Understanding Jesus' Humanity
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ማቴዎስ ኢየሱስን እንደ ንጉስ አቀረበ ፤ ማርቆስ ኢየሱስን እንደ አገልጋይ አቀረበ ፤ ሉቃስ ኢየሱስን እንደ ሰዉ ልጅ አቀረበ ፡፡ ኢየሱስ እንዴት ነዉ የሰዉ ልጅ የሆነው ? የማሪያም ልጅ ነው ነገር ግን ደግሞ ከሰዋዊነት ጋር የተያያዘ ነው ፤ ኢየሱስ የሰዉን ልጅ ለመዋጀት ሰዉ ሆነ ፡፡
የኢየሱስ መወለድ የኢሳ (7፡ 14) “ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል ፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠረዋለች “ የሚለዉ ቃል ተፈፀመ ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ዮሐንስ የጠቀሰው “ በመጀመሪያ ቃል ነበር “ (ዮሐ 1፡ 1) ከዚያም በመቀጠል በግልፅ “ ቃልም ስጋ ሆነ ጸጋንና እዉነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ “ ብሎ ገልፆታል (ቁጥር 14) ፡፡ ኢየሱስ እኛን ወደ ግብዣዉ ሊጋብዘን ወደ ምድር መጣ ፤ ኢየሱስ በደንብ ያዉቀናል እንዲሁም ሁሉንም ነገር ከእኛ ፊት ማስቀመጥ ይፈልጋል ፡፡ ወደ ግብዣዉ የምንመጣ ከሆነ ኢየሱስ የትም ብንሆን ከእኛ ጋር ይገናኛል ፤ ይህ ቀላል(የሚቻል) ነው ምክንያቱም ማሪያም የምትባል አንዲት ወጣት ድንግል መሲሁን ስለወለደች ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (2፡ 1-7)፡ እነዚህ ቁጥሮች የኢየሱስን መወለድ በተመለከተ ጥቂት ዝርዝሮችን ሰጥተዋል ፡፡ ማሪያም አንድ ወንድ ልጅ ኢየሱስ የተባለ ነበራት (ቁጥር 7) ፡፡
ሉቃስ (2፡ 8-20)፡ እረኞቹ የመለካሙ ዜና የመጀመሪያዎቹ መልዕክተኞች ነበሩ ፡፡ እረኞቹ ከመለዓክቱ ትዕዛዝ በኋላ በመከተል መሲሁን ለማየት ወደ ቤተ ልሄም ተጓዙ ሉቃስ ሪፖርት ያደረገው “ አይተዉም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸዉን ነገር ገለጡ “ (ቁጥር 17) ፡፡ ሪፖርታቸዉን የሰማ ሁሉ ተደነቀ ፡፡
ሉቃስ (2፡ 21-24)፡ ስምንተኛዉ ቀን ላይ ኢየሱስ ተገረዘ ፤ የሰዉ ልጅ ነበር ስለዚህ በሰዉ መልክ ልክ እንደኛ ነበር ፡፡ ኢየሱስ የሚለዉ ስም የተሠጠዉ በመለዓኩ ነበር ፡፡ አማኑኤል ማለት “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ ማለት ሲሆን ዬሺዋ ማለት ደግም “ እግዚአብሄር አዳኝ ነው “ ማለት ነው ፤ ድነትን ስለ ማምጣት ሁለቱም ወደ ኢየሱስ ተግባር ያመለክታሉ ፡፡
ሉቃስ (2፡ 25-38)፡ ስምዖን ፃድቅ እና ትጉህ ሰዉ ነበር ፤ “ የጌታን መሲህ ሳያይ “ (ቁጥር 26) በፊት እንደማይሞት መንፈስ ቅዱስ ተስፋ ሰጥቶት ነበር ፡፡ ዮሴፍ እና ማሪያም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መቅደሱ ኢየሱስን ባመጡት ጊዜ ስምዖን ልጁን በእጁ በመዉሰድ አመሰገነዉ (ቁጥር 29-32) ፡፡ “ በዚያዉ ስዓት “ አንዲት ሐና የምትባል ነቢይት ደግሞ “ እግዚአብሄርን አመሰገነች የኢየሩሳሌምንም ቤዛ ለሚጠባበቁ ሁሉ ስለ እርሱ ትናገር ነበር “ (ቁጥር 38) ፡፡
የሉቃስ 2 ቀሪ ነገርእንደ ሰዉ ልጅ ልጅነቱ ላይ በማተኮር የተሳለዉ የኢየሱስ ስዕል ነው ፡፡ የኢየሱስ አባት አናፂ ነበር ፤ አንዳንዶች የእንጨት ስራ ይላሉ ፤ ሌሎች ደግሞ በድንጋይ እና በአለቶች ይሰራል ይላሉ ምክንያቱም ናዝሬት ከዛፎች የሚበልጥ ብዙ አለት ነበር ፡፡ በኢየሱስ ትዉልድ ከተማ ያሉት ሰዎች የህዝብ አገልግሎቱን በማድነቅ “ ይህ የአናፂዉ ልጅ አይደለምን ? “ በመለሱ ጊዜ በማቴ (13፡ 35) የዮሴፍ ስራ የተገለጠ ነበር እንደ አንድ ልጅ ኢየሱስ ቤተሰብ ነበረው፡ ማሪያም፣ ዮሴፍ እና ወንድሞች ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖን እና ይሁዳ እና እንዲሁም እህቶች ፡፡
ሉቃስ (2፡ 39-40)፡ የኢየሱስ ቤተሰብ ወደ ናዝሬት ከተማ ወደ ገሊላ ተመለሱ ፡፡ ኢየሱስም “ አደገም ጠንካራም ሆነ፣ በጥበብ ተሞላ እንዲሁም የእግዚአብሄር ፀጋ በእርሱ ላይ ነበር ፡፡ “ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ የኢየሱስን የሰዉ ተፈጥሮ እድገት እንጂ የመለኮት ተፈጥሮዉን እንዳማይገልፅ ተናግሯል ፡፡ በክስተቱ በምድር ላይ ተወልዶ የነበረ ሙሉ እግዚአብሄር ነበር ፤ ይህ እናንተ እና እኔ የምነለምደዉን ለመልመድ ወደ ሰዉነት እያደገ እንደ ነበር ያሳያል ፡፡
ሉቃስ (2፡ 41-42)፡ በየዓመቱ የኢየሱስ ቤተሰቦች ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛሉ ፡፡ ፋሲካ፣ ጴንቴኮስታ እና የዳስ በዓል በኢየሩሳሌም ይከበር ነበር ፡፡ የፋሲካ በዓል ከዘጸዓት 23 የመጣ ነው ፤ በግብፅ አድርጎላቸዉ የነበረውን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዳሉ ፤ ኢየሱስም እንደ አንድ ወጣት ከቤተሰቦቹ ጋር ያከብራል ፡፡ ኢየሱስ 12 አመት በነበረ ጊዜ በበዓላቸዉ ልምድ መሰረት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ ፤ 12 አመት ላይ ወንዶች ለኃላፊነት ዕድሜ 13 ለነበረው ብዙ ትዕዛዞችን ይቀበላሉ ፤ 13 አመት ላይ ኢየሱስ ህጉን መጠበቅ እንደሚያስፈልገዉ አንድ ሰዉ ወደ ኃይማኖታዊዉ ማህበረሰብ ተቀብለዉት ነበር ፡፡
ሉቃስ (2፡ 43-46)፡ “ እነዚያ ቀናት ካለፉ በኃላ “ ወደ ዘጸዓት 23 ሲጠቅስ የአንድ ቀን ድግስ ሳምንት በሚቆየዉ እርሾ በሌለዉ ቂጣ ያስከተለ ነበር ከሰባት እስከ ስምንት ቀን ይቆያል ፡፡ ቤተሰቡ ወደ ቤታቸዉ ተጓዙ ነገር ግን ኢየሱስ በኢየሩሳሌም “ቆየ “ ፡፡ ለዚህ መሆን ትልቁ የግብዣ ጉዞ እና ቀላሉ ይህ ነበር ፤ ይህ የሰባት ሰዓት ጉዞ ነበር ከብዙ ሰዎች ጋር ደግሞ የአንድ ቀን ጉዞ ፡፡ ማሪያም እና ዮሴፍ ኢየሱስን በዘመዶቻቸዉ መካከል ተመለከቱት ባላገኙትም ጊዜ ደነገጡ ፤ ከሰዎስት ቀን በኋላ ኢየሱስን በመቅደሱ መምህራኖቹን እያዳመጣ እና ጥያቄ እየጤቀ አገኙት ፡፡ እየሰረሰራቸዉ(እየለያቸው) አልነበረም ፤ እንደ ሰዉ በአዋቂዎቹ መካከል ለመማር ህፃን ልጅ ነበር ፡፡ መዝ (119፡ 99-100) ስንመለከት፡ “ ምስክርህ ትዝታዬ ነዉና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ ፡፡ ትዕዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ ፡፡ “ ምን አይነት የትህትና አስደናቂ መልክ ነው ፤ ኢየሱስ ከመምህሮቹ በላይ እንኳን ቢያዉቅም ለማዳመጥ(ለመስማት) ታዘዘ(ቀረበ) ፡፡ ራሳችንን በቃሉ መሰረት ቃሉን በሚያስተምሩ ሰዎች ማስከበብ ያስፈልጋል ስለዚህም ቃሉን መያዝ እንችላለን ፡፡
ሉቃስ (2፡ 47-50)፡ ኢየሱስ 12 አመቱ ላይ ስነ መለኮታዊ ዉይይት ነበረው ፡፡ እርሱን የሰሙት ሁሉም በእርሱ መረዳት እና መልሶቹ ተደነቁ ፡፡ ቤተሰቦቹም ተደነቁ ማሪያምም “ ለምን እንዲህ አደረገህብን ? እነሆ አባትህና (ዮሴፍ) እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበር “ አለችዉ ፤ የማሪያም ጭንቀት ወጣላት ፡፡ ኢየሱስ ለምን ይፈልጉት እንደ ነበር ተገረመ ምክንያቱ “ በአባቱ(በእግዚአብሄር) ቤት ሊሆን ሰለሚገባው “ ፡፡ በኔልስን ማብራሪያ መሰረት ኢየሱስ ያለው የእግዚአብሄርን ስራ እየሰራ ነበር ወይም በዚያ እንዲሆን ተሾሟል (ተልኮ) ነበር ፤ ዮሴፍ እና ማሪያም አልገባቸው ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ለመረዳት ምን ያክል ጊዜ ወድቀዋል ? ሉቃ (9፡ 45) ተመሳሳይ ሀሳብን ይገልፃል ፤ ደቀ መዛሙርቱ ይህን ንግግር አልገባቸዉም ስለዚህም ለመጠየቅ ፈሩ ፡፡
ሉቃስ (2፡ 51-52)፡ ኢየሱስ ወደ ናዝሬት ወርዶ ለቤተሰቦቹ ታዛዥ ሆነ ፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች እናቱ በልቧ ጠበቀች ፡፡ ምንድን ነገር እያካሄደች እንደ ነበረች ምን ታስባላችሁ ? ኢየሱስ ከምኩራብ ተመቶ አይወጣም ፤ በደህና ይመጣ ነበር እንጂ ፤ ሙሉ ቃለ ምልልስ ነበረው ፤ ኢዚያ የነበረዉን ሁሉ አስገረማቸዉም አስደነቃቸው ፡፡ ማሪያም ለማስኬድ ብዙ ነበራት፡ ገብርኤል ተናግሯት የነበረዉን ታውቃለች ፤ ኢየሱስ የሰዉ ልጅ እግዚአብሄር ከእኛጋር ነዉ የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ነበር ታውቃለች ፡፡ በኢየሩሳሌም በመቆየት ኢየሱስ የማይታዘዝ አልነበረም ፤ አሁን ቤተሰቦቹን በማክበር አስእርቱን ትዕዛዝ አከበረ ፡፡ ሉቃስ “ ኢየሱስ በጥበብ እና በቁመት እንዲሁም በእግዚአብሄር እና በሰዉ ፊት በሞገስ አደገ “ በማለት ጨረሰ ፡፡
መዝጊያ
ከመፅሀፍ ስለ ኢየሱስ ልጅነት እናውቃለን ፡፡ በጥንካሬ አደገ በጥበብም ተሞላ ፤ የእግዚአብሄር ፀጋ እርሱ ላይ ነበር በእግዚአብሄር እና በሰዎች ሞገስ አገኘ ፡፡ ደግመው ደግመው ሀተታ ሰጪዎች ኢየሱስ እንደ ሰዉ እንዳደገ ነገር ግን እግዚአብሄር ከመሆን እንደ ማያስቆመዉ አመልክተዋል ፤ ማክአርቱር ዮሐንስ የተናገረው ኢየሱስ “ የመለኮታዊ ባህሪያቱን ጥቅሞችን ለእግዚአብሄር ፈቃድ አቀረበ “ ፤ ኢየሱስ ለአባቱ ለእግዚአብሄር ተሸነፈ(አቀረበ/ታዘዘ) እንዲሁም እነዚህን ችሎታዎች በሚጠቀምበት ጊዜ እንዲያሳየዉ እግዚአብሄር ፈቀደለት ፡፡ “ ስለዚህም ክርስቶስ ለተለመደዉ የሰዉ እድገት ሂደት፣ በአስተሳሰብ፣ በአካላዊ፣ በመንፈሰዊ እና በማህበራዊ ላይ ያተኮረ ነበር ፡፡ “ ለአባቱ መለኮታዊ ባህሪያቱን ያለማቋረጥ በመስጠት እንደ ሰዉ ማደጉም ቀጠለ ፡፡
ሁሉን አዋቂነቱ እይታ ላይ በነበረ ጊዜ ሉቃስ በጊዜ ክስተቶቹን ፅፎአል ፤ እግዚአብሄር ኢየሱስ “የእግዚአብሄርን ኃይልን “እንዲጠቀም በፈቀደለት ጊዜ ያሉት ክስተቶችን ፡፡ ሁል ጊዜ እንደ ማስረጃ በንግግሩ “ ስዓቱን አላዉቀዉም “ (ማቴ 24፡ 36) ሁሉም ነገር ለአባቱ በመታዘዝ ነበር ፡፡ እዚህ ምድር ላይ በአባቱ እቅድ ላይ የመለኮታዉ ባህሪያት ጥቅሞችን ሰጠ ፤ በጊዜዉ እግዚአብሄር ሁሉን አዋቂነት ኃይሉን ለቀቀ ፡፡ እስከ ትንሳኤ በኋላ ድረስ ክርስቶስ በእዉነት ሙሉ መለኮታዉ እዉቀቱን እና ኃየሉን መልሶ እስኪይዝ አልነበረም ፡፡
ይህ የኢየሱስ ልጅነት ነበር ፡፡ ሉቃስ 3 ኢየሱስ እዚህ ምድር ላይ እንደ ነበር አባቱ ልጁ እንደሆነ የገለፀዉን ማረጋገጫ አስደናቂ የእግዚአብሄርን ስዕል ያካትታል ፡፡ የኢየሱስ ልጅነት ቤተሰቦቹን እና ብዙ ወንድሞቹን እና እህቶቹን ያካትታል ፡፡ ኢየሱስ እዚህ ምድር ላይ እንደ ሰዉ ልጅ በጥበብ እና በቁመት አደገ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1254.
Nelson’s Commentary, p. 1254..
John F. MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1280.
MacArhur, p. 1280.
ጥያቄዎች
-
አዉግስጦስ ቄሳር በሮማዉያን ዘመን የህዝብ ቁጥር እንዲወሰድ አዘዘ ፤ የሚክ (5፡ 2) ትንቢት እንዲፈፀም እግዚአብሄር ይህን እንዴት ተጠቀመ ?
-
መለዓኩ ስለ ነገራቸው ለማየት እረኞቹ በሄዱ ጊዜ አድራሻ ወይም የተለየ ስፍራ አልነበራቸውም ፤ ህፃኑን ኢየሱስን ዪያገኙት በምንድን ፍንጭ ነበር ?
-
በዘሌዋዉያን 12 መሰረት ከኢየሱስ ዉልደት በኃላ ለመንፃት ወደ መቅደሱ ከምን ያክል ቀን በኋላ ሄዱ (ሉቃ 2፡ 22) ? በዚህ ጉብኝት ጊዜ በጣም አስፈላጊ የነበረ ምንድን ተካሄደ ?
-
ዮሴፍ እና ማሪያም ኢየሱስ እንደ ሌላ ልጆች እንዳልነበር ቢያዉቁም ሉቃ (2፡ 23) ስለ እርሱ ተነግረዉ በነበሩት ነገሮች ተደነቁ ይላል ፤ ለምን በደንብ እንዳደረጉት ምን ታስባላችሁ ?
-
ሉቃ (2፡ 40, 52) ከፅንስ እስከ ልጅነት የኢየሱስን አድገት ገልጧል ፤ “ የእግዚአብሄር ፀጋ በእርሱ ላይ ነበር “ በሚለዉ ሀረግ ምን ማለት እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
-
በሉቃስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 2:52
“And Jesus increased in wisdom and stature, and in favor with God and with people.”
ኢየሱስ በሕፃንነቱ በሙሉ ጥበብ እና ሞገስ የተወለደ ብቻ አይደለም፡፡ በየዓመታቱ ፥ የሙሴ ህግ ሊቃውንት እና አስተማሪዎች ጋር ተቀምጦ ያዳምጥ ነበር፡፡ ጥያቄ ይጠይቃቸው ነበር፥ ደግሞም ለቤተሰቡ ታዛዥ ነበር፡፡ ከጊዜ ጋር ፥ ኢየሱስ በጥበብ፣ በቁመት እና በሞገስ በእግዚያብሔር እና በሰው ፊት ያድግ ነበር፡፡
ልክ እንደ ኢየሱስ፥ በእግዚያብሔር ቃል ውስጥ ጊዜ ስታሳልፉ፥ ከሌሎች አማኞች ጋር ቃሉን ስትወያዩ እና ለጌታ በመታዘዝ ስትኖሩ፥ በጥበብ ማደግን ትቀጥላላችሁ፡፡ ጌታ ለእርሱ እሺ ባላችሁ ቅጽበት ሁሉም ነገር እንዲኖራችሁ አይጠብቅም፡፡ ሁሉም ነገር ሊኖራችሁ አያስፈልጋችሁም ምክንያቱም ፀጋው በድካማችሁ በቂ ነው፡፡ በክርስቶስ ወደምታድጉበት ስፍራ ራሳችሁን ማስቀመጥን ቀጥሉ፡፡ እርሱን በይበልጥ ለማወቅ እየተዘረጋችሁ፥ በፅናት እና በትዕግስት ተራመዱ፡፡
“ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።”
—ሉቃስ 2:52
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ዕብራውያን 5:12-14 — “ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው። ”
- ያዕቆብ 1:2-4 — “ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። ”
- 1ኛ ጴጥሮስ 2:2-3 — “ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 46
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።