The Gospels Luke

A Place at the Table

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 164 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሚኒዲ ስዕል ለሉቃስ የኔ ምርጫ ይሆናል ፤ ሁሉም ወደ ግብዣዉ ስለ መምጣት እና እንዴት ሁሉም እንደተጋበዙ ፡፡ ወንጌልን ማካፈል እወዳለሁ ስለሆነም በሉቃስ 10 ዉስጥ በመፀለይ 70ባዎቹ ወደ ተላኩበት ምክንያት እና ንስሀ ከሌላቸዉ ከተሞች ጋር በተካፈለው በቀላሉ ተደግፌአለሁ ፤ ነገር ግን የመልካም ሰማሪያን ምሳሌ በተመለከትኩ ጊዜ ወደ ግብዣዉ ስለ ተሳበዉ አስባለሁ ፤ ለዛሬ ጥናታችን ያ ነው ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (10፡ 25-29)፡ አንድ ህግ አዋቂ ኢየሱስን ሊፈትነዉ ፈለገ ፤ ህግ አዋቂዉ በሙሴ ህግ ሊቅ ነበር እንዲሁም ኦሪትን እና ቶራን ያውቃል ፤ የኢየሱስን የኃላ ዳራ በማወቁ ህጉን ቢያዉቅም ሊያምነዉ አልቻለም ፡፡ ህግ አዋቂዉ የተለመደ ጥያቄ አቀረበ (ማቴ 19፡ 16; ማር 10፡ 17; ሉቃ 18፡ 18) ፡፡ ንጉስ ሰለሞን ሁሉም ሰዉ በልቡ ለዚሕ ጥያቄ መልስ እንደሚፈልጉ ተናግሯል ፤ ህግ አዋቂዉ ኢየሱስን “ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ ? “ አለው (ቁጥር 25) ፡፡

እንደ ጥሩ መምህር ኢየሱስ ህግ አዋቂዉን “ በህግ የተፃፈዉ ምንድን ነው ? እንዴትስ ታነባለህ ? ” አለው (ቁጥር 26) ፤ ኢየሱስ ህግ አዋቂዉን ወደ ራሱ ጥናት ተመልሶ እንዲሄድ እና ለእርሱ የተረዳዉን እንዲገልፅለት እያደረገው ነበር ፤ ኢየሱስ ህግ አዋቂዉን እያስቀመጠው ነበር (ገላ 2፡ 16) ምክንያቱም ህግ አዋቂዉ ህጉን ከራሱ መረዳት የኢየሱስን ጥያቄ ሊመልስ የሚችልበት ምንም መንገድ አልነበረም (ገላ 3፡ 21) ፡፡ አዋቂዉ “ ጌታ አምላክህን በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ዉደድ አለው “ (ዘሌ 19፡ 18; ዘዳ 6፡ 5 - የህጉ ዋና ቃል) ፤ መፅሀፍን ጠቀሰ ነገር ግን ርዕሳ ላይ አልነበረም ፡፡ ኢየሱስ ህግ አዋቂዉን እነዚህን ሁሉ 100 ፐርሰንት ማድረግ ከቻለ እንደሚኖር ነገረው (ዘሌ 18፡ 5; ሕዝ 20፡ 11) ፤ ኢየሱስ በመመለስ መፅሀፉን ጠቀሰ ፤ ህግ አዋቂዉም ለማድረግ ቀላሉን አካፍሎት የነበረዉን ያውቃል ስለዚህ ራሱን ለማፅደቅ ሌላ ጥያቄ “ ባልንጀራዬስ ማነው ? ” አለዉ (ቁጥር 29; ገላ 3፡ 10-13) ፡፡ እዉነታው ህግ አዋቂዉ የተመረጠ ቡድን የሚሆነዉ ማን እንደሆነ ለማወቅ መፈለጉ ነው - አንድ የሚመስሉት፣ ተመሳሳይ የሚሸቱት እና ተመሳሳይ የሚያምኑት ፤ ወዳጃችን ማን እንደሆነ ይህን ጨዋታ ለመጫዎት ለእኛ በቤተ ክርስቲያን ቀላል ሊሆን ይችላል ፡፡ መዝ (139፡ 21-22) ይህን ስፍራ ይገልፀዋል፡ “ አቤቱ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን ? ስለ ጠላቶችህም አልተሰቀቅሁምን ? ፍጹም ጥል ጠላኋቸው ጠላቶችም ሆኑኝ ፡፡ “

ሉቃስ (10፡ 30-35)፡ በምላሹ ኢየሱስ እዉነት የሆነ ታሪክን ወይም ምሳሌ መናገር ጀመረ ፤ ኢየሱስ እንደ አንዱ አለየዉም ፤ ኢየሱስ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ይጓዝ ስለ ነበር 3,300 ጫማ እና 17 ማይል ያክል ወደታች ስለ ወረደ አንድ ሰዉ ተናገረ ፡፡ ሰዉዬዉ ልብሱን ወሰዱበት፣ እመቱት እና በሞትና በህይወት መሀከል አድርገዉ ጥለዉት እሄዱት ዘራፊዎች ላይ ወደቀ (ቁጥር 30) ፤ ሰዉዬዉ ራቁቱን እና ተጎድቶ ነበር ፡፡ አንድ ካህን መንገዱ ላይ ወረደ በሞትን በህይወት መካከል ያለዉን ሰዉዬ አየው በስርዓቱ ንፁህ እንደሆነ ለመቆየት በመንገዱ በሌላኛው በኩል ሄደ (ዘላ 21፡ 1) ፤ ካህኑ በሞትና በህይወት መካከል ያለዉን ሰዉዬ ወደ ግብዣዉ ለመጋበዝ በፍፁም አልቻለም ፍቃደኛም አልሆነም ፡፡

ከዚያም አንድ ሌዋዊ በዚያ ስፍራ ደረሰ ሰዉየዉን አየው በመንገዱ በሌላኛዉ በኩልም ሄደ (ቁጥር 32) ፤ የሌዋዉያን ተግባር ለካህናቱ ለመስጠት መስዋዕት መሰብሰብ ነበር ፤ ይህን ሰዉዬ ለመርዳት ይችላል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪ የሚለው “ የኃይማኖት ስርዓቱን ርህራሄ የሌለው እንደሚሆን እና እንደ ተራ ስም እና የተለመደ ቦታ እንደ ማገልገል እድሉን ለማይት ለሚይዙት ቀላል ነው “ ፤ ዛሬ እዚህ ፅሁፍ ላይ ያመጣኝ ምክንያቱ ይህ እንደ ሆነ አስባለሁ ቤተ ክርስቲያን ጠንቃቃ ካልሆነች በብዙ በጣምበብዙ እንደዚህ ካህን እና ሌዋዊ እየሆንን እንቀጥላለን ፡፡

ከዚያም አንድ ሳምራዊ በጉዞዉ ላይ መጣ በሞት እና በህይወት መካከል ያለዉንም ሰዉዬ አየዉ አዘነለትም ፤ ከመንገዱ ወጥቶ በመሄድ (ወደ እርሱ መጣ) ቁስልቹንም በዘይት አስታገሰለት እና በቫንዴጅ አሰራቸው ከዚያም እርቃን እና በደም የተሸፈነዉን ሰዉዬ ወደ ቅርብ ትንሽሄቴል በራሱ እንስሳ(አህያ) ወሰደው ፤ ሰዉዬዉንም ተንከባከበው (ቁጥር 33-34) ፡፡ Bible.org (https://bible.org/) የሚለው ሳምራዊዉ ያሳየው፡ 1) አዘኔታ(ርህራሄ), 2) እንክብካቤ እና 3) የሰዉዬዉን የእንክብካቤ ወጪ መክፈል (ቁጥር 35) ፡፡ 2ቆሮ (9፡ 7) የሚለው “ እግዚአብሄር በደስታ የሚሰጠዉን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ በኃዘን ወይም በግድ አይደለም ፡፡ “ ለሰዉዬዉ መንከባከቢያ ሳምራዊዉ የተወዉ ሁለት ዲናር ለ 24ቀን ቆይታዉ ይሸፍንለታል በተጨማሪም የትንሽ ሆቴል ጠባቂዉን ሌላ ተጨማሪ ወጢዉን ለመክፈል ተመልሶ እንደሚመጣ ነገረው ፤ ያዕ (2፡ 15-16) ፤ ሳምራዊዉ አንድ ሰዉ ለመንከባከብ የሚችለዉን ሰጥቷል ያውም ለማያውቀዉ ፡፡

ኢየሱስ በሰማይ እንደ ሊቀ ካህን ካርዱን መጫወት ይችላል ከሰዎች ጋር መስተጋብር ለማድረግ ወደታች እንደ ሰዉ ልጅ መምጣት አያስፈልገዉም ፤ ሲያየን በሞት እና በህይወት መካከል ነበርን ኢየሱስ በርህራሄ እና ሊንከባከበን ወደታች መጣ ፤ በግልፅ ኢየሱስ ይህን ለማድረግ ህይወቱን ሰጠ ፡፡ ሁሉንም ለራሳችን ልክ እንደ ካህኑ እና ሌዋዊይ ለመኖር በመፈለግ አዘነበልን ነገር ግን ኢየሱስ ለሁሉም ሰዉ ግብዣዉ ላይ የመቀመጥ አድል እንዲኖራቸወ እንደ መጣ ያሳስበናል ፡፡

ሉቃስ (10፡ 36-37)፡ ኢየሱስ ህግ አዋቂዉን ከእነዚህ ከሰዎስቱ (ከካህኑ፣ ከሌዋዊዉ እና ከሳምራዊዉ) ለተጎዳዉ ሰዉዬ ወዳጁ የተኛዉ እንደ ነበር እንደወስን ጠየቀው ፤ ኢየሱስም አዋቂዉን ስለ ህጉ ሁሉንም ነገር ያዉቃል ነገር ግን ለመተግበር ዝግጁ አልነበረም አለው ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሁሉንም ነገር እናውቃለን ነገር ግን በመንገዱ በኩል ላይ ወዳሉት ሰዎች ለመሄድ እምቢ ካልን ማወቃችን ፈፅሞ ዋጋ የለውም ፤ ይህ ወደ ግብዣዉ በፍፁም ያልጋበዝናቸውን ለሚጠፋት እና ለተጎዳ በጣም ርህራሄ የለለው ሆነናል ማለት ነው ፡፡

በቁጥር 37 ኃይማኖተኛዉ ህግ አዋቂዉ ሰዉ “ ምህረት ያደረገለት አለ “ ፤ ህግ አዋቂዉ ሳምራዊዉ አድርጎት ለነበረዉ እንኳን እዉቅና መስጠት አልቻለም በሳምራዊዉ በከፈውተኛ ጥላቻ ተይዞ ነበር ፤ እናም ኢየሱስ ሄዶ ተመሳሳይ እንዲያደርግ ነገረው ፡፡ ለሚለምኗችሁ ሄዳችሁ አዘኔታችሁን አሳዩ ፤ ሄዳችሁ እንደ ሳምራዊዉ ኑሩ ፡፡

መዝጊያ

በBible.org መሰረት ዘራፊዎቹ “ የአንተ ሁሉ የእኔ ነው እቀበልሀለሁ “ ይላሉ ፤ ኃይማኖተኛ ሰዎቹ ደግሞ “ የእኔ ሁሉ የእኔ ነዉ እጠብቀዋለሁ “ ይላሉ ፤ ነገር ግን በደጉ ሳምራዊ እና በኢየሱስ የምናየው “ የእኔ የሆነዉ የአንተ ነው አካፍልሀለሁ ፤ አካፍለዋለሁ እንጂ አልወስደዉምም አልጠብቀዉምም “ ፡፡

ስለ ሰዉ ልጅ በማስብ ጊዜ ያደረገው - ርህራሄዉ፣ እንክብካቤዉ እና የእርሱ ግብዣ ስፍራ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉንም ነገር ሰጠ ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p.1273.

  2. Nelson’s Commentary, p. 1273.

ጥያቄዎች

  1. በቁጥር 2 ለሰራተኞች እንድንፀልይ ተነግሮናል ፤ ራሳችሁን እንደ ሰራተኛ ታዩታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላያችሁትም ?
  2. በቁጥር 19 “ እናንተ/አንተ “ በሚለዉ ቃል ላይ ስማችሁን አስቀምጡ ፤ ለእናንተ የዚህ ቁጥር ትርጉም እና ኃይል ይቀየራል ? ለምን ወይስ ለምን አይቀየርም ?
  3. በቁጥር 25 የዘላለም ህይወት “መዉረስ “ ማለት ምን ማለት ነው ? ይገኛል/የሚገኝ ነው ? ለምን ወይስ ለምን አይገኝም ?
  4. በቁጥር 27 የህግ አዋቂዉ ዘዳ (6፡ 5) እና ዘሌ (19፡ 18) ጠቀሰ ፤ በኢየሱስ ጊዜ ይህ ተመሳሳይ ትርጉም አለው ? ያን ለምን ታስባላችሁ ?
  5. ቁጥር (38-42) ጌታን ስለ ሚወዱት ሁለት እህትማማቾች እና በተለያዬ ነገር እንደ መጡ ይናገራል ፤ በመካከላቸዉ የነበረው ልዩነት ምን ነበር ? በጣም ማንን እንደ ምትመስሉ ታስባላችሁ ፡ ማሪያምን ወይስ ማርታን ? ለምን ?
  6. በሉቃስ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ወስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 10:41-42

“The Lord answered her, ‘Martha, Martha, you are worried and upset about many things, but one thing is necessary. Mary has made the right choice, and it will not be taken away from her.’”

ኢየሱስ ሲጓዝ ሳለ፥ ወደ ቢታንያ መጣ፥ በዚያም የአላዛር እህቶች ፥ ማርያም እና ማርታ፥ በቤታቸው ተቀበሉት፡፡ ኢየሱስ በቤታቸው ተቀምጦ ሲያወራ፥ ማርያም በእግሩ ስር ተቀምጣ የሚናገረውን ስትሰማ፥ ማርታ ግን በብዙ ነገር ተዘናግታ ነበር፡፡ ማርታ የማርያም እንደ ደቀመዝሙር መቀመጧ እና ኢየሱስን ማዳመጧ ረብሿታል፡፡ ማርታ ማርያም እንድታግዛት ትፈለግ ነበር፡፡ ነገር ግን፥ ኢየሱስ ለማርታ የማርያም ምርጫ ትክክል እንደሆነ በመናገር መቀመጧን እና ማዳመጧን አፅንቷል፡፡

የምትኖሩት በሥራ በተጠመደ አለም ውስጥ ነው፡፡ ልክ እንደ ማርያም፥ በጣም ብዙ ሥራዎች አሉን፡፡ ቀናችሁ ለሀያ አራት ሰአት በሚሰሩ ተግባሮች ተሞልተው በሥራ ትጠመዳላችሁ፡፡ የምትሰሩት የእናንተን ሥራ እንኳን ባይሆን፥ ጓደኞቻችሁ ፣ ቤተሰቦቻችሁ እና የሥራ አጋሮቻችሁ እርዳታችሁን ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም በሥራ በመጠመድ ውስጥም ሆናችሁ ትክክለኛው ምርጫ በኢየሱስ እግር ስር መቀመጥ እና የሚናገረውን ማዳመጥ ነው፡፡ ቀናችሁ ምንም ነገርን ይያዝ፥ ተቀምጣችሁ ኢየሱስን ለመስማት ጊዜ ውሰዱ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱስን ከፍቶ የእግዚያብሔርን ቃል ማንበብን ሊመስል ይችላል፡፡ ይህ በእርጋታ ተቀምጦ መፀለይ እና የአለም ትርምስ በዙሪያችሁ እስኪረጋ ቆም ብሎ መጠበቅ ማለት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ዛሬ፥ ብዙ ነገር ማድረግን አቁሙ፡፡ የሥራ ዝርዝራችሁ ባይፈፀምም እንኳን፡፡ ዝርዝሮቹን ከመጀመራችሁ በፊት እንኳን ተቀመጡ፡፡ ኢየሱስ ለልባችሁ የሚያወራውን አዳምጡ፡፡ "ትክክለኛው ምርጫ ይሄ ነው፡፡" ፥ ይላል፡፡ ትክክለኛውን ምርጫ ዛሬ ምረጡ፡፡

“ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።”

—ሉቃስ 10:41-42

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ሉቃስ 10:39 – “ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።”
  • ዮሐንስ 15:4 – “በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። ”
  • ያዕቆብ 4:8ሀ – “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 54