Jesus Casts Out Demons
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሰዉ ልጅ የሚለዉን ሀረግ ለመያዝ ጠንካራ ሊሆን ይችላል ስለዚህ በሉቃስ ጥናት ኢየሱስ ላይ እንደ ሰዉ ልጅ ለማትኮር ሞክረናል ፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሉቃስ የኢየሱስን ምንም የማይሳነዉ ኃይሉን ለማሳየት ይንቀሳቀሳል ፡፡ ይህ ክፍል(ትምህርት) ዛሬ ኢየሱስ በአጋንንት ላይ ኃይሉን ሲያሳይ እንዴት ፍቃዱን ለአባቱ እንዳስገዛ እንመለከታለን ፤ ሉቃስ 8 የኢየሱስን አገልግሎት በደገፈችዉ ሴት ላይ በመመልከት ይጀምራል (ቁጥር 1-3) ከዚያ ቀጥሎ ወደ ዘሪዉ ምሳሌ ይሄዳል (ቁጥር 4-8) ከዚያም በምሳሌ ለምን አስተማራቸዉ ወደ ሚለዉ ንግግር (ቁጥር 9-10) እና ወደ ዘሪዉ ምሳሌ ማብራሪያ ይሄዳል (ቁጥር 11-15) ፡፡ ቀጥሎም ሉቃስ ብርሃን መሆን ማለት ምን እንደሆነ ይገልፃል (ቁጥር 16-18) ከቤተሰቦቹ ጋር የኢየሱስ ግንኙነትን ይመለከታል (ቁጥር 19-21) ከዚያም በመቀጠል ባህሩ ላይ ስላለዉ ማዕበል ሌላ መግለጫ አጋርቷል (ቁጥር 22-25) ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (8፡ 26-39)፡ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ከገሊላ ደቡብ ምስራቅ ዳርቻ ወደ ጌርጌሴኖን ተጓዙ ፤ ኢየሱስ ከጀልባዋ ወደ ምድር እንደወረደ አጋንንት የያዘዉ ሰዉዬ ከከተማ እርሱን ተገናኘው (ቁጥር 26-27) ፡፡ አስታዉሉ አጋንንት ያደረበት ሰዉዬ ወደ ኢየሱስ መጣ ፤ ኢየሱስ ሰዉዬዉን አልፈለገዉም ፤ በአገልግሎት አጋንንት ይገጥማችኋል ነገር ግን ልታድኗቸዉ አያስፈልጋችሁም ፡፡
ኢየሱስን የቀረበዉ ሰዉዬ ለአመታት ከከተማ ዉጭ በመቃብር የሚኖር ነበር ልብስም አለበሰም (ቁጥር 27) ፡፡ በማቴ (8፡ 28) መሰረት ኢየሱስን የቀረቡ አጋንንት ያደረባቸው ሁለት ሰዎች ነበሩ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ሰዉዬዉ በፈለካዊ(በመከተል) ጦርነት እርስ በእርስ በሚቀዋወሙ ስልጣናት ሁለት ጎኖች የተበሳሳ አስፈፃሚ ነው “ ይላል ፡፡ ሰዉዬዉ በኢየሱስ ፊት በመደፋት በታላቅ ድምፅ “ የልዑል እግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ ? እንዳትሳቀየኝ እለምንሀለሁ ! “ አለው (ቀጥር 28) ፡፡ የአጋንንቱ የንስሀ ድምፅ ልክ እንደ ሉቃ (1፡ 31-32) ቋንቋ (የልዑል የእግዚአብሄር ልጅ) ይመስላል ፤ ነገር ግን በአምልኮ አልነበረም ግን ያለው ፡፡
ዋይርስቤ የአጋንንቱን ባህሪያት ይዘረዘራል ፤ መጀመሪያዉ እምነት አላቸው ፤ ኢየሱስ ማን እንደ ሆነ ሙሉ ለሙሉ ተረድተዋል (ኤር 2፡ 19) ፡፡ ሁለተኛው በወደፊት ፍርድ (ማቴ 8፡ 29) እና በወደፊት መሰቃየት የሚደርስባቸዉ እንደሚሆኑ ያምናሉ በተጨማሪም በወደፊት የስቃ ቦታ ያምናሉ (ሉቃ 8፡ 31) ፡፡ አጋንንቶች የወደቁ መለዓክቶች ናቸው ፤ ከሰማይ ሰይጣን በተጣለ(በወጣ) ጊዜ ከእርሱ ጋር አንድ ሰዎስተኛውን መለዓክት ወስዷል ፤ እነዚህ የወደቁ መለዓክት ናቸው በታላቅ ገደል እንደሚቀመጡ ስለ ሚያውቁ እስከዛ ጊዜ ድረስ ምድር ላይ ሲዖልን ይፈጥሯሉ ፡፡ እነዚህ የሰይጣን ተላላኪዎችእንደሚያደርገዉ ተመሳሳይ ነገር ይፈልጋሉ…..እንደሚሰርቀዉ፣ እንደሚገድለው እና ምድር ላይ ሁሉንም ሰዉ እንደሚያጠፋው ማለት ነው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን አንዱ ትልቁ ወደ ታች መዉረድ (ውድቀት) በዉጊያ ላይ እንዳለን ስለ እዉነቱ አለማዉራት ነዉ ብዬ አስባለሁ ፤ አጋንንት በእኛ ላይ እንዲመጡብን የሚጠቀምባቸዉን ጠላቶች እንዳሉን ስለ እዉነታዉ አናወራም ፤ ለዚያ ነው ጳዉሎስ እንድናሸንፈዉ የእግዚአብሄርን እቃ ጦር ልብስ እንድንለብስ የተናገረው (ኤፌ 6) ፡፡
አጋንንቱ ሰዉዬዉን በእስር እና በጥበቃ ስር ቢሆንም እንኳን ደግሞ ደግሞ ይነዳዉ ነበር (ቁጥር 29) ፤ ከዚያም ኢየሱስ የሰዉዬዉን ስም ጠየቀዉ “ ሌጌዎን “ ብሎ መለሰለት ምክንያቱም በእርሱ በጣም ብዙ አጋንንት ስለ ነበረበት ፤ ሌጌዎን የሮማዉያን ሚሊታሪ 6,000 ወታደሮች ስያሜ ነበር ይህም “ ይህ መንፈሳዊ ዉጊያን የሚያመለክት ነዉ “ ፡፡ ከአጋንንት ጋር ራሳችሁን ተፅዕኖ ለማሳደር ባገኛችሁት ጊዜ ለመናገር የምትፈሩት አትሁኑ (በኢየሱስ ስም) ስሙን እንኳን ለመጠየቅ ምክንያቱም በእኛ ዉስጥ ኃይሉ እና ስልጣኑ ስላለን ፡፡ አጋንንቱ ኢየሱስን ወደ ገደል (ጥልቁ) እንዳያስወግዳቸዉ ለመኑት (ቁጥር 31) ፡፡
ሰዉዬዉ አጋንንት ይዞት እንደ ነበር ኢየሱስ እንዴት አወቀ ? ከዶክተር ሉቃስ ምልክቶቹ እነዚህ ናቸው፡ 1) ለሰዉነት ክብር ግዴለሽነቱ (እርቃኑን መሆኑ); 2) ማህበራዊ መገለል (ከሌሎች ሰዎች ኃላ የተሳበ); 3) የረከሰዉ መጠለያው; 4) የኢየሱስን ማንነት እዉቅና መስጠቱ ( አንድ አጋንንት ፊት የክርስቶስን ስም በምትጠቅሱ ጊዜ አንዳንድ የፍራት መገለጫዎች ታያላችሁ ); 5) የንግግሩ ሰይጣናዊ ቁጥጥር; 6) ጩኸቱን ወይም ፈጣን የመገንፈል ስሜቱን ማየቱ እና 7) ታላቅ ጥንካሬ መኖሩ ፡፡ ይህ ሁሉንም ምልክቶች አያካትትም ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ኢየሱስ ያየዉን አጋንንቱን ለመለየት የፈቀደለትን ለማየት መነፅር ይሰጠናል ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ አብዛኛዉ ክርስቲያን በአጋንንት ምክንያት ግልጥ አድርጎ አይመለከትም ወደ ዚያ ለመሄድ እንፈራለን ፤ የሚያስፈራ ምንም ነገር ባይኖርም ፡፡ መጥተዉ ኢየሱስን አገኙት ፤ ወደ ጥልቁ እንዳይሰዳቸዉ ፍቃዱን ለመኑት በጥልቁ እንዳይሆኑ ለተጨማሪ ጊዜ ለመደራደርም ዝግጁ ነበሩ ፡፡ በቁጥር 32 ብዙ የእሪያ መንጋ እየተመገቡ ነበር (ማርቆስ 2,000 እሪያዎች እንደሚያክሉ ተናግሯል) ፤ ኢየሱስ ንፁህ ወዳልሆነዉ አካባቢ -ወደ እሪያዎቹ እንዲሄዱ ፍቃድ ሰጣቸው ፤ አሳማዎቹ ከተራራው እየተጣደፉ በመዉረድ በባህሩ ዉስጥ ሰመጡ ፡፡ አይሁዶች ገደሉን(ጥልቁን) ከመሬት በታች እንደ ዉሃማ ጥልቅ ቦታ ተረድተዉታል እሪያዎቹም ዋጋ አልነበራቸዉም ፤ አጋንንቶቹ የተለየ የዉሃ እስርቤት መፈለጋቸዉ አስደናቂ ነው ፡፡ አጋንንቶቹ ሰምጠዋል ነገር ግን አሁንም የወደፊቱ ፍርድ ይደርስባቸዋል(ይገጥማቸዋል) ፡፡ እረኞቹ ምን እንደተፈጠረ ባዩ ጊዜ በከተማዉ እና በአገሩ ላሉት ሰዎች ለመናገር ሮጡ (ቁጥር 34) ፤ ምን እንደ ተፈጠረ ለማየት ሰዎቹ መጡ ኢየሱስን እና አጋንንቶቹ ለቀዉት የነበረዉን ሰዉዬ ለብሶ ኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙት ፡፡ ባዩት ነገር ተደነቁ ፈሩም (ቁጥር 35) ፡፡ ኢየሱስ ሰዉዬዉን ከሁሉም አጋንንት ነፃ አወጣዉ እንጂ ከእነርሱ ከጥቂቶቹ ብቻ አይደለም ፤ ኢየሱስ በሉቃስ 4 ከምርኮ(ከባርነት) ነፃ ማዉጣት እንደሚፈልግ ተናግሯል ፡፡ የሆነ ሰዉ ከአጋንንት ነፃ በሚወጣበት ጊዜ አድስ ፍጥረት ነው አሮጌዉ ነገር አልፏል (2ቆሮ 5፡ 17) ፡፡ ሁሉም የአካባቢዉ ሰዎች በፍርሀት ኢየሱስን እንዲሄድ ጠየቁት ከእግዚአብሄር ሊመጣ እንደሚችል ምንም መንገድ እንዳልነበር አሰቡ (ቁጥር 37) ፡፡ ኢየሱስ ያለ ምንም መልስ ለመሄድ በጀልባዋ ገባ ነፃ የወጣዉም ሰዉዬ አብሮ መሄድ እንደሚፈልግ ተናገረ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ሰዉዬዉን ወደ ቤቱ እንዲመለስና እግዚአብሄር ለእርሱ ያደረገለትን ሁሉንም እንዲናገር ነገረው (ቁጥር 38) ፡፡ ማርሻል ይህን እንደ “ አርእያ ምን አይነት ቃለ ምልልስ እንደሚካሄድ ለወንጌል ሰባኪ ኃላፊነት “ ገልፆታል ፡፡
ኢየሱስ ሰዉዬዉን ከእርሱ ጋር አልወሰደዉም ምክንያቱም ወደ 12ቱ ደቀ መዛሙርቱ ላይ ማፍሰስ(መሙላት) ላይ እትኩሮ ስለ ነበር ፤ በዚያ ፋንታ ኢየሱስ ሰዉዬዉን በራሱ ማህበረስብ ዉስጥ ሄዶ እንዲናገር ላከው ምክንያቱም ወንጌል የሚሰራጭበት መንገዱ ያ ስለነበር 9ቁጥር 39) ፡፡
መዝጊያ
ቻርለስ ሱፐርገን ሰዉዬዉ ኢየሱስ እግር አጠገብ በተቀመጠ ጊዜ በግልፅ በክርስቶስ ማመኑን መለያ እንደ ነበር እና በመታዘዝ (በመገዛት) ክርስቶስን ለማገልገል ዝግጁ እንደ ነበር ተናግሯል ፡፡ እዉነተኛ ቃለ ምልልስ ሰዎች ከያዛቸዉ ከሁሉም ነገር ነፃ ሲወጡ ማለት ነው ፡፡
ለመዝጋት በአጋንንቶች ላይ ልንጠቀማቸዉ የምንችለዉን ሰባት ነገሮች እንመልከት ፤ አንድ አጋንንት በሚገጥማችሁ ጊዜ፡
- ይህ ለብቻችሁ አታድርጉ (በጥንድ አድርጉ) ፡፡
- ዝግጁ ሁኑ (ሁል ጊዜ ዉጊያ ላይ ነን) ፡፡
- በዉስጣችሁ ባለው በትንሳኤዉ ክርስቶስ ኃይል በስልጣን ተናገሩ ፡፡
- በሂደቱ ታጋሽ ሁኑ ፤ ምናልባት ወዲያዉኑ አይሆንም ፡፡
- ውስብስብ(የባሳ) አታድርጉት ፤ ኢየሱስ ምንም የባሰ (የተወሳሰበ) አላደረገም ፡፡
- የአጋንንቱን ስም ጠይቁት ፡፡
- በሂደቱ ያን ሰዉ ውደዱት ፡፡
Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Luke, p. 139; available at soniclight.com.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1267.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook Publishing, 1989), p. 202.
Wiersbe, p. 1267
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Luke, p. 138; available at soniclight.com.
I. Howard Marshall, New International Greek Testament Commentary series: The Gospel of Luke (Exeter, England: Paternoster Press, 1978), p. 341; quoted in Thomas Constable,
ጥያቄዎች
-
በሉቃ (8፡ 10) ኢየሱስ “ እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተዉሉ “ ምንድን እያለ ነበር (ኢሳ 6፡ 9) ? ኢየሱስ አዉቆ እንዳይረዱ አድርጓቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
“ እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ ፤ ላለዉ ሁሉ ይሰጠዋልና ከሌለዉም ሁሉ ያዉ ያለው የሚመስለዉ እንኳን ይወሰድበታል “ (ሉቃ 8፡ 18) ፤ ኢየሱስ በዚህ ምን ማለቱ ነው ?
-
ኢየሱስ አጋንንት ያደረበትን ሰዉዬ ከፈወሰዉ በኋላ የጌርጌሴኖን ሰዎች ኢየሱስ እንዲሄድ ለምን ጠየቁት (ሉቃ 8፡ 37) ? ምንድን ነበር የፈሩት ? አንድ ሰዉ ባየዉ እና በቀመሰዉ መሰረት እግዚአብሄርን በፈራበት ሁኔታ ሆናችሁ ታውቃላችሁ ?
-
“ ማነዉ የነካኝ “ ብሎ ኢየሱስ ለን ጠየቀ ? (ሉቃ 8፡ 45) ፤ ኢየሱስ ማን እንደ ነበር ቀዶሞ አዉቆ እንደ ነበር ታስባላችሁ ? የለበሰዉ ልብስ እንኳን ኅያል እንደያዘ ንግግሩን አስባችሁት ታውቃላችሁ ? (ማቴ 9፡ 20, ሐዋ 19፡ 11-12)
-
በቁጥር 51 ኢየሱስ ወደ ሞተችዉ ልጅ ለመግባት ለማንም አልፈቀደም ነገር ግን ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን እና ያዕቆብን ቤተሰቧን እንጂ ፤ ለምን ? ልጂቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም ያለዉ ኢየሱስ ለምንድን ነበር ?
-
በሉቃስ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 8:24-25a
“They came and woke Him up, saying, ‘Master, Master, we’re going to die!’ Then He got up and rebuked the wind and the raging waves. So they ceased, and there was a calm. He said to them, ‘Where is your faith?’”
ደቀመዛሙርቱ ቃል በቃል፥ "ልንጠፋ ነው!" በማለት ወደ ኢየሱስ ጮሁ፡፡ በባህር ላይ እየቀዘፉ ሳለ፥ በድንገት በከባድ አውሎነፋስ ውስጥ ራሳቸውን አገኙ፡፡ ውሃው ታንኳቸውን ይሞላ ነበር እና አደጋ ውስጥ ነበሩ፡፡ ወደጌታ ተጣሩ፥ ኢየሱስም ነፋሱን እና ማዕበሉን ገሠፀ እና አውሎነፋሱ ቆመ፡፡ ሰላም ወረደ፡፡
በተለመደውን የህይወት መንገዳችሁ ላይ እየሄዳችሁ፥ በድንገት፥ በአውሎነፋስ ውስጥ ራሳችሁን እንዳገኛችሁት ተሰምቷችሁ ያውቃል? ለራሳችሁ ታስባላችሁ ፦ " ምንም መውጫ መንገድ የለም፥ በጣም ከባድ ስለሆነ፥ መጥፎ ስለሆነ፥ በእርግጥ በዚህ ወጀብ እሞታለውን?" በወጀብ መካከል ማስታወስ ያለባችሁ ቁልፍ ነገር ይህ ነው፤ ወደ ኢየሱስ ጩሁ፡፡ ኃይሉ በውስጣችሁ መሆኑን አስታውሱ፡፡ ኢየሱስ ነፋስ እና ማዕበሉን ገሠጸ፡፡ በኢየሱስ ስም ማንኛውንም ነገር መገሠጽ ትችላላችሁ፡፡ ፀንታችሁ ቁሙ እና አምላክ መሆኑን እወቁ፡፡ ስሙን ስትጣሩ ሰላሙን ይሰጣል፡፡
“ቀርበውም፦ አቤቱ፥ አቤቱ ጠፋን እያሉ አስነሡት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውኃውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ተዉም፥ ጸጥታም ሆነ። እርሱም፦ እምነታችሁ የት ነው? አላቸው። ፈርተውም ተደነቁ፥ እርስ በርሳቸውም፦ እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን እንኳ የሚያዝ ለእርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? አሉ።”
— ሉቃስ 8:24-25
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 34:4 –እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
- መዝሙረ ዳዊት 138:3 – “በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፤ ነፍሴን በኃይልህ በብዙ አጸናሃት። ”
ቆላስይስ 3:15– “በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 52
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።