Finding Rest in the Lord of the Sabbath
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለእረፍት ሰንበትንን መውሰድ እንኳን ብንችል አሁንም ሁሉንም ሀሳቦቻችንን፣ ሁሉንም ስጋቶቻችንን እና እንዲሁም ሁሉንም ስዕለታችንን ለእርሱ መስጠት አለብን ፤ ስለዚህ በእርሱ እረፍታችንን በመፈለግ እንዴት የተሸልን እንሆናለን ? በእስራኤል ሰንበት የእረፍት አስፈላጊ ቀን ነው ጎበኚዎች በትካሻቸዉ ካሜሪ ከተሸከሙ ይበሳጫሉ ፡፡
ዋይርስቤ ሲናገር ሰንበት “ የሰባተኛው ቀን ቅዱስነት ነው “ እንዲሁም “ የአይሁዶች እምነት የተለየ አካል እንደ ነበር” ይናገራል ፡፡ በአሜሪካ ስለ ቤተ ክርስቲያን እናወራለን እንጂ የራሱን የቀኑን ቅዱስነት በእዉነት አናስብም ፡፡ በግልፅ ሰንበት “ በእስራኤል ህዝብ እና በእግዚአብሄር መካከል የነበረ ምልክት ነበር “ (ነህ 9፡ 13-14) ፤ “ ሰንበት” የሚለው ቃል በአጭሩ ማረፍ ማለት ነው ፡፡ ዋይርስቤ አንዳንድ የአይሁች አዋቂዎች(መምህሮች) እስራኤል ሰንበትን እንደ ቅዱስ ቀን በፍፁም እንዴት እንደሚጠብቁ እስኪማሩ ድረስ መሲሁ እንደማይመጣ እንዳሰቡ ያስታዉሳል ፡፡ “ ሰንበት ከስራ በኋላ እረፍትን ይናገራል ከህጉም ጋር ይገናኛል የእግዚአብሄር ቀን ግን ከስራ በፊት እረፍትን ይናገራል ከፀጋ ጋርም ይገናኛል ፡፡ “ ሁሉም ነገር በእስራኤል በሰንበት ዙሪያ ያጠነጥናሉ ፤ ለምዕራፍ 6 ጥናታችን ይህ መነሻ ነው ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (6፡ 1-5)፡ ቁጥር 1 ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ በሰንበት በእህል ማሳ መካከል እንዳለፉ ያወራል ፤ በዉስጡ ሲሄዱ ደቀ መዛሙርቱ ሰዎስት ነገሮች አደረጉ፡ ከስንዴዉ ራስ ላይ ቆረጡ፣ በእጆቻቸዉ አሹት እና በሉት ፤ ያደረጉት ለትርፍ ሳይሆን ለመብላት ነበር ፡፡ ፈሪሳዉያን ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ያልተፈቀደውን ለምን እያደረጉ እንደነበር ጠየቁዓቸው (ቁጥር 2) ፡፡
የኃይማኖት መሪዎቹ በሰንበት መብላት የተከለከለ እንዳልነበር ያውቃሉ ፤ ሁሉም ነገር ፈሪሳዉያን ኢየሱስን ይጠይቁት የነበረው በህጉ እንዲሰራ ነበር (ማቴ 212፡ 12, 19፡ 3, 22፡ 27, 27፡ 6) ፡፡ የኃይማኖተኝነት መንፈስ የተቺነት ቋሚ ሁኔታ ምክንያት እና ለህጋዊነት ይዞ ያቆያል ፡፡
ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳን ዳዊት ወደ እግዚአብሄር ቤት በመግባት ለካህናት እንጂ ለሁሉም ያልተፈቀደዉን የተቀደሰዉን እንጀራ በላ በሚለው ምሳሌ ጥያቄአቸዉን መለሰላቸው (ቁጥር 3፡ 4; 1ሳሙ 21፡ 1-6) ፡፡ የተቀደሰዉ እንጀራ ደግሞ “ የሚታይ እንጀራ “ ተብሎ ይጠራ ነበር ፤ ማክአርቱር የፃፈው “ የመገኘቱ ቅዱስ እንጀራ ሁልጊዜ በካህናቱ ብቻ ይበላ የነበረው በእያንዳንዱ ሰንበት 12 አድስ የተጋገሩ እንጀራዎችን ይዟል “ ፤ (ዘሌ 24፡ 8-9) ፤ ዳዊት እና ሰዎቹ ተርበዋል በዚህ የሚታይ እንጀራ በሉት ፤ ከዚያም ኢየሱስ “ የሰንበት ጌታ እንደነበር “ ነገራቸው በሁሉም ነገር ጌታ ላይ ለመከላከል እየሞከሩ ነበር (ቁጥር 5) ፡፡ ኢየሱስ የህጉ ባለቤት ነው ፡፡
ማክአርቱር የጠቀሰው “ የሰንበት ህጉ የአስፈላጊ ነገሮችን ስራ አይከለክልም (ማቴ 12፡ 3-4) ፤ እግዚአብሄር ለማገልገል (ማቴ 12፡ 5-6) ፤ ወይም የምህረት ድርጊትን አይከለክልም (ማቴ 12፡ 7-8) ፡፡ “
ሉቃስ (6፡ 6-11)፡ “ቀኝ እጁ ሽባ የነበረችዉን “ (ቁጥር 6) አንድ ሰዉ ባዬ ጊዜ “ በሌላ ሰንበት ላይ ኢየሱስ ወደ ምኩራብ ገብቶ እያስተማረ ነበር “ ፤ ፃፎች እና ፈሪሳዉያን “ መክሰሻ ሊያገኙበት “ (ቁጥር 7) በሰንበት ይፈዉሰው እንደሆን ለማየት ኢየሱስን በጥንቃቄ ተመለከቱት ፡፡ የኃይማኖት መሪዎች ምንድን እያሰቡ እንደ ነበር ኢየሱስ ያዉቃል ( ሉቃ 5፡ 22) ስለዚህም የሰለለች እጅ ያለችዉን ሰዉዬ እንዲነሳ እና ወደ እርሱ በመካከላቸዉ እንዲመጣ ነገረው (ቁጥር 8) ፤ ከዚያም ኢየሱስ ፃፎችን እና ፈሪሳዉያንን በሰንበት መልካም ማድረግ ተፈቅዷል ብሎ ጠየቃቸው (ቁጥር 9) ፤ እነርሱን ተመለከተና የሰለለች እጅ ያለችዉን ሰዉዬ “ እጁን እንዲዘረጋ “ ነገረው ፡፡ ሰዉየዉ ኢየሱስ እንደ ጠየቀዉ አደረገ እጁን በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነች (ቁጥር 10) ፤ ይሁን እንጂ የኃይማኖት መሪዎቹ በቁጣ ተሞሉ ስለ ተፈወሰዉ ልጅ አልተደሰቱም እንዲሁም በኢየሱስ ላይ ምንድን እንደሚያደርጉበት መወያየት ጀመሩ (ቁጥር 11; ማቴ 23፡ 6-7) ፡፡ “ ቁጣ “ የሚለው ቃል እንደ ማይረባ ቁጣ መረዳት ይቻላል ፤ ለሉቃስ ይህ አጋጣሚ ኢየሱስን የማሳደድ የኃይማኖተኞች ስልጣን ጅማሬ ነበር ፡፡
መዝጊያ
ዮሴፍ ማትራ የኃይማኖተኝነት መንፈስ ላላቸዉ አስር ምልክቶች ያመለክታል፡
- ሌሎችን ሰዎች በራሳቸዉ ቅርፅ(መልክ) ይዳኛሉ ፡፡
- የእግዚአብሄርን ፍቅር እና ድነት ለማግኘት ይሞክራሉ ፡፡
- ያለ ዉስጣዊ ለዉጥ ለዉጫዊ ቅድስና ለማረጋገጥ ይሞክራሉ ፡፡
- ሁልጊዜ በእግዚአብሄር በሌሎች ሰዎች ጉዞ ላይ ያተኮሩ ናቸው ፡፡
- የቀረበዉ ክርስቲያናዊ ግንኙነታቸው በአገልግሎት እንቅስቃአቸው ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡
- የክርስቲያንን ተግባር ያደርጋሉ ነገር ግን ለእግዚአብሄር ስሜት የላቸው ፡፡
- ከእግዚአብሄር ከሆነ ክብር በይበልጥ በቤተ ክርስቲያን ክብር እና ስልጣን ይፈልጋሉ ፡፡
- ከክርስቶስ ይልቅ በክርስቲያናዊ የህይወት ስርዓት የተነሱ ናቸው ፡፡
- ስለ ኢየሱስ እዉነቱን ያውቃሉ ነገር ግን የኢየሱስን መንገድ አያዉቁም ፡፡
- ፅድቅን ያቅዳሉ ነገር ግን ዉስጣቸዉ በቁጣና በቅሬታ የተሞሉ ናቸው ፡፡
በኃይማኖተኝነት መንፈስ በዚህ ቦታ በምንሆን ጊዜ በእግዚአብሄር በፍፁም ረፍት ማግኘት አንችልም ፤ በእነዚህ በአስሩ በምንኖር ጊዜ በፍፁም መዝ (37፡ 7) መለማመድ አናገኝም፡ “ ለእግዚአብሄር ተገዛ ተስፋም አድርገው ፡፡ መንገድም በቀናችለትና ጥመትን በሚያደርግ ሰው አትቅና ፡፡ “
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 189.
Wiersbe, p. 189.
Wiersbe, p. 190.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1145.
MacArthur, p. 1145.
ጥያቄዎች
-
በቁጥር 2 ፈሪሳዊያን የደቀ መዛሙርቱ ድርጊት አልተፈቀደም ለምን አሉ ? ኢየሱስ እንዴት መለሰላቸው ? ሰንበትን እንዴት ታዩታላችሁ ?
-
በቁጥር 11 ፈሪሳዉያን በሰንበት በኢየሱስ ፈዉስ በሙሉነት በእዉነት ተበሳጭተዉ ነበር ወይስ የጠለቀ ትርጉም ነበረዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ትርጉሙ ምን እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
-
ደቀ መዛሙርቱ ከ12ቱ ሐዋሪያት እንደ አንድ የተመረጡ ሲሆኑ የተሰማቸዉን እንዴት ታስቡታላችሁ ?
-
ቁጥር 45 “ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና “ ይላል ፤ የዚህ ትርጉም ምንድ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
ኢየሱስ አንድን ቤት በአለት መሰረት ላይ እንዲገነባ ለምን አለ ? ሁልጊዜ ጠንካራ መሰረት ነበራችሁ ወይስ መልሳችሁ ትገነባላችሁ ?
-
በሉቃስ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 6:5
Then He told them, ‘The Son of Man is the Lord of the Sabbath.’”
ሰንበትን በትክክል ስለማክበር ፈሪሳዊያን ኢየሱስን መጠየቅ ጀመሩ፡፡ ኢየሱስ ቀጣይነት ባለው የአገልግሎት መረሃ ግብር እና በብዙ ህዝብ ጥያቄ መካከል እረፍትን አካትቷል፡፡ በተወሰነ ቀን ወይም ሰአት ላይ ላይሆን ይችላል፥ ቢሆንም ግን ኢየሱስ ለማረፍ እና ከአባቱ ጋር ለማሳለፍ ጊዜ ወስዷል፡፡ ይህ ከሰንበት ጀርባ ያለው ልብ ነው፡፡ ሆኖም የኢየሱስ ድርጊቶች ከውጪ እንደ ህገወጥ ተፈርጀዋል፡፡
እንደ አማኞች፥ ከሰንበት ህግ ጋር መታሰራችሁ አብቅቷል፡፡ ጌታ በእርሱ እንድታርፉ እና በእርሱ እንድትኖሩ ይፈልጋል፡፡ "በቂ" እንዳረፋችሁ ወይም "በቂ" እንደሰራችሁ እያሰባችሁ ፥ በሌሎች ወይም በራሳችሁ ላይ እንኳን በመፍረድ ከተጠመዳችሁ፥ የሰንበትን ሙሉ ትርጉም ታጡታላችሁ፡፡ እንደ አለታችሁ እና ደህንነታችሁ በኢየሱስ እረፉ፡፡ በእርሱ ታመኑ፡፡ ጌታ እንደሚመራችሁ በፍቅር እና በፀጋ ተሞልታችሁ ወደ ህይወት እና አገልግሎት እንድትመለሱ፥ ከሌሎች ተለይታችሁ በእርሱ እንድታርፉ ጊዜ ውሰዱ፡፡ ከእረፍት ቦታ እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስታገለግሉ፥ ለጌታ ክብር ትሰጣላችሁ፡፡ ሞክሩት፡፡ በረጅሙ ተንፍሱ እና ዛሬውኑ እረፉ፡፡
“የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው አላቸውም።”
— ሉቃስ 6:5
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 37:7 — “ለእግዚአብሔር ተገዛ ተስፋም አድርገው። መንገድም በቀናችለትና ጥመትን በሚያደርግ ሰው አትቅና።”
- መዝሙረ ዳዊት 62:5-8 — “ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና። እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም። መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው። የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው። ”
- ሉቃስ 6:12 — “በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 50
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።