The Gospels Mark

Jesus is Crucified and Buried

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Servant Mark 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 153 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በማርቆስ 14 በጌቴሴማኒ አትክልት ስፍራ ለደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ሁለት ቃላት ነበሩት፡ “ ነቅታችሁ ጠብቁ “ ሰዎስት ጊዜ ኢየሱስ ይህን አላቸው በሰዎስተኛዉ ጊዜ ላይ ኢየሱስ “ ተላልፌ እሰጣለሁ አላቸው “ ፤ ከዚያም ይሁዳ በጌቴሴማኒ ስፍራ ታየ ኢየሱስ ለባለስልጣኖቹ እጅ ላይ ተያዘ ፡፡

ትምህርት

ማርቆስ (15፡ 1-5)፡ ወዲያዉኑ እንደነጋ አለቃ ካህናቶች፣ ሽማግሌዎች፣ ፃፎች እና ሁሉም አማካሪዎች የኢየሱስን እጆች አስረዉ ለጲላጦስ ሰጡት ፤ ጲላጦስ ኢየሱስን የአይሁድ ንጉስ እንደ ነበር በጠየቀዉ ጊዜ ኢየሱስም “ አንተ አልክ “ ብሎ መለሰለት (ማቴ 26፡ 25) ፡፡ የካህናት አለቆች በብዙ ነገሮች ኢየሱስን መክሰስ እንደቀጠሉ ሌላ ምንም አላለም፡፡

ማርቆስ (15፡ 6-15)፡ በበዓሉ ላይ የጲላጦስ ልምድ አንድ እስረኛ መልቀቅ ነበር ፤ ወደ ሁለት ምርጫዎች መጣ፡ ኢየሱስ ወይም በርባን ፡፡ ህዝቡ በርባንን እንዲለቅላቸዉ መረጡ ፤ ከለቀቀላቸዉ በኋላ ጲላጦስ “ እንግዲህ የአይሁድ ንጉስ የምትሉትን ምን ላደርገዉ ትወዳላችሁ ? “ብሎ ጠየቃቸው ህዝቡም እየጮሁ “ ስቀለዉ !” ለምን እንደሆነ ጲላጦስ ማወቅ ፈለገ ነገር ግን “ ስቀለዉ “ እያሉ እንደገና ጮሁ ህዝቡን ለማስደሰት ጲላጦስ ኢየሱስን ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠዉ ፡፡

ማርቆስ (15፡ 16-20)፡ ሰዎስት ጊዜ ኢየሱስ እንደ ሚገደል፣ እንደ ሚቀበር እና እንደ ሚነሳ አመልክቶ ነበር ፤ በሂደቱ ይንጓጠጣል(ይዘለፋል)፣ ይገረፋል እናም በላዩም ላይ ይተፋበታል ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ያለውን የሚደርስበትን ችግር መንገዱን የተመለከተዉን ሁሉንም ትንቢቶች ኢየሱስ እንደኖራቸዉ ያረጋግጣሉ ፡፡

ማርቆስ (15፡ 21-32)፡ እነዚህ ቁጥሮች እዉነተኛዉን የኢየሱስን ስቅለት መዝግበዋል ፡፡

ማርቆስ (15፡ 33-41)፡ ቀትር በነበር ጊዜ በመላዉ ምድር ላይ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ጨለማ መጣ ፤ ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ነበር ሞተም ፤ ማር (10፡ 45) ይህ የኢየሱስ ጎል እንደነበር ያለዉን ያስታዉሳል ፤ “ እንዲሁ የሰዉ ልጁ እንዲያገለግሉት አልመጣም ሊያገለግል እንጂ “ ፡፡ ኢየሱስ እንደ ቤዛ ለብዙዎች ህይወቱን በመስጠት አገለገለ ፡፡ ኢየሱስ የመጨረሻዉን ድምፅ እንዳወጣ ህዝቡ ምንድን እንደሆነ ለመረዳት ሞከሩ ፡፡

ማርቆስ (15፡ 42-43)፡ አሁን ኢየሱስ ሞቶ ነበር በሞቱ እና በትንሳኤዉ መሀከል አስፈላጊዉ ግንኙነት መቀበሩ ነበር ፡፡ ስቅለቱ አርብ ላይ ተካሄደ ለዚያ ነዉ የስዕለት ዕለት የምንለዉ ፡፡ አሁን ምሽት ነበር ስለዚህ ሰንበት ተጀምሮ ነበር ፤ የአርማትያስ ዮሴፍ በድፍረት ጴላጦስን ስለ ኢየሱስ አካል ጠየቀዉ ፡፡ አርማትያስ ከኢየሩሳሌም ሰሜን ምዕራብ 20 ማይል ያክል ላይ የምትገኝ ከተማ ነበረች ፡፡ ዮሴፍ በጣም የሚታወቅ የአማካሪ አባል ነበር ኢየሱስን ለማስወገድ በመፈለጉም ይታወቅ ነበር ፡፡

የካህናት አለቆች፣ ስማግሌዎች፣ ፃፎች እና ሁሉም ፈራጆች ኢየሱስን ወዳሰሩበትና ወደ ጲላጦስ አሳልፈዉ ወደሰጡበት ወደ ማር (15፡ 1) ስንመለስ ፤ ዮሴፍ የዚህ አካል ነበር ? ዮሐ (19፡ 38) ዮሴፍ “ አይሁዶችን በመፍራት በድብቅ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደ ነበር ይገልጣል ፡፡ “ ሉቃ (23፡ 50-51) የሚለው ዮሴፍ በኢየሱስ ላይ የአማካሪዎቹን እቅድ ተስማምቶ ያልነበር ፃድቅ ሰዉ ነበር ፡፡ መፅሀፍ ሁልጊዜ ዮሴፍ ወደ እግዚአብሄር መንግስት እንደተመለከተ ይናገራል ፤ ለምን ነበር ይህ ያስፈለገው ? ኢየሱስን በመቅረብ ይህን ድርጊቱን ያሳያል ፡፡ እንደ ኢየሱስ ድብቅ ደቀ መዛሙርት በአማካሪዎቹ ድርጊት ያልተስማማው በድፍረት ጲላጦስን በመቅረብ ስለ ኢየሱስ አካል ጠየቀው ፤ ይህ ፈጣን ድፍረት ወስዷል ምክንያቱም ወደ ጲላጦስ መሄዱ ከተሰቀለዉ ኢየሱስ ጋር የጠበቀ ትስስር እንደ ነበረው ያመለክታል ፡፡ ዮሴፍ “ ራሱን በመካድ መስቀሉን ተሸክሞ ኢየሱስን ለመከተል “ ፍቃደኛ ነበር (ማር 8፡ 34) ፤ ዮሴፍ ከኢየሱስ ጋር የተለየ መሆን ፍቃደኛ ነበር እንዲሁም የኢየሱስን አካል በመቀበል ለመሞት ፍቃደኛ ነበር ፡፡

ማርቆስ (15፡ 44-45)፡ ኢየሱስ ቶሎ በመሞቱ ጲላጦስ ተገረመ ፤ ጲላጦስ መቶ አለቃዉን ኢየሱስ እንደ ሞተ ቶሎ እንደ ሞተ ጠየቀው ምክንያቱም ስቅለት ረጅም፣ በጣም ከባድ እና አስቸጋሪ ሂደት ስለ ነበር ፡፡ ጲላጦስ በድንኑን(ሬሳዉን) ለዮሴፍ ሰጠው (ይህ የኢየሱስ አካል እንደ ሬሳ የተገለፀበት ብቸኛዉ ጊዜ ነው) ፡፡ ወሴል አንድ ሰዉ ሀገር በመክዳት ከተፈረደበት ሬሳው ለቅርብ ዘመድ እንጂ ለሌላ ለማንም መስጠት ያልተለመደ እንደ ነበር ተናግሯል ፤ ምናልባትም ኢየሱስ ሀገርን በመክዳት ጥፋተኛ እንዳልነበር ጲላጦስ አዉቋል ስለዚህ ሰዉነቱን ለዮሴፍ ሰጠው ፡፡ ጲላጦስ በእዉነት ኢየሱስ ማን እንደ ነበር አውቋል ፡፡

ማርቆስ (15፡ 46)፡ ዮሴፍ ኢየሱስን ከመስቀሉ ላይ አዉርዶ በመዉሰድ ሰዉነቱን በበፍታ በመሸፈን በአለት ዉስጥ በተቆረጠ መቃብር ዉስጥ አስቀመጠው ፤ ከዚያም ዮሴፍ ደጃፉን ለመሸፈን በቦታዉ ድንጋይ አንከባለለበት ፡፡ የመቃብሩ አትክልት ስራ በልማድ ኢየሱስ ተቀብሮበት ነበር የሚለዉ ከሁለቱ አንዱ ስፍራ ነው ፤ መቃብሩ በዉስጥ ሁለት ክፍሎች አሉት ፤ የኢየሱስ አካል በዉስጠኛዉ ክፍል ተቀምጦ ነበር ፡፡

ዮሐ (19፡ 38-42) ኒቆድሞስም የመማክርቱ አባል በመቅበሩ ዮሴፍን እንደረዳዉ ይናገራል ፤ (በዮሐ 3፡ 1-2 ኒቆድሞስ በምሽት ከኢየሱስ ጋር ተገናኝቶ ነበር) ፡፡ ኒቆድሞስ 70ፓዉንድ ያክል ከርቤ እና እሬት አመጣ ፤ እንደ አይሁድ ልማድም በተልባ እፍታ ልብስ ከሽቶ ጋር የኢየሱስን አካል ሸፈኑት ፤ እስካሁን ማንም ተቀምጦበት በማያዉቀዉ በአትክልቱ ስፍራ በመቃብ ሰዉነቱን አስቀመጡት ፡፡

ይህ ዮሴፍ እንደ ኢየሱስ ተከታይ ራሱን የገለጠበት ምናልባትም የመጀመሪያዉ ጊዜ ነበር ፡፡ በዮሐ (7፡ 45-50) ኒቆድሞስ የካህናት አለቆች እና ፈሪሳዉያን የመቅደስ ፖሊሶች ለምን ኢየሱስን እንዳላሰሩት ለማወቅ በፈለጉ ጊዜ ኢየሱስን ተከላከለለት ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው “ እነዚህ ሁለት ሰዎች ወዲያዉኑ ኢየሱስን ለመቅበር እንደ ወሰኑ ማሰብ የለብንም ምክንያቱም በብዙ ዝግጅት ያስፈለገዉን አድርገዋል “ ፤ እነዚህ ሁለት ሰዎች በመፅሀፍት ትንቢቶችን ያጠኑ እንደ ነበር እና “ በመንፈስ በመመራት “ ኢየሱስ ፋሲካ ላይ እንደሚሞት ማስላታቸዉን ያመለክታል ፡፡

ኢሳያስ መሲሁ በሀብታም ሰዉ መቃብር እንደሚቀበር ተንብያል ፤ አንዳንዶች ትንቢቱን በመከተል አጥብቀዉ ይዘዋል ፡፡ ዮሴፍ እና ኒቆድሞስ ይህን አደረጉ ምክንያቱም “ የእግዚአብሄርን መንግስት እየተመለከቱ ነበር “ ኢሳ (53፡ 9)ም አጥንተዉ ስለ ነበር የዚህ አካል መሆንን መረጡ ፡፡ የቀኑን የቀብር ልምድ ፈፀሙ ፤ አካሉ ታጥቧል፣ በቅመም ተቀብቷል (ኒቆድሞስ ባመጣው)፣ በልብስ ተሸፍኗል እንዲሁም በቀብር ቫንዴጅ ተጠምጥሟል እናም ፊቱ በተለየ ልብስ ተሸፍኗል ፡፡ ዮሴፍ እና ኒቆድሞስ እዚያ ቦታ ላይ የሞተዉን አካሉን አገለገሉ ፡፡

ማርቆስ (15፡ 47)፡ የኢየሱስ እናት ማሪያም እና መቅደላዊት ማሪያም የኢየሱስ አካል የት ተቀምጦ እንደ ነበር ተመለከቱ ፤ በአገልግሎቱ ሰዉነቱን ለመቀባት ዘይት እና ሽቶ በማዘጋጀት ኢየሱስን ደግፈዉት የነበሩት ሴቶች ከሰንበት በኋላ አልቆ ነበር ፤ ሰዉነቱ አልነበረም ነገር ግን በማዘጋጀት ዝግጁ አድርገዉት ነበር ፡፡

ከዚህ ሀሳብ ኢየሱስን ስለ ማገልገል ምንድን ልንማር እንችላለን ?

  1. አገልጋዮቹ የተዘጋጁ ነበሩ ፤ ወደ ፊት ወደ እግዚአብሄር መንግስት ተመለከቱ ፡፡ አንድ ቲዎሪ (ያልተረጋገጠ) አማካሪዉ የኢየሱስን ስቅለት በፈለገ ጊዜ በዚያን ጊዜ በመቃብሩ እንደ ተደበቁ ነበር ፡፡
  2. ቃሉን ያዉቁታል ፤ በብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ለምደዉ የነበሩ እና በኢየሱስ ሞት ሲፈፀሙ አይተዋል ፡፡
  3. ደፋር ነበሩ ፡፡
  4. መስዋዕትነትን አድርገዋል ፤ ራሳቸዉን ለመካድ፣ መስቀላቸዉን ለመሸከም እና ኢየሱስን ለመከተል ፍቃደኞች ነበሩ ፡፡
  5. መልካም ባላደራነትን ተለማምደዋል ፤ ዮሴፍ እና ኒቆድሞስ በቁሳዊ ንብረታቸው መልካም ባላደራ ነበሩ ፡፡
  6. የተሟላ(ራዲካል) እምነት ነበራቸው ፡፡

ዮሴፍ እና ኒቆድሞስ የኢየሱስን የሞተ አካል በመቅረብ ወደ ፊት የእግዚአብሄርን መንግስት ተመለከቱ ምክንያቱም እንደ ገና ወደ መኖር ይመጣ እንደ ነበር ስለ አመኑ ፡፡

መግቢያ

ለንጉሱ መምጣት ለማዘጋጀት በንብረታችን መልካም ባላደራ መሆን ያስፈልገናል ፡፡

  1. Walter W. Wessel, “Mark.” In The Expositor’s Bible Commentary: Matthew–Luke, v. 8, ed. Frank E. Gaebelein and J. D. Douglas (Grand Rapids: Zondervan Publishing House, 1984), p. 784.

  2. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 134.

  3. Wiersbe, p. 134.

ጥያቄዎች

  1. በማር (15፡ 2-3) ኢየሱስ ለጲላጦስ ጥያቄ መለሰለት ከዚያም የካህናት አለቆች በብዙ ነገሮች ከሰሱት ፤ ጥቂቶቹ ከሰዉት የነበሩበት ነገሮች ምንድን ነበሩ ? (ማር 14፡ 58, 64; ሉቃ 23፡ 2, 5; ዮሐ 19፡ 7)
  2. ጲላጦስ የካህናት አለቆች ኢየሱስን ለእርሱ አሳልፈዉ የሰጡት ቀንተዉ እንደሆነ ያውቃል ፤ ቅናታቸዉ ስለ ምን ነበር ?
  3. የካህናት አለቆች ህዝቡ ወደ በርባን ምርጫ እንዲሄዱ ተፅዕኗቸዉን ተጠቀሙበት ፤ በኢየሱስ ወደ እምነት እንዲሄዱ ሰዎችን ተፅዕኗችሁን ትጠቀማላችሁ ?
  4. በማር (10፡ 34) ኢየሱስ 12ቱን እንደ ሚዘባበቱበት፣ እንደሚተፉበት፣ እነደ ሚመቱት(እንደ ሚገርፉት) እና እንደ ሚገድሉት ነገራቸው ፤ በማርቆስ 15 መሰረት እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሆነዋል ? እንደ ሚያደርጉት ኢየሱስ እንዴት አወቀ ?
  5. በቀኑ በምንድን ጊዜ ላይ ነበር ኢየሱስ የተሰቀለው ? በምንድን ጊዜ ላይ ሞተ ? በመስቀሉ ላይ ምን ያክል ጊዜ ተሰቃየ ? ይህንን መሰቃየት እንደ ታላቅ ፍቅር ድርጊት እንዴት ታዩታላችሁ ?
  6. በማርቆስ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Mark 15:31-32

“In the same way, the chief priests with the scribes were mocking Him to one another and saying, ‘He saved others; He cannot save Himself! Let the Messiah, the King of Israel, come down now from the cross, so that we may see and believe.’ Even those who were crucified with Him were taunting Him.”

ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት አካላዊ ሥቃይን ብቻ ሳይሆን ስሜታዊ ሥቃይን ተጋፍጧል፡፡ ሰዎች እያለፉ ሰደቡት፥ የካህናት አለቆች ከጻፎች ጋር ዘበቱበት፥ ከአጠገቡ የተሰቀለ ወንጀለኛ እንኳ ሳይቀር ተሳለቀበት፡፡ እስከ መስቀል ሞቱ ድረስ ኢየሱስ ሁሉን ታገሰ፡፡

እንደ ክርስቶስ ተከታይ፥ ስለእምነታችሁ መሰደድ ይመጣል፡፡ በእንደዚህ አይነት ባህል ውስጥ ለጌታ በድፍረት ስትኖሩ፥ ለስድብ፣ ለዘበት እና ለማላገጥ ተዘጋጁ፡፡ ኢየሱስ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ሥቃዩን ከአባቱ በተቀበለው ተልዕኮ ላይ በማተኮር ተቋቋመው፡፡ አንዳንዴ ስሜታዊ ሥቃይ ከአካላዊ ሥቃይ በላይ ያማል፡፡ ሰዎች፥ በመከራ፣ በሥቃይ እና በስደት በማለፍ ውስጥ እንኳን ቢሆንም፥ በውስጣችሁ ያለውን ኢየሱስን የሚያውቁበት ህይወትን መኖር ይሁንላችሁ፡፡ በዚያን ጊዜም፥ በርቱ- ኢየሱስ አለምን አሸንፏል!

“እንዲሁም የካህናት አለቆች ደግሞ ከጻፎች ጋር እርስ በርሳቸው እየተዘባበቱ፦ ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር። ”

— ማርቆስ 15:31-32

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ዮሐንስ 15:18 — “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ። ”
  • ዮሐንስ 16:33 — “በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ። ”
  • 2ኛ ጢሞቴዎስ 3:12 — “በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 43