The Temptation of Christ
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሉቃስ ወንጌል ጭብጥ፡ ኢየሱስ የሰዉልጅ ነው ፤ ሉቃስ ከዉድቀት በኋላ ሰዉን ለመዋጀት ተልኮ የነበረዉን የሰዉ ልጅን ሰዉነት አቀረበ ፡፡ ሉቃ (4፡ 1-13) በምድረበዳ በሰይጣን የኢየሱስን ፈተና ይሸፍናል ፤ ኢየሱስ ይህን ፈተና እንዴት አድርጎ ተቋቋመው ? በእግዚአብሄር ቃል ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (4፡ 14-15)፡ ሉቃስ ኢየሱስ በምድረበዳ ከተፈተነ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደ ገሊላ ተመለሰ ፤ በምኩራባቸዉ አስተማረ “ በሁሉም ተደነቀ “ ፤ በሌላ ቃል ሁሉም ሰዉ ወደዱት፡ ሌሎች አዋቂዎች፣ አስተማሪዎች እና የአይሁድ ሰዎች ፡፡ በአገልግሎቱ በዚህ ሀሳብ ላይ ከኢየሱስ ጋር ችግር አልነበረም ፤ ይናገር የነበረው ምንም ብዙዎቹን አያሰናክልም ነበር ፡፡
ሉቃስ (4፡ 16)፡ “ መጥቶባት ወደ ነበረዉ “ ወደ ናዝሬት ኢየሱስ ተመልሶ መጣ ፤ “ እንደ ሁልጊዜው “ ወደ ምኩራቡ ገባ ፡፡ ሁሉም ሰዉ ኢየሱስ ወደ ምኩራብ መምጣቱን ማየት የለመዱት ነበር ፤ ነገር ግን እዚህ ቀን ላይ ኢየሱስ ጥሪዉን አሳወቀ ፡፡ ማርቆስ እና ማቴዎስ ክስተቱን ይሸፍናሉ ነገር ግን በጣም በአጭር መግለጫ ፤ ለዚህ ክስተተ መነሻ ስለ ሰባቱ መሰረታዊ ነገሮች ወይም አካሎች በአይሁድ ምኩራብ አገልግሎት (እንደ አምልኮ ቅደም ተከተል ተመሳሳይ) እናወራለን፡
- ለእግዚአብሄር በረከት ለመና ማቅረብ ምናልባትም ከመዝ (145-150) በአንዳንድ መዝሙሮች ፡፡
- በዘዳ (6፡ 4-9) ወይም በዘዳ (11፡ 13-21) እንደ ዋና ህግ(ሴማ) አይነቱን የተለመደዉን የእብራዉያንንን የእምነት ቃል ማንበብ(መደጋገም) ፡፡
- ጸሎት (ከ18 ፀሎተኞች ስብስብ የተሳበ) ፡፡
- ከህጉ (ቶራዉ) እና ከነቢያት እንዲነበብ ይታዘዛል(ይደረጋል) ፡፡
- በዚያ ምኩራብ ወይም በሚጎበኝ ስፍራ በሆነ ሰዉ በተሰጠዉ ነባብ ላይ ግልፅ ትምህርት ይደረጋል ፡፡
- በካህናቱ ቡራኬ ይሰጣል ፤ ከዚህ ዉጪ አንድ ተራ ሰው በዘኁ(6፡ 24-26) እንዳለዉ በረከት አይነት በመፀለይ ህዝቡን ይባርካል ፡፡
- ጉባኤዉ(ስብሰባዉ) ይበተን ነበር ፡፡
ዕብ (10፡ 19-25) ወደ እግዚአብሄር ቀርበን እንድንሳብ ያበረታታናል ፤ በተለየም ቁጥር 25 ከአምልኮ ስብሰባችን ረቀን እንዳንቀመጥ ያሳስበናል ፡፡ ይህ በአድስ ኪዳን ሰዎችን በአምልኮ እንዲሰበሰቡ የሚያበረታታ በቸኛዉ ንግግር(ፅሁፍ) ነው ፤ ደቀ መዛሙርቱ አንኳን አላዘዙትም ሞደል ሆኑ እንጂ ፡፡
ሉቃስ (4፡ 17)፡ ኢየሱስ ከነቢያት ከኢሳያስ ጥቅል(ብራና ጥቅል) አነበበ (ከላይ 4ኛዉን ቁጥር) ፤ ከዚያም ኢየሱስ የመሲሁን ተልዕኮ ገለጠላቸው ፡፡
ሉቃስ (4፡ 18-19)፡ የኢየሱስ ተልዕኮ በመፅሀፍት ተገልፆ ነበር ኢየሱስ ከኢሳ(61፡ 1-2) እንዳነበበው ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ቁጥር 2 አንብቦ አልጨረሰዉም ፤ ለምን ? ሁሉም ስለ እግዚአብሄር ጊዜ ነበር ፤ ይህ የመጀመሪያዉ እርምጃ እንጂ ሁለተኛዉ አልነበረም ፡፡ ኢየሱስ “ የተወደደችዉን የጌታን አመት ሊሰብክ “ መጥቶ ነበር (ኢሳ 61፡ 2; ሉቃ 4፡ 19) ነገር ግን “ የአምላካችን የበቀል ቀን “ ቆይቶ ይመጣል (ኢሳ 61፡ 2) ፡፡
ሉቃስ (4፡ 20-21)፡ ኢየሱስ ጥቅሉል(የብራና መፅሀፉን/ጥቁሉን) በመጠቅለል ለአገልጋዩ መለሰለት ከዚያም ተቀመጠ ሁሉም ሰዉ እርሱ ላይ አተኮሩበት ፤ ከዚያም ኢየሱስ “ ዛሬ እንደሰማችሁት ይህ መፅሀፍ ተፈፀመ “ አላቸው ፡፡ ኢየሱስ የተናገረው ከመቶ አመታት በፊት ኢሳያስ ፅፎት የነበረውን እንደፈፀመዉ ነበር ፡፡ አስቡት እስኪ በዚያ ቀን በምከራብ ብትሆኑና የኢየሱስን ቃል ብትሰሙ ፡፡ ተራራዉ ላይ በስብከቱ ኢየሱስ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈፅም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “በማለት ተናግሮ ነበር (ማቴ 5፡ 17) ፡፡ መቼም ቢሆን ሉቃስ ያብራራው “ ዛሬ “ ትልቅ ንግግር ነበር ፤ በሉቃ (2፡ 11) ያብራራው “ ዛሬ አዳኝ ተወልዷል “ ፤ በሉ (5፡ 26) የኢየሱስን ተዓምራት የመሰከሩት ሰዎች “ ዛሬ የሚያስደንቅ ነገር አየን ! “ ብለዋል ፡፡
የመሲሁ ተልዕኮ እየተጀመረ ነበር ፤ ኢየሱስ ከእርሱ በፊት ብዙ ነገሮች ነበሩት፡
ወንጌልን ለድሆች ሊሰብክ መጣ ፡፡ ይህ የገንዘብ ድሆችን ብቻ ሳይሆን በመንፈስ ድሆች የነበሩትን ሁሉንም ያካትታል (ማቴ 5፡ 3) ራሳቸዉን ዝቅ በማድረግ ወንጌልን የሚሰሙትን ፡፡ ሚያዚያ 2 1739 ዮሐንስ ዌስሌይ የቤተ ክርስቲያንን ህፃ በመተው ለድሆች ወንጌልን ለመስበክ ወጥቶ መሄድን የወሰነበት የመጀመሪያዉ ጊዜ ነበር ፤ ያደርግ የነበረዉን ሁሉንም ነገር ተው፣ ህንፃዉን ተው እና ለወንጌል ክፍት የሆኑ ሰዎችን ለመፈለግ ሄደ ፡፡
ለታሰሩት መፈታትን(ነፃነትን) ለማወጅ መጣ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ሲናገር ኢየሱስ እስረኞችን ለመፈለግ እየሄደ ነበር በባርነት የነበሩትን ሁሉንም ሰዎች ይመለከታል ፤ ባርነት በብዙ መልክ ይመጣል - በገንዘብ፣ በሰይጣን፣ በጥፋተኝነት ፤ ኢየሱስ ነፃ ሊያወጣቸው መጣ ፡፡ ነገሮችን በመቀየር ሰዎቹን ፍለጋ መሄድ ይጠበቅብናል ፤ ይህን እንድናደርገ ተቀብተናል ፡፡
ለእዉሮች ማየትን ለመስጠት መጣ ፡፡ ይህ ስለ አካላዊ እይታ የሚያወራ ይሆናል ፤ በወንጌል ኢየሱስ ተዓምራቶችን አድርጓል ፡፡ ሉቃ (7፡ 22) ኢየሱስ ለእዉሩ አካላዉ እይታዉን እንደመለሰለት ያወራል ፤ ኢየሱስ አካላዊ እይታ ተመልሶ ማየት ፈለገ ፤ በተጨማሪም መንፈሳዊ አለምን ማየት እንዲጀምሩ ፈለገ ፡፡ በሐዋ (26፡ 18) ጳዉሎስ ኢየሱስ “ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ስልጣን ወደ እግዚአብሄር ዘወር እንዲሉ አይናቸዉን እንዲከፍት “ ልኮት እንደ ነበር ይናገራል ፤ የኢየሱስ ተግባር አይናቸዉን መክፈት ነበር ፡፡
የተጨቆኑትን(የተጠቁትን) ነፃ ለማዉጣት መጣ ፡፡ መጨቆን ማለት መሰበር፣ በትንሽሽ መሰበር፣ በአለም ወደ ታች መጫን፣ በስጋ፣ በጠላት የተሰበራችሁ ያክል እስኪሰማችሁ ድረስ ማለት ነው ፤ ኢየሱስ ያን ሸክም አርቆ በመዉሰድ ላይ አይወድቅም ፤ “ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ “ (ማቴ 11፡ 28) ብሎ ሰዎችን አሳስቧል ፡፡
የተወደደችዉን የእግዚአብሄር አመት ሊሰብክ መጣ (ቁጥር 19) ፡፡ የተወደደችዉ የእግዚአብሄር አመት የኢዩቢኤልዩ አመት ነበር ፤ የእስራኤላዊያን እዳ የተሰረዘበት እና ባሪያዎች ነፃ የወጡበት ሰባተኛዉ ሀምሳኛዉ አመት ነበር ፤ ኢየሱስ ሁሉንም እዳቸዉን ሊሰርዝላቸዉ እንደመጣ ተናገረ - አድስ ጅማሮ በመስጠት መንፈሳዊ እዳቸዉንም ፡፡ እስከዚህ ጊዜ ድረስ በአገልግሎቱ ኢየሱስ ህዝቡን አላወከም ነበር - እስከዚች ቀን ድረስ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ኢየሱስ ለመልዕክቱ ምላሽ ለሚሰጡት የመንፈሳዊ እዳ ሙሉ ስረዛ እና አድስ ጅማሮ አቅርቧል “ ብሏል፡፡
ወደ መሲሁ መምጣት ወደ መጨረሻዊ ጊዜ ስንቀርብ የእግዚአብሄርን ቃል ልናዉቅ ያስፈልገናል በዚህም ትንቢትን መከተል እንችላለን ፤ በመጨረሻዉ ጊዜ የምንጫወተው ድርሻ ይኖረናል የእግዚአብሄርን ቃል ካላወቅን ግን አንችልም ፡፡
ሉቃስ ( 4፡ 22-24)፡ የኢየሱስን በጎ ነገር ቢያወሩም ማን እንደ ነበር ደግሞ መጠየቅ ጀመሩ ፤ በቅፍርናሆም አድርጎት እንደ ነበረው በናዝሬትም ተመሳሳይ ያደርግ እንደሆነ እያደነቁት እንደነበር ኢየሱስ ያውቃል ፤ እየቀለዱበት እንደ ነበር ያውቃል ፤ ከዚያም “ ነቢይ በገዛ አገሩ አይወደድም “ብሎ መለሰላቸው ፡፡
ሉቃስ (4፡ 25-27)፡ የኢየሱስ ቀጣዩ ቃል ህዝቡን በጣም አስቆጣ ፡፡ በኤልያስ ቀን ብዙ መበለቶች እንደ ነበሩ አስታወሳቸው ፤ ነገር ግን ኤልያስ ወደ ሰራፕታ ተላከ እንጂ በእስራኤል ወዳሉት መበለቶች አልተላከም ፡፡ እግዚአብሄር ወደ አሕዛብ ነቢይ ላከ ምክንያቱም በእስራኤል ያሉት መበለቶች አይቀበሉትም ፤ በተመሳሳይ በኤልያስ ጊዜ በእስራኤል ብዙዎች ለምፅ ነበረባቸዉ ነገር ግን ማንም አልተፈወሰም - የሰሪያዊዉ ነዕማን ብቻ ፤ ኢየሱስ እያለ ያለው መልዕክቱ ለእስራኤል ብቻ አይደለም ለአሕዛብም እንጂ ፡፡
ሉቃስ (4፡ 28-30)፡ “ ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም በምኩራብ የነበሩት ተቆጡ “ ፤ በተራራው ላይ ይጥሉት ዘንድ ከከተማዋ ኢየሱስን አወጡት ፤ ነገር ግን ኢየሱስ በህዝቡ መካከል አልፎ በራሱ መንገድ ሄደ ፤ ሁሉም የጊዜ ጉዳይ ነበር ፡፡
መዝጊያ
የኢየሱስ ተልዕኮ ለድሆች፣ ለታሰሩት(ለእስረኞች)፣ ለእዉሮች እና ለተጨነቁት ነፃ ሊያወጣቸዉ ነው ፤ ነፃ የመዉጣት መልዕክቱ ለአይሁዶች እና ለአሕዛቦች ለሁለቱም ነው ፡፡ ኢየሱስ በዚህ ሊጓዝ መጣ ፤ ጥያቄው ተመሳሳይ እናደርጋለንን ?
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 184.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Luke, p. 75.; available online at www.soniclight.com.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1257.
Radmacher, et al., p. 1257.
ጥያቄዎች
-
በሰይጣን በተፈተነ ጊዜ ኢየሱስ እንዴት አድርጎ መለሰ ? በዚህ መንገድ ኢየሱስ ለምን መለሰ ? በምኞት ላይ በሚገባ ለማሸነፍ በደንብ በሚበቃ ቃሉን አዉቃችኋል ?
-
መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን እንዲፈጠን ለምን ወደ ምድረበዳ መራው ? (ሉቃ 4፡ 1-2; ዕብ 4፡ 15)
-
ሰይጣን መፅሀፍን ማወቁ አስገርሟችኋል (ሉቃ 4፡ 9-11) ? መፅሀፍን በመጠምዘዝ ከሀሳቡ እንዴት አድርጎ አስወጣው ?
-
“ አምላካችሁን እግዚአብሄርን መፈታተን “ ማለት ምን ማለት ነው ( ዘጸ 17፡ 1-7; ዘዳ 6፡ 14-16; ሚል 3፡ 10; ሉቃ 4፡ 12) ? እግዚአብሄርን መፈተን ተገቢ ሆኖ ያዉቃል ? በእዉነት እራሳችንን ለመጠበቅ እና በመፀህፍ መጠምዘዝ የተታለልን ላለመሆን ምንድን ማድረግ ይጠበቅብናል (መዝ 119፡ 11; 2ጢሞ 2፡ 15) ? ሰይጣን እርሱን መፈተኑን ከጨረሰ በኋላ ኢየሱስ እንዴት አድርጎ መለሰ ?
-
የትኛዉ የብሉይ ኪዳን መፅሀፍን ኢየሱስ ተፈፀመ አለው ? ህዝቡ እንዴት መለሰ ?
-
በሉቃስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 4:12-13
“And Jesus answered him, ‘It is said: Do not test the Lord your God.’ After the Devil had finished every temptation, he departed from Him for a time.”
ኢየሱስ አርባ ቀን በመጾም በምድረበዳ አሳለፈ፡፡ ዲያቢሎስ በሶስት የተለያዩ መንገዶች ኢየሱስን ለመፈተን ይህንን ጊዜ ተጠቀመ፡፡ በእያንዳንዱ ጊዜ፥ ኢየሱስ የእግዚያብሔርን ቃል በመጥቀስ ፈተናውን ተቋቋመ፥ ዲያቢሎስም ለጊዜው ከእርሱ ተለየ፡፡
በእያንዳንዱ ቀን፥ ፈተናዎች ያጋጥሟችኋል፡፡ የጠላት አላማ ለመስረቅ፣ ለመግደል እና ለማጥፋት ነው፡፡ ዲያቢሎስ በመንገድ ያለውን ለመዋጥ እንደ ሚፈልግ አንበሳ ይዞራል፡፡ እጅ ባለመስጠት እንዴት ጠንካራ ሆናችሁ ትቆያላችሁ? የእግዚያብሔር ቃል ዲያቢሎስን እንድትቃወሙት፥ ከእናንተም እንደሚሸሽ ይናገራል፡፡ እያንዳንዱን ፈተና በእግዚያብሔር ቃል ውስጥ ባለ እውነት ታገሉ፡፡ የጠላትን ውሸቶች ለዩ እና ውሸትን በእውነት ተኩ፡፡ ዲያቢሎስ እናንተ ብቁ አይደላችሁም ቢል፥ ጮክ ብላችሁ "ውብ እና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለው" በሉ፡፡ ጠላት እናንተ ብቸኛ ናችሁ ቢል፥ ጮክ ብላችሁ ፥" ብቻዬን አይደለውም፥ ጌታ አምላኬ በምሄድበት ሁሉ አብሮኝ አለ፡፡" በሉ፡፡ እውነት በልባችሁ ላይ እንዲገኝ፥ ከኢየሱስ ጋር ጊዜ አሳልፉ እና ቃሉን አንብቡ፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አብራችሁ ስትሄዱ በመንገዳችሁ ሁሉ ሊመራችሁ ቃል ገብቷል፡፡
“ኢየሱስም መልሶ፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎአል አለው። ዲያብሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ።”
—ሉቃስ 4:12-13
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የዮሐንስ ወንጌል 10:10 — “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ”
የያዕቆብ መልእክት 4:7 — “እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል”
1ኛ ጴጥሮስ 5:8 — “ በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 48
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።