢየሱስ ውስጥ በኖራችሁ ቁጥር፥ ብዙ ፍሬ ታፈራላችሁ፡፡ ውስጣችሁ ከኢየሱስ ጋር ሳይገናኝ ፥ ውጪያችሁ ብቻ ክርስቲያን እንዳይመስል ተጠንቀቁ፡፡ ምናልባት በየእሁዶች ቤተክርስቲያን ትሄዱ ይሆናል፥ ነገር ግን በቀረው ሳምንት ውስጥ፥ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ለመኖር እንኳን አታስቡም፡፡ ኢየሱስ በዕየለቱ ከእርሱ ጋር በእምነት እንድትራመዱ ይፈልጋል፡፡ ይህን በማድረግ፥ ተራራን ማንቀሳቀስ ትችላላችሁ፡፡

“በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ። ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም።”

—ማርቆስ 11:12-13

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ማቴዎስ 21:43 — “ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች። ”
  • ገላትያ 5:22-23 — “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ”
  • ዮሐንስ 15:5 — “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 39