The Gospels Luke

Be Persistent in Prayer

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 172 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሉቃስ ወንጌል የሰዉ ልጅ ተብሎ የሚታወቀዉን የኢየሱስን መልክ ስለነዋል ፡፡ ኢየሱስ ከሰዎች ጋር ለመቀራረብ(ለመቀጣጠር) ፍቃደኛ ነበር ፤ የሩቅ አምላክ አልነበረም ፤ ከሰዎች ጋር መስተጋብር የማይፈጥር አምላክ አልነበረም ፤ በሰዉ ስጋ አምላክ ነበር ፡፡ ሁሉንም አካል ወደ ግብዣዉ ጋበዛቸው ፤ የሰዉ መዉደቅ የነበረዉን የነበረንን ዋና ጉዳይ አስወገደልን ፤ ዋጀን ፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴ ስለ እግዚአብሄር በምናስብ ጊዜ ቀረቤታዉን አናስበዉም ፤ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር መተሳሰር ይፈልጋል ፤ ከእኛ ጋር ዝምድና(ግንኙነት) እንዲኖረዉ ይፈልጋል ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (18፡ 1)፡ ኢየሱስ ሁል ጊዜ ተስፋ ሳይቆርጡ የመፀለይን አስፈላጊነት የገለፀ አንድ ምሳሌ ነገራቸው ፤ ሁልጊዜ መፀለይ አስፈላጊ ነው ስለዚህም በህይወት አዘኖች ተስፋ የቆረጥን፣ የተጨነቅን እና ስሜታችን የተጎዳ መሆን የለብንም ፡፡ መፅሀፍ በሁሉም ነገር ምስጋና እንድንሰጥ ይናገራል ፤ በፀሎት በምንጠብቅ ጊዜ ጠላትን መፋለም እንችላለን ፡፡

ሉቃስ (18፡ 2-3)፡ በምሳሌዉ ዳኛው እግዚአብሄርን አይፈራም ሰዉንም አያከብርም ይህ ማለት አማኝ አልነበረም ፤ በዚች ከተማ ያለችዉ መበለቲቱ ወደ እርሱ መሄዷን በመቀጠል በጠላቷ ላይ ስለ ፍትህ ጠየቀችዉ ፡፡ ሉቃስ ከሌሎቹ ወንጌላት ጥምረት በይበልጥ መበለተቶችን ይጠቅሳል ፡፡ መዝ (68፡ 5) የሚለው “ እግዚአብሄር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት ለባልቴቶችም ዳኛ ነው “ ፤ እግዚአብሄር ረዳት የሌላቸዉን የቅርብ ጓደኛቸዉን ያጡትን ይመለከታል ፡፡ ያዕ (1፡ 27) የሚያሳስበን እግዚአብሄር “ ንፁህ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሄር አብ ዘንድ ይህ ነው ፤ ወላጆች የሌላቸዉን ልጆች ባልቴቶችን በመከራቸዉ መጠየቅ “ እንዲህ የሚመስለዉን እንድናደርግ ይጠብቃል ፤ እነዚህ እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ናቸው ፡፡ በሉቃ (7፡ 11-17) ኢየሱስ የሞተዉን ሰዉዬ አስነሳዉ ምክንያቱም “ እርሱም ለእናቱ አንድ ልጅ ነበር እርስዋም መበለት ነበረች “ (ቁጥር 12) ፡፡ በሉቃ (20፡ 47) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከፃፎች እንዲጠነቀቁ አስጠነቀቃቸዉ ምክንያቱም “ የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸዉንም በማስረዘም የሚያመካኙ “ ስለሆኑ ፡፡ ኃይማኖት መሪዎቻቸዉ መበለቶቹን በመመልከት ይበሏቸዋል ምክንያቱም ከእነርሱ የሆነ ነገር ስለ ሚፈልጉ ፤ በዚያ ፈንታ እግዚአብሄር ለመበለቶች እንክብካቤ እንዲያደርጉላቸዉ ህዝቡን አዘዛ፡፡ በዚህ ምሳሌ መበለቲቱ ፍትኋን እንዲሰጣት ለመለመን በመጠየቅ በዳኛዉ ፊት ቀረበች(ተከሰተች) ፤ ዋይርስቤ ከእርሷ በተቃራኒ የሚያሰሩ ቢያንስ ሰዎስት ነገሮች ነበሯት፡ 1) ሴት ስለ ነበረች በቀኑ ባህል አታስፈልግም(ጥቅም የላትም) ፤ 2) መበለት ስለ ነበረች ስለ እርሷ የሚናገርላት አልነበረም ፤ እንዲሁም 3) ምናልባትም ድሀ ስለ ነበረች በአድሎ ለእርሷ ዳኛዉን ለማግኘት ጉቦ ለመክፈል አቅሟ አይችልም ፡፡

ሉቃስ (18፡ 4-5)፡ ዳኛዉ በመጀመሪያ ሊረዳት ፍቃደኛ አልነበረም ፤ እግዚአብሄር ምን እንዲሚያስብ አያስጨንቀዉም እንዲሁም ምን አንደሚያስፈልጋትም አያሳስበዉም ፤ ነገር ግን በመጨረሻ ዳኛዉ ፍትኋን ሊሰጣት ወሰነ በዚህም በማያቋርጥ ጥያቄዋ አታሰለቸዉም ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የተናገረው “ የማይሰማዉ ዳኝ ለመበለቲቱ የማያቋርጥ ጥያቄ የሚመልስላት ከሆነ እግዚአብሄር ለአማኞቹ የማያቋርጥ ፀሎት በእርግጠኝነት ይመልሳል “ ፤ ዋይርስቤ የመበለቲቱን ሁኔታ ከአማኞች ስፍራ ጋር አነፃፅሮታል ፤ መበለቲቱ ለእርሷ ለማይጨነቀዉ ዳኝ እንግዳ ነበረች ፤ ዳኛዉን ለማግኘት አቅርቦ የሚሰጣት ጠበቃ የላትም ፤ በአንፃሩ እንደ እግዚአብሄር ልጅ እግዚአብሄርን ለማግኘት የተከፈተ አቅርቦት(ቀረቤታ) አለን ፤ ደግሞም በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠ ለእኛ የሚለምን ጠበቃ ኢየሱስ አለን ፡፡

ሉቃስ (18፡ 6-8)፡ ከዚያም ኢየሱስ “ ዓመፀኛዉ ዳኛ ያለዉን ስሙ ፡፡ እግዚአብሄር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሳቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸዉንም ? “ ኢየሱስ እግዚአብሄር ለህዝቦቹ በፍጥነት ፍትህ እንደሚያደርግላቸዉ አብራራ ፡፡ እንደ እግዚአብሄር መንግስት ዜጋ ወደ እግዚአብሄር ኃይል ለመግባት ፀሎትን መጠቀም እንችላለን በዚህም የሰዉ ልጅ ሲመጣ ዝግጁ እንሆናለን ፤ ይህ እንዴት አድርገን እንሰራለን ?

አንዳንድ የተለመዱ ጥቅሶችን እንመልከት፡

  • 1ተሰ (5፡ 16-18)፡ “ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ ! ሳታቋርጡ ጸልዩ ፤ በሁሉ አመስግኑ ፡፡ “
  • 1ጴጥ (3፡ 7)፡ “ እንዲሁም እናንተም ባሎች ሆይ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረዉ ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸዉ ፡፡ “ ባሎች ሚስቶቻቸዉን እንደ ክብር በደንብ ሊንከባከቧቸው ይገባል ፤ በአካባቢያችን ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሄርን እንቅስቃሴ አናይም ምክንያቱም በመጥፎ ትዳሮች ፡፡ አስባችሁታል ምንም እንዳልተፈጠረ ሚስታችሁን በደንብ ሳትንከባከቡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወደ እግዚአብሄር ስትመጡ ?
  • ማቴ (7፡ 7-12)፡ “ ለምኑ ይሰጣችኁማል ፈልጉ ታገኙማላችሁ ፤ መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል “ (ቁጥር 7) ፤ መጠየቃችንን በቀጠልን ጊዜ እግዚአብሄር ይመልስልናል ፤ እንደ እግዚአብሄር ልጆች ወደ እግዚአብሄር የተከፈተ አቅርቦት አለን፣ በእርሱም ፉት ጠበቃ እና ጥሩ ነገሮችን ሊሰጠን እንደሚፈልግ እዉቀቱ አለን ፡፡ ለሆነ ነገር ደግማችሁ ደግማችሁ እና ደግማችሁ መፀለይ ትችላላችሁ ? አዎ እስከሆነ ድረስ ማጉረምረም ወይም መጃጃል አይደለም ፤ ማቴ (6፡ 7-8) የሚለው “ ጣዖት አምላኪ ይመስል መደጋገም “ እንደማንችል ወይም እንደምንሰማ እንፀልያለን ፡፡

የፀሎት ዋጋ በብዙ ክርስቲያኖች ተብራርቷል ፡፡

ኢ.ኤም. ባዉንድ የተናገረው፡ “ በተፈበረከ እና በአሳሳች እይታ የታዘዝነዉን ቅንነት ማጣታችንን እና የፀሎት ድካማችንን ሁልጊዜ ለይቅርታ የተዘጋጀን ነን ፤ ብዙ ጊዜ ከጀምርነዉ ወጥተን ፀሎትን እንጨርሳለን ፡፡ ለእኛ በእዉነት ለምንፀልየዉ እግዚአብሄር በሚጠብቀንእና እየጠበቅን ባለ ጊዜ ዝም ብለን እንፀልይ ፤ ከፀሎት በመሰናክል እንርቃለን ወይም ለአስቸጋሪዎች እንሸነፋለን እናም ወደ እግዚአብሄር ፍቃድ በመታዘዝ ጥሩት “ ፤ “ ይሁን እንጂ ፀሎታችን በፍፁም ሳንደክም፣ በመፅናት የካድን ባለመሆን እና በፍፁም የማይወድቅ ጀግንነት በኃይል መግፋት እና መከታተል ያስፈልገዋል “ ፡፡ የፀሎት ሰዉ በመሆን መታወቅ ትፈልጋላችሁ ?

ቻርለስ ሱፐርጎን የተናገረው፡ “ ትክክለኛ ነገር እንደሆነ እርግጠኛ ከሆናችሁ ስለ ምትጠይቁት አሁን ለምኑ ! ከስዓትም ለምኑ ! ማታም ላይ ለምኑ ! ጉዳያችሁን በለቅሶና በእምባ አሰሙ ! “

ጅኦርጅ ሙለር የተናገረው፡ “ ፀሎት ለመጀመር በቂ ባይሆንም አሁን ለመፀለይ ባያስችልም እንዲሁም ስለ ጊዜዉ ለመፀለይ ለመቀጠል ባይበቃም መልሱን እስክናገኘዉ ድረስ በትዕግስት፣ በእምነት በፀሎት መቀጠል አለብን ፡፡ “

ሉቃስ (18፡ 8)፡ ኢየሱስ ምሳሌዉን እንዳጠናቀቀ “ የሰዉ ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን ? “ ብሎ ጠየቃቸው፤ እንደ ፀሎት ሰዎች ኢየሱስ እንደዚያ ያለ እምነት በኑሮአችን እንዲያገኝ ሀሳቡን ለመያዝ እንዴት እናድርግ ? በምንፀልይ ጊዜ ያን አይነት እምነት እናሳያለን ? ያን አይነት ፀሎት መኖር ማለት በፀሎት ኃይል መስራት ነው ፡፡

ማቴ (17፡ 19-20) የእግዚአብሄር መንግስት ዜጋ በምንሆን ጊዜ የሰናፍጭ ዘር የምታክል እምነት እንዳለን ይገልፃል ፤ ኢየሱስ የተመለከተዉን እምነት ማሳደግ ከፈለግን ከሰናፍጭ ዘር በሚያንስ እምነት እንጀምር ፤ ሉቃ (17፡ 5) እምነታችንን እንዲያሳድግ ለእግዚአብሄር እንድንፀልያ ያበረታታንል ፡፡ ሉቃ (18፡ 8) ኢየሱስ ስለ እግዚአብሄር ልጆች በፀሎት በእርሱ ፊት መምጣት ያላቆሙትን እንደሚመለከት ያረጋግጣል ፡፡ መፀለያቸዉን ሲቀጥሉ የተሟላ እምነት አላቸዉ እግዚአብሄርም ይገለጥላቸዋል ፡፡ ሮሜ (10፡ 17) የሚለው “ እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው “ ፤ በእግዚአብሄር ቃል እያደግን ካልሆነ በእግዚአብሄር አናድግም ፡፡ ሁል ጊዜ በእግዚአብሄር ቃል በመሆን በቀላሉ እምነታችንን ማሳደግ እንችላለን ፤ ያዕ (1፡ 22) የሚለው “ ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ “ ፡፡

የእግዚአብሄርን ቃል እንደ ሰማነው እምነታችንን ማሳደግ እና የእግዚአብሄርን ቃል የምናደርግ መሆን እንፈልጋለን ፤ እንደ እግዚአብሄር መንግስት ዜጋዎች በእምነታችን መተግበር(ማድረግ) ያስፈልገናል ፤ ቃሉን የምናደርግ በምንሆን ጊዜ ቃሉን ለመፈተን መርሳት አንችልም ፡፡ ሚል (3፡ 10) የሚለው “ በዚህ ፈትኑኝ “ ፤ በእምነት እዩ እግዚአብሄር ያሳያችኋል ፡፡ ዕብ (11፡ 6) “ ያለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም “ በማለት ያብራራል ፤ ዕብ (11፡ 1) የሚለው “ እምነት ስፋ ስለ ምናደርገዉ ነገር የሚያስረግጥ የማናየዉንም ነገር የሚያስረዳ ነው “ ፡፡ በእምነት በምንጓዝ ጊዜ እግዚአብሄር በሚያሳየዉ ማረጋገጫ አለን ፡፡ ዕብ (4፡ 15-16) የሰዉ ልጅ እዚህ ምድር ላይ ስለተከሰተ “ ምህረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት መቅረብ እንደምንችል “ ያረጋግጥልናል ፡፡ የሰዉ ልጅ ኢየሱስ በድካማችን የሚያዝንልን ወደ እርሱም እንድንመጣ ይጋብዘናል ምህረት እና ጸጋ እንደሚሰጠን ያውቃል ፡፡

መዝጊያ

ሉቃስ (18፡ 1) እንድንፀልይ ይነግረናል በዚህም ተስፋ የምንቆርጥ አንሆንም ፡፡ በየቀኑ ህይወታችን ተስፋ መቁረጥን ለመፋለም በፀሎት ልንቀጥል ያስፈልገናል የልባችንን መሻት ሊሰጠን እና ሊባርከን እንደሚፈልግ ማወቅ አለብን ፤ መዝ (116፡ 2) የሚለው “ ጆሮዉን ወደ እኔ አዘንብሏልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ “ ፡፡ በህይወት እስካለን ድረስ ጉዞአችንን እና ፀሎታችንን በእምነት እንጠብቅ ፤ በእምነት እንዳለቀሰችዉ ፅኑ መበለት መሆን አለብን ፡፡

5 “Great Quotes on Prayer”; available from https://www.epm.org/resources/2009/Mar/28/great-quotes-prayer/.

7 “Great Quotes on Prayer”; available from https://www.epm.org/resources/2009/Mar/28/great-quotes-prayer/.

  1. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 199.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1288.

  3. Wiersbe, p. 199.

  4. Edward M. Bounds, The Reality of Prayer, p. 38.

  5. Charles H. Spurgeon, “The Importunate Widow”; available from https://www.ccel.org/ccel/spurgeon/sermons15.ix.html.

ጥያቄዎች

  1. በቁጥር 1-8 አንዲት መበለት ሴት ስለ ፍትህ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ በአንድ ዳኛ ፊት ሄደች ፤ ምላሻችሁን እስክትቀበሉ ድረስ ደግማችሁ ደግማችሁ የጠየቃችሁበት ጊዜ አለ ? ልክ እንደ ዚህ ለእግዚአብሄር ፀሎታችሁን ወስዳችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አልወሰዳችሁም ?
  2. ኢየሱስ የፈሪሳዉያንን እና የቀረጥ ሰብሳቢዎችን ምሳሌ ተናገረ ፤ አንድ ጊዜ ላይ ወይም ሌላ ጊዜ ከእነዚህ ስፍራዎች አንድኛዉ ላይ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ካለ ምን እግዚአብሄር ገልጦላችኋል ?
  3. በቁጥር 17 እንደ ህፃን የእግዚአብሄርን መንግስት እንድንቀበል ተነግሮናል ፤ ለእናንተ ይህ ምን ይመስላል ?
  4. ኢየሱስ ስለ መንግስቱ ሲል ንብረታቸዉን ወይም ቤተሰባቸዉን የሰጡ በዚህ ህይወታቸዉ አንዱ መልሶ እንደሚከፍላቸዉ ተናገረ ፤ ለእግዚአብሄር መንግስት የሰጣችሁት ነገር አላችሁ ? አዎ ከሆነ በዚህ አካባቢ መመለሱን እንዴት አያችሁት ?
  5. ለምኖ እንደ ነበረው አይነ ስዉር በፀሎታችሁ ደፋር እና ትክክለኛ ናችሁ ? (ዕብ 4፡ 16)
  6. በሉቃስ 18 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 18:1

“He then told them a parable on the need for them to pray always and not become discouraged.”

ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በነበረበት ጊዜ፥ ከባላጋራዋ እንዲፈርድላት ሳታቋርጥ ወደ ዳኛ ትሄድ የነበረችን መበለት ታሪክ ነገራቸው፡፡ መበለቲቱ ትግስቷ እና ተስፋ አለመቁረጧ ከመብዛቱ የተነሳ ለዳኛው አድካሚ ሆነችበት፡፡ በመጨረሻም ዳኛው የጠየቀችውን ፍርድ ሰጣት፡፡

ኢየሱስ ይህንን ምሳሌ የተናገረበት ምክንያትደቀመዛሙርቱ "ሳያቋርጡ መፀለይ እና ተስፋ አለመቁረጥ" እንደሚያስፈልጋቸው ስለሚያውቅ ነው፡፡ ይህ የሚመለከታችሁ ከሆነ እጃችሁን አንሱ! የምትወዷቸው እነዚያው ሰዎች ኢየሱስን እንደ አዳኛቸው አድርገው እንዲቀበሉ ጌታን ለቀናት፥ ለሳምንታት ወይም ደግሞ ለአመታት ፈልጋችሁታል? ወይም የጠፉት ወንድ እና ሴት ልጆች ወደ ቤት እንዲመለሱ? ወይም ትዳራችሁ ለመልካም እንዲለወጥ? ወይም በምርጫዎቻችሁ ውስጥ ጥበብ እና ግልጽነት እንዲኖር? ጌታ ያውቃል፡፡ በመጠበቅ ውስጥ ያለውን የተስፋ መቁረጥ ዝንባሌ ያውቃል፡፡ ኢየሱስ ተስፋ ባለመቁረጥ ዘወትር እንድንፀልይ ይናገራል፡፡ ዛሬም፥ በድጋሚ፥ በጌታ ፊት ከጥያቄያችሁ ጋር ኑ፡፡ ይሰማችኋል እና ይመልስላችኋል፡፡ መልሱ ምናልባት፥ አይሆንም፥ አዎ ወይም ትንሽ መጠበቅ ይሆናል፡፡ ነገርግን በሙሉ ልባችሁ ከፈለጋችሁት እንደሚመልስላችሁ- ቃል ገብቷል፡፡

“ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው”

—ሉቃስ 18:1

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኢሳይያስ 40:31 — “እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ”
  • ማቴዎስ 7:7 — “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። ”
  • 1ኛ ተሰሎንቄ 5:16–18 — “ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 62