The Son of Man Reality
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 23 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሉቃስ 23 የተካሄዱ እንግዳ ነገሮች አሉ ፡፡ እንደ ሰዉ ልጅ ስለ ኢየሱስ ምንድን እንደ ሚመስል እያወራን ነው ፤ ዛሬ የኢየሱስን ሰዋዊነትን እንመለከታለን ፡፡ ብዙ ጊዜ ኢየሱስ ራሱን እንደ ሰዉ ልጅ ጠቅሷል ፤ ዕብ (4፡ 14-16) አንብቡ የኢየሱስን ግንኙነት ያሳዉቃችኋል፡ ተራበ (ማር 11፡ 12) እንዲሁም ተጠማ (ዮሐ 19፡ 28) ፤ ተኛ (ማር 4፡ 38) እንዲሁም አለቀሰ (ዮሐ 11፡ 35) ፤ ተደስቷል ደግሞም ይቀልድም ነበር (ሉቃ 7፡ 34) ፤ ተበሳጭቷል (ማቴ 21፡ 12-13) እንዲሁም ኢየሱስ ተሰቃይቷልም ተገፍቷልም የሀዘንም ሰዉ ነበር (የተጎሳቆለ ሰዉ ነበር) (ኢሳ 53፡ 3) ፤ ዛሬ “ወደ ሰዉ ልጅ “ እዉነታ በሙሉ ዘለን እንገባለን ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (23፡ 1)፡ ጠቅላላ ጉባኤዉ የሽማግሌዎች መማክርት ነበር ( የአዋቂዎች(ፈራጆች) ማለትም “ በአንድ ላይ የተቀመጡት “ ወይም “የተሰበሰቡት” ማለት ነው ) ፤ በእያንዳንዱ ከተማ በአካባቢዉ የተሾሙ የ23 ዳኞች የሚያንሱ አዋቂዎች ነበሩ ፡፡ ታላቅ ከሌሎቹ ተግባሮች መካከል እንደ በላይ ዳኝ የሚሰሩ አዋቂዎች 71 ዳኞች ነበሩ ፤ እንደ ኢየሱስ አይነት ችግር ላይ ታላቅ አዋቂዎች(ፈራጆች) ተሳትፈዋል ፡፡
ሉቃስ (23፡ 2)፡ በዚህ ምዕራፍ በበሩ እንዳሰወጡት ኢየሱስ እንደ ሰዉ ተይቶ ነበር ፤ ፈራጆች (አዋቂዎች) እርሱን ያዩበት መነፀር ያ ነበር ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ሰዉ የሚለዉ ቃል ከኢየሱስ ጋር በተገናኘ ስምንት ግዜ ጥቅም ላይ የዋለ ነው ፡፡ የፈራጆቹ የሽንገላ ክስ በእዉነት በፍፁም የሚያስቅ ነበር ፤ ጅልነታቸው አስገራሚ ነው ፡፡ በሉቃ (20፡ 21) የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን “ ህዝቡን ያጣምማል “ በማለት ከሰሱት ነገር ግን ስርዓቱን ያታለሉት እና እርቃን ያደረጉት አንዶቹ እነርሱ ነበሩ ፡፡ በሀሰት “ ግብርን በመቃወም “ ከሰሱት ነገር ግን ኢየሱስ ከቀረጥ ሰብሳቢዎች ጋር የተቀራረበ ነበር፣ ለሮማዉያን ግብር ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ሸጠዉ የነበሩትን ሰዎችም ይወድ ነበር (ሉቃ 20፡ 24-26) ፤ እንዲሁም ኢየሱስን “ መሲህ ለመሆን ጠይቋል “ ይህን የጠየቁት እና ከእርሱ እንዲወጣ የሚከሩት እነርሱ ቢሆኑም ብሏል በማለት ከሰሱት (ሉቃ 22፡ 71) ፡፡
ሉቃስ (23፡ 3-6)፡ ኢየሱስ ለጲላጦስ ጥያቄ አልመለሰለትም ጲላጦስም በዚህ ሰዉ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም አለ (ቁጥር 3-4) ፤ አይሁዶች ኢየሱስ ህዝቡን በማወክ ችግር ሆኖ እንደ ነበር ተናገሩ ፤ ጲላጦስም ይህ ሰዉ ከገሊላ ነዉን ብሎ ጠየቃቸው (ቁጥር 5-6) ፡፡
ሉቃስ (23፡ 7)፡ ጲላጦስ በዚህ ችግር ለመነጋገር አልፈለገም ፤ በማይመች ሁኔታ መሀከል ላይ ተይዞ ነበር ፤ ጲላጦስ ፈራጆቹን (አዋቂዎቹን) ካልሰማቸዉ አመፅ ሊነሳ ይችላል ቢአዳምጣቸዉ ደግሞ ከኢየሱስ ተከታዮች ያለዉን አመፅ ፈራ ፡፡ ክሱ ጠንክሮ ስለነበር ጲላጦስ ለሄሮድስ አሳልፎ ሰጠው ፡፡
ሉቃስ (23፡ 8-9)፡ ሄሮድስ ኢየሱስን ሲያየዉ ተደሰተ ፤ የሄሮድስ አባት በዋና ዋስትና በሌለዉ ጉዳይ ምክንያት በመቶዎች ለሆኑ አይሁድ በኩሮች ግድያ ተጠያቂ ነበር (ኃላፊነቱን የሚወስድ ነበር) ፡፡ ትንሹ ሄርዶስ የኢየሱስን የአጎት ልጅ መጥምቁ ዮሐንስን ራሱን አስቀልቶት ነበር ምክንያቱም ዮሐንስ በሄርዶስ ትክክል ባልሆነ ፍቺ እና እንደገና የግማሽ ወንድሞን ጋብቻ ላይ ተቃርኖ አስምቶ ስለነበር ፡፡
የሄርዶስ ቤተሰቦች ትክክል ያልሆነ ባህሪ ያላቸዉ ነበሩ ፡፡ ሄርዶስ ከኢየሱስ ክርስቶስ “ከሁሉም የላቀ “ ታዓምራትን ለማየት ሾዉ ፈለገ፡ “ አንተ ክርስቶስ ታላቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሆንህ ፤ ሞኝ አለመሆንህን በመዋኛ ገንዳዬ ላይ በመሄድ አረጋግጥልኝ “ እያለ ሾዉ ፈለገ ፤ ቁጥር 9 ከኢሳ (53፡ 7) –“ አፉን አልከፈተም “ ከሚለዉ ጋር አወዳድሩት ፡፡
ሉቃስ (23፡ 10-14)፡ በቁጥር 10 “ የካህናት አለቆችና ጻፎችም አፅንተዉ ሊከሱት ቆመዉ ነበር “ ፤ ሰይጣን ማለት “ከሳሽ ነው “ እናም በግሪክ “ በኃይል “ የሚለው ቃል “ እቶኖስ “ ሲሆን ትርጉሙም “ በከባድ ሁኔታ፣ በብርቱ ፣ በኃይል “ ማለት ነው ፤ የክርስቶስ ተቀዋሚዉ መንፈስ በኃይል የመቃወም ደረጃ በሙሉ አቅም ነው ፡፡ ጲላጦስ እና ሄርዶስ ለምን ነበር ጓደኞች የሆኑት ? አንዱ ሀሳብ ጲላጦስ ኢየሱስ ማን እንደ ነበር አያዉቅምም ወይም ጉዳይ የለዉም እንዲሁም ደግሞ ሄርዶስ እና ወታደሮቹ ኢየሱስን እንደ ሰርከስ ሾዉ ተመለከቱት ጲላጦስ እና ሄርዶስ ኢየሱስን ለመስቀል ሁለቱም በጋራ ፍቃደኛ አልነበሩም ፡፡ በጠቅላላ በዚህ መግለጫ ዉስጥ ጲላጦስ በፅናት የምክንያት ድምፅ ነው ፤ አምላክ የለሽ እምነት ተከታይ ቢሆንም ጲላጦስ የተለመደ ስሜት ነበረው (ምሳ 6፡ 16-19) ፡፡
ሉቃስ (23፡ 15-21)፡ ጲላጦስ አንድ ሰዉ ይለቅቃል በዚህም ኢየሱስን ሊለቅቀዉ አቀደ ነገር ግን ህዝቡ አመፅ መርቶ እና ሰዉ ገድሎ እስርቤት የነበረዉን በርባን እንዲለቀቅላቸዉ ፈለጉ ፡፡ ኢየሱስ ከአዋቂዎቹ (ከፈራጆቹ) ጋር መሲህ እንደ ነበር ተስማምቶ ነበር ፡፡ ኢሳ (53፡ 9) የሚለው “ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር “ ፤ ማርቆስ በርባን “በአመፅ ታስሮ ነበር “ ይላል ፤ ዮሐንስ “ ሽፍታ “ ብሎ ጠርቶታል ማቴዎስ ደግሞ “ በመጥፎ ነገር የታወቅ እስረኛ “ ነበር ብሎታል ፡፡ ስሙን ለመፃፍ (በር) ማለት ልጅ ሲሆን (ባን) ማለት ደግሞ አባት ነው አስደናቂ ነው ፤ የአባቱ ልጅ ስለ አባቱ ልጅ ቦታዉን ወሰደ ፡፡ እንደ ገና ጲላጦስ ኢየሱስን ሊለቀዉ ቢሞክርም ህዝቡ እንዲሰቅለዉ ለእርሱ መጮኻቸዉን ቀጠሉ ፤ እርግጥ ይህ የዘዳ (21፡ 23) ትንቢት መፈፀም ነው ፡፡
ሉቃስ (23፡ 22-25)፡ ጲላጦስ ለሰዎስተኛ ጊዜ “ ይህ ሰዉ ያደረገዉ ስህተት ምንድ ነው ?” ብሎ በመጠየቅ ሞከረ የጲላጦስ ፅናት አስታዉሉ ፤ እዚህ የሰዉ ልጅ እንደ ተገረፈ ተጨማሪ ትንቢት ተፈፀመ (ኢሳ 53፡ 5) ፡፡ በመጨረሻም ጲላጦስ በመሸነፍ ለፍላጎታቸዉ ሰጣቸዉ ነገር ግን “ ከዚህ ሰዉ ደም ንፁህ ነኝ “ አለ (ማቴ 27፡ 24) ፡፡
መዝጊያ
ይህን ስንዘጋ ኢየሱስን እንደ ሰዉ ልጅ እሚያመለክቱን ሰዎስት ፅሁፎችን እንመልከት፡
መጀመሪያ በኢየሱስ እነዚህ ትንቢቶች ተፈፅመዋል፡
መዝ (22፡ 14-19)፡ “ እንደ ዉኃ ፈሰስሁ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ ፡፡ ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ በጉሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ ወደ ሞትም አሸዋ አወረደኸኝ ፡፡ ብዙ ዉሾች ከብበዉኛልና ፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ ፡፡ አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም ፡፡ ልብሶቼን ለራሳቸዉ ተከፋፈሉ በቀሚሴ ላይ እጣ ተጣጣሉ ፡፡ አንተ ግን አቤቱ ከእኔ አትራቅ ፤ አንተ ጉልበቴ እኔን ለመርዳት ፍጠን ፡፡ “
ሁለተኛ የሰዉ ልጅ ሰንበር አዉጥቶ፣ ተርቦ እና መስቀሉ ላይ ተጠምቶ ነበር፡
ኢሳ (53፡ 5-6)፡ “ እርሱ ግንስለ መተላለፋችን ቆሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ ፤ የደህንነታችንም ተግሳፅ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን ፡፡ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ ፤ እግዚአብሄርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ ፡፡”
ሰዎስተኛ አምላክ ቢሆንም እንደ ሰዉ መጣ፡
ፊል (2፡ 6-8)፡ “ እርሱ በእግዚአብሄር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሄር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰዉም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ ፡፡ “
ጥያቄዎች
-
በጥቅስ 12 ጲላጦስ እና ሄሮድስ እርስ በእርሳቸዉ ጠላት የነበሩ በኢየሱስ ስቅለት ቀን ላይ ገዳኛሞች መሆናቸዉን ሉቃስ ለምን እንደ ጠቀሰ ምን ታስባላችሁ ? (መዝ 2፡ 1; ሐዋ 4፡ 27-28)
-
እስራኤላዊያን እንደ ንጉስ እግዚአብሄርን (ልጁን) በራሳቸዉ ፍቃድ ፍላጎት አለመቀበላቸው እንደ ሌላ ምሳሌ (ማስረጃ) ሉቃ (23፡ 25) ታዩታላችሁ ?
-
ከእኛ ዉስጥ አብዛኞቻችን በሉቃ (23፡ 34) “ ኣባት ሆይ የሚያደርጉትን አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ “ የሚለዉን እናወቀዋለን በዚህ ምን እያለ ነው ? ተገቢ ባልሆ ተመልክታችሁ እና ላደረጉት ይቅርታ ማድረግን መርጣችሁ ታውቃላችሁ ? እንደ እርሱ ተከታዮች ለይቅርታ ተጠርተናልን ? (ማቴ 18፡ 21-22; ማር 11፡ 25-26; ሉቃ 17፡ 3-4; ኤፌ 4፡ 32) ለማድረግ ይህን አስቸጋሪ ነገር ሆኖ አግኝታችሁታል ?
-
ጲላጦስም ሄሮድስም በኢየሱስ ለሞት የሚያበቃ ምክንያት አላገኙበትም (ሉቃ 23፡ 14-15) ፤ ከሌቦቹ አንዱ ምንም ስህተት እንዳላደረገ ተናገረ መቶ አለቃዉም ኢየሱስ ንፁህ እንደ ነበር ተገነዘበ (ሉቃ 23፡ 41, 47) ፡፡ ለማን ወንጀል ተቀጣ ? (ኢሳ 53፡ 5; ሮሜ 4፡ 25; 1ቆሮ 15፡ 3)
-
በሞቱ ኢየሱስ ከክህነት ልብስ በተሰራዉ ፈትል መጠቅለሉ ትርጉም ያለው ነው ? (ዘጸ 28፡ 4-5; ሉቃ 23፡ 53)
-
በሉቃስ 23 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 23:23–24
“But they kept up the pressure, demanding with loud voices that He be crucified. And their voices won out. So Pilate decided to grant their demand and released the one they were asking for, who had been thrown into prison for rebellion and murder. But he handed Jesus over to their will.”
የሰው ልጅ፥ ኢየሱስ፥ ፍፁም አምላክ እና ፍፁም ሰው ነበር፡፡ ሙሉ ጉባኤው ኢየሱስ እንደ ወንጀለኛ እንዲከሰስ ቢፈልግም፥ ጲላጦስ ግን እርሱን የሚከስበት መሬት አላገኘም፡፡ ኢየሱስ እንደ ገሊላዊ ስለሚታይ፥ ጲላጦስ የገሊላ ገዢ የሆነውን ሄሮድስን፥ በውሳኔው እንዲረዳው አመጣው፡፡ አሁንም፥ የሞት ፍርድ እንዲወሰንበት የሚያደርግ ምክንያት አላገኘም እና ሄሮድስ ከጲላጦስ ጋር ተስማማ፡፡ ነገር ግን፥ ሊገርፉት፣ ሊዘብቱበት እና ሊሰድቡት ተስማሙ፡፡ በመጨረሻም ጲላጦስ ለጉባኤው ጩኸት እጅ ሰጠ እና በቂ ምክንያት ባይኖርም ኢየሱስን ለመስቀል ተስማማ፡፡ ስለዚህ፥ ኢየሱስ በመስቀል እሰኪሞት ድረስ ውርደትን እና አካላዊ ህመምን ተቋቋመ፡፡
አዳኛችሁ፥ የሰው ልጅ፥ ኢየሱስ ህመምን ይረዳል እና በህመማችሁ ሊራራላችሁ ይችላል፡፡ ቃሉ መከራ ትቀበላላችሁ ይላል፡፡ ፈተናዎች ይገጥሟችኋል፡፡ ትሰደዳላችሁ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ፥ ኢየሱስ በመከራ፣ በፈተና፣ እና በስደት፣ ውስጥ አልፏል፡፡ ነገር ግን፥ ኢየሱስ ብቻችሁን አይተዋችሁም፡፡ ዛሬ ራሱ ፥ምንም ቢያጋጥማችሁ ወደ ጌታ ተመለሱ፡፡ ህመም እና ሥቃይን ስለሚረዳ የምትፀኑበትን ብርታት ሊሰጣችሁ ቃል ገብቷል፡፡ ኢየሱስ በህመማችሁ መካከል በሥራ ላይ ነው እና ሊጠግናችሁ፥ ሊያፀናችሁ፥ ሊያበረታችሁእና ሊረዳችሁ ቃል ገብቷል፡፡ እርዳታን ጠይቁ፡፡ በድካም ጊዜያችሁ ወደ እርሱ ተመለሱ እርሱም ያበረታችኋል፡፡ ዛሬም አስታውሱ፥ በጭንቀታችሁ ውስጥ ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡
“እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጽንተው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ቃል በረታ። ጲላጦስም ልመናቸው እንዲሆንላቸው ፈረደበት።”
—ሉቃስ 23:23–24
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ዕብራውያን 4:15 – “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። ”
- ያዕቆብ 1:2–3 – “ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት”
- 1ኛ ጴጥሮስ 5:10 – “በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 67
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።