The Kingdom of God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሪቫይቭ ት/ቤት አላማችን እንንተን ወደ እግዚአብሄር አንድ እርምጃ እና ወደ ቃሉ ጥልቀት አንድ እርምጃ መዉሰድ ነው ፡፡ ከሉቃስ 17 የዛሬዉ ርዕስ ስለ እግዚአብሄር መንግስት - መንግስተ ሰማይ መወያየት ነው ፤ አዎ ተመሳሳይ ነገር ናቸው ፡፡ በዛሬዉ የእግዚአብሄር ጥናታችን በኩል በምንድን መያዝ እንደ ምትችሉ እዩ ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (17፡ 20)፡ ፈሪሳዉያን ኢየሱስን “ የእግዚአብሄር መንግስት መቼ ትመጣለች ?” ብለዉ ጠየቁት ኢየሱስም “ የእግዚአብሄር መንግስት አትመጣም “ ብሎ መለሰላቸው ፡፡ ዮሐንስ ፒፐር የእግዚአብሄር መንግስት “ በእግዚአብሄር ንጉስ የሚመራ ነው “ ብሎ ገልፃታል ፤ በሌላ ቋንቋ አገዛዙን፣ ድርጊቱን፣ አምላክነቱን እና ሉዓላዊ አገዛዙን እዚህ አሁን ትቀምሱታላችሁ ፡፡ ፈሪሳዉያን ፖለቲካዊ ንግግር ፈለጉ - ኢየሱስን እንደ ንጉስ ፤ ነገር ግን መንግስቱ በዉጭ በሚታይ አይመጣም እንደ ሚስብ አይሆንምም ወይም እንሱ እንደ ፈለጉት እንደ በስጋዊነት አይመጣም ፡፡
ሉቃስ (17፡ 21)፡ ኢየሱስ “ የእግዚአብሄር መንግስት በመካከላችሁ ነው “ ብሎ ገለፃላቸው ፤ ፈሪሳዉያን የተቀመጠችበትን ቦታ ለማዎቅ ፈለጉ ፤ ኢየሱስም እዚሁ ነች አላቸው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው ስለ መንግስቱ ማደን እንደማያስፈልጋቸዉ ነው ምክንያቱም መንግስቱ ከኢየሱስ ጋር መጥታለች ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ቀጥሎ፡ “ ከሰዉ ልጅ ቀኖች አንዱን ልታዩ የምትመኙበት ወራት ይመጣል አታዩትም “ ፤ አሁን ኢየሱስ ስለ ወደፊቱ እያወራ ነበር ፡፡
ሉቃስ (17፡ 23-24)፡ ኢየሱስ “ እዚያ አለ” ወይም “ እዚህ አለ “ ከሚሏችሁ ኋላ አትከተሉ አላቸው ከዚያም የሰዉ ልጅ “ ከአድማስ እስከ አድማስ “ በሚታይበት ጊዜ የሚሆኑትን የወደፊት ሁኔታዎችን መግለፅ ጀመረ (ቁጥር 24) ፡፡ ቃሉ የዳን (7፡ 13-14) ትንቢትን ወደ አይምሮ ያመጣል፡ “ የሰዉ ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር በዘመናት ወደ ሸመገለዉ ደረሰ “ ፤ እንደ ሉቃስ 11 እነዚህ ምልክቶች የእግዚአብሄርን መንግስት አይቀድሙም ፤ ይሁን እንጂ በማቴዎስ 24 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የሰዉ ልጅ መምጣት ምልክት መጨረሻዉን እንደ ሚቀድም ነገራቸው፡ “ መብረቅ ከምስራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ የሰዉ ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናል “ (ማቴ 24፡ 27) ፡፡ በመጨረሻም ኢየሱስ ለሁሉም እንዲያዩት በደመናት ላይ ይመለሳል ፤ ሰዎች የኢየሱስን መመለስ ስለ መሳት ሊያስጨንቃቸዉ አይገባም ፤ ሁሉም ሰዉ ያውቀዋል ፡፡ “ በዚያን ጊዜም የሰዉ ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል….የሰዉ ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል “ (ማቴ 24፡ 30) ፡፡ ማቴ (25፡ 13) የሚያረጋግጥልን ኢየሱስ እንደ ገና እንደ ሚመጣ ነው መቼ እንደሆነ ብቻ ነዉ የማናውቀው ፤ በሉቃ (12፡ 40) ኢየሱስ የተዘጋጀን እንድንሆን ይናገራል “ ምክንያቱም የሰዉ ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና “ ፤ “ የባሪያዉ ጌታ ባልጠበቀበት ስዓት አንድ ቀን እንደ ሚመጣበት…..እና በማያምኑት ቦታ እንደሚያስቀምጠው “ በማለት ሄደ ፡፡ መቼ እንደሆነ አናውቅም !
በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሄር መንግስት በወደፊት እንደሆነች እያስበች ትመስላለች ፤ አሁን የእግዚአብሄር መንግስት አካል መሆናችንን እረስተናል ፤ በተወለድን ጊዜ ተወልደን የነበረበት አገር ዜጋ ሆነናል ፤ ዜግነት ቅፅበታዊ ነበር ፡፡ እንደ ዮሐንስ 3 ዳግም በተወለድን ጊዜ ወዲያዉኑ የእግዚአብሄር መንግስት ዜጋ እንሆናለን ፤ ኢየሱስ በግልፅ እዚህ አሁን የእግዚአብሄር መንግስት አካል እንድንሆን የሚፈቅድልንን መንፈስ ቅዱስን ሰጥቶናል፡፡ እንደ እግዚአብሄር መንግስት የምንሰራበትን ኃይል ተሰጥቶናል ነገር ግን በዚያ መንገድ እየሰራን አይደለም ፤ መጠበቅ እንዳለብን እናስብ ፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት በኢየሱስ ሞት፣ መቀበር እና ትንሳኤ በኩል የተመሰረት አሰራር አለ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የኢየሱስ የመሪነት አገዛዝን በኛ ኑሮ አንደምታ ይሰጠዋል ፤ የአሁኑ የሚሰራዉ ስራው አለምን ለመዋጀት ነው ፤ የጠፉትን ለማግኘት በምንሄድ ጊዜ ይሆናል ፡፡ ወደፊት ኢየሱስ በሚመለስ ጊዜ መንግስቱ ይመጣል ፤ ጊዜዉን አናዉቀዉም ፤ በድንገት ባልተጠበቀ ሁኔታ ይከሰታል (ይሆናል) ፡፡ አሁን እና ወደፊት የእግዚአብሄር መንግስት ዜጎች ነን ፡፡ በማቴ (10፡ 8) የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በሽተኞችን ፈወሱ፣ የሞተን አስነሱ፣ የቆዳ በሽታ ያለባጨዉን አነፁ በተጨማሪም አጋንንትን አስወጡ ፤ በዉጣችን የትንሳኤዉ ኃይል አለን ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በመካከላችን ነዉ እንዲሁም ወደፊትም ይመጣል ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሄር መንግስት እንደ ሆነች ያስባሉ ፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሄር መንግስት አካል ነች ፤ እግዚአብሄር በዚህ ትልቅ ስዕል አለው ፡፡
ሉቃስ (17፡ 24-25)፡ በእዉነቱ ዳንኤል የሰዉ ልጅ በዳመናት ላይ በኃይል እና በክብር እንደ ሚመጣ ተንብያል ፤ ለዚህ የተዘጋጀን ልንሆን ይገባናል ፡፡ በሰዉ ስጋ ሊያሳጣ በሰበዓዊነት ተመልሶ ይመጣል ፤ ከወደፊቱ መመለስ በፊት ብዙ ነገሮችን ይታገሳል ፤ ስለ ሞቱ፣ ስለ መቀበሩ እና ስለ ትንሳኤዉ እያወራ ነበር ፡፡
ሉቃስ (17፡ 26-27)፡ “ እንደ ኖህ እንደ ነበረዉ ቀን “ ፤ ሁሉም ሰዉ በራሳቸዉ እይታ ትክክል የሆነዉን እያደረጉ እግዚአብሄር ጎርፍ በመላክ ሁሉንም አጠፋቸው ፡፡ በኖህ ጊዜ የሆነው የሰዉ ልጅ እንደ ገና ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ይሆናል ፤ ሰዎች እንደ ተለመደው በሁል ቀን ተግባራቸዉ ዉስጥ እየሄዱ ህይወትን ይኖራሉ ፤ ሰዎቹ ለእግዚአብሄር ትንሽ ትኩረት ያደርጋሉ(ይከፍላሉ) ፤ ስለ ምድራዊ ነገር እያሰቡ በሀብታም ሰዉ አስተሳሰብ ላይ አትኩረዋል ፤ ሰዎች ስለ ዘላለማዊ ነገር ሳያስቡ በየቀኑ ተግባራቸዉ ላይ በይበልጥ ያተኩራሉ ፡፡ ስለ ወደፊቱ የማናስብ ከሆነ ስቃዩ (ሉቃስ 16) ሀቅ ይሆናል ፡፡
ሉቃስ (17፡ 28-29)፡ “ እንዲሁም በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ ፤ ይበሉ ይጠጡም ይገዙም ይሸጡም ይተክሉም ቤትም ይሰሩ ነበር “ ፤ በአሁኑም ጊዜ ሰዎች በዘላለማዊ ሳይሆን በየእለት ህይወታቸዉ አትኩረዋል የኢየሱስን ተመልሶ መምጣት በመጠባበቅ እየኖሩ አይደለም ፤ “ ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነበ ሁሉንም አጠፋ “ (ቁጥር 29) ፡፡
ሉቃስ (17፡ 30-33)፡ “ የሰዉ ልጅ በሚገለጥበት ቀን እንዲሁ ይሆናል ፡፡ “ ብግል ስለ መጨረሻዉ እራይ እያወራን ነው ክርስቶስ በሚታይበት ጊዜ ጠቅላላ ፍርዱ ይመጣል ፤ ለሰዉ ልጅ መመለስ ሰዎችን ዝግጁ ለማድረግ እየሞከራችሁ ነው ? ወይስ ምድራዊ ነገሮች ላይ አትኩረናል ? የእግዚአብሄር መንግስት ዜጋ አስተሳሰብ ሲኖረን ለወደፊቱ ዝግጁ መሆን እንፈልጋለን ፤ ከዚያ ዉጪ ምድራዊ ነገር ላይ ካተኮሩ ሰዎች ጋር እንቀላቀላለን ፡፡ “ በዚያ ቀን “ (ቁጥር 32) የኢየሱስን ሁለተኛ መምጣት ይገልፃል ፤ ሰዎች ያላቸው (ሀብት) ነገረ ጉዳይ አይሆንም ለመሰብሰብ ተመልሰዉ አይሄዱም ፤ ኔልሰን ሰዎች እንደ ማይቆሙ፣ ወደ ኃላ እንደ ማይመለከቱ ነገር ግን በፍጥነት እንደሚጓዙ አብራርቷል ምክንያቱም ቁጣ ስለ ሚመጣ ፡፡
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ የሎጥን ሚስት እንዲያስታዉሱ “ አሳሰባቸው ወደ ኃላ ተመለከተች የጨዉም አምድ ሆነች (ዘፍጥረት 19፡ 26) ፤ የሆነ ነገር በመንፈሷ አሁንም ከምድራዊ ነገር ጋር ተሳስሮ ነበር ፡፡ እንደ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር አይናችን በምድራዊ ነገር ላይ መሆን አይችልም ፤ ዘላለማዊዉ ነገር ላይ ልናተኩር ይገባናል ፡፡ እግዚአብሄር እያደረገ ያለዉን ማየት ባልቻልን ጊዜ ዘላለማዊዉ ላይ አይናችንን ለመጠበቅ ይስቸግራል ፤ በተፈጥሮ ጥሩ ነገር እንዲሰማን በሚያደርግ እንሳባለን ፡፡ “ ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል ነፍሱንም የሚያጠፋ ሁሉ በሕይወት ይጠብቃታል “ (ቁጥር 33) ፤ ይህ ማር (8፡ 34) ሙሉ ለሙሉ እንደ ገና ነው ፡፡ ኢየሱስን ስትከተሉ ራሳችሁን መካድ (የምትወዱትን ምድራዊ ነገር)፤ መስቀሉን ልንሸከም(ልናነሳ) ( ቸግር ለመጋፈጥ እምቢ ለማለት እና ለሰማአታትነት ፈቃደኞች መሆን አለባችሁ) ከዚያም ኢየሱስን ልትከተሉት ያስፈልጋችኋል ፡፡ “ ወደ ኃላ መመልከት “ ወይም “ ወደ እነዚህ ነገሮች መመለስ “ አንችልም ፤ እንደ እግዚአብሄር መንግስት ዜጋ ወደ ፊት መመልከት አለብን ፡፡
ሉቃስ (17፡ 34-36)፡ እነዚህ ጥቅሶች ምናልባት ስለ ዳግም ምፅኣት አያወሩም ስለ ፍርድ እንጂ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ አንዱ በፍርድ የተወሰደ ሲሆን አንዱ ደግሞ በክርስቶስ ለመገዛት ለመኖር የሚቀር ይሆናል ብሎ አብራርቷል ፡፡ ይህ አመለካከት አሁን የእግዚአብሄር መንግስት ዜጋ እንደሆናችሁ ስትረዱ ይሰራል ለእርሱም ተመልሶ መምጣት መጠብቅ አትችሉም ፡፡ ሁልጊዜ ወደ ፊት የምትመለከቱ ከሆነ ወደ ኃላ ለመመልከት ወይም በምድራዊ ነገር ላይ ለመያዝ ጊዜ አይኖራችሁም ፡፡
ሉቃስ (17፡ 37)፡ “ ስጋ ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ “ ፤ ፍርድ በሚመጣ ጊዜ የሞት ግማት ይሸታችኋል ፡፡ ስለ ዚህ አትመለከቱም ምክንያቱም በላተኛ ወፎች በሁሉም ቦታ ይሆናሉ ፡፡
መዝጊያ
ልንረዳዉ የሚያስፈልገን አንዱ ነገር አሁን የእግዚአብሄርን መንግስት በሙሉ ልብነት እንዴት መከተል እና ማስፋት እንደምንችል ነው ? በፀሎት እና በማቴ (6፡ 10) መኖር “ መንግስት ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን “ ፤ ምክንያቱም የወደፊት መመለሱን እና ፍርዱን ስለ ምንጠብቅ ሌሎችን እንዲዘጋጁ ለመረዳት መፈለግ አለብን ፡፡ ሮሜ (13፡ 11-12) “ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርባልና “ ብሎ በማሳሰብ ተመልሶ እስኪመጣ ከመጠበቅ ይልቅ አሁን የህይወትን እቃጦር እንድንለብስ ያነሳሳናል ፡፡
John Piper, “What is the Kingdom of God?”; available at https://www.desiringgod.org/interviews/what-is-the-kingdom-of-god.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1287.
Nelson’s Commentary, p. 1287.
Nelson’s Commentary, pp. 1287–1288.
Nelson’s Commentary, p. 1288.
Nelson’s Commentary, p. 1288..
ጥያቄዎች
-
ለሌላ አማኝ ማሳናከያ ምክንያት መሆን ምን ማለት ነው ? (ሮሜ 14፡ 13; 1ቆሮ 10፡ 32; 1ዮሐ 2፡ 10) የዚጥ ጥቂት ምሳሌዎች ምንድን ናቸው ? ሌላን ሰዉ በእግዚአብሄር ያላቸዉን ጎዞአቸዉን ከማቋረጥ እንዴት ልትጠነቀቁ (ልትጠበቁ) ትችላላችሁ ?
-
በሉቃስ 17 በመጀመሪያዎቹ አራት ጥቅሶች ይቅርታ ትምህርት ነበር ፤ ሐዋሪያቱ ወዲያዉኑ እምነታቸዉን ለመጨመር ኢየሱስን በመጠየቅ ለምን እንደ መለሱ ምን ታስባላችሁ ? (ማር 4፡ 30-32; ያዕ 2፡ 14-26) እምነት እና ይቅርታ እንዴት አብረዉ ይሄዳሉ ?
-
ወደ እርሱ ከመምጣት ይልቅ ለምን ለምፃሞቹ ለምን ርቀው በመቆም ድምፃቸው ወደ ኢየሱስ ከፍ አደረጉ ? (ዘሌ 13፡ 46; ዘኁ 5፡ 2) ልምፃሙ መቼ ነበር የተፈወሰው ?
-
ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ ምንድን እየሰራን እንዲያገኘን ይፈልጋል ? (ሉቃ 12፡ 37, 43; 17፡ 10; ሐዋ 1፡ 6-11)
-
ኢየሱስ “ የሎጥን ሚስት አስታዉስ “ ለምን እንዳለ ምን ታስባላችሁ ? (ዘፍ 19፡ 17, 26; ማቴ 10፡ 39; ዮሐ 12፡ 25) ከክርስቶስ በፊት በህይወታችሁ ዉስጥ ያለ ነገር አለ ፤ ከክርስቶስ በፊት ወዳለው ትመለከታላችሁ ወይስ መመልከት ቀጥላችኋል ?
-
በሉቃስ 17 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 17:15–16,19
“But one of them, seeing that he was healed, returned and, with a loud voice, gave glory to God. He fell facedown at His feet, thanking Him. And he was a Samaritan . . . And He told him, ‘Get up and go on your way. Your faith has made you well.’”
ኢየሱስ እየተጓዘ ሳለ፥ ከባድ የቆዳ በሽታ የነበረባቸው አስር ሰዎች ተገናኙት፡፡ በርቀት ቆመው ኢየሱስ ምህረት እንዲያደርግላቸው ጠየቁት፡፡ ሄደው ራሳቸውን ለካህናት እንዲያሳዩ ነግሯቸው፥ መንገዳቸውን እንዲሄዱ ላካቸው፡፡ ሲሄዱ ሳለ፥ አስሩም ሰዎች ተፈወሱ፡፡ ከአስሩ አንዱ ብቻ ተመልሶ ኢየሱስን አመሰገነ፡፡ የተለየ ነገር ላደረገው ለዚህ ሰው፥ ኢየሱስ አለው፥ "ሂድ፡፡ እምነትህ አድኖሃል፡፡" ይህ ሰው ለምፃም እና የተጣለ ከመሆን ባሻገር፥ የባዕድ አገር ሰው፥ ሳምራዊ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፥ ጌታ በአካላዊውም በመንፈሳዊውም ነገር ፈወሰው፡፡ ጌታ እምነቱን አይቶ ነበር፡፡
ጌታ ያያችኋል ደግሞም ይወዳችኋል፡፡ ልዩ እንደሆናችሁ ይሰማችሁ ይሆናል፡፡ ክርስቶስን ለመከተል ስትመርጡ፥ ከብዙ ሰዎች ተለይታችሁ ልትቆሙ ትችላላችሁ፡፡ ሰዎችን ሳይሆን ኢየሱስን ስትከተሉ ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ነው ደግሞም ያያችኋል፡፡ ዛሬ፥ የጌታን ድምጽ ተከተሉ፡፡ ተለይታችሁ ብትቆሙም እንኳን፥ ራሳችሁን በማዋረድ ለጌታ ምስጋና ስጡ፡፡ አስታውሱ፥ የፈጠራችሁ ጌታ ነው፤ ውብ እና ድንቅ ሆናችሁ ተሰርታችኋል፡፡ ፍቅሩ ከእናንተ ጋር እንደሆነ በማመን፥ በእምነት ተራመዱ፡፡
“ እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፥ እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ። . . . እርሱንም፦ ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው።’”
—ሉቃስ 17:15–16,19
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 139:13–14 — “አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች። ”
- ቆላስይስ 3:17 — “እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት። ”
- የዮሐንስ ራእይ 19:5 — “ድምፅም፦ ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ፥ አምላካችንን አመስግኑ ሲል ከዙፋኑ ወጣ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 61
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።