The Gospels Luke

How to Engage Others With the Risen Lord

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 178 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሉቃስ ወንጌል ይህ የመጨረሻዉ ክፍል ነው ፡፡ ሉቃ (24፡ 1-2) ለዚህ ምዕራፍ መነሻ ይሰጣል ፤ ቀኑ ከተነሳ በኃላ ነው ሴቶቹ መቃብሩ ጋር በደረሱ ጊዜ ደንጋዩ ተንከባሎ ነበር ፤ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ እንደ ሚሞት እና ከሰዎስት ቀን በኋላ እንደሚነሳ ተንብዮአል ፡፡ ሴቶቹ ግራ ተጋብተዉ ነበር ነገር ግን ሁለት ሰዎች በፊታቸዉ በመቆም (ቁጥር 4) የኢየሱስን መነሳት በመናገር (ቁጥር 5-6) የሰዉ ልጅ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ እንደሚሰቀል እና ሰዎስተኛዉ ቀን ላይ እንደሚነሳ ኢየሱስ ነግሯቸዉ የነበረዉን አስታወሷቸው (ቁጥር 7) ፡፡ ሴቶቹ የኢየሱስን ቃል አስታወሱ ለሌሎቹም ለመናገር ተመለሱ (ቁጥር 8-10) ፤ ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ ሴቶቹን አላመኗቸዉም (ቁጥር 11) ፡፡ ጴጥሮስ ወደ መቃብሩ ሮጠ ወደ ዉስጥም ሲመለከት የተልባ እግሩን ልብስ አየው ተደንቆም ቤት ሄደ (ቁጥር 12) ፡፡ ሴቶቹ እና ጴጥሮስ ኢየሱስ ተነስቶ ስለ ነበር ተደስተዉ እና ተደንቀዉ እያሉ ሁለት ደቀ መዛሙርት አሁንም ኢየሱስ የሞተ ነበር ብለዉ በማሰብ ተስፋ መቁረጥ ተሰምቷቸው ኢየሩሳሌም ቀርተዋል ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ በሚገባ ሞትን እንዳሸነፈዉ በዚያም ከሞት እንደ ተነሳ እና ኃጢዓትን ድል እንዳደረገ ማመን አለባት ፤ ከዚያ ይልቅ ግን ቤተ ክርስቲያን አሁንም ኢየሱስ እንደ ሞተ እንዳላሸነፈ የሚመስል ለማድረግ አዘንብላለች ፡፡ ዛሬ ደግሞ በተነሳዉ በእግዚአብሄር ልጅ በኢየሱስ በተሸነፉት ወይም ተስፋ በቆረጡት ለማጋራት የምንችል እንድንሆን እና ወንጌላዊያን እንድንሆን ሊያሰለጥኑን የሚችሉ አራት ቃሎችን እንመለከታለን ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (24፡ 13-16)፡ የኢየሱስን ትንሳኤ በተቀበሉበት በዛዉ ቀን እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርቶች ከኢየሩሳሌም ምዕራብ 7 ማይል አካል ወዳለች አንድ አካባቢ ወደ ኤማሁስ(የስሙ ትርጉም “ የሚሞቅ መታጠቢያ ማለት ነው” እየሄዱ ነበር ፤ ሆኖ ስለነበረው ሁሉም ነገር ስለ ስቅለቱ፣ ስለ ሞቱ፣ ስለ ትንሳኤዉ እና ሴቶቹ ስላሳዩዓቸው ባዶ መቃብር እየተነጋገሩ ነበር ፡፡ ንግግራቸዉ ምናልባት ዜናዉ እዉነት ነበር ወይስ አልነበረም በማለት የሞቀ ሆነ ኢየሱስም ተገልጦ አብሯቸዉ ተጓዘ ፤ ኢየሱስ ሊያገኛቸው ከመንገዱ ወጥቶ ሄደ - ፍቅር መጥቶ አብሯቸዉ ተጓዘ ፤ ይህ በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን ሞደል ተቃራኒ ነው ፤ ሰዎች ወደ እኛ እንዲመጡ እንጠብቃለን ፡፡ ፍቅር ከእግዚአብሄር መጥቷል (1ዮሐ 4፡ 19) ፤ ለእኛ አካባቢዉን ማቅረብ ለመጀመር ፍቅር የመጀመሪያው እርምጃ ነው (1ተሰ 3፡ 12) ፤ ፍቅር የመጀመሪያው ቃል ነው ፡፡

ሉቃስ (24፡ 17-25)፡ ሁለተኛዉ ቃል ማዳመጥ ነው ፡፡ ኢየሱስ ስለ ክርክራቸዉ ጠየቃቸው ፤ ለማዳመጥ ጥያቄ መጠየቅ ያስፈልገናል ፤ ኢየሱስ ለምላሻቸው አልመለሰም ነገር ግን ማዳመጡን ቀጠለ ፡፡ ኮንስታብል እንደ ቀድሞዎቹ ክርስቲያኖች ቀለዩጳ የኢየሱስ አጎት እና የዮሴፍ ወንድም እንደ ነበር እና የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን መሪ እንደ ነበር ጠቅሷል ፤ የማሪያም ባል ሊሆን ይችላል የቀለዩጳ(የተመሳሳይ ስም የተለያዬ ሆሄያት) ሚስት ኢየሱስ ስቅለት ላይ ተገኝታ ነበር ፡፡ እንደ ቀድሞ ምስራቅ ቤተ ክርስቲያን (ባዛንታይም ቤተ ክርስቲያን) ሉቃስ መንገድ ላይ ያልተጠቀሰ ደቀ መዝሙር ነበር ፤ በዚህም ኢየሱስ ራሱን እንደ ነቢይ አድርጎ ለለየው ለአጎቱ አወራው ፤ ስለ ስቅለቱ አወሩ ነገር ግን ስለ ትንሳኤዉ አላወሩም ፡፡ ወደ ሰዎች ስናዳምጥ ወደ ልባቸዉ ጉዳይ ልንሰማ ያስፈልጋል ፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን እስራኤልን የሚበዣት አንዱ ክርስቶስ እንደ ነበር ተስፋ እንዳደረጉ ነገሩት፣ እነዚያ ሴቶች ባዶዉን መቃብር ደረሱበት ኢየሱስ ተነስቷል ያሏቸዉን የመለዓክት ራዕይ አዩ እንዲሁም ጥቂት ደቀ መዛሙርት ወደ መቃብሩ ሄደዉ ነበር ባዶዉንም አገኙት ፡፡ ቃሎቻቸዉ ወደ ኢየሱስ ፈሰሱ (ቁጥር 22-24) ፡፡

ሉቃስ (24፡ 25-27)፡ ኢየሱስ ነቢያት ተናግረዉት በነበረው በማመን “ ጥበብ የጎደላቸዉ እና የዘገዩ “ እንደ ነበሩ ነገራቸው ፡፡ በብሉይ ኪዳን አንድ ሞኝ መፅሀፍትን እንደ ሚያዉቅ ነገር ግን ምን እንደ ሚል እንደ ማይጠብቅ እና ባህሪዉ ላይ ተፅዕኖ እንዲያመጣ እንደ ማይፈቅድ የተለየ ነው ፡፡ ኢየሱስም “ ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን ? አላቸው ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ስለ መሲሁ በፅሀፍት በኩል መራቸው (ቁጥር 27) ፡፡

ሉቃስ (24፡ 28-29)፡ ሰዎስተኛዉ ደረጃ መረዳት (መለየት) ነው ማለትም ከመንፈስ ቅዱስ የሆነን ነገር ለማወቅ ወይም ለመገንዘብ ማለት ነው ፡፡ ኢየሱስ ቀጥሎበት የነበረዉን ዱካ ስጥቷል ፤ መለየት ከመንፈስ ቅዱስ ይመጣል ፡፡ የምናገኛቸዉ ማንኞቹም ሰዎች የተለያዩ ናቸው መለየት (መረዳት) እያንዳንዳቸዉን እንዴት እንደ ምንገናኛቸው እና እንደ ምንቀርባቸው ያሳየናል ፡፡ ከእነርሱ ጋር እንዲቆይ አሳሰቡት ፤ መረዳት የመጊቢያ ሀሳቡ የት እንደ ሆነ ይገነዘባል፡፡

ሉቃስ (24፡ 30-35)፡ አራተኛው ቃል ምላሽ ነው ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደ ሚመለስ ያሳያል ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ በገበታዉ ላይ ቆርሶ ለእነርሱ ሰጣቸው ማን እንደ ነበርም አወቁ ፤ መረዳታቸዉ የመጣው ከጌታ እራት ወይም ከ5000 ሰዎች ምገባ ወይም ኢየሱስ እንዴት የህይወት እንጀራ እንደ ነበር ከትምህርቱ ፡፡ ኢየሱስ እንጀራዉን በማሳየት ለእነርሱ መለሰላቸው ፤ ነገር ግን ወዲያዉኑ አወቁት ኢየሱስም ትቷቸው ከእይታቸው ተሰወረ ፤ ወዲያዉኑ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር እንደ ነበር አወቁ ተነስተዉም አይተዉት እንደ ነበር ለሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ለመናገር ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዙ ፤ በማሸነፍ ተመለሱ ምክንያቱም የተነሳዉን ጌታ ስላዩ ፡፡

መዝጊያ

ሉቃስ መጨረሻ ላይ እዉነቱ ኢየሱሱስ ህያው ነው ፡፡ ዛሬ አንድ ሰዉ ለመዉደድ ሂዱ ፤ እሱ ወይም እሷ የሚለውን አዳምጡ ፤ ያን ሰዉ እንዴት እንደ ምንቀርበው ከመንፈስ ቅዱስ በመረዳት ምናልባትም ያን ሰዉ ወደ ግብዣው በመጋበዝ እንመልሳለን ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Luke, p. 356; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/luke.pdf.

  2. Constable, p. 356.

ጥያቄዎች

  1. ደቀ መዛሙርቱ ለሴቶቹ ሪፖርት ስለ ኢየሱስ ለምን ስለ እንደዛ እንደ መለሱ ምን ታስባላችሁ (ሉቃ 24፡ 11)? በቀላሉ ቃሉን እረስተዉታል፣ አልተረዱትም ወይስ ኢየሱስ ነግሯቸዉ የነበረውን አላመኑትም (ማቴ16፡ 21; ሉቃ 9፡ 22) ?ለእናንት እግዚአብሄር ያላችሁን ከመርሳት ወይም ካለመረዳት እንዴት ልትጠበቁ ትችላላችሁ ? (ዮሐ 14፡ 26)
  2. ወደ ኤማሆስ የሚጓዙት የሁለቱ ተጓዦች ስሜታዊ ሁኔታ ምን ነበር ? በዚህ መልኩ ለምን ነበር የተሰማቸው ?
  3. ከሁለቱ ተጓዦች ጋር በንግግር የኢየሱስን ርህራሄ እና ትግስት እንዴት ታዩታላችሁ ? ወደ እርሱ ልባችንን ማፍሰስ እንደ ምንችል እና እንደ ሚሰማን እና እንደ ሚረዳን እንዴት እናውቃለን ? (መዝ 62፡ 8; ዕብ 4፡ 16)
  4. በተነሳዉ ክርስቶስ እንዲያምኑ ሁለቱን ሰዎች የመሯቸዉ ጥቂት ማስረጃዎች(መረጃዎች) ምንድን ነበሩ ? (ማር 16፡ 6; 6፡ 9, 12, 14; ሉቃ 24፡ 2-3, 6; ዮሐ 20፡ 3-6)
  5. ሉቃ (24፡ 37) (NKJV) ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ለእነርሱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ፈሩና እና እንደ ደነገጡ ይናገራል ፤ ኢየሱስ ደም ስራቸዉን ለማረጋጋት ይህን ጊዜ እንዴት ተጠቀመ (ሉቃ 24፡ 36; ዮሐ 20፡ 19-21)? በኃይለኛ ሙከራዎች ወይም ሁኔታዎች ጊዜ የክርስቶስን ሰላም እንዴት ትረዱታላችሁ ? (ሮሜ 5፡ 1; ፌል 4፡ 6-7)
  6. በሉቃስ 24 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 24:52–53

“After worshiping Him, they returned to Jerusalem with great joy. And they were continually in the temple complex praising God.”

ደቀመዛሙርቱ ከመስቀል ሞቱ በኋላ ኢየሱስን ለመጀመሪያ ጊዜ ከሙታን ተነስቶ እና በአካል ሲያዩት ደነገጡ እና ፈሩ፡፡ ነገርግነ፥ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጊዜ አሳለፈ፡፡ ምሽቱን ከእነርሱ ጋር እንዲቆይ ጠየቁት፡፡ እንጀራን አብረው ተካፈሉ፡፡ ከዚያም፥ መጻሕፍት እንደ መሲህ ስለነበረው ተግባር የተናገሩትን እና ትንቢቶች እንዴት እንደተፈጸሙ ለማብራራት ጊዜ ወሰደ፡፡ አብሮአቸው ከተራመደ በኋላ፥ ምስክሩ እንዲሆኑ ለመላክ ባረካቸው፡፡ ከዚያም ኢየሱስ በድጋሚ ትቶአቸው ሄደ እና ወደ ሰማይ አረገ፡፡ ደቀመዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ጊዜ ስላሳለፉ፥ ስጋታቸው እና ፍርሃታቸው እንዲቀንስ ረድቷቸዋል፡፡ እውነትን እና መልሶችን ከኢየሱስ ይፈልጉ ነበር፡፡ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሰማይ አረገ፥ እነርሱም በታላቅ ደስታ ጌታን ማመስገን ቀጠሉ፡፡

በተመሳሳይ መንገድ፥ ለጥያቄዎቻችሁ መልስ እንዲሰጣችሁ እየፈለጋችሁት፥ በኢየሱስ ህልውና ውስጥ ጊዜ ስታሳልፉ ደስታን ታገኛላችሁ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ለማሳለፍ ጊዜን መውሰዳችሁ ይጠቅማችኋል፡፡ አዎ፥ ህይወት በውጥረት የተሞላች ናት፥ ደግሞም ለጥያቄዎቻችሁ መልስን እና ለፍርሃቶቻችሁ መፍትሔን ፍለጋ ልትሄዱባቸው የምትችሉባቸው ብዙ ቦታዎች አሉ፡፡ ነገር ግን የደቀመዛሙርቱን ምሳሌ ተከተሉ፡፡ዛሬ፥ በኢየሱስ ህልውና ውስጥ ለመቀመጥ ጊዜ ውሰዱ፥ ቃሉን አጥኑ፥ እና በፀሎት ፈልጉት፡፡ስትፈልጉት ፥ በህይወት መንገዳችሁ ይመራችኋል፡፡ ለቀኑ በሚሆን ደስታ እና ብርታት ትሞላላችሁ፡፡

“እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።”

—ሉቃስ 24:52–53

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 16:11 – “የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ። ”
  • መዝሙረ ዳዊት 28:7 – “እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።”
  • ትንቢተ ኤርምያስ 15:16 – “ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 68