The Gospels Luke

True Faith

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 173 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

አንድ ሰዉ በአድስ እና በታደሰ መንገድ ኢየሱስን በሙላት ማግኘት በሚፈልግ ጊዜ ሁሉንም ህዝብ በጥቅል ተፅዕኖ ያመጣባቸዋል ፤ ሉቃስ 19 አንድ “ በጣም አጭር ሰዉ “ ለብዙ በግልፅ ተርቦ ነበር ፤ ስለ ኢየሱስ ብዙ ለመቅመስ (ለመስማት) ፈለገ ስለዚህም ኢየሱስን ወደ ማግኘት የሚወስደዉን ሁሉ አደረገ ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (19፡ 1-2)፡ ኢየሱስ በኩል እያለፈ ዘኬዎስ የሚባል ሀብታም ቀረጥ ሰብሳቢ አገኘ ፤ አለቃ ቀረጥ ሰብሳቢ በመሆኑ የተጠላ ሰዉ ነበር ፡፡ በዚያን ጊዜ በእስራኤል ቀረጥ የሚሰበሰብባቸዉ ሰዎስት ቦታዎች ነበሩ፡ ኢየሩሳሌም፣ ኢያሪኮ እና ቅፍርናሆም ፡፡ ዘኬዎስ በሁሉም ሰዉ የተጠላ ነበር ፤ “ ምናልባትም ዘኬዎስ ትልቅ ቅርንጫፍ ላይ ይቆጣጠራል ለእርሱም የሚሰሩ ብዙ ሰራተኞች ነበሩት “ ፡፡ ቀረጥ ይሰበስብባቸዉ ከነበሩት ብቻ አልነበረም ይሰርቅ የነበረው ምናልባትም ለእርሱም ይሰሩለት ከነበሩትም እንጂ ፡፡ ከተመቸው ከሰዎስቱ ትልቅ ከተሞች ከአንዱ መጣ ፤ ማክአርቱር ይህን ማግኘት ኢየሱስ “ ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሄር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል ! “ (ሉቃ 18፡ 24) ያለዉን የጎበዙን ባለፀጋ ሰዉዬ መግለጫ አነፃፅሮታል ፤ ነገር ግን ኢየሱስ በተጨማሪም “ በሰዉ ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሄር ዘንድ ይቻላል “ በማለት አመልክቷል (ሉቃ 18፡ 27) ፡፡ ዘኬዎስ ባለጸጋ የነበረውን በሙሉነት ይህን ሰዉ ለመድረስ የእግዚአብሄርን እድል መፍቀድ አስፈለገን ፡፡

ሉቃስ (19፡ 3)፡ ዘኬዎስ ኢየሱስን ለማየት ሞከረ ነገር ግን አይችልም ነበር ምክንያቱም አጭር ሰዉ ስለ ነበር በህዝቡ ላይ ማየት አይችልም ፤ ኢየሱስን ለማየት ለምን ፈለገ ? ሀብታም ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር ፤ ምናልባትም ስለ ኢየሱስ የኢየሱስ ቀረጥ ሰብሳቢ ደቀ መዝሙር ከነበረው ከማቴዎስ ስምቶ ነበር ፡፡

ሉቃስ (19፡ 4)፡ ዘኬዎስ ከፊት በመሮጥ አንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ ፤ ሾላ ዛፍ ያነሰ የሚሰራጭ ቅርንጫፎች ያሉት ጠንካራ ዛፍ ነው ስለዚህ ማንኛዉም ትንሽ ሰዉ መዉጣት ይችለዋል ፤አንድ ዛፍ ላይ መዉጣት ህፃን መምሰል እና እናም የማያስከብር አንድ ቀረጥ ሰብሳቢ ዝም ብሎ የማያደርገዉ ነገር ነበር ፡፡ ዮሐንስ ካልቪን የተናገረው፡ “ መጓጓት እና ቀላልነት ለእምነት ዝግጅት መለያ ናቸው “ ፡፡ በሉቃ (18፡ 13) ኢየሱስ የአንድ ቀረጥ ሰብሳቢን ፀሎት ገልፃል፡ “ በሩቅ ቆሞ….አምላኬ ሆይ እኔን ኃጢዓተኛዉን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር “ ፤ ኢየሱስም “ ሕፃናትወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው አትከልክሉአቸው ፤ የእግዚአብሄር መንግስት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና “ ለማለት ሄደ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዛፎች ላይ የሚጫዎቱ ብቸኞቹ ሰዎች ህፃናት ናቸው ፤ ለዚያ ነው የዛፍ ምሽጎች የሚገነቡት ፤ ነገር ግን በዚህ ጊዜ የገንዘብ ሹመኛዉ ሰው በአንድ ዛፍ ላይ ወጣ ምክንያቱም ልብ እየገራ እና እንደ ህፃን ልጅ እምነት እየጀመረ ነበር…..ምናልባትም የማቴዎስን እምነት ሰምቶ ስለ ነበር ፡፡

ሉቃስ (19፡ 5)፡ ኢየሱስ ወደ ላይ ተመለከተና ዘኬዎስን እንዲወርድ ጋበዘዉ ስለዚህ ኢየሱስ ከእርሱ ጋር መቆየት ቻለ ፤ ከዚህ ክስተት በፊት ኢየሱስ ከዘኪዎስ ጋር መስተጋብር ኖሮት ነበረው አናዉቅም ፤ ነገር ግን ኢየሱስ በስሙ ጠራው ፡፡ እግዚአብሄር በስማችን በጠራን ጊዜ በፍፁም የማንረሳዉ ልምድ ነው ፤ መዝ (139፡ 13-18) እግዚአብሄር ስለ እኛ እያንዳንዷን ትንሽ ነገር እንደሚያዉቅ ያረጋግጥልናል ፡፡ ዕብራዊያን 1 ኢየሱስ ፈጣሪ ነዉ ይላል ፤ ኢየሱስ ዘኬዎስ ሲፈጠር ከተራዳ በስሙ ያውቀዋል ፡፡ ከስማችን በሚበልጥ መልካችንን ያውቀዋል ምክንያቱም ስለ ፈጠረን፡፡ ኢየሱስ ዘኬዎስን “ ዛሬ በቤትህ ልዉል ይገባኛል “ ብሎ ነገረው ፤ ዘኬዎስ ለተሸለ እየፈለገ እና እየተራበ ነበር ፤ አሁን ኢየሱስ አገኘው ከእርሱም ጋር ጊዜ ማሳለፍ ፈለገ ፡፡

ዘኬዎስ ራሱን በማዋረድ በመንፈስ ድሀ በመሆን ስለ ኢየሱስ ተራበ ተጠማም (ማቴ 5፡ 3-6) ፡፡ ሰዎች ኢየሱስ እንደ ሚያስፈልጋቸዉ ብቻ መናገር አንችልም ፤ ኢየሱስ ለእነርሱ እንደ ሚያስፈልጋቸዉ እንዲያዉቁትም እንጂ ፡፡

ሉቃስ (19፡ 6)፡ ዘኬዎስ በፍጥነት በመዉረድ በደስታ ኢየሱስን ተቀበለው ፤ ዮሐ (1፡ 47-49) የሚለው ኢየሱስ ናትናኤልን ከበለስ ስር አየውና ማን እንደ ነበር አወቀዉ ፤ “ ፊሊጶስ ሳይጠራህ ……አየሁህ “ (ቁጥር 48) ፤ ናትናኤል ኢየሱስን እንደ እግዚአብሄር ልጅ እዉቅና ሰጠ ፡፡ አንድ ሰዉ ስለ ኢየሱስ በተራበ ጊዜ ኢየሱስ እርሱን ወይም እርሷን ይፈልጋል ፡፡

ሉቃስ (19፡ 7)፡ “ ሁሉም አይተው ከኃጢዓተኛ ሰዉ ጋር ሊዉል ገባ ብለዉ አንጎራጎሩ ! “ ኢየሱስ ከኃጢዓተኛዉ ጋር ስለ ተቃቀፈ(ስለ ተባበረ) አጉረመረሙ ፡፡ ዘኬዉስን ከፈሪሳዉያን ጋር እስኪ እናወዳድር ፤ በዉጭ ዘኬዎስ የኃጢዓተኛ መሰየሚያ ነበር ፤ በዉስጡ አንድ ሾላ ዛፍ ላይ በመዉጣቱ መሰረት ለእዉነት የተራበ ነበር ፡፡ በዉጪ ፈሪሳዉያን ኃይማኖተኞች እና የህጉን ፅሁፍ የተከተሉ ነበሩ ፤ ያ ነገር ደህና እንደሆነ በእዉነት ተጫዉተዋል ፤ ነገር ግን በዉስጣቸው ባዶ እና ለኢየሱስ ረሀብ አልነበራቸዉም እዉነትን አልተቀበሉም ፡፡ ዘኬዎስ ኢየሱስን ተቀበለዉ ፈሪሳዉያን ግን ኢየሱስን ከሰሱት ፤ ዘኬዎስ ለጊዜው የቆሸሸ ነበር ነገር ግን በጊዜው ፈሪሳዉያን በዉጪ ጥሩዎች ይመስላሉ ዉስጣቸዉ ባዶ ነበር ፡፡ በማቴዎስ 23 ኢየሱስ ፈሪሳዉያንን የዋንጫዉን እና የሳህኑን ዉጪ ያፀዳሉ ነገር ግን ዉስጣቸዉ በስስት እና በቅሚያ ሞልቶት እንደ ነበር ነገራቸው ፤ “ አንተ ዕዉር ፈሪሳዊ ! ዉጪዉ ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ ዉስጡን አጥራ “ (ማቴ 23፡ 25-26) ፡፡ ኢየሱስ የኅይማኖተኝነትን ጨዋታ ስለ ሚጫወቱ ኮነናቸው(ወቀሳቸዉ) ፡፡ “ እናንተ ግብዞች ጻፎች እና ፈሪሳዉያን ! ….የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ ወዬዉላችሁ ፤ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በዉጭ ለሰው ጻድቃን ትታያላችሁ በዉስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል “ (ማቴ 23፡ 27-28) ፡፡ ኢየሱስ ከሚፈልጉት ጋር ጊዜ ማሳለፍ ይፈልጋል ፡፡

ሉቃስ (19፡ 8)፡ ዘኬዎስ ለኢየሱስ “ ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታዉን ለድሆች እሰጣለሁ….አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው “ ፤ ታኔንሂል የዘኬዎስን የመልስ ድርጊት “ እንደ ፈጣን ንስሀ “ ገልፆታል ፡፡ “ ህጉ በማጭበርበር ለተወሰደ ገንዘብ እንደ ካሳ አንድ አምስተኛ ቅጣት ይፈልጋል…ህጉ እንስሳት ሲሰረቅ እና ሲገደል ብቻ አራት እጥፍ ይጠይቃል “ ፤ በሉቃ (16፡ 13) እንደ ቀረጥ ሰብሳቢ ዘኬዎስ ስሙን ወዳወቀዉ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ ክርስቶስ መገኘት በመጣ ጊዜ ማን እንደ ነበር ራሱን አየው ፤ ዘኬዎስ ከዛፉ ላይ በወረደ ጊዜ ከገንዘብ መዉጣት እንዳለበት እየፈቀደ ነበር ተገነዘበ ምክንያቱም የእግዚአብሄር እና የገንዘብ ባሪያ መሆን ስለ ማይችል ፡፡ ምላሹ በሉቃ (18፡ 18-23) “ ያለዉን ሁሉ ሸጦ ለድሆች ለመስጠት “ እምቢ ካለው ከባለጠጋው ጎበዝ መሪ ጋር ሙሉ ለሙሉ ይቃረናል ፤ ዘኬዎስ በዙሪያዉ ያለዉን የፋይናንስ ገመድ በመቋቋም ሁሉንም ለኢየሱስ ሰጠ ፡፡

ሉቃስ (19፡ 9)፡ ኢየሱስም “ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነዉና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል “ አለ ፤ ገላ (3፡ 7) “ እንኪያስ ከእምነት የሆኑት እነዚህ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ አወቁ “ በማለት ይገለፃል ፡፡ በክርስቶስ በዘኬዎስ እምነት ምክንያት የአብርሀም ልጅ እንደ ነበር እንደ እምነት ሰዉ ምልክት ተደረገ ፡፡ ሮሜ (2፡ 28-29) የሚለው “ በግልጥ አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ አይደለምና በግልጥ በስጋ የሚደረግ መገረዝም መገረዝ አይደለምና ፤ ዳሩ ግን በስዉር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው መገረዝም በመንፈስ የሚደረግ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በመጽሐፍ አይደለም “ ፤ ይህ በግልፅ በዘኬዎስ ሂዎት ላይ ተከናዉኗል ፤ ልቡ ተገርዟል ፡፡

ሉቃስ (19፡ 10)፡ “ የሰዉ ልጅ የጠፋዉን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና “ ፤ ኢየሱስ ወደ ምድር የጠፉትን በጎች፣ የጠፋዉን ገንዘብ፣ የጠፋዉን የስጋ ልጅ እና ዘኪዎስን ሊፈልግ እና ሊያድን መጥቷል ፡፡ ኢየሱስ በሉቃ (14፡ 17-19) እንዳስታወቀዉ ለጠፉት ነፃነትን እና መዳንን በማምጣት የመሲሁን ተልዕኮ ሊፈፅም መጣ ፡፡

መዝጊያ

አምላክ ይመስገን ኢየሱስ ከኃላችን እየመጣ ነው በዚያም ተስፋ ማግኘት እንችላለን ፡፡

  1. John F. MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1318.

  2. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 202.

  3. Robert C. Tannehill, The Narrative Unity of Luke–Acts: A Literary Interpretation (Philadelphia: Fortress Press, 1986), p. 124.

  4. MacArthur, p. 1318.

ጥያቄዎች

  1. በቁጥር 9 ኢየሱስ ለዘኪዎስ መዳን እንደመጣለት ተናገረ ምክንያቱም እዉነተኛ የአብርሃም ልጅ እንደ ነበር ስላሳየ ፤ እነዚህን ነገሮች ኢየሱስ ለምን አለ ?
  2. በቁጥር 10 በአስተያየታችሁ ኢየሱስ ምን ማለቱ ነው ?
  3. በአስሩ አገልጋዮች ምሳሌ ከንጉሱ ምን ያክሉ አገልጋዮቹ ገንዘብ ተቀበሉ ? ዉጤቱ ምን ነበር ? ቁጥር 26 በራሳችሁ ህይወት እዉነት እንደሚሆን አስተዉላችሁታል ? ለምን ወይስ ለምን አላስተዋላችሁም ?
  4. ቁጥር 40 ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ፍጥረትን ሲያለቅሱ/ሲዘምሩ ሌላ የት ታገኛላችሁ ? (መዝ 19፡ 1-4; 96፡ 11-13)
  5. በቁጥር 42 ኢየሱስ ስላለዉ ምን ታስባላችሁ ? ከአይናቸዉ ሰላም እንዴት ነበር የተሰወረችዉ ? ለምን ? (ዘጸ 7፡ 3-14; ዘዳ 2፡ 30; ኢሳ 6፡ 10)
  6. በመቅደስ ኢየሱስ ያሳየዉ ንዴት የፅድቅ ንዴት ሊሆን(ሊታይ) ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይሆንም ? ኢየሱስ ስለ ንዴት ምን ብሏል ? (ኤፌ 4፡ 26) በፅድቅ ንዴት እና በንዴት መካከል ያለዉ ልዩነት ምንድን ነው ?
  7. በሉቃስ 19 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 19:9–10

“‘Today salvation has come to this house,’ Jesus told him, ‘because he too is a son of Abraham. For the Son of Man has come to seek and to save the lost.’”

ኢየሱስ በኢያሪኮ ውስጥ በሚያልፍበት ጊዜ፥ ብዙ ሕዝብ ተከተለው፡፡ ዘኬዎስ የሚባል ባለጠጋ ቀራጭ ኢየሱስን ለማየት እንዲችል በዛፍ ላይ ወጣ፡፡ ኢየሱስም ባለፈ ጊዜ፥ ዘኬዎስን አየው እና በቤቱ ይውል ዘንድ ስለሚገባው፥ እንዲወርድ ነገረው፡፡ ዘኬዎስ ፈጥኖ ወረደ እና ኢየሱስን ወደ ቤቱ በደስታ ተቀበለው፡፡ ዘኬዎስ ኢየሱስን የሕይወቱ ጌታ ሲያደርግ ሕይወቱ ተለወጠ፡፡ የሰው ልጅ፥ ኢየሱስ፥ የጠፋውን ለመፈለግ እና ለማዳን መጥቷል፡፡ ኢየሱስ ዘኬዎስን በዛፍ ላይ አየው እና ከእርሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍን ፈለገ፡፡ ዘኬዎስ የኢየሱስን ፍቅር በመቀበሉ ህይወቱ ለዘላላም ተለወጠ፡፡

ዛሬ ፥ ህይወታችሁን ለጌታ ስትኖሩ የሚያዩአችሁን ሰዎች ለማየት አይኖቻችሁን ክፈቱ፡፡ ከዚያም ቀጣዩን ነገር አድርጉ፡፡ በቤታችሁ የምግብ ግብዣ አድርጉላቸው ወይም እናንተ ወደ እነርሱ ቤት ለመሄድ ፈቃደኞች ሁኑ፡፡ ከእነርሱ ጋር ጊዜ በማሳለፍ የኢየሱስን ፍቅር አሳዩአቸው፡፡ ከምቹ ክልላችሁ እንድትወጡ ይጠበቅባችሁ ይሆናል፥ ቢሆንም ግን ኢየሱስ ህይወቱን የኖረው እንደዛ ነው፡፡ ወደ ቀራጭ ሰው ቤት በመሄዱ ቢነቀፍም፥ ሆኖም ወደዚያ በመሄድ ፍቅርን አሳየ፡፡ የጠፋውን የመፈለግ እና የማዳን ተልዕኮ አሁን የእናንተም ተልዕኮ ነው፡፡ በመንገዳችሁ ስትሄዱ ፥ ልክ እንደ ኢየሱስ የምትወዱትን አንድ ሰው ለማየት አይኖቻችሁን ክፈቱ!

“ ኢየሱስም፦ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤ የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው። ”

—ሉቃስ 19:9–10

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ሮሜ 1:16 — “በእነርሱም መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ። ”
  • ሮሜ 10:1 — “ወንድሞች ሆይ፥ የልቤ በጎ ፈቃድና ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ልመናዬ እንዲድኑ ነው። ”
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 9:22–23 — “ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ። በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 63