The Coming of the Son of Man
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሉቃስ ወንጌል ክስተቶች ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚገነቡ እና የሚጓዙ ናቸው ፡፡ ሉቃ (21፡ 1-4) ስለ መበለቲቱ ስጦታ ለመቅደሱ ስለ ሰጠቻቸዉ ሁለት ትንሽ ሳንቲሞች ያወራል ፤ ከዚያም ኢየሱስ በሉቃ (21፡ 5-6) የመቅደሱን መፍረስ አመለከተ፣ በሉቃ (21፡ 7-19) የመጨረሻዉ ዘመን ምልክቶች እና በሉቃ (21፡ 20-24) የኢየሩሳሌምን መፈራረስ ያወራል ፤ ነገር ግን በዚህ ክፍል በምዕራፉ የቀሩትን ጥቅሶች ማዉጣት እፈልጋለሁ ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (21፡ 25)፡ ኢየሱስ ተመልሶ መምጣቱ እየቀረበ እንደነበር የሚያመለክቱትን ክስተቶች ገለፀ ፤ እግዚአብሄር ምድር ላይ የሚልከው ፍርድ “ የያዕቆብ መከራ “ተብሎ በሚታወቀዉ በመጨረሻዉ ግማሽ ጊዜ ይሆናል ፡፡ ኤር (30፡ 7) የሚለው “ ወዮ ! ያቀን ታላቅ ነዉና …….ነገር ግን ከእርሱ ይድናል “ ፤ ያ ማለት አሁንም ለአይሁድ ሰዎች ተስፋ አለ ማለት ነው ፡፡ “ የባህሮች እና የሞገዶች ማጉራት “ የሚለዉ ሀረግ በሌላ ጥቅስ ላይ ይገኛል ፤ መዝ (46፡ 1-6) የሚለው “ አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን …..ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ….ዉኆቻቸው ጮኹ ተናወጡ…..እግዚአብሄር ፈጥኖ ይረዳታል ፤ አሕዛብ ተናወጡ መንግስታትም ተመለሱ “ ነገር ግን እግዚአብሄር በምድር ዙሪያ በመናወጥ መሀከል ላይ ራሱን ያቆማል ፡፡ በባህሮች እና ሞገዶች ማጓራት አሕዛቦች ግራ የተጋቡ እንደሚሆኑ እንጠብቃለን ፡፡
ሉቃስ (21፡ 26)፡ “ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሳ ይደክማሉ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና “ ፤ ማቴዎስ በወንጌሉ ተመሳሳይ ንግግር መዝግቧል (ማቴ 24፡ 29) ፡፡
ራዕይ (15-19) የመከራ ሰባት አመታት በሁለተኛዉ አጋማሽ ጊዜ ምድር ላይ እግዚአብሄር ሰለሚልካቸዉ ፍርዶች ይገልፃል ፤ በመጀመሪያዉ ሰዎስት አመት ከግማሽ ላይ አለም ሰላምን ታያለች ፤ የሰባተኛዉ አመት ስምምነት በሁለተኛዉ ግማሽ (ዳንኤል 9) ሀሰተኛዉ ክርስቶስ ስምምነቱን በማፍረስ በመቅደሱ ምስሉን ለመትከል ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛል ፤ ይህ በሚሆን ጊዜ የገለፅናቸዉ ሁሉ መካሄድ(መከሰት) ይጀምራሉ ፤ እግዚአብሄር ቁጣዉን ወደታች መላክ ይጀምራል ፡፡ አማኞች የዚህ መከራ ጊዜ አካል ይሆናሉ ? በቅድመ መከራዉ እይታ ይህ በሚሆን ጊዜ አማኞች እዚህ ምድር ላይ አይሆኑም ፤ በመከራዉ መካከል እይታ አማኞች የዚህ ጊዜ አጋማሽ ድረስ ምድር ላይ ይሆናሉ ፤ በሰላም አመታቶቹ ጊዜ እዚህ እንሆናለን ነገር ግን ቁጣ ከመምጣቱ በፊት እንወሰዳለን ፤ ከመከራ ቦኃላ ባለ እይታ አማኞች በእዚህ ሰባት አመት መከራ ጊዜዎች እዚህ ምድር ላይ እንሆናለን ፡፡ የተኛዉንም ስፍራ ብትወስዱ ችግር የለም ለሚመጣዉ ለሰዉ ልጅ የተዘጋጃችሁ መሆናችሁ የተሻለ ነው ፡፡ አማኞች የተዘጋጁ መሆን አለባቸዉ ምክንያቱም በዚህ ዉስጥ እናልፍ ይሆናል ፡፡
ሉቃስ (21፡ 27)፡ “ በዚያን ጊዜም የሰዉ ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል “ ፤ ይህን ከማቴ (24፡ 30) ሲወዳደር “ በዚያን ጊዜም የሰዉ ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል “ ፤ ሉቃስ የሰዉ ልጅ ምልክት መጀመሪያ እንደ ሚከሰት አያካትትም ፡፡ የሰዉ ልጅ ምልክቶች ምን እንደሆኑ ማንም አያዉቅም ነገር ግን በፍጥነት ይሆናሉ ሁሉም የሰዉን ልጅ በደመናት ላይ መምጣት ያያሉ ፡፡ ምድር ላይ የሆነ ነገር የሰዎችን ትኩረት ሁሉ ይይዛል ለሀዘንም ምክንያት ይሆናቸዋል ፤ እንደ ዳን (7፡ 13-14) ምልክቱ ፍራትን ያመነጫል “ የሰዉ ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር ሲመጣ አየሁ “ ፤ ዳንኤል የሰዉ ልጅ እንደ ሚመጣ ተንብዮአል ፡፡
ራዕ (1፡ 7) የሚለው “ ተመልከቱ ! እነሆ ከደመናት ጋር ይመጣል ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል ፡፡ “ በሩሲያ፣ በአሜሪካ፣ በአዎስትራሊያ፣ በችይና፣ ሞዛምቢክ ብትሆኑም አይን ሁሉ ያየዋል ፤ ምናልባት በሚድያ በኩል ይከወን ይሆናል ፤ ለእርግጠኝነት እንዴት እንደተፈጠረ ለማወቅ መንገድ አይኖረንም ፡፡
ሉቃስ (21፡ 28)፡ “ ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቧልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሱ “ ፤ መዝ (24፡ 7) የሚለው “ ….የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ የክብርም ንጉስ ይግባ “ ፡፡ በሀብታሙ ሰዉዬ እና በአልዓዛር ተመሳሳይ አስተሳሰብ ታይቷል ፤ በቁሶች እና በሚያልፉ ነገሮች በጣም ያተኮረዉ ሀብታሙ ሰዉዬ ራሱ(ሀሳቡ) ወደታች ነበር ፤ ነገር ግን ራሳችሁ(ሀሳባችሁ) ወደ ላይ በሚሆን ጊዜ በሁሉም ነገር ለእግዚአብሄር ትመለከታላችሁ(ታደርጋላችሁ) ፡፡ መዝ (111፡ 9) የሚለው “ መድኃኒትንም ለሕዝቡ ሰደደ….ስሙ የተቀደሰ እና የተፈራ ነው “ ፤ ኢሳ (63፡ 4) የሚለው “ የምበቀልበት ቀን በልቤ ነዉና የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና “ ፤ መከራ እና መቤዠት መጠበቅ እንችላለን ፡፡
ሉቃስ (21፡ 29-33)፡ ኢየሱስ በምሳሌ በመናገር እነዚህን ሁሉ በአንድ ላይ አስቀመጣቸው ፡፡ በቁጥር (29-30) በጋ
መቅረቡን ለማመልከት ቅጠልን በማስቀመጥ የዛፏን ምሳሌ ተጠቀመ ፡፡ በማቴ (24፡ 36) ኢየሱስ የሰዉ ልጅ የሚመለስባትን ጊዜ ምንም እንደ ማያውቃት ተናግሯል ፤ እንደ ሰዉ ልጅ ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረ ጊዜ እንኳን አላወቃትም ፤ ማርቆስ 11 ተመሳሳይ ነገር ይናገራል ፡፡ በቁጥር 30 መሰረት በእዉነቱ የበጋ ጊዜ እንደ ቀረበ ይከሰት ይሆናል ፤ በቁጥር 31 ኢየሱስ “ እነዚህን ነገሮች “ ባዩ ጊዜ የእግዚአብሄር መንግስት እንደ ቀረበች ተናግሯል ፤ ምንድን ነገሮች ? የሰዉ ልጅ ከደማናት ጋር መምጣት ምልክቶች የጠፈር ኃይላት መንቀጥቀጥ፣ ከፍራት እና ከሚመጡት ነገሮች መጠበቅ የተነሳ ሰዎች ፌንት ይሰራሉ፣ በአሕዛብ መካከል ምድር ላይ ይጨነቃሉ ፡፡ ኢየሱስ ግልፅ ነበር የአሁን የእግዚአብሄር መንግስት እና የወደፊት የእግዚአብሄር መንግስት አለ ፤ ኢየሱስ የእግዚአብሄርን መንግስት ለመተግበር ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ ይህ ስለ ወደፊቱ የእግዚአብሄር መንግስት ወሬ ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የተናገረው ፈለካዊ ምልክቶች እና የምድር መናወጦችን በምናይ ጊዜ ቀጥሎም መንፈሳዊ ለዉጦችን እናያለን ፡፡ ኢሳ(27፡ 12-13) የሚለው “ በዚያም ቀን….እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ….በተቀደሰዉም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሄር ይሰግዳሉ “ ፤ በእስራኤል ህዝቦች መካከል መነቃቃት እናያለን ፡፡ ማቴ (24፡ 31) የሚለው “ መለዓክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል …ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ “ ፤ የተመረጡ ህዝቦቹን መሰብሰብ ማየት እንጀምራለን ፡፡ ማቴ (24፡ 34) የሚለው “ እዉነት እላችኋለሁ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትዉልድ አያልፍም “ ፤ አንድ ትዉልድ ይህን ማሳወቅን ያያል ፤ በምንድን ያ ትዉልድ እንሆናለን ? እነዚህን የሰባት አመት ከባድ መናወጦች፣ ሰላም፣ አመፀ፣ ሽግግር፣ የሀሰተኛ ክርስቶስን መታየትን እና የሰዉ ልጅን ተመልሶ መምጣት በምንድን እንተገብረዋለን (እንለምደዋለን) ? በምንድን የዚህ አስቀያሚ ጉዞ አካል እንሆናለን ? እንደ ምንፈልገዉ ለመኖር ተቀምጠናል ፤ የልብ ምታችን “ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !” ይሆናል ፡፡
ሉቃስ (21፡ 33)፡ “ ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ “ ፤ በግልፅ አለም የሚያልፍ ይሆናል ከዚያም አድስ እስራኤል፣ አድስ መዋቅር፣ አድስ ምድር እና አድስ ሰማይ እናያለን ፤ “ ነገር ግን ቃሌ አያልፍም “ ፡፡ በኢሳ (40፡ 8) ተፅፎ የነበረውን ኢየሱስ አረጋገጠው “ ሳሩ ይደርቃል አበባዉም ይረግፋል የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች “ ፤ ሉቃ (16፡ 17) የሚለው “ ነገር ግን ከህግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ሊያልፍ ይቀልላል “ ፡፡
ሁሉም ነገር በብሉይ ኪዳን በአዲስ ኪዳን በአደስ ኪዳን ወደ ፍሬያማነት እና ፍፃሜ ይመጣል ፤ ሁልጊዜ የእግዚአብሄር ቃል በመጀመሪያ እንደተናገረው እዉነት ሆኖ ይቀጥላል ፡፡ የመፅሀፍ ቅዱስ እያንዳንዱ 66 መፅሀፍ ወደ መሲሁ ያመለክታሉ ፡፡ ኢየሱስ ሊያጠፋ አልመጣም ህጉን እና ነቢያትን ለመፈፀም እንጂ (ማቴ 5፡ 17) ፡፡
በመፅሀፍት በተገለፁት ምክንያቶች ሁሉ የሰዉን ልጅ ከደመናት ጋር መመለስ በምንድን ከሚያዩት አካል እንሆናለን? የመሲሁን መምጣት በምንድን ምስክር እናገኛለን ? በምንድን እናየዋለን እንደ ዋይርስቤ ንግግር “ ሕዝቦች በእስራኤል በሚግዶን ሸለቆ በመሰብሰብ በኢየሩሳሌም ሀሰተኛ ክርስቶስን ይዋጋሉ ከዚያም የክርስቶስን ምልክት ያያሉ ከዚያም በመቀጠል የሰዉ ልጅ ወደ ምድር በመመለስ ጠላቶቹን ያሸንፋል በአይሁዶች የተቀበለ ይሆናል የእግዚአብሄርንም መንግስት እዚህ ምድር ላይ ይመሰረታል “ ? ምድር ላይ የ1000 አመት አገዛዙን መነሻ ለማየት በምንድን እናገኘዋለን ?
ቤተ ክርስቲያን ሉቃ (21፡ 34-38) ስትኖረዉ ለማየት ዝግጁ ነን “ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ….ስለዚህ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት አይመጣባችሁም …..እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ በሰዉ ልጅ ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ ፡፡ “ እንደ ቤተ ክርስቲያን መከራዉን ለመቋቋም ጥንካሬ እንዲኖረን አሁን መፀለይ አለብን ያ ከሆነ በሰዉ ልጅ ፊት መቆም እንችላለን ፤ በተመሳሳይ 1ዮሐ (2፡ 28) የሚለው “ አሁንም ልጆች ሆይ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ “ ፤ ይህ ሁላችንም የምንወስደዉ ፈተና እንደ ነበር አስቡ ፡፡ ይህ የሚካሄድ እዉነት ነው ፤ ጥሪያችን ለእርሱ መመለስ ሰዎችን እንድናዘጋጅ ነው ፡፡ የመጨረሻዉን ጊዜ ለመቋቋም ለጥንካሬ በምንድን የመጀመሪያ ደረጃ ፀሎት እንጀምራለን ?
መዝጊያ
ለሰዉ ልጅ መመለስ ለመዘጋጀት ኢየሱስ ብዙ ትዕዛዞችን ሰጠ ፤ እየሆነ ባለዉ የነቃን መሆን አለብን ምክንያቱም ቤዛነታችን ቀርቧል (ሉቃ 21፡ 28) ፤ እነዚህ ነገሮች እየሆኑ በምናይ ጊዜ የእግዚአብሄር መንገስት መቅረቡን ልናዉቅ ይገባናል (ሉቃ 21፡ 31) ፡፡ በተጠንቀቅ መሆን አለብን (ሉቃ 21፡ 34) ስለዚህ ወደ ባለፀጋው ሰዉዬ መንገድ ምድራዊ ነገር አንመለስም ፤ ሀሳባችንን ዘላለማዊዉ ነገር ላይ መጠበቅ አለብን ፤ በማንኛዉም ጊዜ መንቃት አለብን (ሉቃ 21፡ 36) ፤ ንቁ ለመሆን አንዱ መንገድ ለጥንካሬ መፀለይ ነው ፡፡ እንደ ክርስቶስ አካል እምነታችንን ማጠንከር አለብን ፤ ያን ለማድረግ ለእምነት እንፀልይ ፤ ለሰዉ ልጅ መመለስ የተዘጋጀን መሆን አለብን ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 211.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1296.
Wiersbe, n.p.
Wiersbe, pp. 211–212.
ጥያቄዎች
-
የኢየሱስ ተከታዮች “ ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸዉን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአቹሁማል ፤ ስለ ስሜም ወደ ምኩራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈዉ ይሰጡዓችኋል ወደ ነገስታትና ወደ ገዢዎችም ይወስዱአችኋልም “ (ሉቃ 21፡ 12-13 NASB ) ፤ ይህ ወደ ምን እድል እንደሚመራ ኢየሱስ ተናገረ ? በመንግስቱ አይን(እይታ) እድሎች ዉስጥ ችግሮችን አይታችኋል ? አዎ ከሆነ ከአንድ ሰዉ ጋር ታሪኩን ተነጋገሩት (ተጋሩት) ፡፡
-
በሉቃ (21፡ 16) ኢየሱስ የሚያደምጡትን ተላልፈዉ እንደሚሰጡ እና አንዳንዶቹ የሚሞቱ እንደሚሆኑ አስጠነቀቃቸው በቁጥር 18 ግን ከራሳቸዉ አንዷ ፀጉር እንደ ማትጠፋ ነገራቸው ፤ ይህን ምን ማለት እንደሆን ግለፁ ፡፡ (ሉቃ 12፡ 4-9)
-
ኢየሱስ ብዙ ጊዜ እራሱን እንደ ሰዉ ልጅ ጠቅሷል (ሉቃ 21፡ 27, 36) ፤ ለአይሁዶች ይህ ርዕስ ምንድን ማለቱ ነው (ዳን 7፡ 13-14) ? የሰዎስተኛ አካል አመለካከት ለምንድን እንደ ተጠቀመ ምን ታስባላችሁ ?
-
በሉቃ (21፡ 34) የታጠቃችሁ መሆን የሚለው በሉቃስ (21፡ 36) በንቃት ከመጠበቅ እንዴት ይለያል ?
-
በሉቃስ 21 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 21:34
“Be on your guard, so that your minds are not dulled from carousing, drunkenness, and worries of life, or that day will come on you unexpectedly like a trap.”
መሲሁ ኢየሱስ ይመለሳል፡፡ ስለዚህ፥ ኢየሱስ በተደጋጋሚ ደቀመዛሙርቱ እንዲዘጋጁ፣ እንዲጠብቁ፣ ምልክቶችን እንዲፈልጉ፣ እና እንዳይደናገጡ ተናግሯል፡፡ አዕምሮአቸው ዝግጁ እንዲሆን እና በኑሮ ሀሳብ እና በስካር እንዳይደነዝዝ ይፈልጋል፡፡ አይምሮአቸው ከደነዘዘ፥ ቀኑ እንደወጥመድ ይይዛቸዋል፡፡
ኢየሱስ እንዴት በስካር እና በኑሮ ሀሳብ አዕምሮአችሁ እንዳይደነዝዝ መጠበቅ እንዳለባችሁ እንደተናገረ ልብ በሉ፡፡ ግን እነዴት ነው መጠበቅ የምትችሉት? ኢየሱስ በፀሎት፣ በምስጋና፣ እና ሀሳባችሁን በእርሱ ባላችሁ ተስፋ ላይ እንድትጥሉ ተናግሯል፡፡ ፀሎት ፀንታችሁ የምትቆሙበትን እና በወንጌል የማታፍሩበትን ብርታት ይሰጣችኋል፡፡ የኑሮ ሀሳቦች ሲመጡ፥ ለመጨነቅ ወይም ጊዜያዊ ደስታን ለመፈለግ ያለውን ፈተና ተቋቋሙ፡፡ ይልቁኑ፥ ወደ ኢየሱስ ተጠጉ እና ጸንታቸሁ ቁሙ፡፡ ይህንን በማድረግ ለክርስቶስ ዳግም ምጸአት ዝግጁ ትሆናላችሁ፡፡
“ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ”
— ሉቃስ 21:34
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ሉቃስ 21:36 — “እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ። ”
- ቆላስይስ 4:2 — “ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ ”
- 1ኛ ጴጥሮስ 1:13 — “ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 65
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።