ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ማርቆስ 16 የማርቆስ ወንጌል የመጨረሻዉ ምዕራፍ ነው ፡፡ ትናትና ማርቆስ 15 ዮሴፍ እና ኒቆድሞስ ለቀብር የኢየሱስን አካል አዘጋጁ ፤ የሞተ አዳኝ መልካም አይሁን እንጂ እንደማንኛዉም ሰዉ የተለመደ ይሆናል ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ከዚያ የሚበልጥ ነው ፡፡ ሮሜ (4፡ 25) የሚናገረው ኢየሱስ ስለ ሀጢዓታችን አልፎ ተሰጠ ነገር ግን ስለ ፅድቃችን ተነሳ ፡፡ በ 1ቆሮ (15፡ 1-8) ጳዉሎስ ወንጌል አብራርቷል ፤ ኢየሱስ ለኃጢዓትችን ሞተ፣ ተቀበረ እንዲሁም መፅሀፍት እንዳሉት ከሞት ተነሳ ፡፡
ዛሬ ከትንሳኤ በኋላ ስለ ኢየሱስ መልክ እናወራለን ፡፡ ኢየሱስ ለብዙ ሰዎች ተገለጠ (1ቆሮ 15፡ 5-8) ፡፡ ለማርቆስ አንድ ቃላችን አገልጋይ የሚለዉ ቃል ነው ፤ በመጀመሪያዎች 13 ምዕራፎች ኢየሱስ ስላገለገለብን መንገዶች አዉርተናል ፤ በመቀጠል ኢየሱስን ደቀ መዛሙርቱ ስላገለገሉበት መንገዶች አዉርተናል ፤ በማርቆስ 14 በጌቴሴማኔ አትክልት ስፍራ ከኢየሱስ ጋር እያሉ ነቅተዉ ቆይተዉ እና ፀልየዋል ፤ በማርቆስ 15 ኢየሱስ ከተሰቀለ በኋላ ዮሴፍ እና ኒቆድሞስ አካሉን ቀበሩት ፡፡
ሮህዳስ እና ማይካ “ በኢየሩሳሌም በመጨረሻ ሁኔታ ተግሳፁ በተለየ ምሳሌ የሚሆኑ ጥቂት ሰዎች የሁሉም አገልጋይ መሆን እንደሆነ “ ተናግረዋል ፤ ቀድሞ ኢየሱስ ሌሎችን አገልግሏል ፤ አሁን በሚያስፈልገዉ ጊዜ ሌሎች አገልግለዉታል ፡፡ ለምፃሙ ስምዖን ኢየሱስን በቤቱ ተቀብሏል ፤ አንዲት ሴት የአመት ክፍያዋ ዋጋ በሚገመት ቅባት ቀባችዉ ፤ የቀሬናው ስምዖን መስቀሉን ተሸከመለት ፤ ዮሴፍ ከመስቀሉ ላይ አካሉን በመዉሰድ ቀበረዉ ፤ ከሞቱ በኋላ ኢየሱስን ሊቀቡ የሴቶች ቡድን ወደ መቃብሩ ሄዱ ፡፡ እነዚህ የአገልግሎት ድርጊቶች በድፍረት የሰዉትን እና ነገራቸዉን ችግር ዉስጥ ባስገቡ - ገንዘባቸዉን፣ እስራትን፣ ዝናቸዉን - እነዚህን በሚሸከሙ ሰዎች ለኢየሱስ ተደረገ፡፡ እነዚህ ጥቂት ሰዎች ኢየሱስን አገለገሉት ምክንያቱም ኢየሱስ እንዴት እንዳገለገላቸዉ አይተዋል ፡፡
ትምህርት
ማርቆስ(16፡ 1)፡ ሰንበት ባበቃ ጊዜ ሴቶቹ የኢየሱስን አካል ለመቀባት ሽቶ ወሰዱ ፤ የሞተዉን አካል ለማገልገል ዝግጁ ነበሩ ፡፡
ማርቆስ (16፡ 2-3)፡ ፀሀይ መዉጫ ላይ(በማለዳ) ወደ መቃብሩ ሄዱ ሁሉም ከመቃብሩ ደጃፍ ላይ ድንጋዩን ማን እንደ ሚያከባልልላቸዉ እየተነጋገሩ ፤ ድንጋዩን ለማንቀሳቀስ በቂ ጥንካሬ አልነበራቸዉም ፡፡ ስለ ሮማዉያን ወታደሮች እያሰቡ አልነበረም የኢየሱስን አካል ስለ መጠበቅ እንጂ ፡፡ ማቴ (27፡ 62-66) የሮማዉያን ወታደሮች መቃብሩን ለምን እንደሚጠብቁ ይገልፃል ፤ ፈሪሳዉያን መቃብሩ እንዲጠበቅ ጲላጦስን ጠይቀዉት ስለነበር ምክንያቱም “ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ ከሰዎስት ቀን በኃላ እነሳለሁ ስላለ ፡፡ “ ደቀ መዛሙርቱ አካሉን መስረቅ እንደ ማይችሉ እና ቀጥሎም ኢየሱስ ከሞት ተነስቶ እንደ ነበር እንዳይሉ እርግጠኛ መሆን ፈለጉ ፤ ስለዚህ ጲላጦስ መቃብሩን በማሸግ በፊቱ ጥበቃዎችን አስቀመጣ ፡፡
ማርቆስ (16፡ 4-5)፡ የመጀመሪያ አስደናቂ፡ ድንጋዩ በሩቅ ተንከባሎ ነበር ፤ ሁለተኛዉ አስደናቂ፡ ሴቶቹ ወደ መቃብሩ በመግባት ተደነቁ በነጭ ልብስ የተጎናፀፈ አንድ ወጣት ሰዉ (መልዓክት) ባዩ ጊዜ ደነገጡ ፤ ሉቃ (24፡ 4) የሚለው “ በሚያንፀባርቁ ልብሶች በአጠገባቸዉ ቆሙ ፡፡ “
ማርቆስ (16፡ 6)፡ ሰዎስተኛዉ አስደናቂ፡ መልዓኩ ኢየሱስ ከሞት የመነሳት መልዕክቱን አደረሳቸው ፤ ሴቶቹ ይህን መልዕክት ለመስማት ጠብቀዋል ? አልጠበቁም ፤ እንዴት እናዉቃለን ? የቀብሩን ልምድ ለማሟላት ሽቶ ወስደዉ ነበር ፤ የኢየሱስ ሙት አካል አሁንም በመቃብሩ ዉስጥ እንደሚሆን መሉ ግምት ነበራቸው ፡፡
ማርቆስ (16፡ 7-8)፡ መልዓኩ ሴቶቹን ኢየሱስ ወደ ገሊላ ከእነርሱ ቀድሞ እንደሚሄድ ሄደዉ ለኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እና ለጴጥሮስ እንዲነግሯቸዉ ነገራቸው ፡፡ ከሞቱ በፊት ከትንሳኤዉ በኋላ በገሊላ እንደሚያገኛቸዉ ነግሯቸዉ ነበር (ማር 14፡ 27-28) ፤ ስለዚህ ሴቶቹ ከመቃብሩ ሮጡ ፡፡ ማርቆስ በመጀመሪያ ፈርተዉ ስለነበር ማንም እንደሌለ ተናግረዋል ፡፡
ማርቆስ (16፡ 9-10)፡ ይህንን ሀሳብ ከዮሐንስ 20 ጋር በማወዳደር ሴቶቹ ለጴጥሮስ እና ለዮሐንስ ለመናገር ሮጡ ከዚያም በመቀጠል ተመልሰዉ ወደ መቃብሩ መሮጣቸዉን እንማራለን ፤ መቃብሩ ላይ ኢየሱስ ለመቅደላዊት ማሪያም ተገለጠላት ምክንያቱም ሌሎቹ ሴቶች ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲሮጡ በዚያዉ ቆይታ ስለ ነበር ፡፡ ኢየሱስ የተገለጠለት የመጀመሪያዉ ሰዉ ማን ነበር ? አንድ ሴት ፤ ከዚያም መቅደላዊት ማሪያም እያዘኑ እና እያለቀሱ ለነበሩት ደቀ መዛሙርት ሪፖርት አደረገች ፡፡ በሌለኛዉ ወንጌል የሚለው ኢየሱስ ለሌለኛዋ ሴት ተገለጠላት (ማቴ 28፡ 9) ፤ ሉቃ (24፡ 34) የሚለው ኢየሱስ ለጴጥሮስ ተገለጠ ፤ ከ40 ቀናት በላይ በሆነዉ ትምህርት ኢየሱስ ለብዙ ሰዎች ተገለጠ ፡፡
ማርቆስ (16፡ 11-13)፡ ደቀ መዛሙርቱ የመቅደላዊት ማሪያም ሪፖርትን አላመኑም ፤ ከዚያም ኢየሱስ በሀገሪቱ ሲጓዙ “ከእነርሱ ለሁለቱ በተለየ መልኩ “ ተገለጠላቸው ፤ ይህ ኢየሱስ ከሁለቱ አማኞች ጋር በኤማሆስ መንገድ ላይ በሚያወራ ጊዜ ነበር በይበልጥ በሉቃ (24፡ 13-22) ተሸፍኗል ፡፡ እነዚህ አማኞች ይህን ለደቀ መዛሙርቱ ሪፖርት አደረጉ ነገር ግን አንድም ይህን መጋለጫ አላመኑዓቸዉም ፡፡
ማርቆስ (16፡ 14)፡ በኋላም ኢየሱስ ለ 11 ተገለጠ ፤ እዚህ ላይ ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ከሰጠዉ በኋላ ራሱን አጥፍቶ ነበር እናም እስካሁን ማቲያስን አልጨመሩትም ነበር ፡፡ ኢየሱስ የልብቻዉን ድንዳኔ እና አለማመን ገሰፀ ፤ ከትንሳኤ በኋላ አይተዉት የነበሩት ምን ያክል ጊዜ ለማመን እምቢ(ገፍተዉ) ብለዉ ነበር ? ይህ ክስተት እንደሚሆን ምን ያክል ጊዜ ኢየሱስ ነግሯቸዋል ? ኢየሱስ የሰዉ ልጅ መከራ እንደሚገጥመዉ…እና ከዚያም እንደ ገና እንደ ሚነሳ ነግሯቸዋል ፡፡ መልዕክቱ በመቀበሩ አላቆመም ፤ በማር (9፡ 31) ምንድን እንደሚሆን ኢየሱስ ለሁለተኛ ጊዜ ነገራቸው ፡፡ ማር (10፡ 32-33) ኢየሱስ ለሰዎስተኛ ጊዜ እርሱ ላይ ምን እንደ ሚሆን የነገራቸዉን መዝግቧል ፡፡ መቅደላዊት ማሪያም ኢየሱስን እንዳየችዉ ሪፖርት ብታደርግም ሊያምኗት አልፈለጉም ፡፡
ትንሳኤዉ እንዲያሰምጣችሁ(እንዲገባችሁ) የማትፈቅዱ ከሆነ በክርስቶስ ለሆንን ሞቱ እና መቀበሩ ትርጉም የለዉም ፤ ሁሉንም የኃጢዓት ክብደት የቀድሞዉን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱን አሸንፎታል ፡፡ በገላቲያ 3 መሰረት የህግን እርግማን ተሸክሞ አስወገደ ፤ ይህ ሁሉ በተንሳኤዉ በኩል ተወገደ ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ እግዚአብሄር ነግሯቸዉ የነበረዉን ረሰተዉት ነበር ፡፡
ማርቆስ (16፡ 15-16)፡ ኢየሱስም እንዲህ አላቸዉ “ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ “ ፤ ይህ አይሁድን እና አሕዛብን ያካትታል ፡፡ ሁሉም ሰዉ ኢየሱስ እንደ ሞተ፣ እንደ ተቀበረ እና ወደ ህይወት እንደ ተመለሰ መስማት ያስፈልጋቸዋል ፤ ኢየሱስም ደግሞ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል አላቸው፡፡ “ ገለፃዉ በእምነት ላይ እንጂ ትምቀት ላይ አይደለም ምክንያቱም ያላመኑት ይፈረድባቸዋል ( ያልተጠመቁት አይደሉም ) ፤ ድነት በእምነት በኩል ይመጣል ፡፡ ጥምቀት በኢየሱስ ሞት፣ መቀብር እና መነሳት ዉስጣዊ እምነታችሁን በዉጪ የመግለጫ አስደናቂ መንገድ ነው ፡፡ ኢየሱስን የማገልገያ ምርጡ መንገድ በመሄድ ለሆነ አካል ወንጌሉን መናገር ነው ፡፡
ማርቆስ (16፡ 17-18)፡ ኢየሱስ የሚያምኑትን የሚከተሉዓቸዉን ጥቂት ምልክቶችን ገልፃል ፤ አጋንንትን ያስወጣሉ በአድስ ቋንቋ ይናገራሉ (ወደ ቀጣዮቹ ሁለቱ ተመልሰን እንመጣለን) ፡፡ ጤነኛ እንዲሆኑ በታመመ ላይ እጆቻቸዉን ያስቀምጣሉ (ቁጥር 18) ፡፡ እንዚህ ነገሮች ሲሆኑ ለማየት መንፈስ ቅዱስ በእኛ ዉስጥ መንቀሳቀስ ይፈልጋል ፤ ቁጥር 18 ደግሞ እባቦችን ስለ መያዝ ይገልፃል ፤ ይህ እባቦችን አትኩረን እንሄዳለን ማለት አይደለም (ማቴ 4፡ 7 እግዚአብሄርን አትፈትኑ ይላል ) ፤ ነገር ግን ወንጌልን እያካፈላችሁ እንዳለ እና በሆነ ምክንያት እባብ ስትይዙ አትጨነቁ አይጎዳችሁም ፡፡ የሚገድል መጠጥ ብትጠጡም አይጎዳችሁም ፡፡ የእግዚአብሄርን መንግስት በማስቀደም ስትቀጥሉ የኢየሱስ ሞትን፣ የመቀበሩን እና የመነሳቱን መልዕክት በመናገር ደህና(ሰላም) ትሆናላችሁ ፡፡
ማርቆስ (16፡ 19-20)፡ ለእነርሱ ከተናገራቸዉ በኋላ ወደ ሰማይ በማረግ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ ፤ ኢየሱስ በታዓምራታዊ መንገድ በመቃብር አልቆየም ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በመሄድ የኢየሱስን ሞት፣ መቀበር እና ትንሳኤ መልዕክት በሁሉም ቦታ ሰበኩ ፤ ኢየሱስ ህያዉ ነው ! ጌታ ከእነርሱ ጋር በመስራት ቃሎቻቸዉን በተገለፁት በሚከተሉዓቸው ምልክቶች አረጋገጠላቸው ፡፡
መዝጊያ
ታላቁ ተልዕኮ በማቴ (28፡ 18-20)፣ ማር (16፡ 15-18)፣ ሉቃ (24)፣ ዮሐ 20 እና ሐዋ 1 ላይ የሚገኝ ነው ፡፡ የኢየሱስ አግልጋዮች ኢየሱስ በሞት፣ በመቀበር እና በትንሳኤ ዉስጥ እንዳለፈ መረዳት በጀመሩ ጊዜ ከዚያን በኋላ መልካሙን ዜና መያዝ አይችሉም ፡፡ ከዚህህ በኋላ ይህን መልካም ዜና መያዝ አንችልም ክርስቶስ ማን እንደሆነ ለመስበክ እንሄዳለን ፡፡ ለእናንተ ምሞግታችሁ ይህን ነው፡ ከዚህ በኋላ ዝም ብላችሁ አትቀመጡ -ሄዳችሁ ሰዎችን ህያዉ እንደሆነ ተናገሩ !
David Rhoads, Joanna Dewey, and Donald Michie, Mark as Story (Minneapolis: Fortress Press, 1999), p. 132.
ጥያቄዎች
-
በመቃብሩ መልዓክቱ በተለየ ጴጥሮስን ለምን እንደ ጠቀሰዉ ምን ታስባላችሁ ?
-
በማር (14፡ 28) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከተነሳ በኋላ ከእነርሱ ቀድሞ ወደ ገሊላ እንደሚሄድ ነግሯቸዋል ፤ ለምን ገሊላን እንደ መረጠ ምን ታስባላችሁ ? ከደቀ መዛሙርቱ ዉስጥ አንዳቸዉ ከሞት እንደ ሚነሳ የጠበቀ ነበር ?
-
ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ህያዉ እንደ ነበር ከብዙ ምንጮች ሪፖርት ቢሰሙም አላመኗቸዉ ፤ ኢየሱስ የዘለፈባቸዉ(የተቸባቸው) ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው ? ልባቸዉ ለምን ጠንክሮ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? አስቸጋሪ ጊዜ በመጣ ጊዜ ከጠነከረ ልብ ጋር ትታገላላችሁ ?
-
የሚያምኑትን ከሚከተሉዓቸዉ ምልክቶች አንዱ እባቦችን መያዝ እንደሚችሉ እና እንደ ማይጎዳቸዉ ነው ፤ በአዲስ ኪዳን ይህን ሀሳብ የት ታነቡታላችሁ (ሐዋ 28፡ 3-6) ? ይህ ምልክት ከዘፍጥረት 3 በእባብ ላይ ስላለን ስልጣን ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ታስባላችሁ ? (ራዕ 12፡ 9-11)
-
በማርቆስ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Mark 16:8
“So they went out and started running from the tomb, because trembling and astonishment overwhelmed them. And they said nothing to anyone, since they were afraid.”
የኢየሱስን አካል ሽቱ ለመቀባት ሴቶች ወደ ኢየሱስ መቃብር በማለዳ ደረሱ፡፡ የኢየሱስን አካል በመቃብሩ ውስጥ ከማግኘት ይልቅ፥ የኢየሱስን መነሳት እና ወደ ገሊላ የመቅደሙን ዜና የነገራቸውን መልአክ አገኙ፡፡ ኢየሱስ ቃል እንደገባው፥ ሴቶቹን ዳግመኛ ያያቸዋል! ከመልአኩ ተለይተው በሄዱ ጊዜ፥ ኢየሱስ ህያው ነው በሚለው ዜና ከመደንገጣቸው የተነሳ በመንገዳቸው ላይ አንዳች አልተናገሩም፡፡
የተደረገውን ተአምር ለማመን ጊዜ እስኪፈጅ ድረስ እግዚያብሔር በሀይል ሲንቀሳቀስ አይታችኋል? ምናልባት ሰውነታችሁ ተፈውሷል፥ የማይሆን በሚመስል መንገድ ጌታ ገንዘብን አዘጋጅቷል፥ እንደምትወድቁ እርግጠኛ የሆናችሁትን ፈተና አልፋችኋል፥ ወይም ትዳራችሁ ወዲያውኑ ተስተካክሏል፡፡ የኢየሱስን የትንሳኤ ተአምር እንደመሰከሩት ሴቶች፥ አንዳንድ ጊዜ በህይወታችሁ የሚገለጠውን የኢየሱስን አሰገራሚ ሀይል ለመናገር ጊዜ ይወስዳል፡፡ ነገር ግን ሴቶቹ በመጨረሻ የሚገርመውን የኢየሱስን ትንሳኤ እንደተናገሩት፥ ጌታ በአለም ዙሪያ በህይወታችሁ የገለጸውን ተአምራዊ ሀይል የምትናገሩበትን ቃላት እና እድሎች ይሰጣችኋል!
“መንቀጥቀጥና መደንገጥ ይዞአቸው ነበርና ወጥተው ከመቃብር ሸሹ፤ ይፈሩ ነበርና ለማንም አንዳች አልነገሩም። እነርሱም ያዘዛቸውን ሁሉ ለጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ላሉት በአጭሩ ተናገሩ። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።”
— ማርቆስ 16:8
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ማቴዎስ 7:28 — “ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን”
- የሐዋርያት ሥራ 3:11-12 — “እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ?’”
- ሮሜ 15:18-19 — “አሕዛብ እንዲታዘዙ ክርስቶስ በቃልና በሥራ፥ በምልክትና በድንቅ ነገር ኃይል፥ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል በእኔ አድርጎ ከሠራው በቀር ምንም ልናገር አልደፍርም፤ ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ጀምሬ እስከ እልዋሪቆን ድረስ እየዞርሁ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ፤ ሰብኬአለሁ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 44
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።