The Gospels Mark

Stay Awake and Pray!

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 152 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በማቴዎስ ወንጌል ኢየሱስን እንደ ንጉስ ተመልክተነዋል ፤ በማርቆስ ወንጌል ኢየሱስን እንደ አገልጋይ ተመልክተነዋል፡፡ በማርቆስ ኢየሱስ የተናገረዉ ሁሉም ነገር ንጉስ ለመሆን እንደ አገልጋይ መጥቶ እንደ ነበር ያሳያል (መዝ 78፡ 70-72) ፡፡ ማር (10፡ 45) የጠቅላላዉ የማርቆስ ወንጌል ዋና ጥቅስ ነው በተጨማሪም እንደ አገልጋይ ይህን የኢየሱስን መረዳት ይደግፋል፡ “ እንዲሁ የሰዉ ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም ፡፡ “ አገልጋዩ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ እና ለእኔ ህይወቱን ሰጠ ፡፡ በምዕራፍ (14-16) እንዴት ኢየሱስን ማገልገል እንደምንችል የምንምንመለከት ይሆናል ፡፡

ትምህርት

ማርቆስ (14፡ 1-26)፡ ቁጥር (1-2) ኢየሱስን ለመግደል ሴራዉን ይገልጣል ከቁጥር (3-11) ደግሞ በቢኒያ የኢየሱስን መቀባት ይገልፃል ፡፡ ቁጥር (12-16) ለፋሲካ ድግስ አድርገዉት የነበረዉን ዝግጅት ይገልፃል ፤ ቁጥር (17-21) ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ወደ ተቃራኒ ራሱን በማዞር አሳልፎ እንደሚሰጠዉ ቀድሞ የተናገረዉን መግለጫ ይሰጣል ፡፡ ከዚያም በቁጥር (22-26) ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር እራት ተካፈሉ ፤ ያ ነው ለዛሬዉ ጥናት መነሻ ፡፡

ማርቆስ (14፡ 27-31)፡ ራት በልተዉ ከጨረሱ በኋላ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ደብረዘይት ተራራ ወጡ ፡፡ እንደሄዱ ኢየሱስ “ ሁላችሁም በእኔ ትሰናከላላችሁ ፤ እረኛዉን እመታለሁ በጎችም ይበተናሉ የሚል ተፅፎአልና አላቸው “ (ቁጥር 27) ፤ ኢየሱስ ሁሉም ደቀ መዛሙርቱ ችግር በመጣ ጊዜ እንደሚበተኑ አብራራ ፤ ከዚያም ኢየሱስ “ ነገር ግን ከተነሳሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው “ (ቁጥር 28) ፡፡ ከተበተኑ እና ከሸሹ በኋላ በገሊላ ከእርሱ ጋር ሊገናኙ እንደሚችሉ እየነገራቸዉ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ መሸሹን “ ሁሉም ቢሰናከሉም እንኳን “ (ቁጥር 29) አልተቀበለም ፡፡ ኢየሱስም “ እዉነት እልሀለሁ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ሳይጮኽ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው ! “ (ቁጥር 30) ፤ ነገር ግን ጴጥሮስ ከመተዉ በፊት ከኢየሱስ ጋር እእሞታለሁ በማለት አበርትቶ ቀጠለ እንዲሁም ሌሎቹም ደቀ መዛሙርት ተስማሙ (ቁጥር 31) ፡፡ ስለዚህ የመጨረሻዉን አገልጋይ አገልጋዮች እንዴት አገለገሉት ?

ማርቆስ (14፡ 32-36)፡ “ ጌቴሴማኒ “ የሚለዉ ስም በዚህ መፅሀፍ እና በማቴ (26፡ 36) ሁለት ጊዜ የተጠቀሰ ነው ፤ ይህ ለመሄድ የኢየሱስ የለመደዉ ቦታ ነበር (ዮሐ 18፡ 1) ፡፡ ይሁዳም ደግሞ ኢየሱስ እንደሚሆንበት ይታወቃል ፡፡ “ ጌቴሴማኒ “ የሚለዉ ስም “ የወይራ ዛፍ ስብስብ “ ማለት ነው ፡፡ ሮድኔይ ከፐር የፃፈው “ በምሳሌነት(በምልክትነት) አሁን ኢየሱስ ለኃጢዓታችን እንደ መስዋእት ለተልዕኮዉ መፈጸም እያሰበ በኃይል የተጨነቀ ሆነ “ ፤ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲቆዩ እና እንዲፀልዩ ነገራቸው ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብን እና ዮሐንስን ከእርሱ ጋር ራቅ አድርጎ ወደ አትክልት ስፍራ ወሰዳቸው (ቁጥር 32-33) ፡፡ “ ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀምሮ “(ቁጥር 33) ስለ ነበር እዚህ የኢየሱስን ሰዋዊነት በግልፅ ይታያል ፡፡ ከቅርብ ሰዎቹ የዉስጣዉ ስሜት እና አካላዊ ድጋፍ አስፈለገው ፤ የግብረገብ ድጋፍ አስፈለገው ፡፡ ስለ ሚደርስበት ነገር ኢየሱስ በትክክል ያዉቅ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር ብቻቸዉን ሰዎስት ጊዜ ነበሩ፡ በተለወጠበት ተራራ ላይ፣ የኢያኢሮስ ሴት ልጅ ፈዉስ ላይ እና በጌቴሴማኒ (ፊል 3፡ 10) ፡፡

ማክአርቱር “ ደነገጠ(ፈራ) “( “በጣም ተቸገረ(ተቸገረ) ”) የሚለዉን ቃል “ የፍራት ስሜት ከፍተኛነትን እንደሚገልፅ ፤ በኃጢዓት ላይ የእግዚአብሄርን ሙሉ ንዴት መሸከም በመልኩ ላይ የአሰቃቂ እይታዉ ኢየሱስ ጭንቀትን በመያዙ እንደነበር ይገልፀዋል ፡፡” በቁጥር 34 ኢየሱስ “ ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች አላቸው “ ፤ እንደማስበዉ ተጨንቆ ነበር ምክንያቱም የአለምን ኃጢዓት ሊሸከም ስለ ነበር (2ቆሮ 5፡ 21) ፡፡ ማክአርቱር የሚለው “ የኢየሱስ ሀዘን በጣም ከባድ ነበር በዚያ ክስተት ላይ ለሞቱ ምክንያት የሆነ ” ፤ (ሉቃ 22፡ 44) ፤ ሁሉንም ነገር ያለፈዉን፣ ያሁኑን እና የወደፊቱን ኃጢዓት እየወሰደ ነበር ፡፡ ጓደኞቹን ሁሉ የጠየቃቸው ከእርሱ ጋር ነቅተዉ እንዲጠብቁ ነበር (ቁጥር 34) ፡፡ በቁጥር 36 ይመጣ ከነበረዉ ማምለጥ ይችል እንደሆነ ኢየሱስ እየጠየቃቸዉ አልነበረም “ ነገር ግን በእግዚአብሄር እቅድ የሚቻል ከነበር ነበር “ ፤ ኢየሱስ የእግዚአብሄርን እቅድ ለመፈፀም ሌላ መንገድ ከነበረ ኢየሱስ እየጠየቀ ነበር ፡፡ “ ሰዓቲቱ “(ቁጥር 35) የሚገልፀዉ “ በእግዚአብሄር እንደ ተደነገገው የመስዋዕትነት ሞቱን ጊዜን ፤ ተላልፎ ከመሰጠጡ እስከ መከራዉ፣ መዛባበት እና እስከ ስቅለቱ ሁሉንም ነገር ያካትታል ፡፡ “ ( ኢየሱስ “ ሰዓቲቱን “ በአገልግሎቱ ዉስጥ ተጠቅሟታል፡ ዮሐ 2፡ 4; 7፡ 30) ፡፡ ኢየሱስ በዚህ ስዕት ላይ እንድትመጣ እየጠበቀ ነበር እናም አሁን ሌላ መንገድ እንደነበር ጠየቀ (ቁጥር 35) ፤ ይህ ልመና በዕብ (5፡ 7) የተጠቀሰ ነው፡ “ እርሱም በስጋዉ ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸት እና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ እግዚአብሄርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት ፡፡ “ ኣባ ለአባት የሆነ ቃል ነበር ፡፡ እንዲያደርገዉ ተፈልጎ የነበረዉን ምናልባትም ኢየሱስ አልወደደዉም ነገር ግን ተጠይቆ የነበረዉን በፍቃደኝነት አደረገው (ቁጥር 36) ፡፡

ማርቆስ (14፡ 37-43)፡ ኢየሱስ ለመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ጊዜ ተመለሰ የቅርብ ጓደኞቹም ተኝተዉ አገኛቸው ፤ ለአንድ ሰዓት እንኳን ነቅተዉ መጠብቅ አልቻሉም (ቁጥር 37) ፡፡ ኢየሱስም እንደገና እንዲፀልዩ ነገራቸው “ መንፈስ ተዘጋጅታለችና ስጋ ግን ደካማ ነው “ብሎ ነገራቸው (ቁጥር 38) ፡፡ ማክአርቱር ያመለከተው “ ደቀ መዛሙርቱ በፀሎት ለነቁ እና በእግዚአብሄር ለተደገፉ መንፈሳዊ አሸናፊነት እንዲመመጣ እና በራስ መተማመን እና መንፋሳዊ ዝግጁነት ማጣት ወደ መንፈሳዊ ጥፋት እንደሚመራ መማር አስፈለጋቸው ፡፡ “ በጣም በራስ መተማመን በሚኖረን ጊዜ ወደ እግዚአብሄር መመለስ እንደሚያስፈልገን አይሰማንም ወደ መንፈሳዊነት ጥፋት እንቀጥላለን ፡፡

ሁለተኛ ጊዜ ኢየሱስ ፀለየ ለእግዚአብሄር ተመሳሳይ ሀሳብ እያሰማ ከዚያም ቀጥሎ ደቀ መዛሙርቱን ሊፈልግ ተመልሶ መጣ እንደገና ተኝተዋል ፤ ኢየሱስ ሰዎስተኛ ጊዜ ለመፀለይ ሄደ አሁንም እንደገና ደቀ መዛሙርቱ ተኝተዉ አገኛቸው ፡፡ ኢየሱስም “ ሰዓቲቱ ደረሰች እነሆ የሰዉ ልጅ በኃጢዓተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል አላቸው ፡፡” ትንብያዉ እዉነት አልነበረም ፤ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲነቁ እና አሳልፎ የሚሰጠዉን ለማግኘት ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ ነገራቸው (ቁጥር 42) ፤ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እየተናገረ ከአለቃ ካህናቶች፣ ፃፎች እና ሽማግሌዎች ጋር ይሁዳ ደረሰ (ቁጥር 43) ፡፡

መዝጊያ

እንደ ኃያሉ እግዚአብሄር አገልጋዮች እንዴት መፀለይ እና የነቃን እንደምንሆን መማር ያስፈልገናል ፡፡

ቆላ (4፡ 2-4)፡ “ ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ ፤ በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምስጢር እንድንነግር እግዚአብሄር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ ፤ ልናገር እንደሚገባኝ ያህል እገልጠዉ ዘንድ ጸልዩልኝ “ (ሉቃ 11፡ 8; 18፡ 4-5) ፡፡

1ተሰ (5፡ 17)፡ “ ሳታቋርጡ ፀልዩ “ (NASB 1995) ፡፡

ሮሜ (13፡ 11)፡ “ ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና ፡፡ “

እንዴት እንዘጋጅ ? ነቅቶ በመጠበቅ እና በፀሎት !

  1. Rodney Cooper, Holman New Testament Commentary: Mark (Nashville: Broadman & Holman Publishers, 2000), Kindle location 5580.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1252.

  3. MacArthur, p. 1252.

  4. MacArthur, p. 1252.

  5. MacArthur, p. 1252.

  6. MacArthur, p. 1252

ጥያቄዎች

  1. በቁጥር (3-5) ደቀ መዛሙርቱ በጣም አበሳጭቷቸዉ ነበር ? በዚህ ጊዜ በእዉነት ኢየሱስ ማን እንደ ነበር ለማየት አሁንም እንደወደቁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሳበቻሁም ?
  2. በቁጥር (27-31) ጴጥሮስ ኢየሱስን ለሞት እንኳን እንደ ማይክደዉ ተናገረ ፤ ጴጥሮስ ቃሉን መጠበቅ ያልቻለዉ ለምን ነበር ? ይህ ያደረጋችሁት እና የምትጠብቁት ቃል ነው ? ለምን ወይስ ለምን አይደለም ?
  3. ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብን እና ዮሐንስ ከእርሱ ጋር በጌቴሴማኒ እንደነበሩ ነቅተዉ እንዲጠብቁ ለምን ጠየቃቸው ? (ማር 14፡ 32-41)
  4. በማርቆስ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 14:38

“Stay awake and pray so that you won’t enter into temptation. The spirit is willing, but the flesh is weak.”

ኢየሱስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ሥፍራ ወደ አባቱ ፀለየ፡፡ ደቀመዛሙርቱ በቅርብ ተቀምጠው እንዲፀልዩ ነገራቸው፡፡ ሶስት ጊዜ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ተኝተው አገኛቸው፡፡ ሶስቱንም ጊዜ ጠየቃቸው፥ " ልትነቁ አትችሉምን?"

የክርስቶስን መምጣት ስትጠባበቁ፥ ለፀሎት ራሳችሁን በመስጠት በንቃት ቁሙ፡፡ ኢየሱስ መንፈስ እንደተዘጋጀ፥ ሥጋ ግን ደካማ እንደሆነ አስጠንቅቋል፡፡ ሲለዚህ፥ መፀለይ መቀጠል አለባችሁ፡፡ ቀላል ይመስላል፥ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ እንቅልፍ ወስዷቸው፥ ለአንድ ሰአት እንኳን መንቃት አልቻሉም፡፡ መምጣቱን እንደሚጠብቅ የክርስቶስ ተከታይ፥ የፀሎት ህይወታችሁ እንዴት ነው? በፀሎት ጊዜ አሳልፉ እና ለቀኑ እንዴት ብርታት እንደምታገኙ ተመልከቱ፡፡

“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩም፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፥ ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።”

—ማርቆስ 14:38

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ሮሜ 13:11 — “ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።”
  • ቆላስይስ 4:2 — “ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ ”
  • 1ኛ ተሰሎንቄ 5:17 — “ሳታቋርጡ ጸልዩ ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 42