The Gospels Mark

Watch! Be Alert!

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 151 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እስካሁን በማቴዎስ እና በማርቆስ ወንጌል ጥናታችን ከአንድ ጊዜ በላይ ተመሳሳይ ይዘት አላጠናንም ፤ ይሁን እንጂ ማርቆስ 13 እንደ ማቴዎስ 24 በብዛት ቃል በቃል ተመሳሳይ ነው ስለዚህ ምርጫ የለንም ፡፡ በዚህ ዉስጥ እየፀለይኩ ማርቆስ 13 እንዴት የተለየ እንማደርግ እግዚአብሄርን ጠየቁት ፤ መልሱም “አይሆንም !” ነበር በማርቆስ 13 ዉስጥ ስንጓዝ የመጨረሻዉ ዘመን ምንድን እንደሚመስል መመልከት እንጀምራለን ስለዚህም ለእርሱ መመለስ እንዴት ዝግጁ እንደምንሆን ማወቅ እንችላለን ፡፡

ትምህርት

ማርቆስ (13፡ 1-2)፡ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የመቅደሱን ብዙ ድንጋዎች ባመለከተ ጊዜ ኢየሱስም አንድም ድንጋይ በሌለኛዉ ላይ ሆኖ አይቀርም ብሎ መለሰ ፤ በ 70 ዓ.ዓ ስለ ሚመጣዉ የመቅደሱ መጥፋት እየተናገረ ነበር ፡፡ ይህ ተፈፅሞአል ፡፡

ማርቆስ (13፡ 3-6)፡ ቁጥር (3-8) “ የመጨረሻዉን ዘመን ምልክቶች “ ወይም የመጨረሻዉ ጊዜ መቅረቡን የሚያመለክቱትን ይሰጣሉ ፡፡ ኢየሱስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ኪድሮን ሸለቆ አሻግሮ ወደ ቤተ መቅደሱ እየተመለከተ ተቀመጠ ፤ ከአራቱ ደቀ መዛሙርቱ፡ ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብ፣ ከዮሐንስ እና ከእንድሪያስ ጋር ነበር (ቁጥር 3) ፡፡ ከመጨረሻዉ ዘመን በፊት ስለ ሚመጡት ምልክቶች በግላቸዉ ጠየቁት (ቁጥር 4) ፤ መጀመሪያ ኢየሱስ ከሚያስቷቸዉ እንዲጠነቀቁ መለሰላቸው (ቁጥር 5) ፡፡ ኢየሱስም ብዙዎች ከእርሱ ነን እያሉ ይመጣሉ ነገር ግን ይዋሻሉ ብዙዎችንም ያስታሉ አላቸው (ቁጥር 6) ፤ ይህ ሀሰተኛ መሲሆችን እና ሀሰተኛ ነቢያቶችን ያካትታል (ማቴ 7፡ 15; ሐዋ 20፡ 28-31) ፡፡

ማርቆስ (13፡ 7-8)፡ ከዚያም ኢየሱስ በተጨማሪ ምልክቶች ቀጠል፡ ጦርነት እና የጦርነት ወሬ ይመጣል ነገር ግን አሁንም መጨረሻዉ አልመጣም (ቁጥር 7-8) ፤ በተጨማሪም የመጨረሻዉ መጀመሪያ ምልክት የሆኑ የመሬት መናወጥ እና ረሀብ ይሆናል (ቁጥር 8) ፡፡

ማርቆስ (13፡ 9-13)፡ ግድያም(መሰደድም) ይሆናል ስለዚህ የኢየሱስ ተከታዮች በተጠንቀቅ መሆን አለባቸው (ቁጥር 9) ፤ የኢየሱስ ተከታዮች ይታሰራሉማ ይንገላታሉ ነገር ግን ለሁሉም ህዝብ ምስክሮቹ ይሆናሉ (ቁጥር 10) ፡፡ ተከታዮቹም ስለ ምን እንደሚናገሩ መጨነቅ የለባቸዉም ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ለእነርሱ ይናገራቸዋል (ቁጥር 11) ፤ ቤተሰቦች እርስ በእርሳቸዉ ይጣላሉ ለሞት እንኳን ተላልፈዉ ይሰጣጣሉ (ቁጥር 12) ፡፡ ሁሉም አካል የኢየሱስን ተከታዮች ይጠላሉ “ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል “ (ቁጥር 13) ፡፡ አንድ ሀተታ ሰጪ ይህ የመጀመሪያዉ ደረጃ ወይም ጅማሬዉ እንደሆነ ተናግሯል ፤ ከእስራኤል ጋር የሰባት አመት የሰላም ስምምነት የሚያደርግ የ10 ኢሮፓዉያን ህዝቦች አንድ መሪ ይኖራል ፡፡

ማርቆስ (13፡ 14-20)፡ 2 ደረጃው ከሰዎስት አመት ከግማሽ በኋላ ይጀምራል በቁጥር 14-23 የተገለፀ ነው ፡፡ “ ለብቸኝነት ምክንያት የሆነዉ ከፍተኛ ጥላቻ “ ደግሞ እንደ “ ታላቅ መከራ “ (ዳን 9፡ 27) የተጠቀሰ ነው ፡፡ የክርስቶስ ተቃዋሚዉ የሰላም ስምምነቱን ያደረገዉ ከዚያም ከሰዎስት አመት ከግማሽ በኋላ በማፍረስ ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዘዉ ግለሰብ ይሆናል ፤ በዚያ ያለዉ የክርስቶስ ተቃዋሚ (ህግ የለሽ ሰዉየዉ) በኢየሩሳሌም እንደገና በተገነባዉ መቅደስ የራሱን ስዕል ያስቀምጣል (2ተሰ 2፡ 3-4) ፡፡ በእግዚአብሄር መቅደስ ራሱን እንደጌታ በማወጅ ይቀመጣል ፡፡ በጥንቃቄ ልንሆን ልንነቃ ያስፈልጋል ! ለክርስቶስ ተቃዋሚዉ ሌላ ስም የሚያካትተው፡ “ የሚመጣው አለቃ (ልዑል) “ ዳን (9፡ 26) ፤ “ አዉሬዌ ወይም የመጀመሪያ አዉሬ” ራዕ (13፡ 1) ፤ እንዲሁም “በነጩ ፈረስ” ላይ ያለን “ ፈረሰኛን ” ራዕ (6፡ 2) ፡፡

በሰዎስት አመት ከግማሽ ጊዜ መዋቅሩ ላይ እናንተና ቤተ ክርስቲያን ዝግጁ መሆን የተሻለ ይሆናል ፤ ወዴት መሄድ ይጠበቅባችኋል ? ማር (13፡ 14) የሚለው “ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ “ ፤ ቁጥር (15-16) የሚለዉ እቃችሁን በአንድ ላይ ለመሰብሰብ ሳትሞክሩ መሸሽ ፡፡ እርጉዞች እና የሚያጠቡ በሚሸሹበት ጊዜ በአካላዊ ሁኔታ ይቸገራሉ (ቁጥር 17) ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የክርስቶስ ተቃዋሚዉ በክረምት እንዳይመጣ እንዲፀልዩ አዘዛቸው ስለዚህ ተከታዮቹ በአየር ሁኔታዉ አይቸገሩም (ቁጥር 18) ፡፡

ይህ በሚጀምር ጊዜ ሁሉም ገሀነም ይሰበራል ፡ “ በዚያን ወራት እግዚአብሄር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስካ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናል ፡፡ ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር ስጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ወራቶቹን አሳጠረ “ (ቁጥር 19-20) ፡፡

ማርቆስ (13፡ 21-23)፡ በደረጃ 3 ብዙ ሐሰተኛ መሲሆች እና ሀሰተኛ ነቢያቶች አሉ ፤ ቁጥር 23 አማኞች ምንድን ማድረግ እንዳለባቸዉ ያብራራል፡ “ እናንተ ግን ተጠንቀቁ ! እነሆ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ ፡፡ “

ማርቆስ (13፡ 24-27)፡ ከመከራዉ በኋላ “ ፀሀይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ “ (ቁጥር 24-25) ፡፡ የሰዉ ልጅ (ክርስቶስ) በደመና ይመለሳል ሁሉም ያዩታልም ፤ በሐዋ (1፡ 11) ኢየሱስ ሲያርግ እንደሄደበት ተመሳሳይ መንገድ እንደሚመለስ ተናግሯል ፡፡ መልዓክቱን ከማንኛዉም ምድር ጫፍ የተመረጡትን እንዲሰበስቡ ይልካቸዋል ፡፡

ማርቆስ (13፡ 33-37)፡ “ ጊዜዉ መቼ እንዲሆን አታዉቁምና ተጠንቀቁ ! ትጉ ፀልዩ ! “ (ቁጥር 33) ፡፡

መዝጊያ

ኢየሱስ ተመልሶ እንደሚመጣ አሁን እንዳሳመነኝ እስካሁን አልነበረም ! ወደ መጨረሻዉ ጊዜ በጣም እየቀረብን ነው ፤ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ወደ ቦታቸው መዉረዳቸዉን ይጠብቃሉ ፡፡ ለመሲሁ መምጣት ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀች እንድትሆን እፈልጋለሁ ፡፡ ተመልሶ የሚመጣ ነው ፤ የነቃን መሆን ያስፈላገናል !

ጥያቄዎች

  1. በማርቆስ 13 በዘመኑ መጨረሻ ምንድን እንደሚመጣ ኢየሱስ እየገለፀ ነበር ፤ በመጨረሻዉ ዘመን እየኖርን እንዳለ ታምናላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አይደለም ? መልሳችሁን ስትመልሱ መፅሀፍትን ተጠቀሙ ፡፡
  2. በቁጥር 33 ኢየሱስ “በጥንቃቄ እንዲሆኑ “ እና “እንዲነቁ” ተናገሩ ፤ ያ ምን እንደ ሚመስል ምን ታስባላችሁ?
  3. እንደ ክርስቲያን ክርስቶስ ያወራቸዉ የነበረዉ ችግርች እና መከራዎች ይገጥሙናል ? ለምን ወይስ ለምን አይገጥሙንም ?
  4. በማር (13፡ 14) ኢየሱስ ስለ መጨረሻዉ ዘመን እና “ ለብቸኝነት ምክንያት ስለሚሆነዉ ከፍተኛ ጥላቻ “ ተናገረ ፤ ያ ምንድን ነው እንዲሁም ከሚከተሉት ሰዎስት ጥቅሶች ጋር እንዴት ይገናኝል ? (ዳን 9፡ 27; 11፡ 31; 12፡ 11) ይህ ትንቢት ተፈፅሟል ?
  5. ቁጥር 26 ሁሉም ሰዉ የሰዉ ልጅ በደመና ሲመጣ ያዩታል ይላል ፤ እንዴት ቀላል ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  6. በማርቆስ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 13:23

“And you must watch! I have told you everything in advance.”

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ለመጨረሻው ዘመን አዘጋጃቸው፡፡ በዚህ ምዕራፍ፥ ተጠንቀቁ፣ አትደንግጡ፣ ትጉ፣ ንቁ በሚሉ ተመሳሳይ መልዕክቶች ሰባት ጊዜ አበረታታቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱ የመጨረሻው ዘመን ምልክቶችን እንዲያውቁ እና እንዲጠነቀቁ እንጂ እንዲፈሩ አልፈለገም፡፡ ኢየሱስ፥ ማወቅ የሚገባቸውን ነገር በሙሉ ቀድሞ በመናገር አዘጋጃቸው፡፡

ደቀመዛሙርቱ ለመጨረሻው ዘመን በመዘጋጀት ላይ እንደዚህ አይነት አመለካከት ሊኖራቸው እንደተገባ ሁሉ እንደ ክርስቶስ ተከታይ እናንተም እንደዚህ ልታስቡ ይገባል፡፡ ቀናችሁን ስታሳልፉ፥ ለመጨረሻው ዘመን ምልክቶች ንቁ ናችሁን? ደግሞስ ዘላለማዊ በሆነ እና ተስፋን በተሞላ አመለካከት ህይወታችሁን እየኖራችሁ ነው? ምንም ነገር ቢፈጠር፥ ለምን የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጦርነት፣ መከራ፣ ወይም ሀሰተኛ ነቢያት አይሆኑም፥ ሳትደነግጡ ልትነቁ ይገባል፡፡የመዳን ተስፋ እንዳላችሁ አስታውሱ፡፡ ጌታ ቀኖቹን የምታስተውሉበትን ጥበብ እንዲሰጣችሁ እየጠየቃችሁት፥ በመተማመን ተራመዱ፡፡ ዛሬ፥ በአለም ላይ የሚከሰቱ ክስተቶች እና አጋጣሚዎች ምን ይሁኑ ምን፥ ኢየሱስን እመኑት፡፡ ኢየሱስ ሊመጣ ላለው ነገር አዘጋጅቷችኋል፥ ስለዚህ አትፍሩ፡፡ ጌታ ከእናንተ ጋር ነው!

“እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።”

—ማርቆስ 13:23

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ሉቃስ 12:35-36 — “ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ ”
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 16:13-14 — “ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን። ”
  • የዮሐንስ ራእይ 16:15 — “እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 41