The Lord's Supper
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሉቃስን ወንጌል ከሞላ ጎደል እየጨረስን ነው ! በሉቃስ 24 ምዕራፎች አሉ ፡፡ አካታች ወንጌላትን እየሸፈን ነው ፡፡ የማቴዎስ መፅሀፍ ኢየሱስን እንደ ንጉስ ገልፆታል ፣ የማርቆስ መፅሀፍ እንደ አገልጋይ ገልፆታል በተጨማሪም የሉቃስ መፅሀፍ እንደ ሰዉ ልጅ ገልፆታል ፡፡ የኢየሱስን የሰዋዊነት ጎኑን ማየት እንጀምራለን ፤ በጌታ እራት በኩል ዉስጥ እንሄዳለን ፤ የሚያስደንቅ ስዕል ነው ! ክርስቶስ ከእኛ ዉስጥ እያንዳንዳችንን ግብዣዉ ላይ እንድንቀላቀለው ግብዞናል !
ትምህርት
ሉቃስ (22፡ 1-6)፡ የቂጣ በዓል ፋሲካ እየቀረበ እንደ ነበር ይታወቃል ፤ በተጨማሪም ክርስቶስን ለመግደል የሴራዉ ፍሬያማነትን እናያለን ፤ በማርቆስም ኢየሱስ ስለ ሞቱ ሰዎስት ጊዜ አመልክቷል ፡፡
ሉቃስ (22፡ 7-13)፡ ለፋሲካ እንዴት እንዲዘጋጁ ተሾመዉ ነበር ? ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ከተማ በመግባት ማድጋ የተሸከመዉን ሰዉዬ በማግኘት እንዲያስቆሙት ! ጠየቃቸው ይህን ሰዉዬ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ፋሲካን ሊያከብርበት የሚችለዉ የእንግዳ ክፍሉ የት እንደ ነበር ይጠይቁታል ፡፡ እግዚአብሄር ዝርዝሩን ለማድረግ ከፊታችን ይሄዳል (ዘጸ 12፡ 13) ፡፡
ይህ ፋሲካ እንደ እግዚአብሄር በዓል ይህን ጊዜ ኢየሱስ ያስታወሰበትን መልክ እንዲሁም የሙሴን ቃል እንዳከበረ ይስላል ፤ ስለ እግዚአብሄር ግብዣ በምናወራ ጊዜ ሁሉም ነገር ስለ ትዉስታ(ማስታወሻነት) ነው ! ይህም ፋሲካ ደግሞ የወደፊቱ ትንብያ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ የፃፈው “ ፋሲካ የእስራኤላዊያን ከበፊቱ ከግብፅ ዘመን ነፃ የወጡበት መታሰቢያ ሲሆን ነገር ግን ታላቅ “ ነፃ መዉጣት “ መስቀሉ ላይ አደረገ “ (ሉቃ 9፡ 31) እዩ ፡፡
ሉቃስ (22፡ 14)፡ የፋሲካን እራት ለማክበር ለኢየሱስ እና ለደቀ መዛሙርቱ ጊዜ በመጣ ጊዜ ገበታዉ ላይ ተቀመጡ ፤ ዋይርስቤ የፃፈው “ ኢየሱስ እንደ አዘጋጅ አገለገለ “ ፡፡ ሁል ጊዜ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በልምድ አሳሳም ሰላምታ ሰላም ይላቸዉ ነበር ፤ ዮሐ (13፡ 23) ዮሐንስ በቀዩ በኩል እና ይሁዳ በግራዉ በኩል እንደ ነበሩ ያሳየናል ፤ ከዚያም ሁሉንም ደቀ መዛሙርት ሳማቸው ፡፡ በኤፌ (2፡ 20) ሐዋሪያቱ 12 እንደ ነበሩ የተፃፈ ነው ፤ በዮሐ (13፡ 1-20) ከመሳሙ እና ከሰላምታዉ በኋላ ኢየሱስ አንድ ፎጣ አንስቶ እግራቸዉን እንዳጠበ እናያለን ፡፡ ኢየሱስ እግራቸዉን ካጠበ የትህትና እና የማገልገል ምሳሌ እየሆናቸዉ ነበር ፡፡
ሉቃስ (22፡ 15)፡ ከዚያም ኢየሱስ ይህ ከእነርሱ ጋር የመጨረሻ እራቱ እንደሚሆን ገለጠ ፤ ይህ የመጨረሻ እራቱ እንደ ነበር እና ለሚመጣ መፈፀም እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ ኢየሱስ ትንቢታዊ ቃልን እየተከተለ ነበር (ማቴ 5፡ 17) ፤ በዮሐ (13፡ 1) ዮሐንስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንደ ሚወዳቸው እና እስከ መጨረሻም እንደ ወደዳቸው ፅፏል ፡፡
ሉቃስ (22፡ 16)፡ ኢየሱስ “ ይህ የመጨረሻዬ ምግብ ነው !” አለ ፤ ኮንስታብል የፃፈው “ ኢየሱስ የሚጠብቀዉ ፋሲካ ማለትም የራሱ የመስዋዕትነት ሞት ታዉቆ ስለ ነበር በፍፁም እንደ ገና ሌላ የፋሲካ ምግብ እንደ ገና እንደ ማይበላ አሳወቀ (cf.9: 31)….እንደ ገና ከእነርሱ ጋር በቀጣዩ መንግስት በቀጥታ መሲሁ ግብዣ ላይ በመንግስቱ መጀመሪያ ላይ ይበላል፡፡ “ በሰማይ በመሲሁ ግብዣ ላይ እንደ ገና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይበላል ፤ ራዕ (19፡ 9) የመሲሁ ግብዣ አስደናቂ መልክ ነው ፤ ኢየሱስ እያወራ የነበረዉ ይህንን ነው !
ሉቃስ (22፡ 17)፡ ኢየሱስ ፅዋዉን በመዉሰድ አመስግኖ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተካፈሉት ፤ በፋሲካ እራት (ምግብ) ጊዜ ኢየሱስ በእዉነት ስለ ተጠቀመው የትኛዉ ፅዋ እንደሆነ ክርክር አለ ምክንያቱም አራት ፅዋዎች እንደተጠቀሙ ስለ ምናዉቅ ፤ አራቱ የፅዋዎች አይነት እነዚህ ናቸው፡ 1) ቀኑን ለመባረክ በመጀመሪያ ትምህርት የሚጠቅም ; 2) በምስጋና መዝሙሮች ዝማሬ የቀኑን የቤተ ክርስቲያን ስነ ስርዓት ከተገለፀ በኋላ; 3) የጠቦቱን፣ የቂጣዉን እና የመራራ ቅጠሉን ምግብ ተከትሎ እና 4) የምስጋና መዝሙርችን ተከትሎ የሚጠቀሙት ናቸው ፡፡ የተካፈሉት ፅዋ የተለመደ ፅዋ አንድ ብቻ ነው ፡፡
ሉቃስ (22፡ 18)፡ ደግሞም እንደ ገና ኢየሱስ እስከ መሲሁ ግብዣ ድረስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደ ገና እንደማይጠጣ ገለፀ ፤ ኢየሱስም “ ይህ የመጨረሻዬ ነው አለ ! “
ሉቃስ (22፡ 19)፡ ኢየሱስ እንጀራዉን በመዉሰድ አመሰገነ ፤ እንጀራዉ የስጋዉ መወከያ ነበር ፡፡ በዘዳ (16፡ 3) ፀሀፊዉ የቦካ እንጀራ የጥንካሬ እና የኃጢዓት ምልክት እንደ ነበር አጋርቷል ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አንድ ቁራሽ እንጀራ ብቻ የሆነ እንጀራ ሰጣቸው ፤ አንድ ብቻ እንደ ነበር ማስታወስ አስፈላጊ እንደሆነ አስባለሁ የክርስቶስን አንድ አካል ይወክላል ፡፡ የክርስቶስ አካል መሆናችንን እረስተነዋል ፤ እንደ ክርስቲያን የተከፋፈልን መሆን የለብንም !
ፋሲካ የመስዋዕትነት መስዋዕት እንደ ነበር ያስታዉሳል ፤ ይህ የመጨረሻዉ ነበር ምክንያቱም ከሞቱ በኋላ ለመስዋዕትነት መስዋዕት የሚያስፈልግ አይኖርም ፡፡ ኢየሱስ የመጨረሻዉ የመስዋዕትነት መስዋዕት ነበር ፤ (ዘሌ 6፡ 25, 7፡ 15, 1ቆሮ 10፡ 16; 11፡ 26; ዕብ 10፡ 14) ፤ በኤር (ወደ አድስ ኪዳን ሽግግር እናያለን ፡፡
ሉቃስ (22፡ 20)፡ በተመሳሳይ መንገድ ምናልባትም ሰዎስተኛዉን የመዋጀት ፅዋ የነበረውን ፅዋ አነሳ ፤ ኢየሱስም “ ጊዜዬ እየመጣ ነው “ አለ ፤ ቤዛነት በክርስቶስ ደም በኩል ብቻ ይመጣል ፡፡ ዘሌ (17፡ 11) የሚለው “ የስጋ ህይወት በደሙ ዉስጥ ነዉና ደሙም ደሙም ከህይወቱ የተነሳ ያስተሰረያልና በመሰዊያዉ ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት ፡፡”
ሉቃስ (22፡ 21-22)፡ ከዚያም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ በአንዱ ተላልፎ እንደሚሰጥ ነገራቸው ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን እንደ ሰሙ ተቸገሩ (ግራ ተጋቡ) ፡፡ አድስ ዜና አልነበረም ፤ ኢየሱስ ቀደም ብሎ በማቴ (17፡ 22) እና በማቴ (20፡ 10) ይህን ተላልፎ መሰጠት አመልክቷል ፡፡
3 Thomas Constable. Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes on Luke; p. 320; available at http://planobiblechapel.org/constable-notes/.
መዝጊያ
የጌታን እራት ለምንድን እናከብራለን ? ሰዎስት ነገሮች እንድናደርግ ተጠይቀናል ፡፡
እንድናስታዉስ ተጠይቀናል ፡፡
- ሉቃ (22፡ 19) “ እንጀራንም አንስቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸዉና ስለ እናንተ የሚሰጠው ስጋዬ ይህ ነው ፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ ፡፡ “
ክርስቶስ ህይወቱን እንዴት እንደ ኖረ እንድንሳተፍ ተጠይቀናል ፡፡
1ቆሮ (10፡ 16)፡ “ የምንባርከዉ የበረከት ፅዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለዉ አይደለምን ? የምንቆርሰዉስ እንጀራ ከክርስቶስ ስጋ ጋር ህብረት ያለዉ አይደለምን ?
ዮሐ (6፡ 53)፡ “ ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው እዉነት እዉነት እላችኋለሁ የሰዉን ልጅ ስጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ህይወት የላችሁም ፡፡ “
ማር (8፡ 34)፡ “ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ “ ፤ በእንጀራዉ እና በፅዋዉ የምንሳተፈበት ይሄን ነው ፡፡
ሞቱን ወደ አለም ዉስጥ ማወጅ(መናገር) አለብን ፡፡
1ቆሮ (11፡ 25-26)፡ “ እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋዉን ደግሞ አንስቶ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው ፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ ፡፡ ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና ፡፡ “
Warren Wiersbe. The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2008), p. 265.
Wiersbe, p.265.
Darrell L. Bock. Messiah in the Passover (Grand Rapids, MI: Kregel Publications, 2017), p. 73.
ጥያቄዎች
-
መፅሀፍ መሲሁ በጓደኞቹ ተላልፎ የተሰጠ እንደሚሆን ተንብዮአል ፤ ይሁዳ ወይስ የካህናት አለቆች እና ሰራተኞች ለዚህ ትንቢት ተፈፃሚ እንደ ነበሩ ታስባላችሁ (መዝ 41፡ 9; 55፡ 12-14) ?
-
በሉቃ (22፡ 16) ኢየሱስ በእግዚአብሄር መንግስት እስኪፈፀም ድረስ እንደገና ፋሲካን እንደ ማይበላ አወራ(ተናገረ) ፤ ምን ማለት ነው ?
-
ከ12 ደቀ መዛሙርት ጋር እያለ ኢየሱስ ከመካከላችሁ ታላቅ የሚሆን ልክ እንደ ታናሽ መሆን ይጠበቅበታል (ሉቃ 22፡ 26) ብሎ ነገራቸው ፤ ይህ ወደ መንግስተ ሰማይ ለመግባት እንደ ህፃን ሁኑ ብሎ ከተናገረዉ ጋር ይገናኛል ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ማቴ 18፡ 3; ሉቃ 18፡ 17)
-
ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ለመታሰር እና ለመሞት በእርግጠኝነት ፍቃደኛ እንደሚሆን ተናገረ ፤ ጴጥሮስ እንደ ፈራው እና ዝም ብላችሁ ፍራትን ለመከተል ወይም መሰዋትን ወይም መከራን ለማስወገድ ፈርታችሁ ታዉቃላችሁ (ሉቃ 22፡ 33-34, 55-62)
-
በሉቃ (22፡ 69) ኢየሱስ እንደ ገና ለራሱ እንደ ሰዉ ልጅ ጠቀሰ ፤ የሽማግሌዎች መማክርት(ኮሚቴ) በቀጥታ የእግዚአብሄር ልጅ ከነበርክ በለዉ ጠየቁት ፤ ኢየሱስም “ እኔ እንደሆንሁ እናንተ ትላላችሁ “ አላቸው (ቁጥር 70) ስለ እርሱ ምላሽ ለእነርሱ አሳፋሪ ቅሌቱ እና አስፈላጊነቱ ምን ነበር (ዘጸ 3፡ 14, ዮሐ 8፡ 58) ?
-
በሉቃስ 22 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 22:19–20
“And He took bread, gave thanks, broke it, gave it to them, and said, “This is My body, which is given for you. Do this in remembrance of Me. In the same way He also took the cup after supper and said, “This cup is the new covenant established by My blood; it is shed for you.”
ኢየሱስ የመጨረሻውን ማዕድ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በበላ ጊዜ፥ በመስቀል ላይ መከራን ከማሳለፉ በፊት ፋሲካን ከእነርሱ ጋር ሊበላ ይመኝ እንደ ነበረ ነገራቸው፡፡ጊዜው እንደደረሰ ያውቅ ነበር፡፡ ኢየሱስ እናንተ ትድኑ ዘንድ ለአለሙ ሁሉ ኃጢያት በመሞት፥ የኃጢያት መስዋዕት በመሆን አገልግሏል፡፡ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ከነበረው የመጨረሻ ማዕድ ከአመታት በኋሏ፥ አማኞች አሁንም ይህንን ማዕድ መልሰው በማድረግ ይሳተፋሉ፡፡ ቁርባን፥ ወይም የጌታ እራት ፥ ኢየሱስ ለተከታዮቹ የነበረውን የመስዋዕትነት ህይወት ማስታወሻ እና የአምልኮ አይነት ነው፡፡
በማናቸውም እሁድ ወደ ቤተክርስቲያን ስትገቡበቁርባኑ የመሳተፍ እድል ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡ በቤታችሁ ከቤተሰባችሁ እና ከወዳጆቻችሁ ጋር ወይም በሰርግ ሥነ-ሰርአት ላይ ራሱ ሊሆን ይችላል፡፡ በጌታ እራት ላይ ተካፋይ ስትሆኑ፥ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያደረገላችሁን እንድታስታውሱ ትጠየቃላችሁ፡፡ በክርስቶስ ህይወት ተካፋይ እንድትሆኑ ትጠየቃላችሁ፡፡ በድጋሚ እስኪመለስ ሞቱን እንድታውጁ ትጠየቃላችሁ፡፡ ዛሬ፥ ስለ ኢየሱስ እና አለምን ለማዳን ስለተሰዋው ህይወቱ ምስጋና ስጡ፡፡
“እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና፦ ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።”
— ሉቃስ 22:19–20
ተጨማሪ ጥቅሶች
- 1ኛ ቆሮንቶስ 11:24 — “ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።”
- 1ኛ ቆሮንቶስ 11:26 — “ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።”
- ዕብራውያን 10:10, 14 — “በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል። . . . አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 66
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።