Jesus Calls His First Disciples
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዚህ ክፍል ስለ መሲሁ ተልዕኮ እናወራለን ፤ በሉቃስ 4 ኢየሱስ በምኩራብ ቆሞ ከኢሳያስ መፅሀፍ በማንበብ ለሚሰሙት ተልዕኮዉን አሳወቀ ፡፡ አሁን የመጀመሪያዉን ደቀ መዛሙርቱን በመጥራት ኢየሱስ አገልግሎቱን ጀመረ፡፡
ትምህርት
አሁን ሰዎች በኢየሱስ አሰሩ ፤ ከዚህም በኋላ ኢየሱስ የዮሴፍ እና የማሪያም የልጅነት ጊዜ ወይም ለእርሱ ወንድሞች እና እህቶች የአንድ አባት እና እናት አልነበረዉም ፤ ኢየሱስ ማን እንደነበር አዉጆ ነበር ፡፡
ሉቃስ (5፡ 1)፡ ህዝቡ ልክ እንደ ጭንቅንቅ ወይም በአንድ በዓል ዙሪያ እንዳለ ፎቶ አንሺ አጣበቡት ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ቃል መስማት ስለፈለጉ ፡፡ ኢየሱስ የገሊላ ባህር ተብሎ በሚጠራዉ ወይም ከ690 ጫማ በላይ ከባህር ወለል በታች በሆነዉ ትልቅ ንፁህ ዉሃ ሀይቅ በሆነዉ የጥበሪዮስ ሀይቅ በጌንሳሬጥ ሀይቅ አጠገብ ቆሞ ነበር ፤ ለገሊላ አዉራጃ(ግዛት) የዉሃና የንግድ ዋና ምንጭ ነበር ፡፡ ኢየሱስ የገሊላን ባህር እየተመለከተ በተራራዉ ላይ ትምህርቱን(ስበከቱን) አቅርቧል ፡፡ የኢየሱስ ዋና ማስተማሪያ ቅፍርናሆም በባህሩ ላይ ነበር ፤ በኢየሱስ አገልግሎት ሌሎች ብዙ ክስተቶች በገሊላ ባህር ላይ ተካሂደዋል ፡፡
ሉቃስ (5፡ 2-3)፡ ኢየሱስ በዳርቻዉ ላይ ሁለት ጀልባዎች አየ አሳ አጥማጆቹም መረባቸዉን እያጠቡ ነበር ፤ ይህ ቀኑን በማጥመድ አሳልፈዉ እንደ ነበርና እያፀዱ ነበር ምክንያቱም የቀኑን መጨረሳቸዉን ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ ከሁለቱ አንዱ ጀልባዉስጥ በመግባት ስምዖንን ከዳርቻዉ ራቅ አድርጎ እንዲያስቀምጣት ጠየቀው ፤ ህዝቡን ለመቆጣጠር ኢየሱስ ተቀምጦ ከጀልባዋ አስተማራቸው ፤ መብራት አልነበረም፣ የድምፅ መሳሪያ አልነበረም ወይም ካሜራ አልነበረም - በንፁህ ድምፅ ብቻ ፡፡ የገሊላ ባህር በተፈጥሮዉ ክብ አይነት ቅርፅ ነበር አሁንም እንኳን እንዳለነው ፤ ሲያስተምሩ ለአይሁድ መምህሮች እና አዋቂዎች እንዲቀመጡበት(ለመቀመጫነት) የተለመደ ነበር (ሉቃ 4፡ 20) ፡፡ በማቴ (5፡ 1) ኢየሱስ ህዝቡን ባየ ጊዜ “ ተቀመጠ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጡ ፤ ከዚያም ማስተማር ጀመረ “ ፤ ለማስተማር የኢየሱስ መቀመጥ ትርጉም ያዘለ ነበር ፡፡
ሉቃስ (5፡ 4)፡ ለህዝቡ ከተናገረ በኋላ ኢየሱስ ስምዖንን “ ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ “ ብሎ ነገረው ፡፡ በጠቅላላ ያለፈዉ ምሽታቸዉ ምንም እንኳን ያለፍሪ ቢሆንም ወደ ማጥመድ እንዲመለስ ይህን ጰለመደ አሳ አጥማጅ ሰዉዬን ኢየሱስ አሳሰበው ፤ ማክአርቱር የተናገረው “ ኖርማሊይ በቅርቡ ዉኃ በምሽት የሚጠመዱት አሳዎች በቀላሉ በመረቦቻቸዉ ወደ ሚደርሱበት በጣም ወደ ጥልቁ ዉኃ በቀን ብርሃን ሰዓታት ይፈልሳሉ ጴጥሮስ ማታ ላይ የሚያጠምደዉ ለዚህ ነው ፤ ትርጉም ባይሰጠዉም ጴጥሮስ የኢየሱስን ትዕዛዝ አልተጠራጠረም ነገር ግን ዝምብሎ በመታዘዙ ስለ መታዘዙ ተሸለመ ፡፡ “
ሉቃስ (5፡ 5)፡ ጴጥሮስ የመጨረሻ ሙከራቸዉን(ዙራቸዉን) እንደጨረሱ እና እያፀዱ እንደ ነበር ገለፀ ፤ ይሁን እንጂ ጴጥሮስ “ ነገር ግን በቃል መረቦቹን እጥላለሁ አለ “ ፡፡ ቦች ጴጥሮስ በኢየሱስ ላይ እምነቱን እያወጀ ነበር ብሏል ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ “ የጴጥሮስ የእምነት ንግግር “ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ ወደ ዉሃዉ መረቦቹን በመጣል እምነቱን አሳዬ ፤ ሁልጊዜ እምነት መረብን ወደ መጣል ይመራል ፤ የጴጥሮስ መታመን ከአሳ አጥማጅነት ወደ ክርስቶስ ተከታይነት ሽግግሩን ጀመረ ፡፡
ያዕ (2፡ 14) የሚለው “ ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ስራ ግን የሌለው ሰዉ ቢኖር ምን ይጠቅመዋል “ ፤ ያዕቆብ የሚለው እምነት በሚኖራችሁ ጊዜ ያመናችሁትን ተግባራዊ አድርጉት ነው ፤ ያዕቆብ በጥልቀት በመሄድ እምነት ያለስራ የሞተ ነዉ ብሏል (ቁጥር 17) ፡፡ ጴጥሮስ እሺ ብሎ መረቦቹን ባይጥል ግን እምነት የለዉም ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ነዉ እምነት የምታሳየው ?
ዋይርስቤ “ ቢያንስ ሰባቱ ደቀ መዛሙርቶች አሳ አጥማጅ እንደ ነበሩ “ ተናግሯል ፤ የአሳ አጥማጆች ችሎታዎች ምንድን ነበሩ ? የት እንደሚያጠምዱ፣ ቋጠሮዎቹን እንዴት እንደሚያስሩ፣ የትኛዉን መግብ ለማታለያነት እንደመጢቀሙ (አሳየመያዣ ብልሀቶች) ያዉቃሉ ፡፡ ዋይርስቤ አሳ አጥማጆች አንዳንድ ድፍረቶች፣ ትግስቶች እና ቆራጥነት፣ በእዉነት ይህ እንደሚሰራ ታላቅ የእምነት ስምምነት፣ በአንድ ላይ ለመስራት ፈቃደኝነት (ወደ ጀልባዎች መረቦችን ሲያስገቡ) እንዲሁም ስራን በፍጥለነት በብቃት ለመጨረስ በበቂ የመፆም ችሎታን ማሳደግን መቻል እንደሚያስፈልጋቸዉ አመልክቷል ፡፡ በተጨማሪም ደግሞ ተለዋዋጭነትን እና ለማዳነትን መዉሰድ ያስፈልጋቸዋል ፡፡
ሉቃስ (5፡ 6)፡ ትርጉም እንደማይሰጠዉ ባያስብም እንኳን ጴጥሮስ የኢየሱስን ትዕዛዝ በመታዘዙ “ እጅግ ብዙ አሳ ያዙ መረቦቻቸዉም መቀደድ ጀመሩ “ ፤ ተዓምራታዊ መያዝ ነበር ፤ ሁሉም ተደነቁ (ቁጥር 9) ፤ ኢየሱስ በተለያዬ ጊዜ በተለያዬ መንገድ እንደሚያጠምዱ አዞአቸዉ ነበር ፡፡ በኢየሱስ ተልዕኮ ላይ ነን ዝም ማለት አንችልም ፡፡ 2ዜና (15፡ 7) የሚለው “ እናንተ ግን ለስራችሁ ብድራት ይሆንላችኋልና በርቱ ፡፡ “ ምንም ትርጉም በማይሰጣችሁ ጊዜም እንኳን እግዚአብሄር እምነታችሁን ያከብራል ፤ ገላ (6፡ 9) የሚያሳስበን “ ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ስራን ለመስራት አንታክት “ ፤ ሙሉ መያዝ መጣ ምክንያቱም ዝም ስላላሉ በዚያ ፋንታ ሙሉ እምነታቸዉን በእርሱ ትዕዛዝ ላይ ስላደረጉ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ጊዜ አሳለፉ በረከቱን አፈሰሰባቸዉ ፤ ኢሳ (50፡ 10) የሚለው “ ከእናንተ እግዚአብሄርን የሚፈራ…….በእግዚአብሄር ስም የሚታመን ፤ በአምላኩ ስም የሚደገፍ ማነው ፡፡ “ እግዚአብሄር ላይ በምንደገፍ ጊዜ ይመልስልናል ፤ ነገር ግን በፍፁም በኛ ጊዜ ሳይሆን በእርሱ ነው ፡፡
ሉቃስ (5፡ 7)፡ ጓደኞቻቸዉን ምናልባትም የዘብዲዮስ ልጆች ያዕቆብ እና ዮሐንስ መጥተዉ እንዲረዷቸዉ ጠሩዓቸው ፤ ሁለቱንም ጀልባዎች ሞሉ በዚህም በመሞላቱ የመስመጥ አደጋ ዉስጥ ነበሩ ፡፡ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የስራ አጋር ነበሩ አሁን ደግሞ መንፈሳዊ አጋር ሆኑ ፡፡ ጴጥሮስ የኢየሱስን በረከት እንዲቀምሱት(እንዲለምዱት) ሌሎችን ጋበዘ ፤ ሌሎችን መጋበዝ አለብን ይህ ከሆነ በረከቱን መቅመስ(መልመድ) ይችላሉ ፡፡ ዋይርስቤ አሳ አጥማጆቹ ለእነርሱ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን ከሌሎች ጋር በመካፈላቸዉ የበረከት መተላለፊያዎች እንደሆኑ አመልክቷል ፡፡
ሉቃስ (5፡ 8)፡ ቦች ጴጥሮስ ይህ አሳ ከመያዝ የሚበልጥ ቀን እንደነበር እንዳወቀ ተናግሯል ስለዚህ አሁን የጴጥሮስን ንስሀ እና ፍራት እናያለን ፤ ጴጥሮስ በኢየሱስ ጉልበት ላይ በመዉደቅ “ ጌታ ሆይ እኔ ኃጢዓተኛ ነኝና ከእኔ ተለይ ! “ አለው ጴጥሮስ በራሱ ኃጢዓት ላይ እፍረቱን በግልፅ ተናገረ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ጊዜ በምታሳልፉ ጊዜ ማን እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ ፤ ኢሳያስ ተመሳሳይ ንስሀን አድርጓል “ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ …..ዓይኖቼ የሰራዊትን ጌታ ንጉሱን እግዚአብሄርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ “ (ኢሳ 6፡ 5) ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የኃጢዓተኝነት ሁኔታዎቻችንን አናየዉም ምክንያቱም ከኢየሱስ ጋር ጊዜ ስለማናሳልፍ ፡፡
ሉቃስ (5፡ 9-11)፡ ሁሉም በያዙአቸዉ አሳዎች ተደነቁ ፤ የስምዖን ባልንጀሮችም ያዕቆብ እና ዮሐንስም ተደነቅ ፡፡ ኢየሱስ “ አትፍሩ ፤ ከአሁን በኋላ ሰዉ አጥማጅ ትሆናላችሁ ! “ አላቸው ኢየሱስ ስራቸዉን ዘጋው ፤ ወዲያዉነ ወደ ሌላ ወደ ተወሳሰበ መራቸው ፤ ጀልባዎቻቸዉን ወደ ምድር ያመጡት ሰዎች ሁሉን ነገር ትተው ተከተሉት ፡፡
መዝጊያ
በጀልባዋ ላይ ጊዜ በምናሳልፍ ጊዜ ኢየሱስ ይናገረናል እንዲሁም እግዚአብሄር በበረከቱ ያጥለቀልቀናል ፤ በመገኘቱ ዉስጥ ጊዜ በምናሳልፍ ጊዜ የኃጢዓተኝነት ሁኔታችንን እናውቃለን ፤ ከዚያም ክርስቶስ ማን እንደሆነ በምናዉቅ ጊዜ ሌሎች “ እፈልገዋለሁ ” ይላሉ ፡፡
ቦች ጴጥሮስ ያላወቀዉን አመልክቷል ፤ ለአገልግሎት አለመቻልን እና ኃጢዓትን ማመን በእዉነት ምርጡ ቀድሞ የሚያስፈልግ ነገር ነው ፤ ከዚያም እግዚአብሄር ላይ መደገፍ ይችላል ፡፡ የጴጥሮስ ንስሀ ለአገልግሎቱ እንደ ገና መያዣ ሆኖታል ፤ ትህትና ለመንፈሳዊነት ታላቅነት ማንሻ ይሆናል ፡፡
በትህትና ምክንያት ማድረግ ያልቻልነዉን መረዳት እንጀምራለን ፤ ለታላቅነት ብቸኛው መንገድ ትህትና ነው ፡፡ በራሳችን አሳ መያዝ እንፈልጋለን እዉነታው ግን አሳዉን መያዝ አልቻልኩም ስንል ኢየሱስ ሊጠቀምብን ይጀምራል፡፡ በምታደርጉት እርሱን መገልገል ቀጥሉ ምክንያቱም ኢየሱስ ያከብራችኋል ፡፡
John F. MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1285.
MacArthur, p. 1285.
Darrell L. Boch, The IVP New Testament Commentary Series: Luke (Downers Grove, IL: IVP Academic, 2010), n.p.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1259.
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 150.
Wiersbe, p. 150.
Wiersbe, p. 150.
Boch, p. 100.
Boch, p. 100.
ጥያቄዎች
-
በአሳዎቹ ላይ ተፈጥሮ የነበረዉን በተገነዘበ ጊዜ የጴጥሮስ መልስ ምን ነበር ? ለተያዙት ስጦታ ኢየሱስን ዋጋ በመስጠት ይህን እንዴት አሳዬ ? ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ኢየሱስን ለመከተል ወደኃላቸው ምንድን ተው ?
-
በኢየሱስ ቃል የጴጥሮስ ታቅ የእምነት ንግግር ምን ነበር (ሉቃ 5፡ 5) ? በቃሉ ይህን ተመሳሳይ እምነት የሚጠይቅ እንድታደርጉ ኢየሱስ የጠየቃችሁ ምንድን ነው ?
-
ለምፅን በተመለከተ በህጉ መሰረት በዘሌዋዉይን 13 ተገልጧል ኢየሱስ ሰዉየዉን ሲነካዉ ለምን ነበር የተለየው የሆነው ? ኢየሱስ እርሱን ለመፈወስ ፍቃደኝ ለምን እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
-
ሽባ ለነበረዉ ሰዉዬ ኢየሱስ መጀመሪያ ምንድን አደረገ ? ይህ እንዴት የእርሱን አምላክነት ያሳያል ? (ኢሳ 43፡ 25) ምድር ላይ ኅጢዓትን ይቅር የማለት ስልጣን እንደ ነበረው ለእነርሱ በተጨማሪ ሊያረጋግጥላቸዉ ምንድን አደረገ ?
-
ለፃፎች እና ለፈሪሳዉይን ከቀረጥ ሰብሳቢዎች እና ኃጢዓተኞች ጋር ይበላል ብለዉ ቅር ሲሰኙ የኢየሱስ ምላሽ ምንድን ነበር ? እምነታችሁን ለማጋራት ስትሉ ከማያምኑት ጋር አስባችሁበት ጊዜ ታሳልፋላችሁ ?
-
በሉቃስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 5:27-28
“After this, Jesus went out and saw a tax collector named Levi sitting at the tax office, and He said to him, ‘Follow Me!’ So, leaving everything behind, he got up and began to follow Him.”
ኢየሱስ ሲያገለግል እና ተአምራትን ሲያደርግ ፥ ሰዎች እርሱን ለመከተል እና ለማመስገን ይሳቡ ነበር፡፡ ከአሳ አጥማጆች ጀምሮ እስከ ከባድ የቆዳ ህመም ያለው ሰው፥ ከሽባው ጀምሮ እሰከ ቀራጩ፥ በአንድ ወቅት ሉቃስ እያንዳንዳቸውን በዝቅታ ቦታ መሆናቸውን ገልጿል— የትህትና ቦታ፡፡ ነገር ግን እያንዳንዳቸው የኢየሱስን ሀይል ሲያዩ፥ ተነሱ፡፡ ተነስተው እንዲከተሉት ወይም ተነስተው ስለሀይሉ ለሌሎች እንዲመሰክሩ በሚያደርግ መንገድ በኢየሱስ ተፅእኖ አድሮባቸው ነበር፡፡
እንደ ኢየሱስ አማኞች፥ ወደ ኢየሱስ መገኘት ስትገቡ፥ ኃይሉን እና የፈውስ እጁን በህይወታችሁ ስትፈልጉ፥ ይህ እንድትከተሉት ምሳሌ ነው፡፡ ዛሬ፥ ከኢየሱስ ጋር ወደ ትሁት የአምልኮ እና አክብሮት ቦታ ግቡ፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ የእርሱን ኃይል እና ብርታት ስትለማመዱ፥ ተነሱ እና ለሌሎች አውጁ፡፡ የኢየሱስ ኃይል ለራሳችሁ የምትይዙት ሳይሆን፤ ተነስታችሁ ለሌሎች የምታካፍሉት ነው!
“ከዚህም በኋላ ወጥቶ ሌዊ የሚባል ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ ተመለከተና፦ ተከተለኝ አለው። ሁሉንም ተወ፤ ተነሥቶም ተከተለው።”
—ሉቃስ 5:27-28
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ሉቃስ 5:25 — “በዚያን ጊዜም በፊታቸው ተነሣ፥ ተኝቶበትም የነበረውን ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ። ”
- የያዕቆብ መልእክት 4:10 — “በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።”
- Iኛ ጴጥሮስ 5:6 — “እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 49
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።