The Gospels Luke

The Genealogy of Christ

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 157 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሉቃስ 3 ስለ ክርስቶስ ዘር እናወራለን ፤ የሚያምረዉ አካል ከሰዉ ጋር የኢየሱስን ግንኙነት ማየት ነው ፡፡ የኢየሱስ የዘር መስመር ወደ አዳም ይመለሳል ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (3፡ 1-20)፡ እነዚህ ቁጥሮች የመሲሁን አብሳሪ ታሪክ ይናገራሉ ፡፡ መጥምቁ ዮሐነስ ለኢየሱስ መንገድን ጠረገ ፤ በቁጥር 20 የሽግግሩ ንግግር ዮሐንስ በእስርቤት እንደ ተዘጋ ገልጣል ፡፡

ሉቃስ (3፡ 21)፡ “ ሁሉም ህዝብ በተጠመቁ ጊዜ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ ፡፡ “ በማቴ (28፡ 19) ኢየሱስ የተናገረው “ ሄዳችሁ…እያጠመቃችሁ….. ደቀ መዛሙርቴ አድርጉአቸው….” ኢየሱስ ተጠምቆ ከነበር እና ሰዎችን እንድናጠምቅ ካዘዘን ሊዚያ ነዉ የምናደርገው ፡፡ በአንዳንድ ምክንያቶች ሰዎችን ስለ ማጥመቅ አናወራም ፡፡ እንደ ኢየሱስ ተከታይ 1) መጠመቃችሁን እርግጠኛ ሁኑ ፤ ጥምቀት አያድናችሁም ነገር ግን የዉስጠኝዉ እምነት ዉጫዊ መገለጫ ነው ፡፡ 2) እስካሁን አድርጋችሁ ባታውቁም እንኳን ሌሎችን ማጥምቅ ምክንያቱም ኢየሱስ ስላዘዘ ፡፡

ሉቃስ (3፡ 22)፡ መንፈስ ቅዱስ በሰዉ ልጅ ኢየሱስ ላይ ወረደ ፤ እግዚአብሄር በግልፅ ኢየሱስን “የኔ ልጅ “ በማለት ገለፀዉ ፡፡ ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር ተጠምቆ እና ከሰማይ በግልፅ ተቀብቷል ፤ 30 አመቱ ያከል ነበር ይህም ብዙ ሰዎች አገልግት የሚጀምሩበት አመት ይመስላል ፤ በዘፍጥረት (41፡ 46) ዮሴፍ ወደ ግብፅ ንጉስ ፈርዓን አገልግሎት በገባ ጊዜ 30 አመቱ ነበር ፡፡ ዮሴፍና ኢየሱስ ሌላ ስራ ሰርተዉ ነበር ? በእርግጠኝነት ነገር ግን ይህ እግዚአብሄር ኢየሱስን ለአገልግሎት በግልፅ የቀባበት ጊዜ መነሻ(ቀያሪ ሀሳብ) ቦታ ነበር ፡፡ በ2ሳሙ (5፡ 4) ዳዊት እንደ ንጉስ ዘመኑን በጀመረ ጊዜ 30 አመቱ ነበር ከዚያም 40 አመት ገዛ ፡፡ ሕዛ (1፡ 1) በሰላሳ አመቱ ነቢዩ ሕዝቅኤል የእግዚአብሄርን ራዕይ እንዳየና በራዕዮቹ መጓዝ እንደጀመረ ይናገራል ፡፡ በዘኁ (4፡ 3) መሰረት 30 አመት ላይ ካህናቱ በድንኳኑ ማደሪያ ላይ መስራት ይጀምራሉ ፤ ስለዚህ 30 አመት ሲሞላዉ ኢየሱስ የክህነቱን አገልግሎት ጀመረ ፡፡

ሉቃስ (3፡ 23)፡ ኢየሱስ የኤሊ ልጅ የዮሴፍ ልጅ “ እንደሚሆን ይታሰብ “ ነበር ፤ ምናልባት ይህ ሀሳብ ዮሴፍ ኢየሱስን “ አሳድጎት ነበር “ ማለት ሲሆን ይህም በጣም አስፈላጊ ሆኗል ፡፡ ዮሴፍ በኢየሱስ ላይ እንደ ልጅ ተቀብሎ በህግ የኢየሱስ አባት ሆኗል ፡፡ ማቴ (1፡ 16) ያዕቆብ የማሪያም ባልን ዮሴፍን እንደ ወለደ ተናግሯል ፤ የዮሴፍን መስመር ወደ ኃላ ወደ ዳዊት መሳል ትችላላችሁ ፡፡ ሀተታ ሰጪዎች የዮሴፍን አባት መግለጫዎች በሉቃስ እና በማቴዎስ ላይ ያለዉን ልዩነት ለመግለፅ የተለያዩ መንገዶች ያቀርባሉ ፡፡ ቦች ይህ የማሪያም ዘር ሊሆን እንደሚችል ወይም በቀድሞዉመካከለኛዉ ምስራቅ የመፅሀፍ ስርዓታዊ የጋብቻ ልምድ ዉጤት ሊሆን ይችላልል ይህም ያላገባ ወንዱሙ ልጅ ያልወለደላትን ሚስቱን እንድታገባ እንደተፈቀደላት አመልክቷል ፡፡ የሁለተኛዉ ጋብቻ የመጀመሪያ ልጅ የሞተዉ ሰዉ እንደ ህጋዊ ልጅ ይታያል ፡፡

ሉቃስ (3፡ 24-27)፡ እነዚህ ቁጥሮች ስለ እነርሱ ምንም የማናዉቃቸዉን የ17 ሰዎች ስሞችን ዘርዝረዋል ፤ አንዳንዶቹን በዕዝ (2፡ 2) እስራኤል በታላቁ በፋሪስ ከባቢሎን ምርኮ በተመለሱ ጊዜ የይሁዳ ነገድ ራስ እንደ ነበረዉ ልክ እንደ ዘሩባቤል እናዉቃቸዋለን ፡፡

ሉቃስ (3፡ 28-30)፡ “ የይሁዳ ልጅ ፡፡ “ የያዕቆብ ልጁ ይሁዳ ባይሆንም የነገዱ ዘር ነበር ፤ ይህ ለምን አስፈላጊ ነው ? በዘፍ (49፡ 10) የያዕቆብ ምርቃን “ በትረ መንግስት ከይሁዳ አይጠፋም “ የሚለዉን ያካትታል ፤ የይሁዳ ነገድ የንጉሱ ዘር ነገድ ነበር ፡፡ ራዕ (5፡ 5) ኢየሱስን እንደ “ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ስር “ ተገልፃል ፤ ኢየሱስ አገልግሎቱን እንደ ጀመረ እነዚህን ትንቢቶች ፈፅሟቸዋል ፡፡

ሉቃስ (3፡ 31-33)፡ በዚህ ክፍል እዉቅና የሰጠናቸዉን የኢየሱስ የዘር ግንድ ስሞች እናያለን ፡፡ በ 2ሳሙ (7፡ 12-13) እንደ ተገለፀው ኢየሱስ ከዳዊት ዘር ነበር፡ “ ….ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሳለሁ መንግስቱንም አጸናለሁ “ ፤ ከእነዚህ ሁሉም ሰዎች በመፅሀፍት አስፈላጊ ተግባር ነበራቸው ፤ በሩት መፅሀፍት ቡዔዝ ዋና ወንድ ስዕል ነበር ፡፡ የኢየሱስ ቅድም አያቶች ለማንነቱ አስፈላጊ ነበሩ ፤ አሁን የይሁዳ ልጅ የያዕቆብ ቀጥተኛ ዘር ነው ፡፡ ያዕቆብ እንኳን ያልወደዳት ልያ (ያዕቆብ ራሄል ነበረች ምርጫው) የይሁዳ እናት ነበርች ፡፡ የሚያስደንቀዉ ንፅፅር ገብርኤል ማንም ወደ ማያከብራት ናዝሬት ለማሪያም መታየቱ ነበር ፤ ከእግዚአብሄር ጋር ሁሉም ቀላል ነው ፤ ሰዎችን ወደ መሲሁ ለማመልከት ማንኛዉንም መጠቀም ይችላል ፡፡

ሉቃስ (3፡ 34)፡ በዚህ ጥቅስ ዉስጥ ሉቃስ ኢየሱስ የናኮር ልጅ የታራን ልጅ የነበረዉ የአብርሃም ልጅ እንደ ነበር አረጋገጠ ፡፡

ሉቃስ (3፡ 35-36)፡ ሉቃስ ኢየሱስ የኖህ ልጅ የሴም ልጅ እንደ ነበር ለማሳየት ትዉልዱን መፈለጉን ቀጠለ ፤ ኢየሱስ ከኖህ ጋር የተገናኘ ነበር ፡፡

ሉቃስ (3፡ 37-38)፡ ደግሞም ሉቃስ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ የአዳም ልጅ የነበረዉ የሴት ልጅ እንደ ነበር አሳይቷል ፤ ኢየሱስ ከአዳም ልጅ ጋር የተሳሰረ ነበር ፡፡ ፊትዝምየር ይህ ማብቂያ አንዱ አይነት እዉነት እንደ ነበር ተናግሯል ፡፡ ይህን በአንድ ላይ ሉቃስ ለምን አገናኘ ? በሐዋ (17፡ 28) ጳዉሎስ የተናገረው “ እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና…በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን ፡፡ “

ኢየሱስ ከአዳም ጋር ማገናኘቱ ለምንድን ነው አስፈላጊነቱ ? የሰዉን ልጅ ለመረዳት አስፈላጊ ነው ፡፡ በሌላ በሁሉም ኃይማኖት አምላኮቻቸው ሌላ ቦታ ሩቅ ናቸው ፤ መንካት ወይም ነረዳት አትችሉም ፡፡ በሉቃስ ወንጌል በእዉነቱ ከእኛ ጋር የተገናኘዉን እግዚአብሄርን እናያለን ፤ የሰዉ ልጅ ከእናተ እና ከእኔ ጋር ለመገናኘት መጣ ፡፡ ሮሜ (5፡ 12-17) “ ስለዚህ ምክንያት ኃጢዓት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢዓትም ሞት “ ፤ በአዳም በኩል ለሁሉም ሰዉ ኃጢዓት እና ሞት እዉነት ሆነዋል ፤ ኃጢዓት ከህጉ በፊት በአለም ነበር ፤ ህጉ ኃጢዓትን ለመረዳት አስፈላጊ ነበር ፡፡ በቁጥር 15 ጳዉሎስ የፃፈው “ ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም ፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ሞተዋልና ነገር ግን የእግዚአብሄር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ ፡፡ “ በአንዱ መተላለፍ ምክንያት ብዙዎች ሞቱ ፤ ከአዳም ኃጢዓት ፍርድ፣ ኩነኔ እና ሞት መጣ ፡፡ ከስጦታው -ከእግዚአብሄር ፀጋ በክርስቶስ ኢየሱስ መስተካከል፣ የፀጋ መተረፍረፍ፣ ፅድቅ እና ህይወት መጣ ፡፡

1ቆሮ (15፡ 21) “ ሞት በሰዉ ስለ መጣ “ በሚለዉ ሀረግ ይጀምራል ማለትም የተከለከለዉን ፍሬ አዳም ወስዶ በመቅመሱ በኩል ሞት መጣ ፤ ከዚያም ጳዉሎስ “ ትንሳኤ ሙታን በሰዉ በኩል ሆኖአልና “ በማለት ቀጠለ ፤ ጳዉሎስም ሲናገር “ አንድ ሰው “ እንዲሁም የኢየሱስ ዘር ሰዋዊነቱን ማረጋገጫ ይሰጣል ፡፡ ጳዉሎስ ይህንን ሀሳብ ለማብራራት ጳዉሎስ በቁጥር 22 ቀጠለ፡ “ ሁሉ በአዳም እንዲሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና “ እንዲሁም በቁጥር 45፡ “ ፊተኛው ሰዉ አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል ፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ ፡፡ “ እነዚህን ፅሁፎችን ለመረዳት በጀመራችሁ ጊዜ ወደ ሉቃ (3፡ 23-38) ይተሳሰራል ፤ የመጀመሪያዉ እና የመጨረሻ ፤ በሉቃስ ወንጌል በኢየሱስን የዘር ግንድ ያያችሁት በትክክል ይህን ነው ፤ በዚህ ዉስጥ ትልቁን ስዕል እናያለን ፡፡

መዝጊያ

ኢየሱስን ሞትን ሳይሆን ህይወትን ሊሰጥ መጣ ፤ ፅድቅን እና ፀጋን ሊሰጥ መጣ እንጂ ፍርድን፣ ኩነኔን ወይም ሞትን ሊያመጣ አልመጣም ፡፡ በእርሱ ህያዉ ሊያደርጋችሁ መጣ ፤ ኢየሱስ ህይወታችሁን በሙሉ መቀየር የሚችል ህይወት ሰጪ መልዕክት እየሰጣችሁ ነው ፡፡ በተቀመሰዉ አፕል ቁመና ላይ አትቆዩ ፤ ክርስቶስ ወደ ግብዣዉ በመምጣት ማን እንደሆናችሁ ሊያድሳችሁ(ሊመልሳችሁ) ይፈልጋል ፡፡ ያደረጋችሁትን በማስተካከል ለመርዳት ይፈልጋል ፤ በክርስቶስ ሊያድሳችሁ መልሶ ወደ ህይወት ሊያመጣችሁ ይፈልጋል ፡፡

  1. Darrell L. Boch, The IVP New Testament Commentary Series: Luke (Downers Grove, IL: IVP Academic, 2010), pp. 80-81.

  2. Joseph A. Fitzmyer, The Gospel According to Luke I-IX. (New York: Doubleday, 1970), n.p.

ጥያቄዎች

  1. ሉቃስ ይህን ምዕራፍ በፃፈ ጊዜ ስለ ሁሉም አካባቢ መሪዎች ዝርዝር እና የጢባርዮስ ቄሳር የአገዛዝ አመትን ለምን እንዳካተተ ምን ታስባላችሁ ?
  2. በሉቃ (3፡ 7) ህዝቡን በሚደርስ ጊዜ “ የእፉኝት ልጆች “ የሚለዉን ቃል መጥምቁ ዮሐንስ ተጠቀመ ፤ በዚህ ምን ማለት እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  3. ሉቃ (3፡ 9 እና17) ተመልከቱት ፤ በሁለቱ ጥቅሶች በእሳት ተቃጥሎ የነበረው ተመሳሳይ እንደ ነበር ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
  4. በመንፈስ ቅደሱ እና በእሳት መጠመቅ ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ሉቃ 3፡ 16)
  5. በማቴዎስ ካለዉ የዘር ግንድ የሉቃስ የዘር ግንድ ለምን እንደ ተለዬ ምን ታስባላችሁ ? (ማቴ 1፡ 1-16, ሉቃ 3፡ 23-38)
  6. በሉቃስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 3:12,16

“Tax collectors also came to be baptized, and they asked him, ‘Teacher, what should we do?’ . . . John answered them all, ‘I baptize you with water, but One is coming who is more powerful than I. I am not worthy to untie the strap of His sandals. He will baptize you with the Holy Spirit and fire.’”

የዘካሪያስ እና የኤልሳቤጥ ተአምራዊ ልጅ ፥ መጥምቁ ዩሐንስ፥ ለኃጢያት ስርየት የንሰሐን ጥምቀት እየሰበከ፥ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ተጓዘ፡፡ ከሕዝቡ ሶስት የተለያዩ ወገኖች "እንግዲህ ምን እናርግ?" ፥ ብለው ጠየቁት፡፡ ምናልባት ዮሐንስ ይመጣል የተባለው መሲህ ከሆነ ብለው አሰቡ፡፡ ነገር ግን ዮሐንስ ከእርሱ ይልቅ የበረታ አንድ እንደሚመጣ እና በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት እንደሚያጠምቅ በመናገር፥ አረማቸው፡፡

"እንግዲህ ምን እናርግ?" በሚለው ጥያቄ ውስጥ ረሀብ እና ትህትና አለ፡፡ ሕዝቡ ንሰሐ እንደሚያስፈልጋቸው አውቀው ነበር፡፡ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ እና የልብ ለውጥ ማድረግ እንዳለባቸው አውቀዋል፡፡ አውነተኛውን እርካታ የሚያገኙት በአለሙ አዳኝ እንደሆነ ዮሐንስ ያውቅ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከኃጢያታቸው ሊያድናቸው ይመጣል፥ ደግሞም እሳቱ ልባቸውን መለወጥ ይጀምራል፡፡

ዛሬ፥ "እንግዲህ ምን ላርግ?"፥ በማለት ጌታን በትህትና ጠይቁት፡፡ንጹህ ልብ ለመፍጠር እና እውነተኛ የሆነ የህይወት ለውጥ ለማምጣት በህይወታችሁ ውስጥ ንሰሐ ልትገቡበት የሚያስፈልግ ነገር አለ? ወይም ጌታ ልባችሁን ሊያጠራ በፈተና ውስጥ እያሳለፋችሁ ይሆናል፡፡ ጌታን ጠይቁት፥ ድምጹን ስሙት፥ እርሱም ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ይገልጽላችኋል፡፡ አስታውሱ፥ ይወዳችኋል፥ ፀጋውም በቂ ነው፡፡

“ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉት። . . . ዮሐንስ መልሶ፦ እኔስ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን የጫማውን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል”

—ሉቃስ 3:12, 16

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 51:10 — “አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።”
  • ትንቢተ ሚልክያስ 3:3 — “እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።”
  • 1ኛ ጴጥሮስ 1:7 — “ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 47