The Gospels Luke

Showing Compassion One Person at a Time

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 161 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሉቃስ ወንጌል ኢየሱስን እንደ ሰዉ ልጅ እየተመለከትን ነው ፤ ኢየሱስ የሰዉ አካል በመሆን እና ወደ ምድር በመምጣት ራሱን እንደ ሰዉ ልጅ አሳየ ፡፡ ዮሐ (1፡ 14) የሚለው “ ቃልም ስጋ ሆነ ጸጋንና እዉነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ ፤ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነዉን ክብሩን አየን “ ፤ የሰዉ ልጅ ከእኛ ጋር አደረ (ኖረ) ፡፡ ምዕራፍ 7 በመቶ አለቃዉ እምነት ታሪክ ይጀምራል (ቁጥር 1-10) ፤ ከዚያም ለዛሬ ዋና ፅሁፋችንን የመበለቲቱን ልጅ ታሪክ ይሸፍናል ከሞተዉ ጋር የኢየሱስን መስተጋብር(ግንኙነት) እንመለከታለን ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (7፡ 11-14)፡ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ በሞሪያም ተራራ ሰሜን ቁልቁለት ላይ ከቅፍርናሆም ደቡብ ምዕራብ 20 ማይል ርቀት ላይ የምትገኝ እና በምስራቅ በኩል ደግሞ ኢዝራኤል ሸለቆ(በጥናትችንን ቆይተን ስለ ኤልሻ እናወራለን) ላይ ወደ ምትገኝ ናይን ከተማ መንገዳቸዉ ላይ ነበሩ ፡፡ ዛሬ ይቺ ከተማ (ናይን የተባለችዉ) 200 ይህዝብ ብዛት አላት ፤ ወደዚች ትንሽ ከተማ በር(መግቢያ) ኢየሱስ ሲጓዝ አንድ የሞተ ሰዉ በሬሳ ሳጥን አመጡ (ቁጥር 11) ፡፡

ማሳታወስ ያለባችሁ ሁል ጊዜ ኢየሱስ ስለ ጊዜ ነበር ፤ ዮሐ (11፡ 9) የሚለው “ ቀኑ አስራ ሁለት ስዓት አይደለምን ? ብሎ መለሰላቸው ፤ በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን አለም ብርሃን ያያልና ፤ አይሰናከልም ፡፡ “ ዮሐ (13፡ 1) የሚለው “ ከፋሲካ በዓል በፊት ከዚህ አለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አዉቆ “ ፤ ኢየሱስ ጊዜን ይረዳል፡፡ በምንፈስ ቅዱስ ድምፅ በምትታመኑበት ጊዜ በእርሱ እያንዳንዷን እርምጃችሁን ሁልጊዜ ትረዳላችሁ (መዝ 119፡ 105) ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ ኢየሱስ ያየዉን የቀብር ስነ ስርአት ሰልፉን ይገልፃል ፤ መጀመሪያ ሰልፉ ከከተማ ዉጪ ወደ ሚገኘው መቅበሪያ ቦታ ከከተማዋ በር እየወጡ ነበር ፤ የቀብር ስነ ስርዓቱ በሞተበት በተመሳሳይ ቀን ይካሄዳል ስለሆነም በዚያ ምሽት የሞተዉን በመጠበቅ ምንም ቤት የረከሰ አይሆንም ፤ ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት አካሉ ተቀብቷል እንዲሁም ሰልፉ በትንሻ ከተማ ያለዉን ሁሉንም ሰዉ ያከትታል ፡፡ የመበለቲቱ አንድ ልጅ ማጣት ከተማዋን(ሁሉም ህዝብ) ወደ ቀብር ስነ ስርዓት አመጣት (ቁጥር 12) ፡፡

እንደ አማኝ ወደ መበለቶች ልንመለከት (ልናፈስ) ይገባናል (ዘዳ 27፡ 19; መዝ 68፡ 5; 146፡ 9; ያዕ 1፡ 27) ፡፡ ኢየሱስ ብቸኛ አንድ ልጇን ያጣቸዉን መበለት አያት እና ለእርሷ አዘነላት (እራራላት) (ቁጥር 13) ፤ “ የእናቱ ብቸኛ ልጅ “ ከሉቃ (8፡ 42) የኢያኢሬስ ብቸኛ ልጅ እና ከሉቃ (9፡ 42) “ ሞት አፋፍ ላይ “ ስለነበረችዉ የሰዉየዉ ብቸኛ ልጅ ታሪክ ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ ብቸኛ ልጃቸዉን ላጡት ለእነዚህ ሰዎች ኢየሱስ ርህራሄ(አዘኔታ) አለው ፤ በአዘኔታው ምክንያት መበለቲቱን እንዳታለቅስ ነገራት(ዕብ 4፡ 15-16) ፡፡

“ አዘኔታ/ርህራሄ “ የሚለው ቃል ለማስነሳት ቀያሪ ጊዜ ነው ፤ አራት ነገሮች ላይ በማተኮር ርህራሄ ላይ እንዳጠና መራኝ፡ ፍቅር፣ ማዳመጥ፣ መለየት እና መመለስ ፤ እነዚህ አራት ቃሎች በመፅሀፍ የኢየሱስን ርህራሄ ስናጠና አድገዋል ፡፡ ኢየሱስ ወደ ሬሳ ሳጥኑ ሄዱ ነካው ማንም ምንም ነገር አላደረጉም ምክንያቱም ለሰባት ቀን ራሱን ርኩስ ስላደረገው (ዘኁ 19፡ 11) ፤ ኢየሱስ የሬሳ ሳጥኑን ብቻ ሳይሆን የነካው ሳጥኑንም ከፈተው በዚህም የሞተዉን ልጅ አካል ነካው (ቁጥር 14) ፡፡

ለመበለቱቱ ካለዉ ርህራሄ የተነሳ ኢየሱስ “ አንተ ጎበዝ እልሀለሁ ተነሳ ! “ አለው ሁሉም ነገር ኢየሱስ ያደረገው ከፍቅሩ እና ከርህራሄዉ የተነሳ ነው ፡፡ ለእኛ እንደ አማኝ ፀሎታችን “ ጌታ ሆይ ርህራሄዬን ጨምር ያ ከሆነ መበለቶችን እና የረከሰቱን መዉደድ እችላለሁ “ የሚል መሆን አለበት ፡፡ ስለ ወንጌል ሰዎችን በመዉደድ ዉስጥ እንድንሄድ በኃይል ምንድን ፈቃደኞች ያደርገናል ?

ሉቃስ (7፡ 15-17)፡ “ የሞተዉም ቀና ብሎ ተቀመጠ ሊናገርም ጀመር ለእናቱም ሰጣት “ (ቁጥር 15) ፡፡ የተነሳው ልጅ በተናገረው አልተደነቃችሁም ? በመፅሀፍ ኢየሱስ ይህን ሌላ ጊዜ ሁለት ጊዜ ብቻ ሲያደርግ እናያለን፡ የኢያኢሮስ ልጅን (ሉቃ 8፡ 40-56) እና አልዓዛርን (ዮሐ 11፡ 38-44) ፡፡ አስታዉሉ የጎበዙ ልጅ መልስ ፈጣን ነበር ስለነበርም ኢየሱስ ጎበዙን ልጅ ለእናቱ ሰጣት ፤ ሁል ጊዜ ኢየሱስ የሆነን ሰዉ ይነካል ፈጣንም ምላሽ ነበር፡ በህግ የስምዖን ጴጥሮስ እናት ወዲያውኑ ተነሳች (ሉቃ 4፡ 39) ፤ የቆዳ በሽታው (ለምፁ) ወዲያዉኑ ሰዉዬዉን ለቀቀው (ሉቃ 5፡ 13) ፤ በተጨማሪም ሽባዉ ሰዉዬ ወዲያዉኑ ተነሳ (5፡ 25) ፡፡ የምታገለው አንድ ነገር የክርስቶስን ስራ ከአለማየታችን እና ከፈጣኑ ምላሽ ጋር ነው !

“ ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸው ከዚያም እግዚአብሄርን አመሰገኑ “ (ቁጥር 16) ፡፡ ሁል ጊዜ የመለኮታዉ ኃይል መገለጥ(መታየት) እግዚአብሄርን ወደ ማመስገን ይመራል ፡፡ ህዝቡም ኢየሱስን “ እንደ ታላቅ ነቢይ “ አደረጉት(ለዩት) ፤ 1ነገ (17፡ 17-24) እንደ ታላቅ ነቢይ የኤልያስን ሀሳብ እና የኤልሳን እጥፍ አካታችን ይገልፃል ፤ 2ነገ (4፡ 32-37) የሞተዉን እና ተመልሶ ህያዉ የሆነዉን የመበለቲቱን ልጅ ታሪክ ያጋራል ፡፡ ኢየሱስ ህዝቡን እግዚአብሄር ምን ማድረግ እንደሚችል እያስታወሳቸው ነበር ፤ ህዝቡ ምናልባት እግዚአብሄር ለእርዳታ ሌላ ነብይ እንደ ላከ እና ከእነርሱም አንዳንዶች ኢየሱስ መሲህ እንደ ነበር ማሰባቸዉን እየተናገሩ ነበር ፡፡

ቁጥር 17 የኢየሱስ ዜና በመላዉ ይሁዳ እንደተሰራጨ ያጋራል ፤ ብዙ ህዝብም የኢየሱስን ንግግር ለመስማት ታዩ ቃሉም በጠቅላላ በአይሁድ አዉራጃ ተሰማ (ሄደ) ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በእነዚህ ትዕዛዞች “ ድዉዮችን ፈዉስ፣ ሙታንን አስነሱ፣ ለምፃሞችን አንፁ፣ አጋንንትን አዉጡ በከንቱ ተቀብላችሁ በከንቱ ስጡ “ ላካቸው (ማቴ 10፡ 8) ፤ ማቴ (10፡ 8) መጀመሪያ ሰዎችን ካልወደድን በቀር አይሆንም ፡፡ ኢየሱስ ከበር ዉጪ ላለችዉ መበለት እንደ ነበረዉ አይነት ርህራሄ ሊኖረን ይገባል ፡፡

መዝጊያ

የሆነን ሰዉ ለመዉደድ መጀመሪያ ከራሳችሁ መንገድ ዉጡ ምክንያቱም ኢየሱስ ስለ እኛ መጀመሪያ ከራሱ መንገድ ወጥቷል (1ዮሐ 4፡ 19) ፤ ፍላጎታችሁን ወደ ጎት አስቀምጡት ሰዎችን መናቅ አትችሉም (1ተሰ 3፡ 12) ፡፡

በዙሪያችሁ ባሉት ሰዎች ላይ ተፅዕኖ እንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ሁልጊዜ በፍቅር ጀምሩ ፤ ሰዎችን ስትወዱ ሰግንኙነታችሁ ወደ መደማመጥ ያድጋል ፡፡ ጥያቄዎቻቸዉን እና ታሪኮቻቸዉን ልናዳምጣቸዉ ያስፈልገናል (ምሳ 18፡ 2, 13) ፤ ማዳመጥ ከዚያ ወደ መለየት ይመራናል - በከበቡን ሰዎች እንድናደርግ እግዚአብሄር የሚመራን ምንድን ነው (ምሳ 20፡ 5) ? ሰዎቹ ከእናንተ ጋር ምንድን መጋራት እንዳለባቸው እንድትረዱት እንዲረዳችሁ መንፈስ ቅዱስን ጠይቁ ከዚያ በመቀጠል እንደ ተመራችሁት መልሱ ( ቆላ 4፡ 5-6) ፡፡

ይህ ለዉጥ ለሁላችንም መከሰት እንደሚችል አምናለሁ ነገር ግን ኢየሱስ እንዳሳየው በጊዜዉ አንድ ሰዉ ላይ

ሲከሰትማለት ነው ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1263.

ጥያቄዎች

  1. በቁጥር (1-10) በመላዉ እስራኤል የሚበልጥ እምነት አልታየም ፤ በእነዚህ ቁጥሮች ምንድን ሆነ የእምነታችሁን መጠን እንዴት ታስቡታላችሁ ? የሚበልጥ አላችሁ ?
  2. ቁጥር 28 እንዴት ነዉ የሚቻለው ? ምን ማለትስ ነው ? (ሚል 3፡ 1; ማቴ 20፡ 16)
  3. ኢየሱስ ሴቲቱን እምነቷ እንዳዳናት እና በሰላም እንድትሄድ ነገራት ፤ እምነትን እንዴት አሳየች ?
  4. በሉቃስ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 7:13

“When the Lord saw her, He had compassion on her and said, ‘Don’t cry.’”

ኢየሱስ ናይን ወደምትባል ከተማ ከደቀመዛሙርቱ እና ከብዙ ህዝብ ጋር ሄደ፡፡ እየተራመዱ ሳለ፥ ኢየሱስ ቃሬዛ ተሸክመው ሲወጡ አየ፡፡ ቃሬዛው ላይ የሞተ ሰው ነበር፥ እርሱም ለአንዲት መበለት ብቸኛ ልጅ ነበር፡፡ በሚመጡ እና በሚሄዱ ብዙ ሕዝብ መካከል፥ ኢየሱስ መበለቲቱን አይቶ ራራላት፡፡ ኢየሱስ ወደ ቃሬዛው ሄደ እና የሞተውን ሰው እንዲነሳ አለው፡፡ ሰውዬውም ተነሳ፥ ኢየሱስም መልሶ ለእናቱ ሰጣት፡፡

በብዙ ህዝብ መካከል ቢሆንም እንኳን ፥ ስታለቅስ የነበረችን አንዲት መበለት አይቶ፥ ራራላት፡፡ ነገር ግን እዚህ ላይ አላበቃም፤ ሁኔታውን አስተውሎ ለፍላጎቷ ምላሽ በመስጠት እርምጃ ወሰደ፡፡ እንደ አማኝ፥ እናንተም እንደዚሁ ለማድረግ ተጠርታችኋል፡፡ ዛሬ በመንገዳችሁ ስትሄዱ፥ የሌሎችን ፍላጎት እንድትመለከቱ እና እንደ ኢየሱስ እንድትወዷቸው አይኖቻችሁን ክፈቱ፡፡ ተግባራዊ ምላሽ እንዴት መስጠት እንድትችሉ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራችሁ ጠይቁት፡፡ ሁሉም ሰው እንደ ኢየሱስ ሰውን ለመውደድ ጊዜ ቢወስድ፥ አለምን መለወጥ ይቻላል!

“ጌታም ባያት ጊዜ አዘነላትና፦ አታልቅሽ አላት።”

— ሉቃስ 7:13

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 103:13 — “አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል ”
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 1:3-4 — “የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን። ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 3:17 — “ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 51