The Parable of the Vineyard
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ ሌላ ምሳሌ እንድናጠና ማርቆስ 12 እድልን ይሰጠናል ፤ ምሳሌ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለማስተማር የሁሉንም ቀን ነገርን ይጠቀማል ፡፡
ትምህርት
ማርቆስ (12፡ 1)፡ አንድ ሰው የወይን ተክል ተክሎ ዙሪያዋን አጥር አስቀመጠባት ፤ ከዚያም “ መጥመቂያም ማሰለት ግንብም ሰራለት “ (ቁጥር 1) ፤ ባለቤቱም ለአንዳንድ ገበሬዎች አከራይቷቸዉ ሄደ ፡፡ የወይን አትክልቱ፣ አጥሩ፣ ጉድጓዱ፣ ግንቡ እና በታሪኩ ሰዎች ለምሳሌዉ እቃዎች(ነገሮች) ናቸው ፡፡ ግንቡ እንደ ሚታይ ማማ፣ እንደ መጠለያ እና እንደ ማጠራቀሚያ መሳሪያ ነበር ፡፡
ማክአርቱር የሚያብራራው “ ባለቤቱ እንደ ኪራይ ለእርሱ የወደፊቱን ትንሽ መጠን ለሚከፍለዉ አስተማማኝ ጠባቂ ነዉ ብሎ ካመነዉ ሰዉ ጋር ስምምነት አደረገ ፡፡ ” የቀረዉ ገንዘብ ወደ ተከራይ ገበሬዎች ይሄዳል ፤ የወይን አትክልት ስዕል በስፍራዉ በጣም የተለመደ ነበር ፡፡ ማክአርቱር የሚለው “ የፍልስጤም ተራራማዉ አካል በኢኮኖሚ ጀርባ አጥንታቸው በወይን አትክልት ፍሬ የተሸፈነ ነበር ፡፡ “ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በጥሩ እየሰራ በሆነ ጊዜ መላዉ ሀገሪቱ በደህና የምትሰራ ትሆናለች(ደህና ትሆናለች) ፤ የጀርባ አጥንት በተሰበረ ጊዜ መላዉ ሀገሪቱ ትቸገራለች ፡፡ የወይን አትክልት ለእስራኤል ለሁለቱም ለመልካም እና ለመጥፎ እንደ ምልክት ይቅም ነበር (መዝ 80፡ 8-16; ኤር 2፡ 21) ፤ ኢየሱስ ለዚህ ምሳሌ እንደ መነሻ ኢሳ (5፡ 1-2, 7) ስለ እስራኤል (የወይን ተክል) እና እግዚአብሄርን (ባለቤት) ተጠቅሟል ፡፡
ማርቆስ (12፡ 2-5)፡ ከወይን አትክልቱ ፍሬ እንዲሰበስብ አንድ ባሪያ ተላከ ነገር ግን አንገላቱት ያለምንም ነገር ላኩት (ቁጥር 2-3) ፤ ከዚያም ባለቤቱ ያሰፈሩትን ሌላ ባሪያ ለከ (ቁጥር 4) ፤ ባለቤቱ ሌሎች ብዙ ተንገላተው ወይም/እና ተገድለዉ የነበሩ ላከ ከዚያም ቀጥሎ ሌሎች ብዙዎች ላከ ጥቂቶቹም ተገደሉ (ቁጥር 5) ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው “ ማር (12፡ 2-5) ፍሬዉን ያልተጠቀሙበትን ሰዎስት አመታትን የሚሸፍን ከነበር በመቀጠል የተወደደዉ ልጁ ተልኮ የነበረው በአራተኛዉ አመት ነበር ፡፡ “ ስለዚህም እነዚህ ባሪያዎች ከእግዚአብሄር የሆነዉን መልዕክት ለማወጅ ተናግረዉ የነበሩትን ነቢያትን ወደ ሚመጣዉ መሲህ ያለሟቋረጥ በማመልከት ይወክላሉ ፤ በዚህ ምሳሌ እግዚአብሄር ሰዎችን ወደ ተከራይ ገበሬዎች(በዚህ ምሳሌ የአይሁድን የኃይማኖት መሪዎችን ይወክላሉ) እንዲናገሩ እየላከ ነበር ፡፡ በተደጋጋሚ የኃይማኖት መሪዎች ከነቢያቱ የሆነዉን መልዕክት ለመስማት እምቢ አሉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ያመለከተው “ ይህ ታሪክ እግዚአብሄር በእስራኤል የጠነከረ ተዕግስት እንደነበረው ያሳያል ፡፡ “
ማርቆስ (12፡ 6-8)፡ ባለቤቱ(እግዚአብሄር)ለመላክ የቀረ አንድ ሰዉ ነበረው -ልጁ (ቁጥር 6) ፡፡ ቅጠርኛ ገበሬዎቹ ልጁ እንደሚወርስ ስለሚያዉቁ ሊገድሉት ወሰኑ ከዚያም ዉርሱን እንደሚቀበሉ (ቁጥር 7) ፤ ማክአርቱር የሚለው “ አትክልተኞቹ “ስግብግብ” እና ሁሉንም መኸር እና የአትክልት(ከወይኑ) ስፈራዉን ለራሳቸዉ ይፈልጉ ነበር ፡፡” ቅጥረኞቹ ለራሳቸዉ ሁሉንም ነገር ፈለጉ ስለዚህም ልጁን ገድለዉ “ ከወይኑ ስፍራ ዉጪ” ወረወሩት (ቁጥር 8) ፤ ኢየሱስም ከበሮቹ ዉጪ ተቀመጠ (ዕብ 13፡ 12-13) ፡፡ በማርቆስ ሰዎስት ጊዜ ኢየሱስ ስለሞቱ፣ ስለመቀበሩ እና ስለትንሳኤዉ አመልክቷል ፤ በዚህ ምሳሌ ኢየሱስ ቀድሞ ሆኖ እንደ ነበር ያሳያል ፡፡ አራተኛዉ አመት “ ለእግዚአብሄር ፍሬዉ የቀረበበት አመት ነበር (ዘሌ 19፡ 24) “ ፤ ይህ የልጁ መምጣት በጣም በአስፈላጊነት ለእግዚአብሄር እንደ መስዋዕት መሰጠቱን ያደርጋል ፡፡
ማርቆስ (12፡ 9-11)፡ “ እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋል ? “(ቁጥር 9) ፤ ገበሬዎቹን በማጥፋት የወይን አትክልት ስፍራዉን ለሌሎች ይሰጣቸዋል ፡፡ የገበሬዎቹ መጥፋት የተካሄደው በ 70 ዓ.ዓ ሮም መቅደሱን ባጠፋች ጊዜ ፡፡ ማክአርቱር የሚያብራራው የወይኑን አትክልት ለሌሎች መስጠት “ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ምስራት እና በብዛት አህዛብ በሆኑ መሪዎቻ የተፈፀመ ነበር “ ፤ (መዝ 118፡ 22-23) ፡፡
ማርቆስ (12፡ 12)፡ ስለ ወይኑ አትክልት ኢየሱስ ምሳሌ ነገራቸው በዚህ ጊዜ የኃይማኖት መሪዎች ምሳሌዉን ተረዱት፡፡
የወይኑ አትክልት አይሁዶችን ይወክላል ፡፡ እግዚአብሄር የወይን አትክልቱን ለእኛ ሳይሆን ለአይሁዶች ለምን ሰጠ ? ዮሐንስ ፒፐር የጠቀሰው “ አይሁዶች በአህዛቦች ላይ በእግዚአብሄር እንደተመረጠ ህዝብ ቅድሚያ አላቸው “ (ዘፍ 12፡ 1-3; ዘጸ 19፡ 6; ዘዳ 14፡ 2; ነህ 9፡ 7; አሞ 3፡ 2) ፡፡ ሁለተኛው ፒፐር የጠቀሰው “ በእግዚአብሄር የተለየ መገለጥ እንደ ሞግዚትነት አይሁዶች በአህዛብ ላይ ቅድሚያ አላቸው - ብሉይ ኪዳን መፅሀፍት “(ሮሜ 3፡ 1-2; 9፡ 4) ፡፡ ሰዎስተኛው ፒፐር የጠቀሰው “ መሲሁ ራሱ ኢየሱስ መጀመሪያ እንደ አይሁዶች ለአይሁዶች ስለመጣ አይሁዶች በአህዛብ ላይ ቅድሚያ አላቸው “ (ማቴ 10፡ 5-6; 15፡ 24; ሮሜ 1፡ 3; 9፡ 5) ፡፡ አራተኛው ፒፐር የጠቀሰው “ ከአይሁድ በሆነ ድነት አይሁዶች በአህዛብ ላይ ቅድሚያ አላቸው “ (ዮሐ 4፡ 22) ፡፡
ዮሐ (1፡ 11-12) የሚለው፡ “ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም ፡፡ ለተቀበሉትም ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሄር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው “ ፤ ባለመቀበላቸዉ ምክንያት (ማር 12፡ 9) እግዚአብሄር ገበሬዎቹን በማጥፋት የወይን አትክልቱን ለሌሎች ይሰጣል ፡፡ ሮሜ (11፡ 11-12) ሌሎቹ እንማን እንደሆኑ ያብራራል - አህዛቦችን ፤ ሮሜ (11፡ 25) ይህን ያጠቃልላል፡ “ ወንድሞች ሆይ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምስጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪ ገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው ፡፡ “
መዝጊያ
በዚህ ሁሉ እግዚአብሄር እቅድ ነበረው ፤ ነቢያቶቹ እና ልጁ የተገፊ ቢሆንም እግዚአብሄር አህዛብን ያካተተ እቅድ ነበረው - እኛን ያካተተ !
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1240.
MacArthur, p. 1240.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 151.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1230.
MacArthur, p. 1240.
Wiersbe, p. 151.
MacArthur, p. 1240.
John Piper, “To the Jew First, and Also to the Greek”; available online at https://www.desiringgod.org/messages/to-the-jew-first-and-also-to-the-greek.
ጥያቄዎች
-
ኢየሱስ ለአይሁድ አድማጮቹ ስለ ወይን አትክልት ነገራቸዉ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን እንደ ምን ስዕል በመጠቀም የወይን አትክልትን ስለ ሚያዉቁ ነበር ? (ኢሳ 5፡ 1-7)
-
በማር (12፡ 10-11) ኢየሱስ የትኛዉን የብሉይ ኪዳን ጥቅስ እየጠቀሰ ነበር ? የኃይማኖት መሪዎቹ የወይን አትክልት ባለቤት እርግማን ምሳሌ እንዴት ምላሽ ሰጡ ? በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ነገር በተወቀስን(በተወንጀልን) ጊዜ እንዴት መመለስ አለብን ?
-
በማር (12፡ 14) ኢየሱስ በማመስገን ለማጥመድ እና ለማሰረ ለምን ሞከሩ ? ይህ ማመስገን በትህትና ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልነበረም ?
-
ኢየሱስ ሰዱቃዉያን መፅሀፍትን ወይም የእግዚአብሄር ኃይል እንደ ማያዉቁ ተናገረ ፤ የእግዚአብሄርን ኃይል መረዳት እና መፅሀፍትን ማወቅ ለምን አስፈላጊ ነው ?
-
በመሰብሰቢያ ሳጥኑ ዉስጥ ድሀዋ መበለቲት ሴት በሰጠችዉ መጠን ኢየሱስ ለምን ነበር በጣም የተደነቀው ? (2ሳሙ 24፡ 24; 2ቆሮ 8፡ 12)
-
በማርቆስ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Mark 12:42-43
“And a poor widow came and dropped in two tiny coins worth very little. Summoning His disciples, He said to them, ‘I assure you: This poor widow has put in more than all those giving to the temple treasury.’”
ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ በሙሉ በቤተመቅደሱ መዝገብ ቤት ነበሩ፡፡ ኢየሱስም፥ ለአምልኮ የሚመጡ ሰዎች የፈቃድ መባቸውን በሚያስቀምጡበት፥ አስራ ሶስት የመለከት ቅርጽ ባላቸው መሳቢያዎች ውስጥ ሰዎች ገንዘባቸውን ሲጥሉ አየ፡፡ ባለጠጎች ብዙ ገንዘብ ሲጥሉ እና፥ አንዲት መበለት ትንሽ መጠን ያላቸው ሁለት ሳንቲሞችን ስትጥል አየ፡፡ ነገርግን ኢየሱስ መዝገብ ውስጥ ገንዘባቸውን ከሚጥሉ ሰዎች በላይ በሚሰጡበት ጊዜ ልባቸውን ያይ ነበር፡፡ መበለቲቱ የሰጠችው መጠን በአካል በጣም ትንሽ የተገባው ቢሆንም፥ በመንፈሳዊው ግን ፥ የልቧ ስጦታ ከሌሎቹ ሁሉ የሚበልጥ ነበር፡፡
ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ታላቁ ትእዛዝ ጌታ አምላካቸውን በፍጹም ልባቸው፣ ነፍሳቸው፣ ሀሳባቸው እና ሀይላቸው መውደድ እንደሆነ ቀደም ብሎ አካፍሏቸዋል፡፡ መበለቲቱ ለጌታ ለአምላኳ ያላትን ፍቅር በተግባር አሳየች፡፡ ለጌታ ገንዘባችሁን፣ ጊዜያችሁን ወይም ችሎታችሁን ስትሰጡ፥ ባላችሁ ሁሉ ኢየሱስን ከምትወዱበት ከልባችሁ ቦታ ስጡ፡፡ ህግ ወይም ግዴታ ስለሆነ ብቻ እንድትሰጡ አይጠራችሁም፡፡ አይሆንም፥ ለእርሱ ካላችሁ ፍቅር እንድትሰጡ ይፈልጋል፡፡ ደግሞም፥ ኢየሱስን ስለምትወዱት፥ ሌሎችን ትወዳላችሁ፡፡ ስለዚህ፥ ባላችሁ ነገር እና በሆናችሁት ልክ መስጠት ደስታ ነው፡፡ ዛሬ፥ ልባችሁን መርምሩ፡፡ የምትሰጡት ኢየሱስን ከሚወድ ልብ ነው ወይስ የክርስትና ግዴታችሁ እንደሆነ በማሰብ ነው?
“አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች። ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች”
—ማርቆስ 12:42-43
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ማቴዎስ 6:21 — “መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። ”
- 2ኛ ቆሮንቶስ 8:1-3 — “ወንድሞች ሆይ፥ ለመቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እናስታውቃችኋለን፤በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፤እንደ ዓቅማቸው መጠን ከዓቅማቸውም የሚያልፍ እንኳ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁና። ”
- 2ኛ ቆሮንቶስ 9:7 — “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 40
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።