The Gospels Luke

Disciples, Apostles, Ambassadors

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 163 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሉቃስ ወንጌል ስዕሉን ወድጄዋለሁ ፤ በምመለከተዉ ጊዜ ሁሉም በእዉነት የሰዉ ልጅ እጆች እንደሆኑ አያለሁ ፡፡ በእዉነት መረዳት በሉቃስ 9 አገልግሎቱ ለተከታዮቹ ተመልሰዉ የክርስቶስ አካል እና የኢየሱስ እግር እና እጅ ለሚሆኑት የተሰጠ ሆነ ፡፡ የሰዉን ልጅ እንዴት እንደ እግዚአብሄር ልጅ ታደርጉታላችሁ ?

ትምህርት

ሉቃስ (9፡ 1-5)፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ በመጥራት በአጋንንት ሁሉ ላይ ኃይል እና ስልጣን እንዲሁም በሽታን እንዲፈዉሱ ኃይል ሰጣቸዉ በተጨማሪም የእግዚአብሄርን መንግስት እንዲሰብኩና በሽተኞችን እንዲፈዉሱ ላካቸው (ቁጥር 1-2) ፡፡ በጉዞ አቸዉም ከእነርሱ ጋር ምንም ነገር -ምግብ፣ ገንዘብ፣ የጉዞ በትር እና ተጨማሪ ኮት እንኳን እንዳይዙ ነገራቸው (ቁጥር 3) ፤ በአንድ ቤት ከገቡ በዚያ ይቆያሉ ፡፡ የማይቀበሏቸዉ ከሆነ በዚያ አሉት ሰዎች ላይ እንደ ምስክርነት እንዲቀር የከተማዉን አቦራ ከእግራቸዉ ላይ በማራገፍ ከተማዉን ይለቃሉ (ቁጥር 4-5) ፡፡

በሉቃስ 8 ኢየሱስ አጋንንት ከያዘዉ ሌጊዎን(ቁጥር 26-39) ተብሎ ከሚጠራዉ ሰዉዮጋር ብቻ አልነበረም የተገናኘው የኢያኢሮስን የ12 አመት ሴት ልጅ ፈዉሷል (ቁጥር 40-42, 49-56) እና አንዲት ሴት የቀሚሱን ዘርፍ በነካች ጊዜ ከእርሱ የፈዉስ ኃይል ሲወጣ ተሰምቶታል (ቁጥር 42-48) ፤ እነዚህ አጋጣሚዎች ወይም መስተጋብሮች ለምዕራፍ 9 መነሻዎች ናቸው ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ እነዚህን ክስተቶች ተመልክተዋል ለመፈወስ እና አጋንንቶችን ለማስወጣት ኢየሱስ የነበረዉን ኃይል ይመሰክራሉም እንዴት እንደሰራቸዉም ተደንቀዋል ፡፡

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን(ከግሪኩ ማቴትስ ወይም ተማሪ ከሚለዉ ቃል የመጣ ነው) በአንድ ላይ ጠራቸው ምናልባትም ከቀኑ በፊት ሆኖ የነበረዉን ለእነርሱ በመግለፅ ኃይልን ሰጣቸዉ ስለዚህ ከእርሱ ተቀብለዉት የነበረዉን ስልጣን እና ኃይል ይረዱታል ፡፡ ኃይል ለሚለዉ ኢየሱስ የተጠቀመዉ የግሪክ ቃል ዳይናሚስ ሲሆን ትርጉሙም “ ችሎታ “ ወይም የሆነን ነገር ከራስ በላይ የመስራት ችሎታ ማለት ሲሆን ስልጣን ለሚለው ኢየሱስ የተጠቀመዉ የግሪክ ቃል ኤክሶሺያ ሲሆን ትርጉሙም “ ኃይልን የመለማመድ መብት “ ማለት ነው እናም የነበረዉን የሆነ ነገር ደቀ መዛሙርቱ የነበራቸዉን ያምናሉ ፡፡ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ምንም ነገር እንዳይዙ ነገራቸዉ ስለዚህም እንዲያደርጉ የነገራቸዉን ለማድረግ በኢየሱስ እጅ ላይ የሚደገፉ ይሆናሉ ፡፡ ኢየሱስ መንግስቱን አሳይቷቸዉ ስለ ነበር እንዴት እንደሚሰራ ያዉቃሉ እንዴት ሁሉም እንደሚሰራ ማየት ችለዋል ፤ ያም የሚያስደነቁ ተዓምራቶችን እንዲሁም ክስተቶች (ልክ እንደ ጴጥሮስ መልኩ መለወጥ ላይ እንዳየው) ሰዎቹ ኢየሱስን በተቹት ጊዜ፣ ሲስቁበት እና ሲዘባበቱበት እንኳን ለማየት ይፈቅድላቸዋል ፡፡

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ(ተከታዮቹ) እስካሁን ባልታየዉ ነገር ግን ተስፋ በሆነው በመንግስቱ ዜግነት አላቸው ፤ ደቀ መዛሙርቱ ማን እንደሆነ ይረዱታል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እስካሁን ድረስ ብዙ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ከደቀ መዛሙርነት ዉጪ ናቸዉ እንደዉም ምን ማለት እንደሆነ እንኳን አያዉቁም ፤ ይሁን እንጂ በሉቃስ 9 ኢየሱስ ይህን እያደረገ ነበር ፡፡ አንድ ደቀ መዛሙርት አንድን ነገር ካላወቀ/ች ወይም ካልተረዳ/ች ስለዚህ ይወስደዋል/ትወስደዋለች ፡፡

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለእነርሱ ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ እንዲያደርጉ እየነገራቸው ነበር ነገር ግን ከተፈጥሮ በላይ የሆነ እና የሌላ መንግስት የነበረን የሆነን ነገር ሊሰጣቸው ፈለገ ፡፡ ኢየሱስ የሰዉ ልጅ እና የእግዚአብሄር ልጅ ነው ፤ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ስለሆነ የሰዉን መንግስት ወረረ ስለዚህም የሰዉ ልጅ መሆን በመቻሉ የእግዚአብሄርን መንግስት አሳያቸው ፤ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ የማይታየዉን መንግስት እና መልክ እንዲያዩ ፈለገ ምክንያቱም ነገር መንካት ስለሆነ ፡፡ እነዚህ ሁለት መንግስት ወደ ግጭት በሚመጡ ጊዜ መለዓክት ወደ ምድር አካባቢ ለመናገር እንኳን ሲመጣ በምድር ለመሬት መናወጥ ምክንያት ይሆናል ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የምድርን መንግስት በወረረ ጊዜ በእግዚአብሄር መለኮታዊ ኃይል እና በሰዉ ተፈጥሮአዊ ኃይል መካከል እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ በዚያ ምክንያት ምድር ላይ የሚሆኑ ነገሮች አሉ መቅሰፍት እንደሚኖር አምናለሁ ፡፡

በሉቃስ 8 ኢየሱስ በሁኔታዉ ተጓዘ ለጌዎንም የእግዚአብሄር ልጅ ሆይ ለምን ወደኛ መጣህ ብሎ በመጠየቅ ተናገረው ፤ በእግዚአብሄር በእዉነተኛ ኃይል እና ስልጣን በተገኘ ጊዜ ሁል ጊዜ ማስፈራራት በጣላት ላይ በመሆን ይሰራል ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በዚህ ስልጣን እንዲሄዱ እና አይተዉት የነበረዉን እንዲሰብኩ ነገራቸው - የእግዚአብሄርን መንግስት ( በሰማይ እንዳለ በምድር ላይ መንግስቱ ይመጣል የተፈፀመ ይሆናል) እንዲሁም ከእነርሱ ጋር ምንም አይነት ምርኩዝ……ማንኛውንም እንዲያደርጉት ከተላኩበት አይምሯቸዉን የሚወስድ ነገር እንዳይዙ ነገራቸው ፡፡ ከራሳቸዉ ከሆነዉ ኑሮ ምንም እንዳይወስዱ ፈለገ በዚህም በእግዚአብሄር መለኮታዉ ኃይል እና ስልጣን ላይ መደገፍ ይችላሉ ፡፡

ለጥቂት ጊዜ በሪቫይቭ ት/ቤት ናችሁ አሁን ፤ እያጠናችሁ እና እያነበባችሁ ነዉ ከእናንተብ አብዛኞቻችሁ ራዕዮች አሉዓችሁ ፤ ከእናንተ ዉስጥ አንዳንዶቻችሁ ወደ ሆነ ቦታዎች ተጉዛችኍ ወዲያዉኑ በዚያ ቦታ የእግዚአብሄር መገኘት እንዳለ አዉቃችኋል ወይም በዚያ እግዚአብሄር እንደሌለ የታወቀ ነው ፤ እያደረጋችሁት ያለው በጠለቀ ደረጃ በመንፈስ ቅዱስ ለመጓዝ እየተማራችሁ ነው በተጨማሪም የት እንደ ምትኖሩ በተፈጥሮ መረዳት ጉዞ የላችሁም ማለት ነው ፡፡

በመፅሀፍ ደቀ መዛሙርቶች አሉ ከዚያም በመቀጠል ሐዋሪያቶች፣ ዜግነት አለ ከዚያም በመቀጠል አምባሳደርነት (አምባሳደር የላከዉ ተወካይ ነው) እንዲሁም የማስተማር ችሎታ አለ ከዚያ በመቀጠል ኃላፊነት አለ ፡፡ ለምሳሌ ሙሴ እስራኤላዊያንን ከምድረበዳ ባወጣቸዉ ጊዜ የወተት እና የማር የሆነች ምድር ተስፋ ተገብቶላቸዉ ነበር ፤ ነገር ግን ሰላዮቹ ተመልሰዉ በተስፋይቱ ምድር የነበሩት ጠላቶቻቸዉ ምን ያክል ትልቅ እንደ ነበሩ ህዝቡን ነገሩት ፤ በቂ እምነት ከመኖር ይልቅ የምርኮኝነት አስተሳሰብ ስለ ነበራቸው ህዝቡ እንዲያደርጉት ተሰጥቷቸዉ የነበረዉን ማድረግ እንደማይችሉ ተናገሩ ፤ በዚያም ፋንታ በምድረበዳ የደቀ መዛሙርትነት 40 አመት አሳለፉ ፡፡ አጭር ጉዞ ላይ ደቀ መዝሙርነትን አልተማሩም ስለዚህ የረጅም ጊዜ ት/ቤት ዉስጥ ገቡ (ሄዱ) ፤ መሄድ የቻለው ህዝብ የእግዚአብሄርን ተስፋ በፍፁም አልቀመሱም በምድረበዳ ሞቱ ፡፡

በሚያናድድ ሁኔታ በኡኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን አካል የሞተ ነው ፤ በእግዚአብሄር ኃይል እና ስልጣን አልተጓዝንም ነገር ግን የረጅም ጊዜ የደቀ መዝሙርነት ፕሮግራም አድርገነዋል ፡፡ ወደ አምባሳደርነት አልገባንም ወይም ከመማር ሁኔታ ይልቅ በብዙ ኃላፊነት ሁኔታ ለመጋዝ አልተማርንም የእግዚአብሄርንም ኃይል በእኛ እንዳይሰራ ካድን ፡፡ በመልክ የኢየሱስን ፊት ለማየት እንፈልጋለን ስለዚህም ሁል ጊዜ የምንገለገል አንዶቹ ነን ፤ ኢየሱስ ያን ሊያደርግ አልመጣም ፡፡ በሰዉ ልጅ ልብስ እንደ እግዚአብሄር ልጅ መጣ ስለዚህም የሰዉ ልጆች እንደሆንን እንዴት የእግዚአብሄር ልጆች እንደምንሆን ማስተማር ቻለ ፤ የመንግስቱ ሀሳብ መረዳት ያ ነው ፡፡ ስልጣን ሊሰጠን መጣ - የመንግስቱን ዜግነት ሀሳብ በመቀበል በሌላ መንግስት የዚያ መንግስት አምባሳደሮች አደረጋቸው ፤ ስለዚህም የብርሀን ልጆች በምንሆን ጊዜ አሁን በጨለማዉ መንግስት ዉስጥ የእግዚአብሄር መንግስት አምባሳደሮች ነን ፤ ይህ ማለት በዚህ አለም የተረጋጋ(ደህና) የሆኑ ሰማያትን ኢምባሲዎች መትከል እንችላለን ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን የታዘዘችዉ ይህን ነው …የመፅናኛ እና የመታደሻ ቦታ ሲሆን የምንኖርበት ቦታ አይደለም ፡፡ በመንግስቱ እንኖራለን እንጂ በኢምባሲዉ አይደለም ፤ በሌላ ህዝብ መስራት እንችላለን ነገር ግን አሁንም በሀገራችን ስልጣን ስር ነን ፡፡

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በአጋንንት ሁሉ ላይ እና ደዌዎችን እንዲፈዉሱ በኃይል እና በስልጣን ላካቸው ፤ ያ ማለት አግኝተዉታል ? በማቴ (17፡ 14-21) (ማር 9፡ 17-27) አንድ ሰዉ የሚጥል በሽታ የነበረበትን ልጁን እንዲፈዉሱለት ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው ነገር ግን አልቻሉም ፡፡ ሰዉዬዉ እምነት ስለጎደላቸዉ ደቀ መዛሙርቱን የገሰፃቸዉን ኢየሱስን ነገረው ከዚያም ከልጅዬዉም ላይ አጋንንቱን አስወጣው ልጁም ተፈወሰ ፤ ከዚያም በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን እነርሱ ለምን አጋንንቱን ማስወጣት እንዳልቻሉ ጠየቁት ኢየሱስም እምነት ጎድሏቸዉ እንደ ነበር መለሰላቸው ፡፡ ቁጥር 21 “ ይህ አይነቱ ግን ከፀሎት እና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው “ በማለት ያጠቃልላል ፡፡ የመንግስቱ ደቀ መዛሙርት ከሆንን ከሚኖሩበት ከግጭት መንግስት ጥገኝነት ለሚፈልጉት ወደ ነፃነት እና ደህና ስፍራ እንድ ናመጣቸዉ ለሚፈልገዉ አምባሳደሮች እንሆናለን ፡፡

ቁልፍ መርህ አለ - የተሰጠ ስልጣን እና ከፀሎት እና ከፀሞ የሚመጣ በዚህ መንግስት ልምድ የተረዳዉን ስልጣን አለን ፡፡ ኢየሱስ በአጋንንት ሁሉ ላይ ስልጣን ሰጥቷቸዉም ስኬታማ አልነበሩም ሌላ ቁልፎች ያስፈልጋቸዉ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች ማን እንደ ነበር ማን እንደሚሉት እና ማን እንደ ነበር እንደሚያምኑ ጠየቃቸው ጴጥሮስ “ አንተ የህያዉ እግዚአብሄር ልጅ ክርስቶስ ነህ “ አለው ፤ ኢየሱስም ይህ መረዳት ከመለኮት እንደተሰጠዉ መለሰለት እና የመንግስቱን ቁልፎች እሰጥሀለሁ አለው ፡፡ እነዚህ ቁልፎች ሲመለሱ ኢየሱስ የነገራቸዉን እንደሚያካትት አምናለሁ - አጋንንቶችን የማስወጣት ኃይል በፀሎት እና በፆም በኩል ብቻ እንደሚሆን (የመንግስቱ ሁለት ቁልፎች ) ፡፡

መዝጊያ

ማቴ (13፡ 58) የሚያወራው ኢየሱስ በተወለደበት አገር ነበር ባለማመናቸዉ ምክንያት ብዙ ነገሮችን አላደረገም ፤ በዚያ ስፍራ ለመስራት እንደ ሰዉ ልጅ መጥቶ የነበረው ከእግዚአብሄር ልጅ ከነበረው ከኢየሱስ ጋር ምንም ትብብር አልነበረም ፤ አላገለገላቸውምክንያቱም ሊያገለግሉት ስላልቻሉ ፡፡

በሉቃ (9፡ 10) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በአንድ ላይ እንደ መምህራቸው ጠራቸው (አስታዉሉ በሉቃ(9፡ 1) ባደረገው “ሐዋሪያት” የሚለዉን ማዕረግ አልተጠቀመም) ፡፡ በመንፈስ ለመጓዝ ስልጣን እና እዉቀት እንደ ነበራቸው አሳያቸው ፤ በብዙ የኢየሱስ እጆች ለመሆን ኃላፊነት፣ ኃይል እና ስልጣን አለን ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Luke, p. 144; available at www.soniclight.com.

ጥያቄዎች

  1. በቁጥር 3 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ለመስበክ በሄዱ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ምንም ነገር እንዳይዙ ለምን አዘዛቸው ?
  2. 12 ሙሉ ቅርጫት መትረፉ መጠቀሱ አስፈላጊነቱ ምንድን ነበር ?
  3. የሉቃስ 9 ጥብቅ ጥቅሶች 23-25 ፤ መስቀሉን መሸከም እና ኢየሱስን መከተል ማለት ምን ማለት ነው ? ለእናንተ ይህ ምንድን ይመስላል ? ነፍሱን የሚያድናት ያጣታለ ማለትስ ? አለምን ሁሉ ቢያገኝ የሚያገኝ ነፍሱን ያጣል ማለትስ ? በዚህ አገላለፅ (ሀሳብ) “ ህይወትን “ እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
  4. በዘጸ (34፡ 29-30) እና በሉቃ (9፡ 29) መካከል ልዩነቶቹ ምንድና ናቸው ? ተመሳሳይነቶቹስ ምንድን ናቸው?
  5. ከቁጥር 62 ኋላ ስላለዉ ትርጉም ምን ታስባላችሁ (2ጢሞ 4፡ 10) ? በራሳችሁ ህይወት ይህ ምን ይመስላል?
  6. በሉቃስ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 9:23

“Then He said to them all, ‘If anyone wants to come with Me, he must deny himself, take up his cross daily, and follow Me.’”

ደቀመዛሙርቱ ጌታ ከአምስት እንጀራ እና ከሁለት አሣ በተአምራዊ ሁኔታ ለአምስት ሺህ ሰዎች (ሴቶች እና ህፃናትን ሳይጨምር) ያዘጋጀውን የዳቦ እና የዓሣ ቅርጫት በማከፋፈል ረዱት፡፡ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ማስተማሩን እና ማዘዙን ቀጠለ፡፡ አላቸው፥ " በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡" በመሰረቱ እውነተኛ የእርሱ ደቀመዝሙር ለመሆን ፥ ራሳችሁን መካድ አለባችሁ እያለ ነበር፡፡ አዎ፥ መስቀልን መሸከም የሚያም እና የሚያዋርድ ቅጣት ስለሆነ ህመም ይኖረዋል፡፡

ዕለት ዕለት ማለት በየቀኑ ማለት ነው፡፡ በየዕለቱ፥ በህመም እና በመከራ ውስጥ እንኳን ቢሆን፥ ራሳችሁን እንድትክዱ እና እንድትከተሉት ኢየሱስ ይጠይቃችኋል፡፡ ዛሬ ራሳችሁን መካድ ለእናንተ ምን ይመስላል? ራሳችሁን በመካድ እና ደስታችሁን እና ምኞቶቻችሁን በመተው፥ እውነተኛውን ማንነታችሁን እንደምታገኙ ኢየሱስ ቃል ገብቷል፡፡ ደስታን ታገኛላችሁ፡፡ ሰላምን ታገኛላችሁ፡፡ ነፃነትን ታገኛላችሁ፡፡ አለም የሚለው ምንም ይሁን ምን፥ ገፍታችሁ ሂዱ እና በእርሱ ታመኑ፡፡ እርሱ ታማኝ ነው፡፡

“ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።”

—ሉቃስ 9:23

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ዳንኤል 1:8 – “ዳንኤልም በንጉሡ መብልና በሚጠጣው ጠጅ እንዳይረክስ በልቡ አሰበ፤ እንዳይረክስም የጃንደረቦቹን አለቃ ለመነ። ”
  • ሮሜ 8:12-13 – “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕዳ አለብን፥ እንደ ሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም። እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። ”
  • 1ኛ ጴጥሮስ 2:11 – “ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 53