The Gospels Luke

The Angel Announces the Birth of Two Sons

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 155 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ወደ ሰዎስተኛዉ አካታች ወንጌል ወደ ሉቃስ ወንጌል ጥናት እንኳን በሰላም መጣችሁ ፡፡ ይህን መግለጫ ለሮማዉዊ ባለስልጣን ለቴዎፍሎስ የፃፈዉ ሉቃስ ሀኪም ነበር ፤ ቴዎፍሎስ ምናልባትም ከ60-61 ዓ.ዓ ወደ ክርስቶስ የተመለሰ ከሲዛርዬስ ቤት ነበር ፡፡ ሉቃስ ይህንን ከሮም በጵዉሎስ እስራት ጊዜ ሳይሆን አይቀርም የፃፈው ፤ በዚህ ወንጌል ሉቃስ የመዘገበዉ ጳዉሎስ ለሉቃስ ስለ ህይወቱ አዉርቶታል ፡፡

ለሉቃስ ወንጌል የእኛ ሀረግ የሰዉ ልጅ ነው ፡፡ እንደ ሉቃስ መግለጫ(አገላለፅ) የምናጠናው ስለ ኢየሱስን ሰዋዊነት የምናወራ ይሆን ፡፡ ኢየሱስ ለሁሉም ገበታን ከፍቷል ፤ ሀብታምን፣ ድሀን፣ ህመምተኛን እና ጤነኛን እናያለን ፡፡ ኢየሱስ ከእነዚህ ዉስጥ አንዱንም ለማጨት አልፈራም ነበር ነገር ግን ወደ እርሱ እንደሚመጡ ጋብዟቸዋል ፡፡

የአንድ ሀኪም ባህሪያት ብልጥ መሆን እና ስለ ዝርዝር መመለክተትን የሚያካትት ነው ፤ ሉቃስ ለጥናቱ እና ለጽሁፉ እነዚህን ባህሪያት አምጥቷል ፡፡ ታሪኩ እንደ ሚናገረው ዝርዝሩን አብራርቶታል ፤ ቅፅ 2 ወደሆነው ወደ ሐዋሪያት ስራ ለመፍሰስ ሉቃስ ቅፅ 1 ነው ፡፡ ሉቃስ አህዛቦች ስለ አይሁዶች ባህል ያልተረዱባቸዉን ችግሮችን ለመግለፅ ሞክሯል ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (1፡ 1-4)፡ ሉቃስ ፅሁፉን ለቴዎፍሎስ በማቅረብ ከፈተ ፡፡ ክስተቶቹን በጥንቃቄ በማጥናት በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸዉ ፅፏል ስለዚህም እንባቢዎቹ ለምን እንዳመነና በምንድን እንዳመነ መረዳት ይችላሉ ፡፡

ሉቃስ (1፡ 5-25)፡ ገብርኤል ለዘካሪያስ እና ለኤልሳቤጥ ስለ ወንድ ልጃቸዉ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድ አመለከታቸው ፡፡ መልአክቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለሚመጣዉ መሲህ መንገድን ማዘጋጀት እንደሚሆን ለመግለፅ ከእግዚአብሄር የተላከ ነበር ፤ ይህ ክስተት ከመለአክቱ መልዕክቷን እንድትቀበል ለማሪያም መነሻ ነበር ፡፡ የዘካሪያስ እና የኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ እንደ ተዓምራታዊ ይታይ ነበር ምክንያቱም ልጅ ከሚወልዱበት እድሜ አልፈዉ ስለ ነበር ፡፡ ይህ ክስተት ለሌላ ተዓምራት በዝግጅት ላይ ነበር ፡፡ ለአምስት ወራት ኤልሳቤጥ ራሷን በማግለል አቆየች ፡፡

ሉቃስ (1፡ 26)፡ በኤልሳቤጥ እርግዝና ስድስተኛዉ ወር ላይ መልአኩ ገብርኤል በእግዚአብሄር ወደ ናዝሬት ተላከ ፡፡ ናዝሬት ከሰሜን ኢየሩሳሌም 70 ማይል ያክል ነበረች ፡፡ የተከሰተባት ከተማይቱ ዝነኛ ያልሆነች እና በብሉይ ኪዳን አልተጠቀሰችም ፡፡ በኋላም ፊልጶስ ለወንድሙ ለናትናኤል የዮሴፍ ልጅ የሆነዉን ከናዝሪት መሲሁን እንዳገኘዉ በነገረዉ ጊዜ ናትናኤል መልካም ነገር ከናዝሬት ሊወጣ ይችላልን ብሎ በመጠየቅ መለሰለት (ዮሐ 1፡ 43-46) ፤ ስለ ከተማዋ የነበረዉ አስተሳሰብ ይህ ነበር ፡፡

ሉቃስ (1፡ 27)፡ መልአክቱ ከዳዊት ቤት ለነበረዉ ለዮሴፍ ታጭታ ወደ ነበረችዉ ድንግል ማሪያም ለምትባል ተቀለጠላት ፤ ድንግል ወሲባዊ ግንኙነት ያልነበረዉ ነው ስለዚህ ማሪያም ከዮሴፍ ጋር ግንኙነት አልነበራትም ፡፡ በዚያን ጊዜ የታጨ መሆን ማለት ብዙ ጊዜ መጠኑን አንገነዘበዉም ፤ መተጫጨት ህጋዊ ነበር (ህጋዊ ትስስር) እናም ማሪያም ለዮሴፍ ቀድማ የተሰጠች ወይም “ ያገባች “ ነበረች ፡፡ ቁልፉ ሀሳብ ዮሴፍ ከዳዊት ቤት እንደ ነበር መጠቀሱ ነው ፤ በ 2ሳሙ (7፡ 12-16) እግዚአብሄር ዳዊትን የዳዊትን መንግስት እንደሚመሰረት እና ዙፍኑም ለዘላለም እንደሚሆን ነግሮታል ፤ አይሁዶች ከዳዊት የዘር ሀረግ በኩል እንደሚመጣ ያዉቃሉ ፡፡

ሉቃስ (1፡ 28)፡ መልአኩ ማሪያምን እንደ “ ተከበረች ሴት “ ደረሳት ፤ በዚያን ክፍለ ዘመን ጊዜ ሴቶች በጣም በከፍተኛነት ወይም የታወቀ ተግባር እንዲኖራቸዉ የሚፈቀድላቸዉ አልነበሩም ፡፡ የመሲሁን መወለድ ለማምጣት እግዚአብሄር ማሪያም የምትባለዉን ይቺን ድንግል መረጠ ፡፡ የዚያን ጊዜ ሴቶች የመሲሁ እናት ስለ መሆን ማሰባቸዉን ልናደንቅ ይገባናል ፡፡

ሉቃስ (1፡ 29)፡ ማሪያም በመለዓክቱ ንግግር በኃይል ተደናግጣ ነበር ፤ ገብርኤል ለምን እንደሆነ ሳይነግራት እንድትደሰት ነገራት ፡፡

ሉቃስ (1፡ 30)፡ መልዓኩ ማሪያምን በእግዚአብሄር ሞገስ በማግኘቷ አትፍሪ ብሎ ነገራት ፤ ሁለት ጊዜ ማሪያም በእግዚአብሄር ሞገስ እንዳገኘች ተነገራት ፡፡ አሳታዉሉ ምንም እንኳን ድንግል ብትሆንም ኃጢዓተኛ ነበረች በወሲብ ኃጢዓት ምክንያት ሳይሆን ማንም ፍፁም ባለመሆኑ ምክንያት እንጂ ፡፡ አዎ እንደ መሲሁ እናት የተመረጠች ነበረች ግን ያ ማለት እናመልካታለን ማለት አይደለም ፤ እግዚአብሄር ስለሚመጣወ መሲሁ ለማምጣት እንደ መተላለፊያ እንድትሆን መረጣት ፡፡

ሉቃስ (1፡ 31)፡ መልዓኩ ማሪያምን “ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትዩዋለሽ “ አላት ፡፡ ዬሹዋ ማለት “ እግዚአብሄር አዳኝ ነው “ ማለት ሲሆን ፤ ይህ የኢሳ (7፡ 14) ትንቢት “ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች “ ትርጉሙም “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ ለሚለዉ መፈጸም ይሆናል ፡፡

ሉቃስ (1፡ 32)፡ ገብርኤል ኢየሱስ ማን እንደሚሆን እና እግዚአብሄር የአባቱን የዳዊትን ዙፋን እንደሚሰጠዉ አብራራ ብዙ መግለጫዎችንም ሰጠ ፤ እንደገና የ(2ሳሙ 7፡ 12-16) ትንቢት መፈፀም ተገለጠ ፡፡

ሉቃስ (1፡ 33)፡ ገብርኤል በያዕቆብ ቤት ላይ ለዘላለም እንደሚገዛ ተናገረ ፡፡ የኦሪት (የህግ) ትንቢቶች በኢየሱስ የሚፈፀሙ ናቸው ፡፡ ዳን (2፡ 44) ይህ መንግስት ለዘላለም ይኖራል እንጂ በፍፁም አይጠፋም ፡፡

ሉቃስ (1፡ 34)፡ ማሪያም “ ወንድ ስለማላዉቅ ይህ እንዴት ይሆናል ? “ ብላ ጠየቀችዉ ሉቃስ ተግባራቶቹን ሸፍኗቸዋል ፤ ማሪያም ፍፁም(ንፁህ) ነበረች ስለዚህ ልጅ እንዴት ልትፀንስ ትችላለች ?

ሉቃስ (1፡ 35)፡ ገብርኤል መንፈስ ቅዱስ በእርሷ ላይ እንደሚወርድ ገለፀ ፤ በመላዉ በሉቃስ ፅሁፍ ዉስጥየመንፈስ ቅዱስ ተግባር ተብራርተዋል ፡፡ በኢየሱስ መወለድ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል በመግለፅ ጀመረ ፡፡

ሉቃስ (1፡ 36)፡ ከዚያም ገብርኤል ማሪያምን አንድ ምልክት ሰጣት “ ዘመድሽ እልሳቤጥ በእርጅና እድሜዋ ልጅ ፀንሳለች እናም አሁን በስድስተኛ ወሯ ነው ፡፡ “

ሉቃስ (1፡ 37)፡ “ በእግዚአብሄር የምይቻል ነገር የለም ፡፡ “ ገብርኤል የመሲሁ ትንቢቶች በማሪያም እንደሚፈፀሙ አብራራ ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ኃይል እና ብቃት ንግግር በማቴ (19፡ 26) ኢየሱስ “ ይህ በሰዉ ዘንድ አይቻልም በእግዚብሄር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል “ ባላቸዉ ጊዜ ተደግሞ ነበር ፤ ማር (10፡ 27) ተመሳሳይ ንግግርን መዝግቧል ፡፡ የእናንተ ያምያችሉ ሁኔታዎች በትዳራችሁ፣ በልጆቻችሁ፣ በፋይናሳችሁ፣ በትምህርት በ/ታችሁ ወይም በጓደኞቻችሁ ያጠቃለለ ይሆናል ፡፡ ወደ ራሳችን በምንነሳ ጊዜ ምንም ነገር አይሆንም ፤ ነገር ግንበእግዚአብሄር ከእግዚአብሄር ቃል ጋር እስከተስማማን ድረስ ሁሉም ነገሮች ቀላል ናቸው ፡፡ በአሜሪካ አማኞች ባለማቋረጥ በራሳቸዉ ጥንካሬ ነገሮችን ለመስራት ይሞክራሉ ፤ በእዉነቱ በኑሮአችን እንዲሰራ እግዚአብሄርን እድል ልንሰጠዉ ያስፈልጋል ፡፡ እግዚአብሄር በእኛ በኩል ለመስራት ይፈልጋል ነገር ግን ብዙ ጊዜ ወደ ግብዣዉ መምጣት አንፈልግም ፡፡

ነቢዩ ኤርምያስም ደግሞ “ ከአንተ የሚያቅት ነገር የለምና “ (ኤር 32፡ 17) ፤ ኤርምያስ እግዚአብሄር እስራኤልን ከግብፅ አዉጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለማስገባት አድርጎአቸዉ የነበሩትን ድንቅ እንደገና ከጠቀሰ በኃላ እግዚአብሄር “ እነሆ እኔ የስጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሄር ነኝ ፤ በዉኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን ? በማት አረጋገጠ (ኤር 32፡ 27) ፡፡ በህይወታችሁ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ለእግዚአብሄር ስጡት እንደሚያሳያችሁም እመኑት ፤ “ አለማመኔን እርዳ ፤ አምላኬ ምን ያክል ትልቅ እንደሆንህ አሳየን “ ብላችሁ ፀልዩ ፡፡

ሉቃስ (1፡ 38)፡ እግዚአብሄር የማይቻለዉን ለመስራት በሚጠይቀን ጊዜ እንዴት እንደምንመልስ ማሪያም አሳየች ፤ ማሪያም “ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልህ አለች ፡፡ “ መፅሀፍት በሚሉት መሰረት በህይወቷ እግዚአብሄር የፈለገዉን እንዲሰራ ፈለገች ፤ ከዚያም መልዓኩ ትቷት ሄደ ፡፡

መዝጊያ

በመፅሀፍ ቁጥር ከቁጥር በኋላ እግዚአብሄር ምን ያክል ትልቅ እንደሆነ እና የማይቻለዉን እንዴት እንደሚያደርገዉ ያወራል ፤ ይህ ቀይ ባህርን በመክፈል፣ ዮርዳኖስ ወንዝን መክፈትን በዚህም ሚሊዬኖች በመካከሉ ተጓዙ እና ወሀዉን ወደ ወይን መቀየሩን የእግዚአብሄርን ድስታ ይመስላል ፤ እግዚአብሄር ያደረጋቸው እነዚህ ክስተቶች ለሰዎች እንደማይቻሉ ያሳያል ፡፡

አንድ የማይቻል ተስፋ ከተገባላችሁ “ በእኔ “ በማለት መልሱ ፤ ከዚያም እግዚአብሄር ክብር ያገኛል ፡፡

  1. John F. MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), pp. 1264-1265.

ጥያቄዎች

  1. ሉቃስ ለማን ነበር የፃፈው ? በተለየ ለእርሱ ለምን እንደፃፈ ምን ታስባላችሁ (ሐዋ 1፡ 1) ?
  2. ኤልሳቤጥ ወይም ዘካሪያስ ብትሆኑና ስለ ልጃችሁ መምጣት ብትሰሙ እንዴት ይሰማችኋል ?
  3. የእግዚአብሄር መለዓክ ለእነርሱ የልጆቻቸዉን ዜና ባመጣላቸዉ ጊዜ የዘካሪያስ ምላሽ እና የማሪያም ምላሽ እንዴት ይለያያል ? ለዜናው በብዙ እንደ ዘካሪያስ ወይስ እንደ ማሪያም እንመልሳለን ብላችሁ ታስባላችሁ?
  4. በሉቃ (1፡ 78-79) የተጠቀሰው “ የማለዳ ኮኮብ “ ወይም “ የወጣ ኮኮብ “ ማን/ምንድን ነበር ?
  5. ሉቃ (1፡ 32-33) ሰለሞንን ወይስ ኢየሱስን ይገልፃል ?ሰለሞን እንዴት የኢየሱስ ጥላ ነበር ? (1ዜና 22፡ 9-10, 29፡ 23-25; ኢሳ 9፡ 7)
  6. በሉቃስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 1:37

“For nothing will be impossible with God.”

እግዚያብሔር መልአኩ ገብርኤልን ማርያም ለምትባል ወደ አንዲት ወጣት ድንግል ላከው፡፡ እርሱም ይህንን ዜና አካፈላት፥ " ማርያም ሆይ፥ በእግዚያብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻል እና ፥አትፍሪ ፡፡ አሁንም አድምጪ፡ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጂያለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፡፡ ስለዚህ፥ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚያብሔር ልጅ ይባላል፡፡" ከዚያም መልአኩ ይህንን እውነት አስታወሳት፥ "ለእግዚያብሔር የሚሳነው ነገር የለም፡፡" "የጌታ ባርያ ነኝ፡፡ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ፡፡ " ፥ በማለት፥ ማርያም በትህትና እና በመገዛት መልስ ሰጠች፡፡

ዛሬ ያጋጠማችሁ ምንም ይሁን ምን፥ የሀላፊነታችሁ፣ የጥሪያችሁ፣ እና የፈተናዎቻችሁ መጠን ምንም ይሁኑ ምን፥ እነዚህን እውነቶች ለራሳችሁ ህይወት እመኑ፤

  1. አትፍሩ፡፡
  2. እግዚያብሔር ያያችኋል፥ ደግሞም ሞገሱ በእናንተ ላይ ነው፡፡
  3. አላማ አላችሁ፡፡
  4. ለእግዚያብሔር የሚሳነው ነገር የለም፡፡

ዛሬም፥ እንደ ማርያም እምነት እና ትህትና ይዛችሁ፥ ከጌታ ጋር ተራመዱ፡፡ ጌታ ለእናንተ አላማ አለው፥ ደግሞም የማይቻለውን የሚቻል ያደርጋል!

“ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።”

—ሉቃስ 1:37

ተጨማሪ ጥቅሶች

ትንቢተ ኢሳይያስ 41:10 — “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። ”

ትንቢተ ኤርምያስ 32:17-18 — “አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም። ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፥ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ፤ ስምህ ታላቅና ኃያል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። ”

ማቴዎስ 17:20 — “ኢየሱስም፦ ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 45