Meeting the Sadducees Challenge
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አብዛኛዎቹ የኢየሱስ መስተጋብር ከኃይማኖት መሪዎች ጋር ነበር ፤ በብዛት እነዚህ መስተጋብሮች አንዳንድ የፍቅር ዉትረት አይነት ነበሩ ፡፡ በኃጢዓተኞች እና በቀረጥ ሰብሳቢዎች መወደዱ በአንዳንድ ምክንያት ሰዎች ተበሳጩ ፤ ኃይማኖተኛ ሰዎች ከልምድ ወይም ከ613 ህጎች፣ ደንቦች እና መተዳደሪያዎች ጋር ባለመጣጣሙ በሁሉም ነገር ተቸግረዉ ነበር ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (20፡ 1-8)፡ የኢየሱስ ስልጣን በመቅደሱ በካህናት አለቆች እና ፃፎች ተቃዉሞ ገጥሞት ነበር ፡፡
ሉቃስ (20፡ 9-19)፡ ኢየሱስ አገልጋዮቹን በአትክልት ስፋራዉ ላይ እንዲያረጋግጥ ስለ ላከው ስለ ወይኑ ተክል ቦታ ባለቤት አንድ ምሳሌ ነገራቸው ፤ ተከራይ ገበሬዎቹም ባሪያዎቹን መቱበት ልጁንም ገደሉት ፡፡ ምሳሌዉን ከተናገረ በኋላ ኢየሱስ “ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን እራስ ሆነ “ (ቁጥር 17) ፤ የኃይማኖት መሪዎእ ኢየሱስን ሊገድሉት አሰቡ ምክንያቱም ምሳሌዉ ስለ እነርሱ እንደ ነበር ስላወቁ ፡፡ የሰዉ ልጅ ከእኛ ጋር ለመገናኘት እና ነፃ ሊያደርገን በሰዉ ስጋ ወደ ምድር መምጣት እንደሚያስፈልገዉ እግዚአብሄር ያውቃል ፤ እንደዉም ሰዎች የአካባቢያቸዉን ባለስልጣን እንካን አለማክበር እንደ ማያስፈልጋችሁ አስተምሯቸዋል ፤ ኢየሱስ ህዝቡን ለማንቀሳቀስ እና አጉል ነገር ለመስራት እዚያ አልነበረም ፡፡ ሰዎችን ከነበሩበት ባርነት ነፃ ሊያወጣ መጣ ፡፡
ሉቃስ (20፡ 27)፡ ሰዱቃዉያን ፈሪሳዉያን አክብረዉት የነበረዉን የቃል ባህል አልተቀበሉትም ነበር ፤ ሁሉም ትምህርታቸው በህግ የመጀመሪያዎቹ አምስት መፅሀፍት - አሪት ላይ የተመሰረተ ነዉ ፤ በትንሳኤ፣ በመለዓክት እና በመንፈስ አያምኑም (ሐዋ 23፡ 8) ፡፡ ምንድን ለማድረግ ነበር የሚኖሩት ?ዋይርስቤ የተናገረው “ ትንሳኤ መልሶ ግንባታ አይደለም ፤ በአሮጌዉ አካል ቀጣይነት ያለዉ ነገር ግን ተመሳሳይነት የሌለው ተዓምራታዊ የአድስ አካል ስጦታ ነው “ ፡፡ በሐዋ (4፡ 1-2) “ በኢየሱስ የሙታን ትንሳኤ “ ደቀ መዛሙርቱን ተቃወሟቸው ፤ በማንኝዉም ጊዜ ትንሳኤ ሲሰበክ ሰዱቃዉያን በዚህ ጉዳይ ነበራቸው ፤ በዮሐ (12፡ 10-11) የካህናት አለቆች አለዓዛርን ለመግደል ወሰኑ ምክንያቱም ሰዎች በኢየሱስ እንዲያምኑ የሱ ትንሳኤ ምክንያት ስለ ነበር ፡፡ ለኢየሱስ በዚህ ተቃዉሞ ከሞት መነሳት እንደሌለ ለማረጋገጥ ፈለጉ ፡፡
ሉቃስ (20፡ 28-33)፡ ሰዱቃዉያን ለኢየሱስ ያቀረቡት ታሪክ በጋብቻ ልምዳቸዉ ላይ የተመሰረተ ነበር ፡፡ እንደ ዘዳ(25፡ 5-6) አንድ ሰዉ ልጅ ሳይኖረዉ ሲሞት ሚስቲቱም የሞተዉ ወንድሙን ስም የሚሸከም ልጅ ለመዉለድ ወንድሙን ታገባለች ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የተናገረው “ ህጉ ተዘጋጅቶ የነበረው ያለ ልጅ የሞተዉን ሰዉዬ ስም ለማስቀጠል ነበር “ ፡፡ በዚህ ታሪክ ሴትየዋ ሰባት ወንድማማቾችን አገባች ሁሉም ልጅ ሳይኖራቸዉ ሞቱ ፤ በመጨረሻም ሴቲቱም ሞተች ፤ ከዚያም ሰዱቃዉያን “ በትንሳኤ ከእነርሱ ለማንኛቸው ሚስት ትሆናለች ?” ብለዉ በመጠየቅ ትንሳኤ ወደ መጥፎ ዉጤት እንደሚመራ ለማሳየት ፈለጉ ፡፡
ሉቃስ (20፡ 34-36)፡ ኢየሱስም “ የዚህ አለም ልጆች ያገባሉ ይጋባሉም ያን ዓለም እና ከሙታን ትንሳኤ ሊያገኙ የሚገባቸው እነዚያ ግን አያገቡም አይጋቡምም እንደ መለዓክት ናቸዉና ሊሞቱም ወደ ፊት አይቻላቸዉም የትንሳኤም ልጆች ስለ ሆኑ የእግዚአብሄር ልጆች ናቸውና “ አላቸው ፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች በዚያን ጊዜ አካል ለመሆን ዋጋ እንዳላቸዉ ቢቆጥሩም እንኳን - በወደፊቱ በእግዚአብሄርሰ መንግስት - በተንሳኤ የተሳተፉ ቢሆኑም እንካን አያገቡም ፤ የኢየሱስ መልስ የወደፊቱ ዘመን ከአሁኑ ዘመን የተለየ እንደሚሆን ገለጠ ፡፡ በሰማይ በጣም ክርስቶስ ላይ ያተኮርን እንሆናለን ተረጂ አስተሳሰብ አያስፈልገንም ፡፡
ሉቃስ (20፡ 37-38)፡ በሚቃጠለዉ ቁጥቋጦ መገናኘት እግዚአብሄር ራሱን የአብርሃም አምላክ፣ የይሳቅ አምላክ እና የያዕቆብ አምላክ ብሎ ጠርቷል (ዘጸ 3፡ 6) ፡፡ ኢሳያስ ትንሳኤን ተንብዮአል፡ “ ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ ሬሳዎችህም ይነሳሉ…..ምድርም ሙታንን ታወጣለችን “ (ኢሳ 26፡ 19) ፤ ዳን (12፡ 2) የተናገረው “ በምድርም ትቢያ ዉስጥ ካንቀላፉት ብዙዎቹ ፤ እኩሌቶቹም ወደ ዘላለም ህይወት እኩሌቶቹም ወደ እፍረት እና ወደ ዘላለም ጉስቁልና“ ፡፡ ትንሳኤ እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ተገልፆአል “ ጌታ እራሱ …ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመዉ ይነሳሉና ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ህያዋን ሆነን የቀረን…እንነጠቃለን “ (1ተሰ 4፡ 16-17) ፤ የሙታን ትንሳኤ በዚያን ቀን በዚያን ጊዜ ይሆናል ፤ በሚሆን ጊዜ መጋባት እና ሞት አይኖርም ፡፡ ማቴ (24፡ 31) የሚለው “ መለዓክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል….ከአራቱም ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ “ ፡፡ በዮሐ (5፡ 28) ኢየሱስ የተናገረው “ በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምጽን የሚሰሙበት ይመጣል …..ለህይወት ትንሳኤ……ለፍርድ ትንሳኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ “ ፡፡ በዮሐ (11፡ 25) ኢየሱስ ያለው “ ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ህያዉ ይሆናል ፡፡”
ሉቃስ (20፡ 39-40)፡ ፃፎች “ መምህር ሆይ መልካም ተናገርህ “ ብለዉ ለምን መለሱለት ? ኢየሱስ ነቢያትና ህጉ የተናገረዉን ደግሞ እየተናገር ነበር ፤ እንደ መፅሀፍታቸዉ የኢየሱስ መልስ ትክክል ስለ ነበር “ ምንም ነገር ሊጠይቁት አልፈለጉም “ ፡፡ እነርሱን በመዉደድ ዉስጥ ለእነርሱን ማዳመጥ ኢየሱስ ለመስማት ምንድን እንደሚያስፈልጋቸዉ ተረዳ ፤ በኢየሱስ ዉስጥ ያለዉ መንፈስ ቅዱስ በሁኔታዉ ላይ በመመለከት በትክክል መልስ እንዲሆናቸዉ እንደአስፈለጋቸው መለሰላቸው ፡፡ በ 1ቆሮንቶስ 9 ጳዉሎስ ከሰዎች ጋር እንዴት መስተጋብር እንደምናደርግ አሳይቶናል ፤ ጳዉሎስ ራሱን “ የሚበልጡትን እንድጠቅም እንደ ባሪያ ራሴን አስገዛሁ ፤ አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁዳዊ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ “ (ቁጥር 18-19) ፡፡ ኢየሱስ በእርሱ እንዲያምኑ ለማሸነፍ ከፃፎች ጋር ምንድን በማድረግ መስተጋብር አደረገ ? ኢየሱስ ለመስማት የሚያስፈልጋቸዉን በትክክል የእነርሱን ንግግር ተናገረ ፤ ኢየሱስ ዘጸዓትን፣ ሙሴን እና የሚነድደዉን ቁጥቋጦ ታሪክ ደገመው ፡፡ ጳዉሎስ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት “ ከህግ ስር “እንዳሉት ወይም “ ህግ እንደሌላቸው” ሆነ (ቁጥር 20-21) ፤ ለደካሞች ጳዉሎስ ደካማ ሆነ ( ሀሳባቸዉን ባለ መናቅ) “ አንዳንዶችን ለማዳን በሁሉ ነገር “ ይጠቀማል (ቁጥር 22) ፡፡ ኢየሱስ እና ጳዉሎስ ከጠፉት በጎች ኃላ ሄዱ ፡፡ ብዙ ጊዜ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም ነገር ከሌላ ቦታ ይመርጣሉ ፤ ሌሎች የሚያደርጉትን ያደርጋሉ በተጨማሪም በአካባቢያቸዉ ላሉት ሰዎች ፍላጎት በሚስማማ መንገድ ከመግባባት ይልቅ በሌላ ቤተ ክርስቲያን የሰራዉን በማህበረሰባቸዉ ዉስጥ ይተገብራሉ ፡፡ ኢየሱስ በደህና የኃይማኖት መሪዎችን ስላቀረባቸው በተናገረው ላይ አመሰገኑት ፤ ባይስማሙም እንኳን ወደ ተመሳሳይ ሀሳብ መጡ ፡፡
ሉቃስ (20፡ 41-44)፡ ኢየሱስ በዚህ አላቆመም ይልቁንም አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው “ ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ ? ዳዊትም ራሱ በመዝሙራት መፅሀፍ፡ ጌታዬ ጌታዬን ….በቀኜ ተቀመጥ አለው ይልላ …ጌታ ብሎ ይጠራዋል እንዴትስ ልጁ ይሆናል ? ኢየሱስ ከመዝ (110፡ 1) የዳዊትን ቃል ጠቀሰ ፡፡
ሉቃስ (20፡ 44)፡ “ እንዴት መሲሁ ልጁ ሊሆን ይችላል ? ” ዳዊት ራሱን እንደ ጌታ ካሳወቀ መሲሁ የእርሱ አምላክ ይሆናል የሚቆጣጠረው መሲሆ ይሆናል ፤ ኢየሱስ እንደ ሰዉ ልጅ ተለይቶ ነበር ፤ የመጀመሪያዉ ሀረግ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሄር ለይቶታል ሁለተኛዉ ሀረግ እንደ ሰዉ ለይቶታል ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እና የሰዉ ልጅ ነው፡፡ በሐዋ (2፡ 32-36) ጴጥሮስ እግዚአብሄር ኢየሱስን አስነስቶ በእግዚአብሄር ቀኝ ከፍ እንዳደረገው ምስክሮች እንደ ነበሩ ይገልፃል ፤ ጴጥሮስ “ እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሄር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ ይወቅ “ (ቁጥር 36) ፡፡ በሐዋ (13፡ 22-23) ጳዉሎስ እግዚአብሄር ወደፊት አዳኙን ኢየሱስን ከዳዊት ዘር እንደሚያመጣ ቃል ገብቶ እንደ ነበር ያረጋግጣል ፤ ለዳዊት ይህ የተፈፀመው የእግዚአብሄር ተስፋ በ 2ሳሙ (7፡ 12-14) ላይ ልጁ ከዳዊት ዉስጥ እንደሚመጣ የተባለው ነው ፡፡
መዝጊያ
ሮሜ (1፡ 3-4) የሚለው “ ይህም ወንጌል በስጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሳት የተነሳ በኃይል የእግዚአብሄር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው ፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ “ ኃይማኖተኞች ጌታን እንደ ሰዉ ልጅ ለመያስ አስቸጋሪ ጊዜ የነበራቸዉ ምክንያት በትንሳኤ ስለ አላመኑ ነበር ፤ ለእዉነት ልባቸው ደንድኖ ነበር አይናቸዉም ታዉሮ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከእነዚህ ኃይማኖት መሪዎች እንዲጠነቀቁ አስጠነቀቃቸዉ ምክንያቱም በራሳቸዉ እዉነት እና ማንነት ለሞኝ ሰዎች እንደ ሽፋን ይህ የታሰበ ግብዛነት ስለ ነበራቸው ፤ ሰዎችን ወደ መጨረሻዉ(ወደ ትክክለኛዉ) እዉነት ማመልከት ባለመፈለግ “መሲሀቸዉን ባለ መቀበል እንዲሰቀል መረጡት “ ፡፡ ብሉይ ኪዳን ስለ ሙታን ትንሳኤ የሚያወራው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ እንደሚመጣ በፍፁም ወደ እዉነቱ ስላልመጡ (በፍፁም እዉነቱን ስላልገዙት) በጊዜአቸው ህዝቦችን ወደ ኪሳራ መሩ ፡፡ የኃይማኖት መሪዎች ልባቸዉን አደነደኑ ፤ ዕብ (3፡ 7-8) እነርሱን እንዳንመስል ያስጠነቅቃል ፡፡ ልባችንን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤና ህይወት እዉነት ማደንደን የለብንም ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 207.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1293.
Nelson’s, p. 1293.
Wiersbe, p. 208.
Wiersbe, p. 208.
ጥያቄዎች
-
ኢየሱስ በመቅደስ አስተማረ ወንጌልንም ሰበከ ፤ “ ወንጌል “ ማለት ምንድን ነው ? በወንጌል እንዳመናችሁት ትኖራላችሁ ? ከሌሎች ጋር ይህን ትጋሩታላችሁ ? አይደለም ከሆነ እንዳታደርጉት ምን ከለከላችሁ ?
-
የካህናት አለቆች፣ ፃፎች እና ሽማግሌዎች ኢየሱስን ተቃወሙት (ሉቃ 20፡ 1-2) ፤ ከእርሱ ጋር ጉዳያቸዉ ምን ነበር ? “ ኃይማኖታዊ ሰዎች “ ተቃዉመዋችሁ ነበር (ያወቃሉስ) ? ይህ ዋስትና ሆኗል ? (ማቴ 18፡ 15-17; 1ጢሞ 5፡ 1-2; 2ጢሞ 4፡ 2)
-
በሉቃ (20፡ 25) ኢየሱስ “ እንኪያስ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሄርንም ለእግዚአብሄር አላቸው “ ፤ የእግዚአብሄር የሆኑት ነገሮች ምንድን ናቸው ?
-
በሉቃስ 20 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 20:39–40
“Some of the scribes answered, ‘Teacher, You have spoken well.’ And they no longer dared to ask Him anything.”
ፃፎች እና የካህናት አለቆች ኢየሱስን ለማስወገድ ስለፈለጉ እጃቸውን የሚጭኑበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡ ያጠምዱት ዘንድ ፥ ኢየሱስን ብዙ ጥያቄዎች ጠየቁት፡፡ ኢየሱስ እርሱን በመጠየቅ ውስጥ ያለውን ተንኮል ስላስተዋለ፥ ለመናገር ይዘገይ ነበር፥ በሚመልስላቸው ጊዜ ጥበብን ይጠቀም ነበር፡፡ በጥሩ ሁኔታ ከመመለሱ የተነሳ፥ በቀጣይ ጥያቄ ለመጠየቅ አልደፈሩም፡፡
ከኢየሱስ ጋር በምትሄዱበት ጊዜ፥ በእምነታችሁ እንድትሰናከሉ በመሞከር በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ጥያቄን ሊጠይቋችሁ ይችላሉ፡፡ አስታውሱ፥ ተንኮል የጠላት መሳሪያ ነው፡፡ በገነት ውስጥ እባቡ ሄዋን ላይ ተንኮለኛ እንደነበር ፥በክርስቶስ ኢየሱስ ያላችሁን እምነት ለማናወጥ ጠላት ተንኮለኛ ሰዎችን በመንገዳችሁ ይልካል፡፡ ነገርግን፥ እንደ ኢየሱስ ሁኔታዎችን መለየትን እና ጥበብን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልታችኋል፡፡ መልስ በምትሰጡበት ጊዜ፥ ለመናገር ዘግዩ፥ በሌሎች አትናደዱ፡፡ በክርስቶስ ባላችሁ ስልጣን ተራመዱ እና እውነትን በፍቅር ተናገሩ፡፡ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፡፡
“ከጻፎችም አንዳንዶቹ መልሰው፦ መምህር ሆይ፥ መልካም ተናገርህ አሉት። ወደ ፊትም አንድ ነገር ስንኳ ሊጠይቁት አልደፈሩም።”
— ሉቃስ 20:39–40
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ዘፍጥረት 3:1 — “እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።”
- ሉቃስ 12:12 — “መንፈስ ቅዱስ በዚያች ሰዓት ልትናገሩ የሚገባችሁን ያስተምራችኋልና። ”
- ኤፌሶን 4:14–15 — “እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 64
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።